Great Mention TV Ethiopia

Great Mention TV Ethiopia Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Great Mention TV Ethiopia, TV/Movie Award, ethiopia, Addis Ababa.
(1)

Great Metion TV
🎥 Christian Media Ministry
📖 Sharing the Gospel of Jesus Christ with the world.
🕊️ Faith • Hope • Love
🇪🇹 የኢየሱስ ክርስቶስን ወንጌል ለዓለም እናደርሳለን።
📺 የክርስቲያን ዜና፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እና የመንፈሳዊ መልእክቶች።
🙏 God Bless You | እግዚአብሔር ይባርካችሁ

“ የቄስ በሊና ሳርካ ምክር “"ሰዎችን ከማገልገልህ በፊት፣ መድረክ ላይ ከመቆምህ በፊትህ፣ ከመፀለይህ በፊት፣ ከመምከርህ በፊት፣ ወንጌል ከመናገርህ በፊት፣ መንፈሳዊ ስራን ለመስራት ቢሮ ከመ...
19/08/2026

“ የቄስ በሊና ሳርካ ምክር “

"ሰዎችን ከማገልገልህ በፊት፣ መድረክ ላይ ከመቆምህ በፊትህ፣ ከመፀለይህ በፊት፣ ከመምከርህ በፊት፣ ወንጌል ከመናገርህ በፊት፣ መንፈሳዊ ስራን ለመስራት ቢሮ ከመግባትህ በፊት፣ ለመምከር ሆነ ለመገሰፅ ከመነሳትህ በፊት፣ ከመፃፍህ በፊት ፣ከወንድሞችህ ጋር አብረህ ከመሰባሰብህና ከመጨዋወትህ በፊት፣ ስጦታን ከመስጠትህ በፊት በሁሉ በፊት ቆም ብለህ #ልብህን መዝነው፣ በውስጥህ #ፍቅር ከሌለህ ምንም አታድርግ #ኢየሱስ ከፍቅር ውጪ ምንም አድርጎ አያውቅም እኛንም ምንም እንድናደርግ አይፈልግም"
(🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 )
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯
|
sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯

19/08/2026
የመግደል ሙከራ ፈፅሞ ለዓመታት ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።ተከሳሽ አሳየው በዛብህ በየካ ክፍለ ከተማ የካ አባዶ አካባቢ በቀደመች የፍቅር ጓደኛው ላይ በጥቅምት ወር 2012 ...
19/08/2026

የመግደል ሙከራ ፈፅሞ ለዓመታት ሲፈለግ የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ።

ተከሳሽ አሳየው በዛብህ በየካ ክፍለ ከተማ የካ አባዶ አካባቢ በቀደመች የፍቅር ጓደኛው ላይ በጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም የመግደል ሙከራ ወንጀል ፈፅሟል።

ተበዳይ ግንኙነታቸውን አቋርጣ የራሷን ሕይወት መምራት በመጀመሯ በተከሳሹ ላይ ባደረበት የቅናት ስሜት የተነሳ ወደ መኖሪያ ቤቷ ሄዶ ጥቃት አድርሶባታል።

ተከሳሹ ተበዳይን በቦክስ ከደደበደባት በኋላ የሽንኩርት መክተፊያ ቢላዋ በማንሳት ጎኗንና እጇን በመውጋት ከባድ ጉዳት አድርሶባት መሰወሩን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ በሰውና በሕክምና ማስረጃ የተደገፈ መዝገብ አደራጅቶ ለአቃቤ ሕግ ያስረከበ ቢሆንም፣ ተከሳሹ በወቅቱ በተፈቀደለት የዋስትና መብት ከወጣ በኋላ በፍርድ ቤት ቀጠሮው ሳይገኝ ቀርቷል።

ጉዳዩን በሌለበት የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት፣ በጥቅምት ወር 2015 ዓ.ም በተከሳሹ ላይ የ7 ዓመት ከ8 ወር ፅኑ እስራት ውሳኔ አስተላልፎበታል።

ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ፖሊስ ላለፉት ሦስት ዓመታት ባደረገው ክትትል ተከሳሹን በቁጥጥር ስር በማዋል ወደ ማረሚያ ቤት አስረክቧል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ወንጀል ፈፅመው ከሕግ ለማምለጥ የሚደብቁ ግለሰቦችን ለሕግ ለማቅረብ ሕብረተሰቡ የሚያደርገውን አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል።

Via የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ

ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! ለእናት እና ለልጃቸው የተዘረጋው የደግነት እጅ ለእናት እና ብሩህ ልጃቸው ኤብሴ፣ማህበረሰባችን አስደናቂ የሆነ የፍቅር እና የደግነት እጅ ዘርግቶላቸዋል።የእናትን ድካ...
19/08/2026

ሁሉም ነገር ለበጎ ነው! ለእናት እና ለልጃቸው የተዘረጋው የደግነት እጅ

ለእናት እና ብሩህ ልጃቸው ኤብሴ፣ማህበረሰባችን አስደናቂ የሆነ የፍቅር እና የደግነት እጅ ዘርግቶላቸዋል።

የእናትን ድካም ለማቃለል እና ስራቸውን ለማግዝ ዩኒቨርሳል ታክሲ እና ዴሊቨሪ አዲስ ዘመናዊ የልብስ ማጠቢያ ማሽን በስጦታ ያበረከተላቸው ሲሆን፣ በተጨማሪም የልጃቸውን የኤብሲንም ሙሉ የትምህርት ወጪ በመሸፈን የትምህርት ቤት ዝውውሯን ሙሉ በሙሉ ዋስትና ሰጥተዋል!

ይህ ድንቅ የደግነት ተግባር ማህበረሰባችን በአንድነት ሲቆም በፍቅር፣ በስኬት እና በተስፋ ማንኛውንም ፈተና ማሸነፍ እንደሚቻል ማረጋገጫ ነው።

ለአዲሱ ተስፋ እና ብሩህ ወደፊት መልካም ይመኝላቸው!

በድጋሚ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው

🙏🙏🙏

በደብረ ብርሃን የቡሄ በዓል ባህላዊና መንፈሳዊ እሴቶቹን ጠብቆ በድምቀት ተከበረ # Great Mention TV Ethiopia  I በደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል መንፈሳዊና...
19/08/2026

በደብረ ብርሃን የቡሄ በዓል ባህላዊና መንፈሳዊ እሴቶቹን ጠብቆ በድምቀት ተከበረ

# Great Mention TV Ethiopia I በደብረ ብርሃን ከተማ የቡሄ (ደብረ ታቦር) በዓል መንፈሳዊና ባህላዊ እሴቶቹን በጠበቀ መልኩ በተለያዩ ህዝባዊና ሃይማኖታዊ ዝግጅቶች በከፍተኛ ድምቀት መከበሩ ተገለጸ።

ባለሐገሩ አስጎብኚ ድርጅት ከደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ይህ በዓል ጥሪ የተደረገላቸው በርካታ እንግዶች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና የሃይማኖት አባቶች በተገኙበት በታላቅ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል። በስነ-ስርዓቱ ወቅት የቡሄ በዓል መገለጫ የሆኑት የጅራፍ ማጮህ፣ የሙልሙል ዳቦ መጋገር እና ስጦታ፣ የችቦ መለኮስ እንዲሁም የቡሄ ጨዋታዎችና ባህላዊ ዜማዎች በስፋት ቀርበዋል።

በፕሮግራሙ ላይ እንደተገለፀው በዓሉ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ ከማከበር ባለፈ ለቀጣይ የቱሪዝም እንቅስቃሴና ለባህል እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። ሁነቱ የአካባቢውን መልካም ገጽታ ከማሳወቅ ባሻገር የማህበረሰቡን አንድነትና ወንድማማችነት የበለጠ ያጠናከረ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

በሥነ ሥርዓቱ ላይ የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸትን ጨምሮ የከተማው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት የሥራ መሪዎች፣ የባላገሩ አስጎብኚ ድርጅት አመራሮች እና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዋል።

19/08/2026

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Seunet Alemo, Ariki Nugus Tselm, Debela Anbes Debela Bayisa, Dejene Bayisa Guta, Rihad Ahamad, Wonde Eriso, Ebisa Bayesa, Kedir Ali Ali, Terefe Lulu, Eth Elshawariya, Tezra Bejeda, Sidistu Siyam Husen, Surafel Mulu, Nigusu Atnafu, Jigsaa Tadese Tadese Ganati, ለምለሚቱ ለሚ, Tamene Bayessa, Yøw Džž Abđŭ, Meles Yihdego, Abdulaziz Nurye, የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን., Yezid Abdurahman, Yeshambl Amsal, Nesra Kedir, Nuradin Haji, Abdu Ayaleaw, Karayu K Dassa, Mebrate Zewdu, Belachew Ameya, Nure Hameyu, Seid Hussen Ali, Teklu Getachew, Rana Rashad Bashir, Tiifuu Yandoo, Nigus Golja, መሰፍን በየኔ ባዛ, Semahegn Tewabe, Teshome Abdela, Kirubel Molla, Agood Love, Jiine Nus Yosef Ibsa, Lamesa Etana, Bonsa Olana, Abdulkerim Tadese, Endirias Simbire, Tekle Gezahegn, Aye Z Sun, Hayatu Hundita, Mearg Hiwot, Niema Ahmed

"እናታችን ናፈቀችን" ብለው ተሚማን ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የሳዑዲ መንትዮችነገሩ እንዲህ ነው፤ እህታችን ተሚማ እተፋ ትባላለች። በሳዑዲ ዓረቢያ ለአሥር ዓመታት ያህል በማዳም ቤት በሞግ...
19/08/2026

"እናታችን ናፈቀችን" ብለው ተሚማን ፍለጋ ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የሳዑዲ መንትዮች

ነገሩ እንዲህ ነው፤ እህታችን ተሚማ እተፋ ትባላለች። በሳዑዲ ዓረቢያ ለአሥር ዓመታት ያህል በማዳም ቤት በሞግዚትነት ሥራ ላይ ተሰማርታ ስታገለግል የኖረችው በፍቅርና በታላቅ መከባበር ነበር። የቤተሰቡ አባላት ሁለት መንትያ ልጆች ነበሯቸው፤ ልጆቹም የኦቲዝም (Autism) ሁኔታ ይገኝባቸው ነበር። እህታችን ተሚማ እነዚህን ህፃናት ለ10 ዓመታት ያህል ልዩ በሆነ የእናትነት ፍቅርና እንክብካቤ ስታሳድጋቸው ቆየች።

ጊዜው ደርሶ የገዛ ሀገሯ ተመልሳ ኑሮዋን ለመቀጠል ወደ ኢትዮጵያ ስትመለስ፣ ፍቅራቸው ግን በሐገር ርቀት አልተገደበም። ስልክ ይደዋወሉ ነበር፤ ነገር ግን የስልክ ድምፅ ብቻ የህፃናቱን ናፍቆት ሊወጣው አልቻለም። የልጆቹ ወላጆች «ተሚማ እኛም ናፈቅሽን፤ ልጆቻችንም ቀን ከሌሊት እያለቀሱ 'እናት እናታችን ናፈቀችን' እያሉ አስቸገሩን» በማለት በፍቅር ታስረው ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ወሰኑ።

እናም ከሁለት ሳምንት በፊት ህፃናቱን አስከተው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መጡ።
እሷም በክብራቸው ልክ በፍቅርና በደስታ ተቀበለቻቸው። እነሱም ቀን ቀን ተሚማ ቤት እየወጡና ከእሷ ጋር ከተማዋን እየጎበኙ፣ ማታ ማታ ደግሞ ወደ ማደሪያ ሆቴላቸው እየተመለሱ ለአንድ ሳምንት ያህል በፍቅር አብረው አሳለፉ። በመጨረሻም የናፍቆት እራባቸውን ተወጥተው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ይህን ልብ የሚነካ እውነተኛ ታሪክ ያነሳሁበት ምክንያት፣ ሰሞኑን የሀገራችን ስም በሳዑዲ ዓረቢያ ወንድሞቻችን ዘንድ በመጥፎ እየተነሳ ባለበት ወቅት፣ የእውነትና የእውነተኛ ፍቅር መገለጫ የሆነውን የኢትዮጵያውያንን ደግነትና መልካም ስብዕና ለማስታወስ ነው።

Via Mame Yasin

🙏🙏🙏

Feestivaalli UKEE Wanciitti KabajameFeestivaalli Ukee, Hagayya 10,2026 Wanciitti kabajameera.  dhaabbanni Piromooshinii ...
18/08/2026

Feestivaalli UKEE Wanciitti Kabajame

Feestivaalli Ukee, Hagayya 10,2026 Wanciitti kabajameera. dhaabbanni Piromooshinii Aartii aadaa dagatame qoranno irratti taasisun ayyaana UKEE /TAABOREE sadarkaa Feestivaalaatti olguddisun bifa waalatawaa ta’en waggaa waggaan kabajamaa akka addunyaatti akka beekamu gochuuf tokko jedhee imalasaa eegaleera.

Feestivaalli kunis,
~Aadaa bade deebisuuf
~Qorannoo duudhaa Oromoo ganamaaf haala mijeessuuf
~Daa’imman egeree biyyaa ta’an araddaa tokkotti akka wal argan haala mijeessun tokkummaaf jaalala aadaa fi seenaa isaani akka walirraa baran carraa uumuf
~Hawwata Tuurizimii ta’ee akka tajaajilu haala mijeessuufi kanneen kana fakkaataniif bu’aa akka qabaatutu akeekama.

Qaamoleen kallattii garaagaraan hojii kana nu waliin hojjechuu barbaaddanis, gamanumaan waamicha isiniif gochuu feena. Galatoomaa!
Borati art promotion
Visit Oromia
Back to the future!

''የደከመ ማህበረሰብ ብየ ስሳደብ የአዕምሮ ህመም ነበረብኝ'' አሁን ታክሜ ተሽሎኛል....... ሚኮ ማይክበመሴ ሾው ቀርቦ፣ የሚኮ ማይክ (Miko Mike) ድርጊትና የሰጠው ማስተባበያ አሳዛ...
18/08/2026

''የደከመ ማህበረሰብ ብየ ስሳደብ የአዕምሮ ህመም ነበረብኝ'' አሁን ታክሜ ተሽሎኛል....... ሚኮ ማይክ

በመሴ ሾው ቀርቦ፣ የሚኮ ማይክ (Miko Mike) ድርጊትና የሰጠው ማስተባበያ አሳዛኝ እና ተጨማሪ ኃላፊነት የጎደለው ድርጊት ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብን “የደከመ ማህበረሰብ” ብሎ መስደብ እና የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም ለብሶ መጫወትና ለቪዲዮ ማታለያ ሲያደርግ ቆይቶ ''ይባስ ብሎ፣ ድርጊቱ ያመጣውን ህዝባዊ ቁጣና ተጠያቂነት ለመሸሽ “የአእምሮ ህመምተኛ ነበርኩ” የሚል የሰካራም ማስተባበያ ማቅረብ ህዝቡን የመናቅ ውጤት ነው።

አእምሮ ህመም በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን የሚታገሉት፣ የህክምና እና የእርዳታ እንክብካቤ የሚሻ ከባድ ጉዳይ እንጂ የሰራቸውን ወንጀልና የፈጸማቸውን የስነ-ምግባር ብልሹነት የሚደብቅበት የፖለቲካ ወይም የሶሻል ሚዲያ ጋሻ አይደለም።

የህዝብን ስሜት መጉዳትና ማቃለል በቪዲዮ ማብራሪያ ብቻ የሚታለፍ አይደለም። ማህበረሰቡን እንደፈለጉ እየሰደቡና እየተሳደቡ፣ ነገሩ ሲጠነክር ደግሞ “ታሞ ነው” በሚል ሽፋን ሊያመልጥ ተከስቷል።

ድርጊቱ ማህበረሰብን ብቻ ሳይሆን እውነተኛ የአእምሮ ህመምተኞችንም የሚያሳንስ እና የሚያዋርድ ነው። በሰራው ጥፋት ሙሉ ኃላፊነት በመውሰድ በይፋ ህዝቡን ይቅርታ ማለት በጀመርክበት መንገድ ከመሔድ ውጭ፣ የማይበላ ማስተባበያ ማቅረብ ሌላ ጥፋት ነው።

ሀሳብዎን ያካፍሉን?

ሰላም ለኢትዮጲያ
ሰላም ለህዝባችን

የአስቸኳይ ጥሪ፦ ይህንን በዓል ከአባትና እናት አልባ ልጆች ጋር እናሳልፍ! 🙏በዚህ በዓል በሰላም ደረሳችሁ!የገጼ ተከታዮችና በጎ አድራጎትን የምትወዱ መላው ማህበረሰብ፤ ይህንን በዓል አስመል...
18/08/2026

የአስቸኳይ ጥሪ፦ ይህንን በዓል ከአባትና እናት አልባ ልጆች ጋር እናሳልፍ! 🙏
በዚህ በዓል በሰላም ደረሳችሁ!
የገጼ ተከታዮችና በጎ አድራጎትን የምትወዱ መላው ማህበረሰብ፤ ይህንን በዓል አስመልክተን አቅመ ደካማ የሆኑና ቤተሰብ የሌላቸውን ልጆች ለመርዳት አንድ መርሃ ግብር አዘጋጅተናል። እውነተኛ ደስታችን የሚሆነው ያጡትን ሰዎች ደስታ ስንካፈል ነው።
ስለዚህ ሁለት ዋና ሥራዎችን ለማከናወን አቅደናል፦
🍲 1. የምግብ ድጋፍ፦ ለእነዚህ ልጆች የበዓል ምግብ ለማዘጋጀት ዶሮ፣ ዘይትና አምስት ኪሎ ዱቄት ለመግዛት።
🏠 2. የቤት እድሳት፦ በጣም የተጎዳውንና ለዝናብ የተጋለጠውን የመኖሪያ ቤታቸውን ለመጠገንና ለማደስ።
የእናንተ እርዳታ ለምን ያስፈልጋል?
ይህንን ሥራ እኔና ጥቂት ሰዎች ብቻ ማከናወን አስቸጋሪ ስለሆነ፣ የእናንተን ድጋፍ እንፈልጋለን። በአገር ውስጥና በውጭ አገር የምትኖሩ ሰዎች፣ እንዲሁም አቅሙ ያላችሁ ባለሀብቶች፣ በቻላችሁት መጠን ከጎናችን እንድትቆሙ በአክብሮት እንጠይቃለን። በገንዘብ፣ በግንባታ ቁሳቁስ (ቆርቆሮ፣ ሚስማር ወዘተ) ወይም በጉልበት ልትረዱን ትችላላችሁ።
ግልጽነት (Transparency)፦
ከእናንተ የምንቀበለው ገንዘብና ድጋፍ ሁሉ በሕጋዊና በተገቢው መንገድ ብቻ ለሥራው የሚውል ሲሆን፣ የግዢ ደረሰኞችንና የሥራውን ፎቶ/ቪዲዮ በሙሉ በዚህ ገጽ ላይ በግልጽ እናቀርባለን። እናንተ የምትሰጡት እርዳታ በቀጥታ ለእነዚህ ልጆች ይደርሳል።
💳 የባንክ ሂሳብ፦
የንግድ ባንክ ኦፍ ኢትዮጵያ (CBE): 1000526422728
ስም፦ SEID KEDIR
እግዚአብሔር ለምታደርጉት መልካም ነገር ይባርካችሁ፤ በእጥፍም ይመልስላችሁ!
ይህንን መልዕክት በማድረግ ለጓደኞቻችሁና ለሌሎች ሰዎች እንድታደርሱልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
#በጎአድራጎት #ድጋፍ #በዓል #የልጆችእርዳታ

Address

Ethiopia
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Great Mention TV Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share

Category