
04/06/2025
የኮሪደር ልማት ትሩፋት ለማን ነው??
***********************
ከሰሞኑ የፀደቀው የውጭ ሀገር ዜጎች የቋሚ ንብረት ባለቤት የሚያደርገው አዋጅ በቀላሉ የሚታይ ጉዳይ አይደለም።
መንግስት ምንጩ ከማይታወቅ ውይም መንገር ከማይፈልገው ገቢ ላይ ይህን ሁሉ ህዝብ ሀላፊነት በጎደለው ሁኔታ አፈናቅሎ መንገዶች አስፍቶና አሳምሮ ሲጨርስ የልማቱ ሀሳብና የገንዘቡ ምንጭ ማን እንደሆነ ሚጠቁም አዋጅ አ'ሰፀድቋል።
ይህ አዋጅ የሀገሪቷን የአየር ንብረት ለመኖሪያነት የሚቋምጡት አረቦቹና ነጮች ነባሩ ህዝብ እንዲፈናቀልላቸው ካደረጉ በኋላ ከተማዋ በሚመቻቸው መልኩ ካሳመሩ በኋላ በመጨረሻም መሬት ገዝተው ቤት ገንብተው ለመኖር እንዲመቻቸው አዋጁን አሳወጁ።
ይህም የሚያሳየው ሀገሪቷ ምን ያህል ለህዝቧ ሳይሆን ለውጪ ዜጎች እያመቻቿት እንደሆነ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።
ሀገራችን ዳር ድንበሯ አስከብረውና አክብረው የቆዩ ጀግና ህዝብ የነበራት ቢሆንም ሀገሩን አምርሮ የሚጠላ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያደርግና ሀገርን ከውስጥ የሚቦረቡር መንግስት ተነስቶብናል።
ይህ ትውልድ ውስጥ አውቆም ሆነ በጥቅም ተታሎ ከዚህ ሀገር አፍራሽና የሰላም ፀር የሆነ መንግስት ጎን የሚቆምም ሆነ የሚደግፍ ኋላ ከታሪክ ተወቃሽነትና ከህሊና ፀፀት የሚድን አይሆንም።
ሰላምና ሉኣላዊነት ለሀገራችን።