
18/06/2023
| "እሱን ቀድሜ ሜዳልያ ብወስድ እናቴ ምን ትለኛለች?"🥰
⭕ስፔናዊው አትሌት ኢቫን ፈርናንዴዝ እና ኬንያዊው አትሌት አቤል ሙታይ በአንድ የሀገር አቋራጭ የሩጫ ውድድር ላይ ለሜዳልያ ፉክክር እያደረጉ ነበር። ኬንያዊው አቤል ሙታይ ውድድሩን እየመራ ስፔናዊው ኢቫን ፈርናንዴዝ ደግሞ ሁለተኛ ሆኖ እየተከተለው ትንቅን ላይ ነበሩ።
በድንገት ግን ከውድድሩ ፍጻሜ መስመር ላይ ሊደርሱ በግምት 10 ሜትር ገደማ ሲቀራቸው ኬንያዊው የውድድሩ መሪ አቤል ሙታይ ውድድሩን ያጠናቀቀ መስሎት በስህተት ውድድሩን አቋርጦ ቆመ:: ይህንን ክስተት የተመለከተው ስፔናዊው ሯጭ አቤል ሙታይ ውድድሩን እንዲቀጥል እና መስመሩን እንዲያቋርጥ ከኃላው ሆኖ ይጮህበት ጀመር።
የስፓኒሽ ቋንቋ ጆሮውን ቢቆርጡት የማይሰማው አቤል ሙታይ ምን እንደተፈጠረ ሊገባው አልቻለም:: በመሆኑም ስፔናዊው ሯጭ ኢቫን መስመሩን አቋርጦ ውድድሩን ከማሸነፍ ይልቅ አቤል ሙታይን በመግፋት ውድድሩን አሸንፎ የወርቅ ሜዳልያውን እንዲያሸንፍ አደረገው
ውድድሩ መጠናቀቁ ተከትሎ አንድ ጋዜጠኛ ለኢቫን ጥያቄ አቀረበለት
"ለምን እንደዚያ አደረግክ?"
"የእኔ የህይወት ህልም አንዳችን ሌላችንን በመግፋት አሸናፊ እንድንሆን ማገዝ ነው:: ህልሜ እርስ በእርሱ ተደጋግፎ አሸናፊ የሚሆን ማህበረሰብ ተፈጥሮ ማየት ነው" ሲል መለሰለት
"ለምን ኬንያዊው እንዲያሸንፍ አደረግክ" ደግሞ ጠየቀው
"እኔ እንዲያሸንፍ አላደረግኩትም:: እሱ መጀመርያም ሊያሸንፍ ነበር"
"ግን እኮ አሸንፈህ የወርቅ ሜዳልያውን ማጥለቅ ትችል ነበር" ጋዜጠኛው አሁንም ጠየቀው
"ድል የማድረግ መርሁ እና ጣእሙ ምንድነው? እንዲህ ሆኖ የማሸንፈው ሜዳሊያ ክብሩ ምንድነው? እናቴ ይህንን ስታይ ምን ትለኛለች?" ሲል ጋዜጠኛውን አስደመመው
አሸንፍ ሌሎችም እንዲያሸንፉ አድርግ ❤️🙌🏼