01/09/2025
የበርበሬ ሰብልን የሚጎዱ ዋና ዋና የበሽታእና የተባዮች መከላከያ ዘዴዎች
1) አመዳይ (POWDERY MILDEW (Leveillula taurica))
የበሽታው ምልክቶች
በቅጠሉ የታችኛው ክፍል ላይ ተለጥፎ የሚታይ ነጭ ፓውደር (ዱቄት) መሰል ምልክት ሲሆን እየሰፋ በመሄድ ቅጠሉን ሙሉ ለሙሉ ይሸፍናል፤ የላይኛው የቅጠሉ ክፍል ቢጫ ወይም ፈዘዝ ያለ ቡናማ መልክ ያለው ጠባሳ ምልክት ያሳያል፤በዚህ በሽታ የተጠቃ ቅጠል ጫፉ ወደ ላይ መጠቅለል ይጀምራል፤
በሽታው እየጎላ ሲሄድ ቅጠሉ ይረግፍና የበርበሬውን ፍሬ ለጸሀይ ያጋልጠዋል፤ ይህም በፍሬው ላይ በጸሀይ የመጠበስ
ምልክት እንዲያሳይ ያደርገዋል
የተቀናጀ ተባይ የመከላከል ዘዴ (IPM)
የማሳ አሰሳና ክትትል በማድረግ የበሽታውን ምልክቶች በትክክል መለየት፤ በተለይ አየሩ ሞቃት እርጥበት አዘል በሚሆንበት ወቅት፤ አረምን በየጊዜው ተከታትሎ በማስወገድ ለበሽታ መነሻና
መተላለፊያ እንዳያገለግሉ የማሳውን ንጽህና መጠበቅ፤ ዋንኛው የዚህ በሽታ መከላከያ መንገድ የኬሚካል ርጭት ነው፤
የበሽታ መከላከሉ ሂደት ውጤታማ እንዲሆን በኬሚካል ርጭት ወቅት የተክሉን ቅጠል ሙሉ ለሙሉ እንዲያገኝ ማድረግ ያስፈልጋል፤
የተመዘገቡና ለዚህ በሽታ የሚመከሩ ኬሚካሎችን ብቻ መጠቀም፤
• Kresoxim-methyl 500 g / l
• Trifloxystrobin + Tebuconazole
• Triadimefon 500 g a.i./kg.
2) የበርበሬ ስር አበስብስ በሽታ (PEPPER ROOT ROT (Phytophtora capsici))
የበሽታው ምልክቶች
ችግኞች እንዳይበቅሉ ያደርጋል ወይም ከበቀሉ ወዲያው እንዲሞቱ ያደረጋል፤
ወደ አፈሩ ወረድ ብሎ የሚገኘው የተክሉ ግንድ ላይ ጠቆር ያለና የተኮማተረ ጠባሳ ምልክት ይታያል፤አፈሩ እርጥብ ቢሆንም ተክሎቹ ከአደጉ በኋላ በማንኛውም የእድገት ደረጃ ላይ ጠውልጎ ሊሞት ይችላል፤በሽታው እየተባባሰ ሲሄድ ቅጠሉ ሙሉ ለሙሉ ሊረግፍና ተክሉም ጠውጎ ሊሞት ይችላል፤ዋናው ስርና ሌሎቹ ትናንሽ ስሮች ውሃ የቋጠረ ጥቁር ወይም ቡናማ የሆነ ምልክት ይታይበታል፤ አብዛኞቹ ስሮች ያልቁና በጣም ትንሽ ቀጫጭን ስሮች ብቻ ይቀራሉ፤
የተቀናጀ ተባይ መከላከል ዘዴ (IPM)
የማሳ አሰሳና ክትትል በማድረግ የበሽታው ምልክቶች በሽታ አምጪ ተህዋሲያኖቹን በትክክል መለየት፤ ተከላ ከማከናወናችን በፊት የአፈሩን ውሃ በደንብ ማጠንፈፍ፤ከፍ ያለ መደብ ማዘጋጀት፤
በሽታውን መቋቋም የሚችሉ ዝርያዎችን መርጦ መጠቀም፤ ከበሽታ ነጻ የሆኑ ዘርና ችግኞችን ብቻ መርጦ መጠቀም፤ አፈሩ ቀዝቃዛ በሚሆንበት ወቅት ተከላ መከናወን የለበትም፤ በችግኝ ማፍላት ወቅት የርጭት መስኖን መጠቀም የበለጠ ውጤታማ ያደርጋል፤
የስር አበስባሽ ወይም ደካማ የሆነ የውሃ ማጠንፈፍ ታሪክ ባለው መሬት ላይ ለመከላከያነት የሚያገለግሉ ጸረ-ፈንገስ ኬሚካሎችን መርጨት፤
ለዚህ በሽታ የሚመከሩና የተመዘገቡ ኬሚካሎችን ብቻ መጠቀም፤
• Mancozeb 64% + Metalaxyl 8%
በይበልጥ የሚመከሩትና ውጤታማ የሆኑ እንደ
Phosphoric acid እና Fluopicolide ያሉት ኢትዮጵያ
ውስጥ ያልተመዘገቡ ናቸው፤
3) ቆራጭ ትል (CUTWORMS (Spodoptera, various Noctuidae)
የጉዳቱ ምልክቶች
ብዙ ጊዜ ጉዳት የሚያስከትለው ተክሉ ገና በለጋነቱ እድሜ ወቅት ነው፤የችግኝ ወይም ለጋ ተክሎች ከስር ወይም አፈሩ አካባቢ ላይ
ተቆርጦ መውደቅ ምልክት፤
በምሽት ወቅት አጠቃላይ የተተከለበት መስመር ተቆርጦ ወድቆ ሊገኝ ይችላል፤
ትሎቹ