Philosophical qoutes

Philosophical qoutes Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Philosophical qoutes, Media, AA, Addis Ababa.

የሚሸጥ ዘመናዊ ቤት ለመኖሪያ በጣም   >>>  ® ሰፈር       72 አካባቢ ® ስፋት      72m2® ዋጋ       12ሚ ብር ይባላል  🙏ዉድ ደንበኞቻችን  ስለመረጣቹን      እናመሰግ...
11/06/2022

የሚሸጥ ዘመናዊ ቤት ለመኖሪያ በጣም >>>

® ሰፈር 72 አካባቢ

® ስፋት 72m2

® ዋጋ 12ሚ ብር ይባላል

🙏ዉድ ደንበኞቻችን ስለመረጣቹን እናመሰግናለን!

☎️ ለበለጠ መረጃ፡-📞0969130026

28/05/2022
02/09/2021

በአይነቱ ልዩ የሆነ ህዝባዊ የንቅናቄ ጥሪ!
ለመላ ኢትዮጵያውያን!
*****************
ይህ መልዕክት የተላከላችሁ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ከዩኒቨርሲቲውም ለሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ እጅግ የሚጠቅም ሀሳብ መንጭቷል። የመነጨውም ሀሳብ ያለምንም ወጪ በመላ ሀገራችን የህዝባዊ ንቅናቄ ማዕበል ለመፍጠር የሚቻልበትን መንገድ ያሳያል። ይህን ንቅናቄ “እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም!፡- ህዝባዊ የህብረ-ዜማ ማዕበል” ብለን የጠራነው ሲሆን፤ ንቅናቄውም የሚካሄደው በዋናነት “እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም” የሚለውን የጋሽ መሀሙድ አህመድን ታዋቂና መሳጭ ዜማ፣ መላ ኢትዮጵያውያን በያሉበት ሆነው፣ በተመሳሳይ ጊዜ በጋራ እንዲያዜሙት በማድረግ ነው፡፡ ይህ ንቅናቄ እንዲካሄድ ያቀድነውም በአዲስ አመት ዋዜማ፣ ጳጉሜን 5 ቀን 2013 ዓ.ም፣ ከረፋዱ 04፡00 – 04፡06 ባሉት 6 ደቂቃዎች ነው፡፡
የንቅናቄው ዋነኛ ዓላማ ሀገራችንን ለማፍረስ ያሰፈሰፉት ምዕራባዊ ሀገራት የከፈቱብንን ውስብስብና መጠነ ሰፊ ጥቃቶች እኛ ኢትዮጵያውያን በአንድነት ቆመን ለመመከት ያለንን ቁርጠኝነት ከዳር እስከ ዳር በሚያስገመግም ልዩ ህብረ-ዝማሬ ማዕበል ለጠላቶቻችን ማሳየት ነው፡፡
ከዋነኛ አላማው ጋር አያይዞ ንቅናቄው የሚከተሉትን ዝርዝር አላማዎችም አንግቧል፡፡
- የህብረ-ብሔራዊ አንድነታችንን የማይናወጥ ፅናት ልዩ ስሜትን በሚፈጥር የህብረ-ዝማሬ ማዕበል ለመላው አለም በተጨባጭ በተመሳሳይ ሰዓትና ደቂቃ ማሳየት፤
- በሀገሩ ላይ የሚሰነዘረውን ማንኛውንም አይነት ቅጣት የሚመክተው መላው ህዝብ መሆኑን ማስገንዘብ፤
- ሀገራችንን ለመቀማት እና ለማፍረስ ለመጣ ወራሪ ሀይል ልዩነቶቻችን አንድነታችንን ማስተሳሰሪያ ቃል ኪዳናችን እንደሚሆን ዛሬም እንደጥንቱ ለጠላቶቻችን ማስገንዘብ፤
- በየሀገሩ ያሉ ሀገር ወዳድ ዲያስፖራ ወገኖቻችንንም በያሉበት ይህን ህብረ-ዝማሬ በጋራ እንዲያስተጋቡ ማነቃቃትና ማነሳሳት፤
- ለህብረ-ዝማሬው የተመረጠው ዘፈን ግጥም ይዘት በእንግሊዝኛ ተተርጉሞ የማህበራዊ የመገናኛ ድረ-ገፆችን እንዲያጥለቀልቅ ማድረግ፤
- በዚህ እና በቀጣይ ህዝባዊ ማዕበሎች አማካይነት ምዕራባውያን በሀገራችን ላይ የያዙትን አቋም መልሰው እንዲያጤኑት ማስገደድ፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡

የንቅናቄውን ትልመ ሀሳብ አዘጋጅተን ለዩኒቨርሲቲያችን፣ ፋናን፣ ኢቢኤስን፣ ኢሳትን፣ ለመሳሰሉ የሚዲያ ተቋማትም ከ11 ቀናት በፊት፣ በኢሜይል ልከናል፡፡ ንቅናቄውን አስቀድመን ለህዝቡ ለማሳወቅ ያለው ጊዜ እጅግ አንሶብናል። እንደሀገር ወዳድ ዜጋ አላማና ግቡን ተገንዝባችሁ፣ ንቅናቄው የናንተንም እገዛ ስለሚፈልግ ቸል ሳትሉ ከጎናችን እንድትቆሙ በአክብሮት እንጠይቃለን። ትልመ-ሀሳቡንም ሆነ ተጨማሪ ማብራሪያና ዝርዝር ጉዳዮች ከፈለጋችሁ ከዚህ በታች ባኖርንላችሁ ስልኮች ደውሉልን፡፡
ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!

05/06/2021

፨ ዘርህ ምንድነው ?

ሁለት ሰዎች በማዳበሪያ የታፈነ እህል ይዘው ገበያ መሀል ይገናኛሉ ። በአጋጣሚ ሁለቱም ሊሸጡ ያሰቡበት ቦታ እኩል ደረሱና አንደኛው ሌላኛውን..
" ዘርህ ምንድነው ? " ሲል ጠየቀው ።
" ስንዴ !.. ያንተስ ? " አለ እሱም በተራው !
" የኔም ስንዴ ነው ።"
" እንግዲያው አንዱን መስፈሪያ ስንት ልትሸጥ አስበሃል ?"
" ስምንት ብር " ጠያቂው ይህን ሲሰማ ፈቀቅ ብሎ ብቻውን ተቀመጠና..
" ስንዴ በ8 ብር ... ምርጥ ስንዴ በ8 " እያለ የአላፊ አግዳሚውን ትርምስ ወደርሱ ለመገልበጥ ቻለ ። ይህን ሲመለከት የቆየ አንድ የፎቶ ግራፍ ባለሙያ ገዢ ወዳጣው ነጋዴ ተጠግቶ ...
" የሁለታችሁም ዘር ስንዴ ሆኖ ሳለ... መስፈሪያውን እኩል በስምንት ብር ተምናችሁት.. ገዢ ያጣኸው ለምንድነው ? " ሲል ጠየቀው ። ነጋዴውም ..
" እሱ ስለጮኸ እኔ ደግሞ ዝም ስላልኩ! " አለ ።
" ለመሸጥ ከመጣህ ለምን አትጮህም ? "
" የኔ ጩኸት ሌላውን ስለሚረብሽ አልጮህም ! እስኪ ተመልከት ሁሉም ነጋዴ በርሱ ረብሻ ተሸፍኗል ! ገዢዎችም ለጮኸው ተሸናፊ ናቸው ! "
" ለመሆኑ ይህ ሰው አዲስ ነጋዴ ነው ? " ሲል ጠየቀ ።
" እንደዛ ነገር... ገበያው ሁሉ የሱ ይመስለዋል ። "
" እንግዲያው ልትከስሩ ነዋ ! "
" አይደለም ! የጮኸ ቶሎ ጨራሽ ነው ። እሱ እሪ ብሎ ሲጨርስ እኔና ወዳጆቼ ለገበያው ሰላም ዝም ብለን እንሸጣለን !" ብሎ ወደስራው ተመለሰ.. እኛም ወደ ስራችን ፣ ወደ ዝምታችን እንመለስ ። እሱ እንደሆነ አሁን ይጨርሳል ።


የስብዕና ልህቀት

06/05/2021

ማራኪ አባባሎች

"ፍቅርን መፍራት ህይወትን መፍራት ነው። ህይወትን የሚፈራ ሶስት እጅ የሞተ ነው።"
በርትራንድ ረሰል

"ከጌታዬ ሶስት ነገሮችን አጥብቄ እፈልጋለሁ አንድ ጥበብ ሁለት ጥንካሬ
ሦሥት ፍቅር። ከነዚህ ከሦስቱ የበለጠ የምሻው ግን ፍቅርን ነው።ፍቅር ሲኖረኝ ሁሉም ነገር አለኝ ነፃነትም ቢሆን "
ማርቲን ሉተር ኪንግ

"ያንተ ሀሳብ ሳይጨመርበት ማንም የበታችነት እንዲሰማህ አያደርግህም።"
ኤለኖር ሩዝቬልት

"ዝነኛው ፍቅር ሆይ አንዳንዴ አውሬን ሰው ታደርገዋለህ። አንዳንዴ ደግሞ ሰውን ወደ አውሬነት ትለውጣለህ።"
ዊሊያም ሼክስፒር

"የፍቅር ስሜቶች ልክ እንደ አውሎ ንፋስ ናቸው። መቼ ፣የት ና ወዴት እንደሚነሱ ማንም አያውቅም።"
ፓትሞር

"ሴቶች ልታይ ልታይ ባይ ለብ ለብ ወንድ ይፈልጋሉ። ወንዶች ደግሞ ሴቶች የሚፈልጉትን ለመሆን መከራቸውን ያያሉ።"
ማርጋሬት ሚድ

"የምፅዐት ቀንን አትጠብቅ በየቀኑ እየተፈፀመ ነው።"
አልበርት ካሙ

"ከመጠን ያለፈ አድናቆት በመጨረሻ ገዝግዞ ነው የሚጥለን።"
ጅለ ክርስቲ

"ፓለቲከኛ የሰውን ልጅ በሁለት መደብ ይከፍለዋል። ጠላት መምቻ መሣሪያ እና ጠላት"
ፍሬድሪክ ኒቼ

ምንም አያውቅም ግን ሁሉንም የሚያውቅ ይመስለዋል። ፖለቲከኛ ማለት እሱ ነው።
በርናርድ ሾው

ፖለቲከኛ እራሱ የሚናገረውን ራሱ አያምንም ሌሎች ሲያምኑት ግርም የሚለው ለዚህ ነው።
ቻርል ደጎል

"በሥልጣን ላይ ያለ ጓደኛህን እንዳጣኸው ቁጠረው።"
ሔነሪ አዳምስ

"የሰው ልጅ ክፋትን ለመስራት ያለው አቅም ዲሞክራሲን አስፈላጊ ያደርገዋል። የሰው ልጅ ደግ ለመስራት ያለው አቅም ደግሞ ዲሞክራሲን በስራ ላይ እንዲውል ያደርገዋል።"
ኒያቡኸር

ቅናትን የሚፈጥረው ፍቅር ሳይሆን ራስ ወዳድነት ነው።"
ዋሊንግተን

"ፍቅር ዕርቃኑን ያለ ህፃን ማለት ነው። ታዲያ ለገንዘብ ማስቀመጫ ኪስ ያለው ይመስላችኋል?"
ኦቬድ

"የሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ ዋናው ነገር በሌሎች የመሞገስ ጉጉት ነው።ስለዚህ ከሰዎች የምትፈልገውን ለማግኘት የተፈላጊነት ስሜት እንዲሰማቸው አድረግ።"
ዊሊያም ጀምስ

ነፃ የምንሆነው ስለነፃነት ባለን የግንዛቤ ልክ ነው።
ሉተር ኪንግ

"ጊዜ ማንኛውንም ሀዘን የሚያስወግድ ጥሩ መድሀኒት ነው።"
ሲፈለክስ

"እያንዳንዱ ሰው እግዚአብሔር ከጎኔ ይኖራል ብሎ ያስባል። ባለፀጋና ጠንካራ ሰው ግን እግዚአብሔር በእርግጥ ከጎኑ መኖሩን ያውቃል።"
ዣን አንዊ

"ልብህ ይናገር ዘንድ ምላስህ ዝም ይበል። እግዚአበሔር ይናገር ዘንድ ደግሞ ልብህ ዝም ይበል።"
አባራሀኒ

"ጠቅላላው የአለም ታሪክ በድምሩ ሲታይ ሀገሮች ጠንካራ ሲሆኑ ሁልጊዜ ፍትሀዊ ሆነው አይገኙም።ፍትሀዊ እንሁን ባሉ ጊዜ ደግሞ ጠንካራ ሆነው አይገኙም።"
ዊንሰተን ቸርችል

አቅራቢ -Ab

06/02/2021

⚡አንድ ተማሪ ክፍል አርፍዶ ስለገባ ብላክቦርድ ላይ የተፃፉ ሁለት የሂሳብ ጥያቄዎች የቤት ስራ ወይም አሳይመንት መስለዉት በደብተሩ ፅፏቸው ወደቤቱ ይሄዳል ።

⚡ ታዲያ ቤቱ ገብቶ የቤት ስራ የመሰለውን ሁለት ጥያቄ ለመስራት ሲሞክር በጣም ይከብደውና ከተለመደው ውጪ ስለሆኑበት ግራ ይጋባል ። በመጨረሻም ግን በብዙ ጥረት እና ልፋት ጥያቄዎቹን በትክክል ሰርቶ ጨረሳቸው ። አስገራሚው ነገር ጥያቄዎቹ የቤት ስራ ወይም አሳይመንት ሳይሆኑ በሂሳብ ታሪክ ውስጥ መልስ ያልተገኘላቸው ታዋቂ የስታስቲክስ ጥያቄዎች ነበሩ ። ይባላል ። በመጨረሻም ምን አለ መሰላቹ እኔ ከመጀመሪም መልስ ያልተገኘላቸው ጥያቄዎች መሆናቸውን ባውቅ ኖሮ አልሞክራቸውም ነበር አለ ።

15/11/2020

አ ገ ር
┈•✦•┈
አገር፤ በታሪክ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በልማድ፣ በተስፋ፣ በደስታና በመከራ ተሳስሮ የሚኖር አንድ ወገን የሆነ ሕዝብ የሚኖርበት የዓለም ክፍል ነው።

አገር፤ ማለት አያት ቅድም አያት የተወለዱበት፣ አድገውም በጀግንነት ከውጭ ጠላት እየተከላከሉ ለሕዝብና ለመንግሥት የሚጠቅም ሥራ ሠርተው ዕድሜአቸው ሲደርስም ልጆቻቸውን ተክተው የተቀበሩበት ጉድጓድ ነው።

በመወለድ እትብት፣ በመሞት አካል ከአፈሩ ጋራ ስለሚዋሐድ የአገሩ አፈር ሕዝቡ በላዩ የሚኖርበት ማለት ነው።

እግዚአብሄር ከምድርዋ ፍሬ ሕይወት እንዲገኝባት በማድረጉ አገር፤ እያጠባች የምታሳድግ፣ ፍቅርዋ በአጥንት በሥጋ ገብቶ የማይደመሰስ የሆነች እናት ማለት ነው።

ከልጅነት ጀምሮ ወንዙን፣ ተራራውን፣ ሜዳውን፣ ቆላውንና ደጋውን በማየት ስለ ማደግ፤ አባቶች በሕይወትና በሞት የሠሩበት ደግ ሥራ በአእምሮ ታትሞ ስለ ቀረ በአገር እስካሉ ሲታይ፣ በስደት ሲሆኑ ሲታሰብ ፍቅርና ናፍቆት የሚያሳድር አገር ነው።

አገር፤ አባት፣ እናት፣ ዘመድ፣ ምግብ፣ ጌጥና ሀብት በመሆኑ ድኽነትና ጥቃት በመጣ ቁጥር እስከ ሞት ድረስ እንዲሠራበት ከአያት ከቅድም አያትና ከአባቶች በጥብቅ የተሰጠ ያደራ ገንዘብ ነው።

ሕ ዝ ብ
┈•✦•┈
ሕዝብ በአንድ አገር፣ በአንድ መንግሥት በአንድ ሰንደቅ ዓላማ፣ በአንድ ሕግ ጥላ ተሰብስበው የሚኖሩ ሰዎች ማለት ነው።

አንድ ሕዝብ በትውልድ፣ በቋንቋና በሃይማኖት በመገናኘት ብቻ ሳይሆን ባለፈው ኑሮው ደስታንና መከራን በአንድነት የተካፈለ፣ በአስተዳደሩም በልዩ ልዩ ሥራ የተሳሰረ፣ ለወደፊትም እሠራዋለሁ በሚለውና ስለ አገሩና ስለ መንግሥቱ ያለው ተስፋ አንድ የሆነ ማለት ነው።

10/06/2020

" ምርምርህ የትም ያድርስህ የት ህይወትህን ልትመረምረው ይገባል...ያልተመረመረ ሕይወት እርባና የለውም "

ሶቅራጥስ

10/06/2020

10 Rules For Success:

1. Find your confidence.
2. Love what you do.
3. Learn from failure
4. Find spontaneity.
5. Just listen.
6. Overcome obstacles.
7. Be in the moment.
8. Study the greats.
9. Always do your best.
10. Don’t give up.

Address

AA
Addis Ababa
ABEBE1

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Philosophical qoutes posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category