Deginet Demeke ze bata

Deginet Demeke ze bata 0933055802

✍️ይነበብ ሼር( Share share በማድረግም ይተባበሩ ውድ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተለያዩ የሀገራችን ክፍልና በባህር ማዶ የምትገኙ በከምባታ ጠምባሮና አላባ ሀገረ ስብከት በጠምባሮ ልዩ...
10/06/2025

✍️ይነበብ ሼር( Share share በማድረግም ይተባበሩ

ውድ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን በተለያዩ የሀገራችን ክፍልና በባህር ማዶ የምትገኙ በከምባታ ጠምባሮና አላባ ሀገረ ስብከት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የምትገኘው የጎፎሬ ደብረ መንክራት በአታ ለማርያም ቤተክርስቲያን በእናንተው ድጋፍና ትብብር የተለያዩ ሥራዎች ተከናውኗል።

ለዚህም መልካም ልግስነችሁ በልዑል እግዚአብሔርና በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እናመሰግናለን።

👉የተከበራችሁ ውድ ኦርቶዶክሳውያን በአሁን ጊዜ ለይ በተለይም የገጠሪቷ ቤተክርስቲያን ደጇ እንድከፋትና እንድሁም ምዕመናን የአገልግሎቱ በረከት ተካፋዮች እንድሆኑ እየተደረገ ያለው ድጋፍ የሚደነቅ ነውና ለዚህም የጎፎሬ ደብረ መንክራት በአታ ለማርያም ቤ/ክ ተጠቃሸ ነች።

👉ይችን የተዳከመችውን የበአታ ለማርያም መቃኞ እናንተን ተስፋ በማድረግ በአድስ መልኩ እየተሠራች ትገኛለች ይሁን እንጅ በእናንተው በተገኘው ገንዘብ የፓድና ኮሎን ሙሌት ተጠናቆ ለዙሪያ ግንባታ የሚሆን ድንጋይ ለመቅረብ ከለመቻላችን የተነሳ ሥራው ተቋርጧል!!!!

👉የተከበራችሁ ውድ ኦርቶዶክሳውያን በተለያዩ የሀገራችንም ሆነ የአለማችን ክፍል የምትገኙ የተለመደውን ድጋፍና ትብብር እንድታደርጉ በልዑል እግዚአብሔርና በእናቱ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም እንማጸናለን!!!

👏እነሆ፥ እግዚአብሔር ለመቅደስ የሚሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መርጦሃልና ጠንክረህ ፈጽመው።"
ዜና መዋዕል ፳፰፥፲ /28፥10/

የእግዚአብሔርን ቤት እንስራ፣ ከበረከቱም ተካፋይ እንሁን !!!

👏የጎፎሬ ደብረ መንክራት በዓታ ለማርያም ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ

👉የባንክ አካውንት፥
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ /CBE/
1000624326281
ዓባይ ባንክ
362111107991610 (አጭር ቁጥር 10799161)

👉 ለበለጠ መረጃ የህንጻ አሰሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲያቆን ደግነት- +251933055802
+251911414852
👏👏👏ሼር ሼር ሼር እናድርግ !!!!

✍️ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ "ችግሮች በሰላማዊ ውይይት" እንዲፈቱ እና "ሀገር እፎይታ እንድታገኝ" ጠየቁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማት...
14/05/2025

✍️ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ "ችግሮች በሰላማዊ ውይይት" እንዲፈቱ እና "ሀገር እፎይታ እንድታገኝ" ጠየቁ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የሚያግባቡ ጉዳዮች ተፈልገው "ችግሮችን በሰላማዊ ውይይት" እንዲፈቱ በማድረግ "እናት ሀገር እፎይታ እንድታገኝ" እንዲደረግ ጠየቁ።

"በተለያየ ምክንያት" ከሲኖዶሱ የወጡ ወገኖች እንዲመለሱ ማድረግ የቤተ ክርስቲያኗ ሲኖዶስ ጉባኤ "ተቀዳሚ ተልዕኮ" እንደሆነም ፓትርያርኩ አስታውቀዋል።

የቤተ ክርስቲያኗ ፓትርያርክ ይህንን ጥሪ ያስተላለፉት ረቡዕ ግንቦት 6/2017 ዓ.ም. በተጀመረው ዓመታዊ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።

ዛሬ የተጀመረው ይህ ጉባኤ፤ የቤተ ክርስቲያኗን "መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና አስተዳደራዊ" አፈጻጸሞች "በመገምገም ለቀጣዩ ጊዜ የሥራ አቅጣጫን" የሚያስቀምጥ እንደሆነ ፓትርያርኩ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልጸዋል።

አቡነ ማትያስ፤ በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሁሉም የዓለም ክፍሎች እንደምትገኝ መናገራቸውን በቤተ ክርስቲያኗ መገናኛ ብዙኃን ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተሠራጨው የፓትርያርኩ ንግግር አመልክቷል!!!!

✍️"ከመቸውም ጊዜ በላይ በመሥራት ለእግዚአብሔር መታዘዘ፣ሕዝቡንም ማገልግል ይገባናል!"፡-ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ(ግንቦት 06 2017 ዓ.ም)ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያር...
14/05/2025

✍️"ከመቸውም ጊዜ በላይ በመሥራት ለእግዚአብሔር መታዘዘ፣ሕዝቡንም ማገልግል ይገባናል!"፡-ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

(ግንቦት 06 2017 ዓ.ም)

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬው ዕለት የጀመረውን የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ አስመልክቶ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት መግለጫ ሰጥተዋል።

ቅዱስነታቸው በመግለጫቸውም ለእኛ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተቀበልነው ጸጋ እና ሐዋርያነት እንዲሁም በተሰጠን ኃላፊነት መሠረት መለኮታዊ ጥሪያችንን በዓለም ውስጥ ላለው ሕዝበ እግዚአብሔር አገልግሎት ላይ ማዋል ከእኛ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

አክለውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምእመናን በተለያዩ ዓለም ክፍሎች የሚገኙ በመሆናቸው ሊቃነ ጳጳሳት ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ባሻገር የየአካባቢውን ሕዝብ በማስተማር የተጣለባችሁን ሐዋርያዊ ተልእኮ በትጋት እና በንቃት መወጣት ይኖርባችኋል ሲሉ በሰጡት መግለጫ አሳስበዋል፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባልተስፋፋባቸው አካባቢዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመሥራት እና ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ይኖርብናል ያሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከመቸውም ጊዜ በላይ በመሥራት ለእግዚአብሔር በመታዘዘ ሕዝቡን ማገልግል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

አያይዘውም እኛ አባቶች ያለንን ዓቅም እና ብቃት በአግባቡ በመንገዘብ ትልቅ ጸጋ የሆነውን ለፈጣሪ በቆራጥነት የሚታዘዝ ምእመንን፣ ወጣቶችን እና ካህናትን ከጎናችን በማድረግ በሐቅ፣በቅንነት፣በትጋት እና በታማኝነት ሕዝበ እግዚአብሔርን በአባትነታችን ማገልገል ይጠበቅብናል ብለዋል በመግለጫቸው፡፡

ኢትዮጵያ ወደ ተሻለ ልማት፣ዕድገት እንድትሻገር እንዲሁም ከሰላም እጦት የተነሣ እየተጎዳ ያለው ሕዝብ ሰላም፣ፍትሕ እንዲያገኝ በጸሎት፣በትምህርት እና በምክር ተግተን መሥራት አለብን ለዚህም ሁሉን በሚያግባባ ሁኔታ በሰላማዊ መንገድ ውይይት በማካሄድ ችግሮችን መፍታት እንደሚያስፈልግ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊ፣ማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በመገምገም ቀጣይ የሥራ አቅጣጫን ለማስቀመጥ የርክበ ካህናቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖናዊ ጉባኤ መካሄድ ተጀምራል።

👉ለገጠሪቷ የጎፎሬ ደብረ መንክራት በኣታ ለማርያም ቤተክርስቲያን እንድረስለት!!! ✍️በአታ ለማርያም ትጣራለች  ልጆቼ ድረሱልኝ ትላለች    በከምባታ- ጠምባሮና አላባ ሀገረ ስብከት በጠምባሮ...
11/05/2025

👉ለገጠሪቷ የጎፎሬ ደብረ መንክራት በኣታ ለማርያም ቤተክርስቲያን እንድረስለት!!!

✍️በአታ ለማርያም ትጣራለች ልጆቼ ድረሱልኝ ትላለች
በከምባታ- ጠምባሮና አላባ ሀገረ ስብከት በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጎፎሬ ደብረ መንክራት በዓታ ለማርያም ቤተክርስቲያን
# #100 ብር ጀምሮ ለበዓታ እናታችን 🤲🤲ቤተመቅደስ መሣሪያ
#ሥራ ፓድና ኮሎን ተሞልቶ ድንጋይና አሻዋ እንድሁም ጣጣር በማጣት ተቋርጧል
ጥቂት ምዕመናንና አንድ ካህን ብቻ የሚገኙበት በመብረቅ የተካለለችው ተአምራዊቷ የጎፎሬ ደብረ መንክራት በኣታ ለማርያም ቤተ-ክርስቲያን

1000624326281 ንግድ ባንክ
0933055802 ስልክ
0911414852
❤ሼር ሼር ሼር እናድርግ!!!!!

✍️ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ።ሚያዚያ ፲፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ; አዲስአበባ -ኢትዮጵያ +++++++++++++...
23/04/2025

✍️ቋሚ ሲኖዶስ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ቅድስት ድንግል ማርያምን በማስመልከት ባስተላለፉት ትምህርት ዙሪያ ተወያየ።
ሚያዚያ ፲፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም ; አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
+++++++++++++++++++++++++++++++++
ቋሚ ሲኖዶስ ዛሬ ማለዳ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ባለፈው አርብ በስቅለት ዕለት በፎኖተ ጽድቅ ቴሌቪዥን በቅድስት ድንግል ማእያም ዙሪያ ያስተላለፉትን ትምህርት በተመለከተ ውይይት አድርጓል።
ብፁዕነታቸው የተላለፈውን ትምህርት ዝርዝር ሁኔታን በመመርመርም ውሳኔ ለማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ሁሉም የቋሚ ሲኖዶስ አባላት በምልዓት በተገኙበት ለረቡዕ ሚያዝያ ፳፪ ቀን
፳፻፲፯ ዓ.ም ቀጠሮ ተይዟል።
በተያያዘ ዜና የሮም ካቶሊክ ቤተክርስቲያን መሪ በሆኑት በብፁዕ ፖፕ ፍራንሲስ ሥርዓተ ቀብር ላይ፦
ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ በየምሥራቅ ጎጃም እናጨበአውሮፓ ጀርመን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የጣልያንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቤተክርስቲያናችንን በመወከል እንዲገኙ ተወስኗል።

✍️ እንኳን   እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                ❤  ። ❤ በዚች ቀን አባታችን አዳምም ከፈጣሪው ጋር ታረቀልን በማለት "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ...
18/04/2025

✍️ እንኳን እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

❤ ።

❤ በዚች ቀን አባታችን አዳምም ከፈጣሪው ጋር ታረቀልን በማለት "ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃዶ፤ በመስቀሉ ሰላም አደረገ ትንሣኤውን ገለጠ" ሊቁ ቅዱስ ያሬድ። እያልን የተድላ፣ የደስታ ምልክት ወይም መገለጫ የሆነ ልምላሜ ያለውን ቆጽለ ሆሣዕና ወይም ቄጤማ ግጫ ይዘን የምሥራች እንባባላለን፡፡ ኤፌ. 2፥14-15 "ወዘእንበለ ምሳሌሰ ኢተናግሮሙ፣ ያለ ምሳሌ አልተናገረምና እንዳለ" ማቴ 13፥34-35 በኖኅ ጊዜም ርግብ "ሐጸ ማየ አይኅ፣ ነትገ ማየ አይኅ፣ የጥፋት ውኃ ጎደለ፣ አለቀ" እያለች ቈጽለ ዕፀ ዘይት ይዛ ለኖኅ አብስራዋለች፡፡ ዘፍ. 8፥8-11 ርግብ የካህናት፣ ኖኅ የምእመናን፣ ኖኅ እጁን ዘርግቶ ርግብን እንደተቀበላት ካህናትም በየመንደሩ እየዞሩ ክርስቶስ ተመረመረ ዲያብሎስ ታሰረ በማለት ቄጤማ ሲያድሉ ምእመናንም እጃቸውን ዘርግተው መቀበላቸው የዚህ ምሳሌ ነው፡፡ ስለዚህ አሁንም ቢገኝ የወይራ ልምላሜ ቢታጣ ግጫን እየታደልን የምሥራች መባባላችን ነፍሳት ከሲኦል ለመውጣቸው መታሰቢያ ነው፡፡ ይህን ቈጽለ ልምላሜ ይዞ ተድላ፣ ደስታ መግለጽ ከጥንት ጀምሮ ሲያያዝ የመጣ ነው እንጂ እንግዳ ነገር አይደለም፡፡ ለዚህ በመጀመሪያዪቱ ቀን ከበጎ እንጨት ፍሬን የሰሌንና የተምር ዛፍ ልምላሜ ይዛችሁ በየዓመቱ ሰባት ቀን ተድላ፣ ደስታ ታደርጋላችሁ ብሏል፡፡ ዘሌ. 23፤40-44

❤ #አክፍሎት።

❤ አክፍሎት ማለት ማካፈል፣ ማጠፍ፣ መደረብ፣ ሁለቱን ቀን አንድ አድርጎ መጾም፣ ጌታ ከተያዘበት እስከተነሣበት ድረስ ይህ ሥርዓት የመጣው በቤተ ክርስቲያናችን ትምህርት እመቤታችን፣ ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታን ትንሣኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሣኤ በመቆየታቸው ምክንያት ነው፡፡ በሀገራችን ብዙ ሰዎች ሐሙስ ማታ የቀመሱ እሑድ የትንሣኤ ዕለት ብቻ እህልና ውኃ የሚቀምሱት፤ ያልተቻላቸው ግን ዓርብ ማታ የቀመሱ እስከ ትንሣኤ ይሰነብታሉ፡፡ የሁለት ቀን ማክፈሉ እንኳ ቢከብድ ቅዳሜን ማክፈል ሥርዓት ነው፡፡ ቅዳሴው በመንፈቀ ሌሊት ስለሆነ በልቶ ማስቀደስና መቁረብ እንዳይሆን፡፡

✝ ✝ ✝
❤ ፦ "አንሰ ሰከብኩ ወኖምኩ። ወተንሣእኩ እስመ እግዚአብሔር አንሥአኒ። ኢይፈርህ እምአእላፍ አሕዛብ"። መዝ 3፥5-6 ወይም መዝ 125፥2። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 5፥6-ፍ.ም፣ 1ኛ ጴጥ 3፥15-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥12-15። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 27፥62-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ቅዳሴ ነው።

❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበሰላም።

❤ መልካም በዓልና የአፍሎት ጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን።

✥✥✥ዕለተ ሐሙስ✥✥✥✍️ከስቅለት በፊት ያለው ሐሙስ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፡፡1. ጸሎተ ሐሙስ ይባላል ምክንያቱም1.1. ጌታ ኅብስቱን በባረከ ጊዜ ስለጸለየ1.2. በየሐ.17 ላይ ያለውን ...
16/04/2025

✥✥✥ዕለተ ሐሙስ✥✥✥

✍️ከስቅለት በፊት ያለው ሐሙስ በተለያዩ ስያሜዎች ይጠራል፡፡
1. ጸሎተ ሐሙስ ይባላል ምክንያቱም
1.1. ጌታ ኅብስቱን በባረከ ጊዜ ስለጸለየ
1.2. በየሐ.17 ላይ ያለውን ጸሎት ስለጸለየ
1.3. በጌቴ ሴማኒ በዚህ ዕለት ስለጸለየ ነው

2. የትእዛዝ ሐሙስ ይባላል ምክንያቱም
2.1. ከኅጽበተ እግር በኋላ ጌታችን ደቀመዛሙርቱን እናንተም እንዲሁ አድርጉ ብሎ ስላዘዘ
2.2. በጌቴሴማኒ ‹‹ወደፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ ብሎ ያዘዘት ዕለት በመሆኑ››
2.3. ሥርዓተ ቁርባንን ከሠራ በኋላ ‹‹ከመዝ ግበሩ›› መታሰብያን አድርጉ በማለት በዚህ ዕለት ያዘዘበት በመሆኑ ነው፡፡

3. የነፃነት ሐሙስ፡- ይኸውም ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ወዳጆች ግን ብያችኋላሁ ያለውን የነፃነት ቃል ለማስታወስ

4. ኅጽበተ እግር፡- ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር ማጠቡን የምናስብበት እና ዛሬም ጌታችን አብነት አድርገው ጳጳሳት ኢጴስ ቆጶሳት ቀሳውስት ከበታች ያሉትን ዝቅ ብለው እግር የሚያጥቡበት ዕለት ነው፡፡

5. አረንጓዴው ሐሙስ ይባላል፡፡ በዚህ ዕለት ጌታችን በአትክልት ቦታ መጸለዩን የሚያስታውስ ስያሜ ነው፡፡

6. የሐድስ ኪዳን ሐሙስ፡- ጌታችን በዚህ ዕለት ምሽት ጌታ ‹‹ይህ የሓዲስ ኪዳን ደሜ ነው›› በማለት የሰጠንን ዘላዓለማዊ ኪዳን የሚያስታውስ ስያሜ ነው፡፡ ኪዳን ማለት በሁለት ወገን የሚደረግ ውል፣ ስምምነት መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊ የቃል ኪዳኑ ፈጻሚዎች ጠባቂዎች መሆናችንን ለማጠየቅ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል፡፡

7. የምሥጢር ቀን ይባላል፡፡ ከሰባቱ ምሥጢራተ አንዱ የሆነው ምሥጢረ ቍርባን በዚህ ምሽት የተመሠረተ በመሆኑ ነው፡፡

8. ፋሲካ በአልዓዛር ቤት ይባላል፡፡ ጌታችን የአይሁድን የፋሲካ በዓል ያከበረበት ታላላቅ ምሥጢራትን የፈጸመበት በአልዓዛር ቤት በመሆኑ ነው፡፡

➕ በጠቅላላው በዚህ ሐሙስ ዕለት ቅዳሴ በለሆሳስ ይቀደሳል፣ እንደ ቃጭል ሆኖ የሚያገለግለው ጸናጽል ነው፡፡ ምክንያቱ ፦

1. ይሁዳ ጌታን ለማስያዝ በሰውር መምከሩን እና አይሁድ ጌታን ለመያዝ ሲመጡ በለሆሳስ እየተገጋገሩ መምጣታቸውን ለማሰብ

2. በዘመነ ብሉይ ጸሎት ዋጋው ምድራዊ እንደነበር ለማጠየቅ ነው፡፡

- በቅዳሴው ጸሎት ኑዛዜ አይደረግም ሥርዓተ ቁርባን ግን ይፈጸምበታል፡፡ ይህም ጌታችን የሰጠው ዘላዓለማዊ ቃል ኪዳን ለማሰብ ነው፡፡

❤ ፦ "ትነዝኀኒ በአዛብ ወእነጽሕ። ተሐፅበኒ ወእምበረድ እጸዓዱ(ወእጻዓዱ)። ታሰምዓኒ ትፍሥሕተ ወኃሤተ። "። መዝ50፥7-8። የሚነበበው ወንጌል13፥1-20።

✝ ✝ ✝
❤ ፦ "ወሠራዕከ ማእደ በቅድሜየ። በአንፃሪሆሙ ለእለ ይሣቅዩኒ። ወአጽሐድከ በቅብዕ ርእስየ"። መዝ 22፥5 ወይም መዝ 40፥9። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 11፥23-34፣ 1ኛ ጴጥ 2፥11-25፣ የሐዋ ሥራ 10፥34-43። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 26፥20-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ ነው። መልካም የጸሎተ ሐሙስ በዓልና የሰሞነ ሕማማት ጊዜ ለሁላችን ይሁንልን።

❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበሰላም።

❤ መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

✍️ ንብረታችንን ማን መጠቀም አይችልም እንግዲህ እራሳችሁን ቻሉ !!!!
15/04/2025

✍️ ንብረታችንን ማን መጠቀም አይችልም እንግዲህ እራሳችሁን ቻሉ !!!!

✥✥✥ ዕለተ ረቡዕ ✥✥✥✍️የምክር ቀን (ምክረ አይሁድ) እና መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል፡፡ -    በዚህ ቀን ከቅንዓትም በላይ በጌታችን ላይ ቂምና ጥላቻ ያደረባቸው የአይሁድ ሊቃነ ...
15/04/2025

✥✥✥ ዕለተ ረቡዕ ✥✥✥

✍️የምክር ቀን (ምክረ አይሁድ) እና መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል፡፡

- በዚህ ቀን ከቅንዓትም በላይ በጌታችን ላይ ቂምና ጥላቻ ያደረባቸው የአይሁድ ሊቃነ ካህናት እና ጸሓፍት ወቅቱ የፋሲካን በዓላቸውን የሚያከብሩት በመሆኑ ይልቁንም ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱን የሚያደንቁ በመሆናቸው ሁከት ሳይፈጠር ጌታን መያዝ እንደሚችሉ ምክር ያደርጉበት ዕለት ነው፡፡ የዚህ መጥፎ ምክራቸው ተባባሪ የሚሆናቸውን ይሁዳንም በዚህ ዕለት በማግኘታቸው እንዴት እንይዘዋለን የሚለው ጭንቀታቸው ተወግዶላቸው የተደሰቱበት ዕለት ነው፡፡ (ማቴ.26፥1-16፣ ማር.14፥1-11፣ ሉቃ.22፥1-6)

➕ መልካም መዓዛ ያለው ቀንም ይባላል፡- ይኸውም ጌታችን በስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ የራሱ የስምኦን ፣ የአልዓዛር ፣ የማርታ እህት የሆነችው ማርያም ወደ ጌታችን ቀርባ እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ ዋጋ ያለውን ሽቱ እየቀባችው በጠጉሯም ያበሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ ማቴ ፳፮/ ማር ፲፬ /

❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበሰላም አሜን።

❤ መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾምና የስግደት ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

✍️ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና ከ፲ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተ...
15/04/2025

✍️ከበሮ፣ጸናጽል፣መቋሚያና ከ፲ በላይ ቅዱሳት መጻሕፍትን የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለሥልጣን በቅጂና ተዛማች መብቶች ሥራ ተመዝግቦ ከሚያዚያ ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አእምሯዊ ንብረት መሆኑ ተረጋግጧል።
ከዚህ ቀደምም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የቅርስ ጥበቃ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ በአእምሯዊ ንብረት ዐቢይ ኮሚቴ አማካኝነት በርካታ የቤተክርስቲያን ንብረቶች ተመዝግበው እውቅና ማግኘታቸውን የመምሪያው ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ ገልጸዋል።
© የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

✥✥✥ዕለተ ማግሰኞ (የሰኞ ማግስት)✥✥✥✍️ይህ ዕለተ የጥያቄ ቀን እና የትምህርት ቀንም በመባል ይታወቃል፡፡ በዕለተ ሰኑይ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ፈሪሳውያን ቀርበው ከቤተ ሌዊ ሆነህ...
14/04/2025

✥✥✥ዕለተ ማግሰኞ (የሰኞ ማግስት)✥✥✥

✍️ይህ ዕለተ የጥያቄ ቀን እና የትምህርት ቀንም በመባል ይታወቃል፡፡

በዕለተ ሰኑይ ባደረገው አንጽሖተ ቤተ መቅደስ ፈሪሳውያን ቀርበው ከቤተ ሌዊ ሆነህ ክህነትን ምክንያት አድርገህ፣ ከቤተ ይሁዳ ሆነህ ንግሥናን ምክንያት አድርገህ እንዳይባል ከሁለቱም ወገን አይደለህም ማስተማርህ፣ ተአምር ማድረግህ፣ ቤተ መቅደስ ማጽዳትህ በየትኛው ሥልጣንህ ነው ብለው ስለጠየቁት የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

- ፈሪሳውያንን ጌታችንን ከገሊላ ወገን ይመስላቸው ነበር እንጂ ከቤተ ይሁዳ መሆኑን አያውቁም ነበር፡፡ (ዮሐ.7፥5) ስለዚህ የቤተ መቅደስን ሥርዓት ማስጠበቅ የሌዋውያን የካህናቱ ሥልጣን ነው፣ የሃገርን ሥርዓት ማስጠበቅ ደግሞ የነገደ ይሁዳ የነገሥታቱ ሥልጣን ነው፡፡ አንተ ከነዚህ ወገን ሆነህ ተቀብተህ ስትሾም አላየንምና በየትኛው ሥልጣን ነው ይህን የምታደርግ ብለው ጠየቀውታል፡፡ (ማቴ.21፥23-27/
ማር.11፥22-33/ ሉቃ.20፥18)

- ጌታችን ግን ንግሥናም ሆነ ክህነት የባህርይው እንጂ እንደምድራውያን በመቀባት ያገኘው አይደለም፡፡ ስለዚህ ጌታችን መልሶ ለጠየቁት ፈሪሳውያን ‹‹ አንድ ነገር እጠይቃችኃለሁ እናንተ ብትነግሩኝ በማን ስልጣን እነዚህን እንዳደርግ እነግራችኋለው፣ የዮሓንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረች ከሰማይ ወይስ ከሰው ኣላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ነው ብንል ለምን ኣልተቀበላችሁትም ሕዝቡ ይለናል ከሰው ነው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሓንስን እንደ ነቢይ ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፣ እርሱም በማን ስልጣን እነዚህን እንደማደረግ እኔም አልነግራችሁም ኣላቸው፡፡››

- ነገርን ለመረዳት የቀረበን ሰው ብዙ ምሳሌ ኣምጥቶ ማስተማር ይገባል፡፡ የፈሪሳውያን ጥያቄ ግን ክፋት የተመላበት ስለነበር መልስ አልሰጣቸውም፡፡

➕ በዚህ ዕለት ጌታችን ረጅም ትምህርት በማስተማሩ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ቀድሞ እንዳልነው የሃይማኖትን ምሥጢር ለማወቅ የሚሹትን፣ ደክመው የበደሉትን፣ ከፍቅረ እግዚኣብሔር የራቁትን ትኩረት በመስጠት ሊረዱት በሚቻላቸው ትምህርት ማስረዳት ይገባልና፡፡ ይህንን ሊያስተምር ኣርአያ ሊሆነን ነው፡፡ በማቴ.21፥28 ‚25፥46፣ ማር.12፥2‚ምዕ 13፥37፣ ሉቃ.20፥9‚ምዕ.21፥38 ላይ የሚገኘው ሁሉም የማግሰኞ (የሰኞ ማግስት) ትምህርት ነው፡፡

❤ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስም ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀንም ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባ ሲያስተምር ነው፡፡

❤ እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ፃዕማ ወድካም አመ ከመዮም ያብጽኀነ ያብጽዕክሙ እግዚአብሔር በፍስሃ ወበሰላም አሜን።

❤ መልካም የሰሞነ ሕማማት የጾምና የስግደት ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።

Address

Hossaen
Addis Ababa
210323

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Deginet Demeke ze bata posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share