16/10/2025
ቻይና የኢትዮጵያ ዕዳ መክፈያ ጊዜ የሚያራዝም አወቃቀር ለመደገፍ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
****
የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ዕዳ መክፈል አቅቶት ከአበዳሪ ተቋማትና ሀገራት ጋር ያልተሳካ ድርድር እያደረገ ባለበት ጊዜ ከቻይና መንግሥት አዎንታዊ ምላሽ አግኝቷል።
የቻይና መንግሥት የኢትዮጵያ እዳ ክፍያ ጫና ያቃልላል የተባለ አዲስ የክፍያ አወቃቀር መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከቻይና የፋይናንስ ተቋማት እና ሌሎች አበዳሪዎች ጋር ያላት ግንኙነት የበለጠ ውጤታማ እንድትሆን የሚያስችል ትልቅ እድገት ነው ብሎታል ኤምባሲው።
የመግባቢያ ሰነዱ የኢትዮጵያን የዕዳ ጫና ለማቃለል ብቻ ሳይሆን ወደፊትም አዳዲስ የትብብር እና የጋራ ዕድገት ዕድሎችን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል።
©️ማለዳ ሚዲያ