Ethiopian Christian Media

Ethiopian Christian Media We Share Gospel!

😊
29/06/2025

😊

ተመራቂዎቹ ወንጌል እየሰበኩ ነው"ኢየሱስ ያድናል!" "መዳን በሌላ በማንም የለም!"
21/06/2025

ተመራቂዎቹ ወንጌል እየሰበኩ ነው
"ኢየሱስ ያድናል!"
"መዳን በሌላ በማንም የለም!"

ስደክም ታበረታኛለህ እግዚአብሔር ሆይ ። ትጥቅ እንዳልፈታ ለልቤ ጀግንነትን ፤ ከአላማዬ እንዳልስት ለእግሮቼ ፅናትን ፤ በሃሳቤ እንዳልደክም ለጉልበቴ ሃይልን ሰጥተኸኛል። ጉዞው የአንተ ነው ...
19/06/2025

ስደክም ታበረታኛለህ እግዚአብሔር ሆይ ። ትጥቅ እንዳልፈታ ለልቤ ጀግንነትን ፤ ከአላማዬ እንዳልስት ለእግሮቼ ፅናትን ፤ በሃሳቤ እንዳልደክም ለጉልበቴ ሃይልን ሰጥተኸኛል።

ጉዞው የአንተ ነው ሳንካውን ታነሳልኛለህ ፤ ደግሞ እኔም እራመዳለሁ። ይቀጥላል አሁንም ይቀጥላል አገለግልሃለሁ። እንዳገለግልህ በሕይወት እኖራለሁ በሕይወት እንድኖር ደግሞ አገለግልሃለሁ።

" ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአብሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።"
(መዝ 23: 6)

Endalkachew Zenebe

10/06/2025

“ሰው ዝም ብሎ የእግዚአብሔርን ማዳን ተስፋ ቢያደርግ መልካም ነው።”
— ሰቆ. 3፥26

ኢየሱስ በቂ ከበቂም በላይ ነው 🙌---------------------------------------የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ተጫዋች
09/06/2025

ኢየሱስ በቂ ከበቂም በላይ ነው 🙌
---------------------------------------
የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ተጫዋች

ወደ ጎን ያየንበት ዘመን ተሰናብቶ፣ የሸንበቆ ምርኩዝ ታጥፎ፣ ሰዋዊ ግድግዳ ተንዶ፣ ከልካይ ወደሌለው ሰማይ ቀና ብለናል። አቤት ደግነት፣ አቤት ርህራሄው፣ አቤት ፍቅሩ፣ ግሩም!!! ዝቅ ብሎ ...
06/06/2025

ወደ ጎን ያየንበት ዘመን ተሰናብቶ፣ የሸንበቆ ምርኩዝ ታጥፎ፣ ሰዋዊ ግድግዳ ተንዶ፣ ከልካይ ወደሌለው ሰማይ ቀና ብለናል። አቤት ደግነት፣ አቤት ርህራሄው፣ አቤት ፍቅሩ፣ ግሩም!!!

ዝቅ ብሎ ከፍ አደረገን፣ ከማዳኑ በላይ ጉዳይ፣ ከደሙ ሚልቅ ቋንቋ የለም። ይህ ስለ ሁሉ የፈሰሰ የአዲስ ኪዳን ደም ነው፣ ያመኑበት ሁሉ የሚድኑበት፣ የሰው ሳይሆን የስላሴ አዋጅ ነው።

በተቋማት በጎነት፣ በኮሚቴ ውሳኔ አልተቀበልነውም፣ እንዲሁ በፀጋው እንጂ። ፀሐፍትና ፈሪሳውያን ወደ ተፀየፉአቸው እንደመጣ፣ በልጁ የሆነው ፅድቅ በወደቅንበት አገኘን፣ ነፃም አወጣን። ስለዚህ ለሞተልንና ለተነሳልን፣ በቅድስና እንኖራለን። ክብር ለወደደን!

Endalkachew Zenebe

 ..😭😭ዘማሪት የምስራች ከዚህ አለም በሞት ተለይታ ወደ ጌታ ሄዳለች። እግዚአብሔር ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን ያድርግ!እህታችን ጨጓራዋ አከባቢ ከነበረው 4ኛ ደረጃ ካንሰር በተዓ...
02/06/2025

..😭😭

ዘማሪት የምስራች ከዚህ አለም በሞት ተለይታ ወደ ጌታ ሄዳለች። እግዚአብሔር ለቤተሰቦቿ፣ ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን ያድርግ!

እህታችን ጨጓራዋ አከባቢ ከነበረው 4ኛ ደረጃ ካንሰር በተዓምራት ተፈውሳ እግዚአብሔርን እያመሰገንን መቆየታችን ይታወሳል ከጊዜያት በኋላ ቼካፕ ስታደርግ ጀርባዋ አከባቢ ሶስተኛው አጥንት ላይ እና ሳንባዋ ላይ ካንሰር ከባድ ሳል ታክሎበት በፍጥነት ፅኑ ሕሙማን ክፍል እንድትገባ የተደረገች ቢሆንም ከደቂቃዎች በፊት ወደ ጌታ መሄዷ ታዉቋል።

እግዚአብሔር የወደደውን አደረገ 😪

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሥነ ሥርዓት የአመራር ርክክብ አካሄደች!---------------------------------የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ግንቦት 22...
30/05/2025

የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሥነ ሥርዓት የአመራር ርክክብ አካሄደች!
---------------------------------
የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ግንቦት 22 ቀን 2017 ዓ.ም በደማቅ ሥነ ሥርዓት የአመራር ርክክብ አካሄደች፡፡

ተሰናባችና አዲስ የተመረጡ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የብሔራዊ ቦርድ፣ የሥራ አስፈጻሚ አባላት፣ ከኤስ.አይ.ኤም ኢትዮጵያና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በታደሙበት ይኸው መርሃ ግብር በዋናው ጽ/በት ቅጥር ጊቢ ውስጥ በደማቅ ሁኔታ ተካሂዷል፡፡

የመርሃ ግብሩን መድረክ የመሩት አዲሱ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ምክትል ዋና ጸሐፊ ዶ/ር ወንድሙ አበበ ሲሆኑ አጠቃላይ ውሎው በጸሎትና በዝማሬ ተጀምሯል፡፡

በመቀጠልም መጋቢ ቴዎፍሎስ ተስፋዬ ቃለ እግዚአብሔርን ያካፈሉ ሲሆን፣ በመልእክታቸውም ለቤተ ክርስቲያን ራዕዩና ተልዕኮ ስኬት በጋራ መስራት እንደሚገባ፣ ቤተ ክርስቲያን ለተልእኮ መፈጠሯን እንጂ ተልእኮው ለቤተ ክርስቲያን አለመፈጠሩን፣ እውነትን በፍቅር በመነጋገር ግልጽነትን ማስፈንና፣ ከሁሉ አጀንዳ አስቀድሞ ለነፍሳት ጉዳይ ልዩ ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በመቀጠልም የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ዋና ጸሐፊ የሆኑት ዶ/ር ስምዖን ሙላቱ ባስተላለፉት መልእክት ተሰናባችና አዲስ የተመረጡ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፕሬዚዳንቶች፣ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ የብሔራዊ ቦርድና የሥራ አስፈጻሚ አባላትን ከልብ አመስግነዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው አያይዘውም ከተሰናባች አገልጋይ መሪዎች ጋር የነበራቸው ቆይታ ፍሬያማና ሰላማዊ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ዋና ጸሐፊው ተሰናባቹን የቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጣሰው ገብሬን ወደ መድረክ ጋብዘዋል፡፡

ዶ/ር ጣሰው ገብሬ በበኩላቸው የአገልግሎት ቆይታቸው ሰላማዊና ፍሬያማ እንደነበር አስታውሰው፣ ይህ ማለት ግን ደካማ ጎኖች አልነበሩንም ማለት አይደለም ብለዋል፡፡

ዶ/ሩ ገለጻቸውን በመቀጠል ባለፉት ስድስት የአገልግሎት ዓመታት የሰሯቸውን ፍሬያማ ሥራዎች በዝርዝር አስታውሰው፣ ያልተጠናቀቁትን ዕቅዶች ተረካቢው አመራር ዳር እንዲያደርሳቸው አደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ወደፊት ሊከናወኑ ይገባቸዋል ያሏቸውን ዝርዝር ዕቅዶች ለጉባዔው ተሳታፊዎች አስታውቀው በምስጋና የስንብት ቃላቸውን ደምድመዋል፡፡

በመቀጠል መድረክ የያዙት አዲሱ የኢትዮጵያ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት ዶ/ር ስምዖን ሔሊሶ የቀድሞ አመራሮች የጀመሯቸው ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመግለጽ አዳዲስ ተቋማዊ ለውጦችን ለማምጣት እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡

ዶ/ሩ ገለጻቸውን በመቀጠል አገልግሎቱን የሚረከበው አዲሱ አመራር የተሰናባቸ አመራሮችን እገዛ፣ ድጋፍና ምክር እንደሚሻ አሳስበዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ከኤስ.አይ.ኤም ኢትዮጵያ ዳይሬክተር ተጋብዘው የተገኙት ወ/ሮ ሰራዊት ተከተል በአጋርነታቸው እንደሚቀጥሉ የሚያስረግጥ ንግግር አድርገዋል፡፡

በመጨረሻም ለተሰናባቹ የቤተ ክርስቲያኒቱ ፕሬዚዳንት ለዶ/ር ጣሰው ገብሬ፣ ለብሔራዊ ቦርድ እና የሥራ አስፈጻሚ አባላት የምስጋና ሥጦታ እና የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸው መርሃ ግብሩ በጸሎት ተጠናቋል!

27/05/2025

የአብስራ ተክሉን #እናሳክመው.. please ቅዱሳን እንጸልይለት! በምንችለው ሁሉ ደግሞ በገንዘብም ለሌሎች በማድረግም እንርዳው! የባንክ አካውንቱ ከታች አለ

👇
ንግድ_1000626591748
አቢሲኒያ_217812666
ብርሃን_1010883494813
ቴሌ ብር_0939196996

በጣም  የምንወደውና የምናከብረው የቃሉ ሰባኪና አስተማሪ፥ ወንድማችን ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን (ያሬዶ)፣ ሰባተኛ መጽሐፉ የሆነውን “ #እውነተኛ  #ክርስቲያናዊ  #ኑሮ”  የተሰኘ የሐዋርያው ...
27/05/2025

በጣም የምንወደውና የምናከብረው የቃሉ ሰባኪና አስተማሪ፥ ወንድማችን ወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን (ያሬዶ)፣ ሰባተኛ መጽሐፉ የሆነውን “ #እውነተኛ #ክርስቲያናዊ #ኑሮ” የተሰኘ የሐዋርያው ያዕቆብ መልእክት - ትንታኔን በቅርቡ ለንባብ ሊያበቃ በመሆኑ በጣም ደስ ብሎልናለ።

በብዙ ክንውን መጽሐፉ ወደ እጃችን ያስገባት ዘንድ ሁላችንም በጸሎታችን ከወንድማችን ጋር እንሁን።

አድርጉ ቅዱሳን!

27/05/2025

ጴንጤ ሞራ ገላጭ ሳይሆን ነው!
ኢየሱስ ብቻውን በቂ ነው!

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 21:00 - 10:00
Tuesday 21:00 - 10:00
Wednesday 21:00 - 10:00
Thursday 21:00 - 10:00
Friday 21:00 - 10:00
Saturday 21:00 - 10:00
Sunday 21:00 - 10:00

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Christian Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share