01/05/2025
የ19ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓውያን ሆን ብለው አፍሪካን የመከፋፈል ሂደት አህጉሪቱ የራሷን የተፈጥሮ የባህል እና የፖለቲካ ዝግመተ ለውጥ እንዳትከተል ተፅዕኖ አድርጓል፡፡ ይሁን እንጂ የአውሮፓውያን ወረራ ፍጥነት፣ የመግባቱ ጥልቀት እና የቁጥጥሩ መጠን ሁልጊዜ ሀብቷን ለመበዝበዝ በሚሯሯጡ የውጭ ሰዎች ብቻ የሚመራ አልነበረም። በአድዋ ጦርነት በሚያስደንቅ ሁኔታ ተምሳሌት በሆነው ተቃውሞ አፍሪካ በአውሮፓ እና በሰሜን አሜሪካ ፖለቲካ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድራለች። አፍሪካ በቅኝ ግዛት ለመገዛት ተዘጋጅታ የተቀመጠች “ጨለማ አህጉር” ብቻ አልነበረችም፤ ወይም በአንደኛው ጫፍ ባርነት ያለው ኢሰብአዊ በሆነው የሶስት ማዕዘን ንግድ ውስጥ አስፈላጊ ትስስር ልትፈጥር የተዘጋጀች ጉዑዝ ብቻ አልነበረችም። እሷም የአልገዛም ባይነት፡ የእምቢተኝነት፣ የድል እና የኩራት ምድርም ጭምር እንጂ፡፡ በኢትዮጵዊያን ጀግኖች አባቶቻችን የተገኘዉ የዓድዋ ድልም የዚህ የአፍሪካዊያን የአልገዛም ባይነት ምልክትና የኩራት ምንጭና ሕያዉ የጥቁር ህዝቦች የነፃነጽ ምልክጽ ኆኖ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡
The Scramble in which the Europeans of the 19th century willfully subdivided Africa among themselves has not allowed the continent to follow its own natural course of cultural and political evolution. However, the speed of European conquest, the depth of its pe*******on and the magnitude of its control were not always dictated by the outsiders who were vying to exploit its resources. Through resistance, dramatically symbolized by the Battle of Adwa, Africa has also affected the politics of Europe and North America. Africa was not simply a “dark continent” out there to be colonized, nor was it simply a necessary link in the inhuman triangular trade, with slavery at one end. It was — and is — also a land of defiance, symbol of victory and pride for the Africans and the Black nations in the world forever!
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የቱሪዝም ሚኒስቴር-ኢትዮጵያ Ministry of Tourism-Ethiopia