Habesha Daily

Habesha Daily ፈጣን እለታዊ የሀገር ውስጥ የውጭ ዜናዎች እንዲሁም አዳዲስና ትኩስ የሀገር ውስጥና የውጭ ስፖርት ዜናዎች ይደርሶታል።

አሳዛኝ ዜናበጣም የሚያሳዝን መርዶ ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ አረፈ:: በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል መምህር የነበረው ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ፣ ከቅርብ  ዓመታት ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲ...
21/08/2024

አሳዛኝ ዜና
በጣም የሚያሳዝን መርዶ

ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ አረፈ::

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ክፍል መምህር የነበረው ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ መድረክ ብቅ ብሎ የሰላ ሒስ በመተቸት ይቴወቅ ነበር።

አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተወልዶ ያደገው ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያዝ ለቀቅ የሚያደርገው ህመም በርትቶበት በተለያዩ ሆስፒታሎች ሲታከም ቆይቶ ዛሬ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ላይ አርፏል:: :

ነፍስ ይማር!

የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የቀብር ሥነ ስርዓት ነገ፣ ነሐሴ 16 ቀን 9:00 ሰዓት ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተክርስቲያን ይፈጸማል::😭

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልጇን በግፍ ለተነጠቀቸው ሕጻን ሄቨን እናት የመንግስት መኖሪያ ቤት አበርክቷል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ...
21/08/2024

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ልጇን በግፍ ለተነጠቀቸው ሕጻን ሄቨን እናት የመንግስት መኖሪያ ቤት አበርክቷል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ የሄቨንን እናት በማግኘት አጽናንተዋል፡፡

ልጇን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ፍትሕ ሳታገኝ ለቆየችው ሲስተር አበቅየለሽ የፍትሕ ሒደቱን ለመከታተል፣ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላትና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት መኖሪያ ቤት አበርክቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሙያዋ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ነው ከንቲባ አዳነች የገለጹት፡፡

የህጻን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትሕ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ከንቲባዋ አስገንዝበዋል፡፡

መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁሉም ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአዲስ አበባ 43 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት “በከተማዋ መግቢያ” ቦታዎች ሊከናወን ነውአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እንደ ...
21/08/2024

በአዲስ አበባ 43 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት “በከተማዋ መግቢያ” ቦታዎች ሊከናወን ነው

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሁለተኛውን ምዕራፍ የኮሪደር ልማት እንደ ኮዬ አደባባይ፣ ጎሮ እና ሰሚት ባሉ “የከተማዋ መግቢያ” እና “ማስፋፊያ ላይ በሚገኙ” አካባቢዎች ሊያከናውን ነው።

43 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ፤ ከሸገር ከተማ የኮሪደር ልማት ጋር “በማስተሳሰር” እንዲከናወን ታቅዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር “የኮሪደር ልማት” ሲል የጠራውን ዋና ዋና መንገዶችን የማስዋብ፣ የእግረኛ መንገድን የማስፋት፣ መዝናኛ ቦታዎችን የመገንባት እንዲሁም የመንገድ ዳር መብራት እና ቴሌኮሚዩኒኬሽን መስመሮችን በዘመናዊ መንገድ የመዘርጋት ሥራ የጀመረው በዚህ ዓመት የካቲት ወር ላይ ነበር።

የከተማዋን ታዋቂ እና ነባር አካባቢዎችን የሸፈነው የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት፤ አምስት መስመሮችን የያዘ ነው። በመጀመሪያው ምዕራፍ ግንባታ ከተከናወነባቸው አካባቢዎች መካከል ፒያሳ፣ አራት ኪሎ፣ ቦሌ፣ መገናኛ፣ ሜክሲኮ እና ሲኤምሲ ይገኙበታል።

የኮሪደር ልማቱ ሲከናወን ተለይም በፒያሳ አካባቢ ጥንታዊ ኪነ ሕንጻዎችን ጨምሮ በርካታ ቤቶች የፈረሱ ሲሆን፣ በዚሁ ግንባታ ምክንያት 11 ሺህ ገደማ ነዋሪዎች ከአካባቢው መነሳታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታውቀው ነበር።

የከተማ አስተዳደሩ፤ በድምሩ 48 ኪሎ ሜትር ለሚሸፍነው ለመጀመሪያው ዙር የኮሪደር ልማት፤ 33 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉንም መግለጻቸውም ይታወሳል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ግምገማ እየተደረገበት የተካሄደው ይህ የኮሪደር ልማት፤ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነችን ጨምሮ ከፍተኛ የከተማዋ ኃላፊዎች ግንባታ የሚከናወንባቸውን መስመሮች ተከፋፍለው ሥራውን መርተውታል።

ከኮሪደር ልማቱ መስመሮች ውስጥ ቀድሞ የተመረቀው በከንቲባዋ ክትትል ስር የነበረው ከአራት ኪሎ ፒያሳ የሚደርሰው መንድ ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት ሰኞ የተመረቀውን ከመገናኛ ሲኤምሲ የተዘረጋውን ልማት ጨምሮ ሌሎቹ መስመሮች በተለያዩ ጊዜያት ክፍት ሆነዋል።

ሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ በአምስት መስመሮች ላይ የሚከናወን ነው። ከእነዚህ መስመሮች ውስጥ ከፍተኛ ዝርመት ያለው “ከአንበሳ ጋራዥ - መብራት ኃይል - ጎሮ - ኮዬ አደባባይ” የሚደርሰው መንገድ ነው። ይህ መስመር 14.8 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ነው።

“ከቦሌ ካርጎ - ቡልቡላ - ኮዬ አደባባይ” የሚደርሰው ሁለተኛው ረጅም መስመር ደግሞ 12.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት አለው። በሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት ውስጥ የተካተተው ሌላኛው መስመር “ከቦሌ ድልድይ” ተነስቶ “በቦሌ ሆምስ - በአየር መንገድ ቪአይፒ መግቢያ” አድርጎ መዳረሻው “ጎሮ” አካባቢ ነው።

“ከጎሮ አደባባይ” የሚነሳው አራተኛው መስመር አምስት ኪሎ ሜትር ርዝመት እንደሚኖረው በጥናት ሰነዱ ላይ ሰፍሯል። ይህ መስመር “ከጎሮ አደባባይ - በሰባ ሁለት አካባቢ - ሰሚት ለስላሳ ፋብሪካ አካባቢ - ፍየል ቤት - ሲ ኤም ሲ አደባባይ” አካባቢዎችን ይሸፍናል።

“ከፍየል ቤት - ፊጋ - ሰሃሊተ ምህረት አደባባይ - ጃክሮስ” የሚደርሰው አምስተኛው መስመር ደግሞ 5.9 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ነው።

ምነሰጭ፦ቢቢሲ አማርኛ

 "ቦሌ ቡልቡላ ዶክተሮች ሰፈር አንዲት የ 5አመት ህፃን ሰፈር ውስጥ ለመጫወት ከቤት ትወጣለች!ለረጅም ሰአት ድምጿ ሲጠፋ አክስትም ለመፈለግ ከቤት ትወጣለች!ፈልጋ ስታጣት አንድ በእድሜ ገፋ ...
20/08/2024



"ቦሌ ቡልቡላ ዶክተሮች ሰፈር አንዲት የ 5አመት ህፃን ሰፈር ውስጥ ለመጫወት ከቤት ትወጣለች!ለረጅም ሰአት ድምጿ ሲጠፋ አክስትም ለመፈለግ ከቤት ትወጣለች!ፈልጋ ስታጣት አንድ በእድሜ ገፋ ያለ የሰፈር tele tawor ሚጠብቅ ጥብቃ አለና እሱጋ ሄዳ ስታንኳኳ አልከፍትም ይላታል! ከውስጥ የልጅቷን ድምፅ ስትሰማ ሰፈሩን በጩኸት ቅልጥ ታደርገዋለች!

የሰፈሩ ሰው ተሰብስቦ በሩን ሰብረው ውስጥ ሲገቡ ህፃኗ አልጋ ላይ ተኝታለች!ሰውዬው ደሞ ሱሪን አውልቆ ቆሞ ነበር!አሁን ፖሊሶች ሰውዬውን በባጃጅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውት ሄደዋል! ልጅቷ ደሞ ሆስፒታል ቼክ ለማስደረግ እየሄዱ ነው! "
እባካችሁን ህጉ ይሻሻልልን‼️
via-ጉርሻ

የታንዛኒያ የፖሊስ አዛዥ በቡድን ጾታዊ ጥቃት የደረሰባትን ሴት "የወሲብ ንግድ ሰራተኛ ናት" በማለታቸው ከኃላፊነት ተነሱ በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዶዶማ በቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ደርሶባ...
20/08/2024

የታንዛኒያ የፖሊስ አዛዥ በቡድን ጾታዊ ጥቃት የደረሰባትን ሴት "የወሲብ ንግድ ሰራተኛ ናት" በማለታቸው ከኃላፊነት ተነሱ

በታንዛኒያ ዋና ከተማ ዶዶማ በቡድን የአስገድዶ መድፈር ጥቃት ደርሶባታል የተባለችውን ሴት ጉዳይ ከወሲብ ስራ ጋር በማያያዝ አወዛጋቢ አስተያየት መስጠታቸውን ተከትሎ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ አንዲት ወጣት ሴት ላይ ጾታዊ ጥቃት ሲደርስባት የሚያሳይ ቪዲዮ በስፋት​​​ተሰራጭቷል። በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ታንዛኒ ድርጊቱ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል።አራት ሰዎች ሰኞ እለት በተጠረጠሩበት ጾታዊ ጥቃት ሰኞ እለት ፍርድ ቤት ቀርበው ክስ ቢመሰረትባቸውም ወንጀሉን አለመፈፀማቸውን ተናግረዋል። እሁድ እለት በዋና ከተማዋ ዶዶማ የሚገኙት የፖሊስ አዛዥ የሆነችው ግለሰብ ለታንዛኒያ ጋዜጣ ጥቃት የደረሰባት ሴት የወሲብ ንግድ ሰራተኛ ነች ሲሉ ተናግረዋል።

ይህንን አስተያየት ተከትሎ የታንዛኒያ ብሄራዊ የፖሊስ ሃይል ይቅርታ በመጠየቅ የፖሊስ አዛዧን ወደ ሌላ ቦታ ማዘዋወሩን ገልጿል። የብሔራዊ ፖሊስ ቃል አቀባይ ዴቪድ ሚሲሜ እንደተናገሩት የፖሊስ ሃይሉ በመገናኛ ብዙኃን በተሰራጨው መግለጫ የተናደዱትን ሁሉ ይቅርታ መጠየቅ ይፈልጋል ብለዋል።ሚሲሜ አክለውም የዶዶማ ክልል የፖሊስ አዛዥ የሆነችው ቴዎፒስታ ማሊያ ለሃገር ውስጥ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ተጎጂዋ የወሲብ ሰራተኛ ብትሆንም "እንዲህ አይነት ጥቃት ሊፈፀምባት አይገባም" ሲሉ መናገራቸው ቁጣን ፈጥሯል።

በማህበራዊ ድረ-ገጽ ኤክስ ላይ የፖሊስ አዛዧ ማልያ አስተያየት "ፖሊስ በሴቶች መብት ላይ ያለውን ጭካኔ የሚያሳይ ማስረጃ ነው" ሲሉ በርካቶች ተደምጠዋል። የህግ ባለሙያዋ እና ታዋቂዋ የመብት ተሟጋች ፋቲማ ካሩሜ በኤክስ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት በወሲብ ንግድ የሚሰማሩ ሰዎች ሊደፈሩ አይችሉም ማለት ነው ስትል ተናግራለች። ተጎጂዋ ጥቃት ሲደርስባት በሚያሳየው ቪዲዮ ላይ ተጠርጣሪዎቹ “አፋንዴ”ን ይቅርታ እንድትጠይቅ ሲያስገድዷት ይታያል። በታንዛኒያ "አፋንዴ" የሚለው ቃል ወታደርን ወይም የፖሊስ መኮንንን ለመጥራት ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ይውላል።

በርካታ የመብት ተሟጋቾች እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ዘንድ በፀጥታ ሀይሉ ትብብር ጾታዊ ጥቃት ሲፈፀም ቆይቷል በማለት ቁጣቸውን ገልፀዋል።ከስልጣን የተነሳችው የፖሊስ አዛዥ በንግግሯ በአልኮል እና በአደንዛዥ እፅ ተፅእኖ ውስጥ ያሉ ሰዎች ጥቃት ከፖሊስ ጋር አይያያዝም ተናግራለች። አክላም ጥቃት የደረሰባት ሴት በወሲብ ስራ ላይ የተሰማራች ትመስላለች ማለቷ የታንዛኒያን ህዝብ አስቆጥቷል።ቪዲዮው መቼ እንደተቀረፀ ግልፅ ባይሆንም ተጎጂው በሀገሪቱ የንግድ ዋና ከተማ ዳሬሰላም ውስጥ ነዋሪ እንደሆነች ተነግሯል።

ምንጭ ፦Dagu Journal

በሕጻን ሄቨን ላይ ስለተፈፀመው ፀያፍ ወንጀል የምርመራ፣ ክስ እና ፍርድ ሂደት በተመለከት ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ፡-በቅድሚያ በልጃችን በሕጻን ሄቨን ላይ የተፈፀመውን...
20/08/2024

በሕጻን ሄቨን ላይ ስለተፈፀመው ፀያፍ ወንጀል የምርመራ፣ ክስ እና ፍርድ ሂደት በተመለከት ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ፡-

በቅድሚያ በልጃችን በሕጻን ሄቨን ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ፣ ከማኅበረሰቡ ባሕል እና ወግ ያፈነገጠ ፀያፍ ወንጀል ድርጊት እያወገዝን ሰሞኑን እናቷ ሲስተር አበቅየለሽ ሚዲያ ላይ ያደረገችውን ቃለ መጠየቅ እና የፍትሕ ጥያቄ መነሻ በማድረግ ድምጽ ለኾናችሁ፣ ትምህርት ለሰጣችሁ፣ ወንጀሉን እና ፈጻሚውን፣ በወንጀል ድርጊቱ እና ድህረ ወንጀል ተባባሪ ነበሩ በሚል ድርጊታቸውን ላወገዛችሁ አንቂዎች፣ ባለሙያዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ምሥጋናችን የላቀ መኾኑን እናሳውቃለን፡፡

ይህ ለፍትሕ ሲባል በቅንነት፣ ለሕግ የበላይነት በገባን ልክ ድምጻችንን ያሰማንበት እንደኾነ እንገነዘባለን፡፡ በተለይ ይህ ዓይነት ድምጽ ለፍትሕ ሥርዓቱ ጉልበት በሚኾንበት አግባብ በዕውነት በማስረጃ መሰጠት ሲችል ደግሞ ትርጉሙ ብዙ እንደሚኾን እናምናለን፡፡ ነገር ግን በስሜት ከወንጀሉ ዘግናኝ ባህሪ አኳያ ወይም የፍትሕ ተቋማት አሠራርን ሳንረዳ ወይም ኾነ ብለን ያንቋሸሽን ከኾነ ደግሞ ተገቢ አለመኾኑን እንድታውቁት ውጤቱ እና ተፅዕኖውም አሉታዊ መኾኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ ስለኾነም የክልሉን መንግሥት አሠራር በማንቋሸሽ፣ የሕዝቡን ዕምነት እና ባሕሉን፣ የፍትሕ ተቋማት መልካም ስም በሚያጠፋ ሁኔታ ዘገባዎችን የሠራን ቆም ብለን እራሳችንን ልናይ እና ማስረጃን፣ ሁኔታን እና ምክንያትን እንድናገናዝብ አስፈላጊ ይኾናል፡፡
ስለኾነም ለመረጃ ይኾነን ዘንድ፣ ድጋፋችሁም መረጃን መሠረት አድርጎ፣ ዕውነትን በአረጋገጠ፣ ሕግን በጠበቀ ሁኔታ እንዲሰነዘር ፍላጎታችን መኾኑን በማመን በአማራ ክልል ፍትሕ ተቋማት ይህንን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ተከትሎ ምን ተደረገ፣ ጉዳዩስ ምን ላይ ነው የሚለውን በተመለከተ አጭር መረጃ እንደሚከተለው መስጠት አስፈልጓል፡፡ ጉዳዩ በሕግ የመጨሻ ውሳኔ ያልተሰጠበት እና ውሳኔ የሚጠብቅ ስለኾነ ማንኛውም ጫና አሉታዊ ተፅዕኖ በፍርድ ቤቶች እንዳያሳድር በሚቻልበት ሁኔታ ድጋፋችሁን እንድታደርጉ መረጃው ጠቃሚነት እንዳለው ትረዱ ዘንድ መረጃ መስጠቱ አስፈልጓል፡፡
ድርጊቱ የተፈጸመው ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም ነው፡፡ የድርጊቱ ቦታ ቀበሌ 14 ተብሎ ይጠራ ከነበረው አካባቢ ሲኾን ወቅቱ ሰላም የጠፋበት፣ መረጋጋት የሌለበት፣ ከፍተኛ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ግጭት (ጦርነት) የነበረበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ወቅት ብዙ ወንጀለኞች ግጭቱን እንደሽፋን በመቁጠር ብዙ ወንጀል ፈጽመውበታል፣ እራሳቸውን በግጭቱ ሸፍነው ብዙ አድርገዋል፡፡ በዚህ ወቅትም ልጃችን ሄቨን አንዷ የእነዚህ ግጭቱ ዕድል ለፈጠረለት ሰው ተጠቂ ኾናለች፡፡
ሕጻኗ ምን ኾነች፣ እንዴት ተገኘች፣ የት ተገኘች፣ ጉዳዩ ወደ ሕግ ቦታ እንዴት መጣ ሕጻኗ የተገኘችው ሻወር ቤት ውስጥ ነው፣ ስትገኝም ሕይወት ነበራት በሚባል ሁኔታ ላይ አይደለም፡፡ ፖሊስም ባለበት ከቦታው ወደ ሆስፒታል (መጀመሪያ የግል ጤና ተቋም)፣ ቀጥሎም የመንግሥት ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዳለች፡፡ ሁለት ቦታ ምርመራ ተሠርቷል፡፡ ፖሊስ አብሮ በሂደቱ እና ሂደቱንም እየተከታተለ ስለነበር እና ሕጻኗ በተገኝችበት ቤት ሌላ ሰው አለመኖሩ ሲረጋገጥ ጥርጣሬውን ቤት ውስጥ ከነበረ ሰው ጋር አድርጎ ምርመራውን ቀጥሏል፡፡ በመኾኑም ይህ ፍርደኛ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡
በምርመራው የአካባቢ ምስክር ድርጊቱን ያዬ ባለመኖሩ በቤት ውስጥ ሌላ ሰው አለመኖሩን እና በሕጻኗ አካል ላይ የደረሰውን ጉዳት የሕክምና ምርመራውን መሠረት አድርጎ ተካሂዷል፣ (ከ27 ጀምሮ በተለይ ባሕርዳር ከተማ ከፍተኛ ብጥብጥ እና ግጭት በመኖሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረው የአሁኑ ፍርደኛ ወጥቶ ነበር)፡፡ ከተማው ተረጋግቶ በቁጥጥር እስኪውልም በነጻነት ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ (የህግ አስፈፃሚዎችም ሲስተር አበቅየለሽም በዚህ ሂደት ለጥቃት ተጋላጭ ነበሩ)፡፡
ስለሆነም በአስቸጋሪ ወቅት ግጭት በነበረበት ወቅት ሐምሌ 25/11/2015 ዓ.ም ጥቃቱ ተፈጽሟል፡፡

በፍትሕ ተቋማቱ (በፖሊስ፣ በጠቅላይ አቃቢ ሕግ እና በፍርድ ቤት ምን ተከናወነ ? )

1.ምንም እንኳ ወቅቱ አስቸጋሪ ቢኾንም የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶ ተጠርጣሪው ወዲያው በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

2.ፖሊስ ጣቢያው በታጠቁ ኃይሎች ሲሰበር እና ሲዘረፍ መውጣቱን እና የተጎጅ ቤተሰብን፣ የሕግ አካላትን ሳይቀር ተጽዕኖ ለማድረስ ቢሞክርም ተመልሶ በፖሊስ ኃይል ለሕግ ቀርቧል፣ በቁጥጥር ስርም ውሏል፡፡

3.ምርመራው ተደርጎ በምርመራው እና ባሉት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች መነሻነት ፍትሕን ለማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ የሀገሪቱ አግባብ የኾነውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ ተጠቅሶ ከፍተኛ ቅጣት በተደራራቢ ወንጀል ሁለት ክስ ማቅረብ ተችሏል፡፡

4.ክሶችም የግፍ ግድያ የወንጀል ሕጉ 539 እና በመድፈር መግደልን 620 (3) ያጣቀሰ ነበር፡፡ ይህም የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ እስራት ድረስ የሚያስቀጣ ነው፡፡

5.በክርክር ሂደት ተከሳሽ ክዶ ጠበቃ አቁሞ የተከራከረ ሲኾን ይህም ሕጋዊ አሠራር ነው፤ በክርክሩ የታዩ የሙያ ሥነ ምግባር ጉዳዮች ወይም ወንጀል ከተፈጸመ ማየቱ እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንደተጠበቀ ኾኖ፡፡

6.መጨረሻ ግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ የቀረበው ማስረጃ የግፍ ግድያን ሳይኾን (539) በመደፈር መሞቷን የሚያረጋግጥ መኾኑን በማረጋገጥ ተጠርጣሪው በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ሊቀጣ ውሳኔ አርፎበታል፡፡ ስለኾነም ፍርደኛው አሁንም ማረሚያ ቤት ይገኛል፡፡

7.በአሁኑ ወቅት ፍርደኛው የፍርደኛ ይግባኝ አቅርቦ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በመመርመር ላይ ይገኛል፣ ይሄም ሕጋዊ እና የተለመደ አሠራር ነው፡፡ ዐቃቢ ሕግ የስር ፍርድ ቤት የወሰነው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በሕጉ አግባብ መኾኑን ቢያንሰው እንጂ የሚበዛበት አለመኾኑን ከወንጀሉ አሰቃቂነት አኳያ በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ፊት ቀርቦ አስረድቷል፡፡ ጉዳዩም ለውሳኔ ለሚቀጥለው ዓመት ተቀጥሮ አድሯል፡፡ አሁንም ፍትሕ ቢሮው ጉዳዩን በአግባቡ እየተከታተለው ይገኛል፡፡ ምናልባት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ በአሉታዊ ቢኾን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በዐቃቢ ሕግ በኩል የሚቀርብ እንደኾነም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

እንደመውጫ፡-
በሕጻናት ላይ የሚፈፀም ወንጀል በሀገር ላይ፣ በትውልድ ቀጣይነት ላይ፣ ሕግን ብቻ ሳይኾን ሰው መኾንን የተቃረነ አውሬነት መኾኑን አውቀን ልንዋጋው፣ ልናስቆመው የሚገባ ነው፡፡ ሕግን ብቻ ሳይኾን ፍትሕን፣ እኩልነትን፣ ሞራልን፣ ርትዕን በአጠቃላይ የተቃረነ ፀያፍ ወንጀል ሲኾን ሁላችንም በአንድነት በቅንጅት በእኩል ተቆርቋሪነት ልንታገለው ይገባል፡፡ ወደፊት የሕግ ማሻሻያ ሥራዎችንም ታሳቢ አድርገን ድምፃችንን ለመስጠት ዕድሉ አለ፡፡ በዲስፕሊን የሚታዩ ጉዳዮች፣ በወንጀል የሚያስጠይቅ በሂደቱ የተንፀባረቁ ጉዳዮች ካሉ በጥሞና (በጥቆማችሁ መነሻነት) ይታያሉ፡፡ ለሕግ፣ ለፍትሕ፣ ለርትዕ እንሠራለን!

ነፍስሽ ትረፍ ህጻን ሄቨን!!!

በቃ ይበለን!

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ዳግመኛ የህወሓት ሊቀመንበር ሆነዉ ተመረጡ👉🏼አቶ ጌታቸዉ ረዳ ከምክትልነት ቦታቸዉ ተነስተዉ አቶ አማኑኤል ተስፋይ የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር ተብለዋልዶ/ር ደብረ...
19/08/2024

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ዳግመኛ የህወሓት ሊቀመንበር ሆነዉ ተመረጡ

👉🏼አቶ ጌታቸዉ ረዳ ከምክትልነት ቦታቸዉ ተነስተዉ አቶ አማኑኤል ተስፋይ የፓርቲው ም/ል ሊቀመንበር ተብለዋል

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ መመረጣቸውን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል።

አቶ አማኑኤል አሰፋ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የፓርቲው የምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ህወሓት ሁለቱን የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ያደረገው ላለፉት ስድስት ቀናት በመቐለ ከተማ ሲያደርገው የነበረውን አወዛጋቢ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ሲያጠናቅቅ ነው። በዛሬው የጉባኤ ውሎ፤ ዘጠኝ አባላት ያሉበት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም ተከናውኗል።

ምንጭ፦ኢትዮጵያ ኢንሳይደር




ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ?" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋበሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮ...
19/08/2024

ትግራይን ዳግም ወደ ጦርነት የሚያስገባ ተጨባጭ ስጋት አለ ?

" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው። ወደ ጦርነት የሚያስገባ ምንም ነገር የለም " - አቶ አማኑኤል አሰፋ

በሊቀ - መንበሩ ደብረጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው የ14ኛው የህወሓት ጉባኤ ቃል አቀባይ አማኑኤል አሰፋ ፤ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ጦርነት የሚያስገባ ነገር የለም ብለዋል።

አቶ አማኑኤል ፥ " በአንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ተሰብስቦ ስለ አንድ ድርጅት ውስጣዊ ጉዳዮች መወሰን ወደ ጦርነት የሚያስገባ አንድም ምክንያት የለም " ሲሉ ተናግረዋል።

" ጦርነት በዚህን ያህል ኢትዮጵያ ውስጥ ርካሽ አይደለም " ብለዋል።

" ጦርነት አስፈላጊ ሆኖ አማራጭ ቢሆን ኖሮ ትግራይ ውስጥ ያሉት ችግሮች ሌላ ጦርነት ይጋብዙ ነበር " ሲሉ ተደምጠዋል።

እንዚህ ችግሮች ለተፈጸሙ ወንጀሎች የተጠያቂነት አለመረጋገጥ ፣ በህገመንግስት ላይ የተቀመጠው የክልሉ ግዛት አለመመለስ ፣ የተፈናቃዮች ወደ ቄያቸው አለመመለስ ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ ...ወዘተ እንደሆኑ ነው የጠቆሙት።

" ዛሬም ትግራይ ውስጥ ብዙ ችግሮች አሉ። ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለባቸው ነው ግን የተጀመረውን የሰላም ተስፋ ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንዲሸጋገር ህዝቡ መስእዋትነት እየከፈለ እየኖረ ነው " ብለዋል።

" ያሉ ችግሮች ወደ ጦርነት ሳያስገቡ አንድ ህወሓት የሚባል ድርጅት በፕሪቶሪያ ስምምነት አካል የሆነ ባለቤት የሆነ ውስጣዊ ችግሮች አጋጥመውት ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ሰላሙን ዘላቂ ለማድረግ የሚያስችል ስራ በመስራቱ ወደ ጦርነት ሊገባ አይችልም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደዚህ ብለዋል ... እንዲህ ብለዋል ተብሎ የተለያየ ትርጉም ከተሰጠው በኃላ ይሄን በሚመለከት ህወሓት ጠቅላይ ሚኒስትሩን engage አድርጓል። " ብለዋል።

" በዚህ ደረጃ ጦርነት ውስጥ የሚያስገባን ነገር እንደሌለ ግልጽ ሆኗል " ሲሉ አክለዋል።

" ህወሓት አንድ ድርጅት ነው " ያሉት አቶ አማኑኤል አሰፋ ፥ " የተለያዩ ስራዎች ሊሰራ ይችላል ፤ ያን ስራ በሚመለከት መወያየትና መነጋገር ይቻላል። ችግሮች ካሉ ለመወያየት እና አብሮ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የተጀመረ የሰላም ማዕቀፍ አለ ያን መሰረት አድርጎ መወያየት እና መፍታት ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" ኢትዮጵያ ውስጥ በተከታታይ የተደረጉ ጦርነቶች ናቸው የዛሬውን ችግር ያመጡት " የሚሉት አቶ አማኑኤል " ብዙ ችግር ባለበት ሀገር ሆነን አሁንም ጦርነት ውስጥ ለመግባት የሚያስችል ምንም ምክንያት የለም " ብለዋል።

" ስለተሰበሰብን ፣ አንድ አዳራሽ ውስጥ ገብቶ ህወሓት የሆነ ነገር ስላደረገ ጦርነት አይመጣም ፤ እንዴት ጦርነት በዚህ ልክ ርካሽ ይሆናል ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

" ይሄ የአንድ ድርጅት ጉዳይ ነው ፤ ውስጣዊ ችግሩን ለመፍታት ነው ጉባኤ የሚደረገው " ሲሉ ለወይን በሰጡት ቃለ መጠየቅ ተናግረዋል።



የአማራ ክልል ፖሊስ በህፃን ሄቨን ጉዳይያወጣው  መግለጫ ህፃን ሄቨንን በተመለከተ ፖሊስ የሚጠበቅበትን ተወጥቷል፤የአማራ ክልል ፖሊስ ቀዳሚ ተልዕኮው ወንጀል መከላከል ነው። በተለይም ልዩ ጥበ...
19/08/2024

የአማራ ክልል ፖሊስ በህፃን ሄቨን ጉዳይ
ያወጣው መግለጫ

ህፃን ሄቨንን በተመለከተ ፖሊስ የሚጠበቅበትን ተወጥቷል፤
የአማራ ክልል ፖሊስ ቀዳሚ ተልዕኮው ወንጀል መከላከል ነው። በተለይም ልዩ ጥበቃ የሚያስፈልጋቸውን ህፃናትና አረጋዊያን ከመጠበቅ አልፎ ወንጀል ሲፈፀም መርምሮ ለፍርድ ማቅረብ ቀዳሚ ተግባሩ ነው። ለዚህም የሴቶችን ጉዳይ ብቻ የሚከታተል የስራ ክፍል አቋቁሞ ፍትህ ለተነፈጋቸው በሚችለው ደርሷል።

ከሰሞኑ በልዩ ልዩ ማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች አዲስ ሆኖ ብዙዎቹን ያሳዘነው የህፃን ሄቨን ጉዳይ ለክልሉ ፖሊስ በተለይም ለባህርዳር ከተማ 8ኛ ፖሊስ ጣቢያ ከአመት በፊት ሐምሌ 25/ 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4:00 ሪፖርት ከደረሰን ጀምሮ እስከ ፍርድ ቀን አብሮን የዘለቀ ጉዳይ ነው።

በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ ቆጠጢና አካባቢ የ7 አመት ከ 8 ወር ታዳጊዋ ህጻን ሄቨን ላይ የተፈጸመውን አሰቃቂ ድርጊትና ህልፈተ ህይወት መርምሮ ለፍርድ ለማቅረብ ከፍትህ ነጣቂዎች ጋር ታግለን መረጃና መስረጃ አሟልተን ለፍርድ አቅርበናል።

በዚህ ሂደት ለሙያቸው ታምነው ለፍትህ መረጋገጥ የሚችሉትን ለፈፀሙ ፖሊሶቻችን ምስጋና እናቀርባለን።ጉዳዩ ብዙ ሂደቶችን አልፎ ውሳኔ ከተሰጠ በኅላም ልዩ ትኩረት በመስጠት ለህዝብ ተደራሽ እንዲሆን በአማራ ፖሊስ ቴልቨዥን ፕሮግራም በተደጋጋሚ እንዲተላለፍ ተደርጓል።

ከሰሞኑ የህፃኗን ጉዳይ ህብረተሰቡ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መከታተሉ የሚደነቅ ሆኖ አንዳዶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተቋማችን ኀላፊነቱን እንዳልተወጣ ይልቁንም የችግሩ አካል አድርገው ለማቅረብ ሲሞክሩ ታዝበናል።

ትችት ለጋራ መሻሻል ጠቃሚ ቢሆንም መርህ አልባ ሲሆን የተግባር እንቅፋት ይሆናል። እንደተቋም ለፍርድ የማቅረብ ተልኳችንን ተወጥተናል ወደፊትም ተጠናክሮ ይቀጥላል።

ከህፃን ሄቨን በተጨማሪ በክልሉ በ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ከ92 በላይ አስገድዶ መድፈር ወንጀሎች ተፈፅመዋል።
የቤት ውስጥ ጥቃቶች በቅርብ ሰውና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ አዳጋች በሆነበት አግባብ የሚፈፀም በመሆኑ ለፖሊስ የምርመራ አስቸጋሪ ነው።

ስለሆነም ማህበረሰቡ የህፃን ሄቨን ጉዳይ በማህበራዊ ሚዲያ ትኩረት እንደሰጠው ሁሉ ነገ ለሌሎችም የወንጀል ድርጊቶች መረጃና ማስረጃ በመሆን ፍትህን በጋራ እንድናረጋግጥ እንጠይቃለን ።
አማራ ክልል ፖሊስ
ነሐሴ 13/2016 ዓ.ም
ባህርዳር

በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የወጡ ህጎች መላላታቸው ጥቃት በአሳሳቢ ደረጃ እንዲጨምር አድርጓል ተባለበኢትዮጵያ በሴቶች ላይ እየደረሱ ያሉ ጾታዊ ጥቃቶች ከጊዜ ...
19/08/2024

በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የወጡ ህጎች መላላታቸው ጥቃት በአሳሳቢ ደረጃ እንዲጨምር አድርጓል ተባለ

በኢትዮጵያ በሴቶች ላይ እየደረሱ ያሉ ጾታዊ ጥቃቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውን የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር አስታውቋል።

በሴቶች ላይ የሚርሱ ጾታዊ ጥቃቶች እንዲባባሱና ሁኔታውን አሳሳቢ ካደረጉት ጉዳዮች መካከል በዋናነት ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የወጡ ህጎች መላላት እንደሆነም ተገልጿል።ከዚህም ባለፈ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተለያዮ ቦታዎች በተፈጠረው የሰላም እጦት ሳቢያ በርካታ ሴቶች ለጾታዊ ጥቃቶች ተጋላጭ እንዲሆኑ አድጓቸዋል ተብሏል።የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ወሲባዊ እና ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት ተጎጂዎችን ሰብአዊ መብት ማስከበርን አስመልክቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በባህርዳር ከተማ ከሰሞኑን የውይይት መድረክ ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ወ/ሪት አሜን ግርማ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ከተለያዩ የህግ አስከባሪ ፣ ፣ የፍትህ አካላት፣ የአካባቢ ማህበረሰብ መሪዎችን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መልኩ በጉዳዮ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።ከአውሮፓ በተገኘ ድጋፍ ኤግል ከተሰኘው ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ተጎጂዎች ፍትህ የማግኘት እንቅፋቶችን በመለየት ነፃ የህግ ድጋፍ እና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት ታስቦ መድረኩ ተዘጋጅቷል።ከባህልና ሀይማኖታዊ እሳቤዎች ጋር ተያይዞ ሴቶች ጾታዊ ጥቃት በሚደርስባቸው ወቅት ወደ ፍትህ አካላት ቀርበው ሪፓርት የማያደርጉበት ሁኔታ መኖሩ በመድረኩ ላይ እንደ አንድ ክፍተት ተነስቷል ሲሉ አስተባባሪዋ ጨምረው ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በፀጥታ ችግር የተነሳ ፍርድ ቤቶች ላይ ጫና መኖሩን በዚህ ወቅት ለማወቅ ተችሏል ያሉት ወ/ሪት አሜን የህግ አስፈፃሚ አካላት እንዲሁ በቂ አቅም የሌላቸው መሆኑ ተረጋግጧል። ችግሩን ለመፍታት ሴቶች እና የአካባቢው ማህበረሰብ የተለያዩ ጾታዊ ጥቃት ሲደርስባቸው ጉዳዮን ለሚመለከተው አካል እንዲያሳውቁ ለማድረግ የግንዛቤ ስራዎችን ከመስራት ባለፈ ለህግ አስፈፃሚ አካላት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት ይገባል ነው ያሉት።

ይህን አሳሳቢ ችግር የሚፈቱ ተግባራዊ ምክረ ሃሳቦችን በማንሳት በባህር ዳር ከተማ የሚገኙ ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች ፍትህ እና አስፈላጊ የድጋፍ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል የጋራ የድርጊት መርሃ ግብር መዘጋጀቱን አስተባባሪዋ ገልጸዋል።በተዘጋጀው የእቅድ መርሃ ግብር መሰረት በቀጣይ በጉዳዩ ዙሪያ የሚሰሩ ተቋማት እርስ በእርሳቸው በመገማገም ለችግሩ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስራ እንደሚሰራ ማህበሩ ገልጻል።

ምንጭ፦Dagu Journal

ሕፃን ሔቨንን በተመለከተ ከአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ(ነሀሴ 12/2016ዓ.ም) ~~~~~~ሕፃን ሔቨን ዕድሜዋ 7 ዓመት የሆናት ባ/ዳር ከተማ ውስጥ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም በ...
18/08/2024

ሕፃን ሔቨንን በተመለከተ ከአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር የተሰጠ መግለጫ
(ነሀሴ 12/2016ዓ.ም)
~~~~~~
ሕፃን ሔቨን ዕድሜዋ 7 ዓመት የሆናት ባ/ዳር ከተማ ውስጥ ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም በተፈጸመባት የአስገድዶ መደፈር (የግብረ ስጋ ድፍረት በደል) ሕይወቷ ማለፉን እና በዚህ ወንጀል የተጠረጠረው አቶ ጌትነት ባይህ የተባለ ግለሰብም ምርመራ ተጣርቶበት በባ/ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ ቀርቦበትና በማስረጃ ተረጋግጦ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን በማህበራዊ ሚዲያው ከተለቀቀው ውሳኔ ለመረዳት ችለናል።

ማኅበሩ በሕፃን ሔቨን ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ ወንጀል በእጅጉ ያዝናል። ድርጊቱም ከሃይማኖትና ከባሕል ያፈነገጠ በመሆኑ በጥብቅ ያወግዛል። ሆኖም በእኛ ሀገር ወንጀል እና ወንጀለኛ የሚዳኝበት ሕግና ስርዓት እያለ እና ጉዳዩም በዳኝነት አካሉ በይግባኝ እየታየ ባለበት ሁኔታ ከትናንት ጀምሮ ከዳኝነት ነጻነት እና ከሕግ የበላይነት መርህ ባፈነገጠ መልኩ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴሩን ጨምሮ በማህበራዊ ሚዲያው ቅጣት አንሷል፣ ተከሳሹ ይግባኝ ሊጠይቅበት አይገባም እና መሰል ነገሮችን በማናፈስ ዳኞች ህግና ማስረጃን ብቻ መሰረት አድርገዉ በነፃነት እንዳይሰሩ ያልተገባ ጫናን የሚፈጥር ተግባር እየተፈፀመ የሚገኝ በመሆኑ ይህንን መግለጫ ለማውጣት ተገደናል።

የሕግ የበላይነት መከበር የሚጠቅመው በቅድሚያ ለራስ በመሆኑ ፍ/ቤቶች ነፃና ገለልተኛ ሆነው እንዲዳኙ መፍቀድ ተገቢ ነዉ፡፡ ፍርድ ቤቶች የሚሰጧቸዉ ዉሳኔዎች ስህተት አለባቸዉ ቢባል እንኳ በተቀመጠዉ የይግባኝ ስርዓት መሰረት ከሚታረሙ በስተቀር ማንኛዉም የመንግስት አካልም ሆነ ግለሰብ ሊያከብራቸዉ የሚገቡ መሆናቸዉን ህገ መንግስታዊ እዉቅና ካለዉ የህግ የበላይት መርህ መገንዘብ የምንችለዉ ነዉ፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ሁላችንም ውሳኔውን ከሰጠውም ሆነ ጉዳዩ በይግባኝ ከቀረበለት ፍ/ቤት ትችት ላይ መረባረብ ማቆም ይገባናል።

ከይግባኝ መብት አንፃርም በአገሪቱ በተቋቋሙ ፍ/ቤቶች በወንጀልም ሆነ በፍትሐብሄር የተፈረደበት ወገን ይግባኝ የመጠየቅ ህገ-መንግስታዊ መብት እንዳለው ከሕገ መንግስቱ ከአንቀጽ 20(6) ስር ተመላክቷል። ሆኖም ግን ሚኒስቴሩን ጨምሮ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ ተከሳሹ ይግባኝ ማቅረብ የለበትም የሚለው ዘመቻ የአገሪቷን በሕግ የመዳኘት መብትን (Due process of law) አደጋ ላይ የሚጥል እና በይግባኝ የሚመለከተዉ ፍርድ ቤት ላይ ያልተገባ ጫና በማሳደር የዜጎችን ፍትህ የማግኘት መብት የሚጥስ ተግባር ነው።

በመሆኑም ማህበሩ የትኛዉም ፍትህ ፈላጊ አካል ነፃና ገለልተኛ በሆነ የዳኝነት አካል ፊት ቀርቦ እንዲዳኝ እና ዳኞችም ህግንና በማስረጃን ብቻ መሰረት አድርገዉ በነፃነት እንዲወስኑ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩ በማድረግ የህግ የበላይነት እንዲከበር የሚሰራ ከመሆኑ አኳያ ሚኒስትሩም ሆነ ሌላ አካል በሕፃን ሔቨን ላይ በተፈፀመዉ ወንጀል ፍርድ ቤቱ የሠጠዉን ዉሳኔ ስህተት አለበት ብሎ ካመነ በሕግ አግባብ እንዲለወጥ መስራት ከሚችሉ እና ይግባኝ ሰሚዉ ፍርድ ቤትም በነፃነት አከራክሮ እንዲወስን ከመፍቀድ ባለፈ የፍ/ቤቶችን የመወሰን ነጻነት በሚጋፋ መልኩ የሚደረገው የሚዲያ ዘመቻ አግባብነት የለዉም ብለን እናምናለን።

ማህበሩ በሕፃን ሔቨን ላይ የተፈፀመውን ድርጊት በእጅጉ እያወገዘ ለወላጆቿ እና ለመላዉ ቤተሰቧ ፈጣሪ መጽናናትን ይስጥልን ዘንድ እንመኛለን።

የአማራ ክልል ዳኞች ማኅበር

ከመገናኛ ሲኤምሲ የተዘረጋውን የባቡር መስመር ለማንሳት ሲካሄድ የቆየ ጥናት መጠናቀቁ ተሰማከመገናኛ ሲኤምሲ የተዘረጋውን የቀላል ባቡር መስመር ለማንሳት ሲደረግ የነበረ ጥናት መጠናቀቁ ተገለጸ...
18/08/2024

ከመገናኛ ሲኤምሲ የተዘረጋውን የባቡር መስመር ለማንሳት ሲካሄድ የቆየ ጥናት መጠናቀቁ ተሰማ

ከመገናኛ ሲኤምሲ የተዘረጋውን የቀላል ባቡር መስመር ለማንሳት ሲደረግ የነበረ ጥናት መጠናቀቁ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ድርጅት ያስጠናው ጥናት ‹‹የባቡር መስመሩ መፍረስ አለበት ወይስ ሌላ የመፍትሔ አማራጭ አለ›› የሚለውን ለመመልከት የሚረዳ መሆኑን፣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የሪፖርተር ምንጭ ገልጸዋል። ጥናቱ ይፋ የተደረገ አለመሆኑን የገለጹት የመረጃ ምንጭ፣ ትናንት ቅዳሜ ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት እንደሚቀርብ አረጋግጠዋል።

የባቡር መስመሩ መቆየት ወይም መፍረስ አለበት የሚለው ፖለቲካዊ ውሳኔ ጭምር የሚጠይቅ መሆኑንም ገልጸው ዝርዝሩን ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

የከተማው ቀላል ባቡር መስመር የሚጠበቅበትን አገልግሎት ባለመስጠትና ለከተማው የትራፊክ ፍሰት እንቅፋት ነው በሚል፣ ሙሉ በሙሉ ሊነሳ እንደሚችልና ለዚህም ጥናት እየተደረገ እንደሆነ ቢነገርም፣ በተጨባጭ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ማረጋገጥ አልተቻለም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የመገናኛ ሲኤምሲ የኮሪደር ልማት ባስመረቁበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ነሐሴ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ከመገናኛ እስከ ሲኤምሲ ያለውን የባቡር መስመር አስመልክቶ ከከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ጋር መወያየታቸውን አስታውቀው ነበር። ‹‹ከመገናኛ ሲኤምሲ ያለውን መስመር ምን ማድረግ እንችላለን የሚለውን ከአዲስ አበባ አመራሮች ጋር ስናይ ቆይተናል፤›› ማለታቸው አይዘነጋም።

ከመገናኛ ሲኤምሲ ያለው መንገድ ሰፊ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እየተካሄ ያለው ውይይት ከተጠናቀቀ በኋላ አራትና አምስት ተሽከርካሪዎች በአንድ ጊዜ ማስተናገድ የሚችልና ትራንስፖርቱን የሚያሳልጥ እንደሚሆን ተናግረው ነበር። በአካባቢው በርካታ ግንባታዎች እየተካሄዱ መሆናቸውንና ፈጣን መንገድ መገንባት ካልተቻለ፣ የትራንስፖርት ችግሩን መፍታት እንደማይቻልና በዚህ ምክንያት የሚባክን ጊዜ የአገርን ሀብት ጭምር የሚያሳጣ እንደሆነም ገልጸው ነበር።

በ2008 ዓ.ም. አገልግሎት መስጠት የጀመረው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት፣ ሥራውን ሲጀምር 41 ባቡሮችን በመያዝ ነበር፡፡ ባቡሮቹ አገልግሎት መስጠት በጀመሩ በጥቂት ጊዜያት ብልሽት ሲያጋጥማቸውና አገልግሎት መስጠት ሲያቆሙ መመልከት የተለመደ ነበር።

ከ475 ሚሊዮን ዶላር በላይ የወጣበት የከተማዋ የቀላል ባቡር ፕሮጀክት፣ የታሰበውን ትርፍ በማግኘት ዕዳውን መክፈል ቀርቶ፣ ለመለዋወጫ ዕቃዎች ግዥና ለሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎች ድጎማ እየተደረገለት ቆይቷል።

የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ለአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት ገብቶ በነበረው ውል መሠረት፣ ዋናውን ብድርና ወለዱን በዓመት ሁለት ጊዜ እየከፈለ በአሥር ዓመታት ውስጥ የተገነባበትን ወጪ እንዲከፍል መስማማቱን፣ ከዚህ በፊት ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ለሪፖርተር መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ ነገር ግን ከ2008 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 2013 ዓ.ም. ድረስ 16 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ማስመዝገቡን ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡

ዘገባው የሪፖርተር ነው።

ምንም ፦ሪፖርተር

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Habesha Daily posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share