Ariti tube

Ariti tube Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ariti tube, News & Media Website, Addis Ababa.

"ከፕሮቴስታንት ፓስተሮችና ደህንነቶች ጋር አገኘኋቸው።"".... 'አንተ ጥሩ ሰው ነህ እባክህ ሽማግሌ ሁንና አስታርቀን' ብለው ደውለውልኝ ልምጣና በአካል እንነጋገር ብያቸው  አዲስ ከበባ ወ...
07/02/2023

"ከፕሮቴስታንት ፓስተሮችና ደህንነቶች ጋር አገኘኋቸው።"

".... 'አንተ ጥሩ ሰው ነህ እባክህ ሽማግሌ ሁንና አስታርቀን' ብለው ደውለውልኝ ልምጣና በአካል እንነጋገር ብያቸው አዲስ ከበባ ወሰን አካባቢ ቀጥረውኝ ወዳሉበት ስፍራ ሂጄ ነበር። ከእሳቸው ጋር ወደ 6 የሚሆኑ የፕሮቴስታንት ፓስተሮችና ደህንነቶች አብረዋቸው ነበር። ደህንነቶችም ' አንተ ነፍጠኛ አይደለህ ለምን መጣህ? በማለት አፋጠጡኝ እኔ ግን በዘር፣ በቋንቋና በብሄር ሳይሆን በእጄ በያዝሁት መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ እንደማምን ነገርኳቸው። ከብዙ ወከባ በኋላ ተመልሼ ሄድኩ።

በማግስቱ ለጳጳሱ ደወልኩና ሌላ ስፍራ እንገናኝና እንወያይ ስላቸው 'ተው አይሆንም ደግሞ ከጴንጤ ጋር ታዬ ተብዬ ሌላ ችግር ልፍጠር' አሉኝ። እውነት ለመናገር ሁሉም አፈንጋጮች ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ የሚመሩትን ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠይቀው ወደ ቤታቸው መመለስ ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ልክ ወጥመድ ውስጥ እንደገባች አይጥ መውጫ አጥተዋል።....

"ይሁን እንጂ የብልጽግና መንግስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ያወቃት አይመስለኝም። ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መከራ በመጣባት ጊዜ ሁሉ ይበልጥ የምትፀና፣ በሯ በተንኳኳ ቁጥር አጥብቃ የምትቆልፍ ረቂቅ ቤተክርስትያን መሆኗን መረዳት ነበረበት። አሁን በኦርቶዶክስ ላይ እየሆነ ያለውን ሁሉ ሁላችንም አጥብቀን የምናወግዘው ከመሆኑም ባሻገር ከቤተክርስትያኒቷ ጎን በመቆም አብሮነታችንን መግለጽ እንፈልጋለን።"

ፓስተር ቢንያም

የዛሬ ታሪክ ነው ቱርካዊ አባት የፋብሪካ ሰራተኛ ነው  ጥዋት ልጆቸን በሰላም ተሰናብቶ ወቶ ማታ ከስራ ሲመለስ ለእለት ጉርሳቸው ነዉና ድካሙ ዳቦ ሸክፎ  ከስራ ሲመጣየሆነው ሌላ ነው  በአከባ...
07/02/2023

የዛሬ ታሪክ ነው ቱርካዊ አባት የፋብሪካ ሰራተኛ ነው

ጥዋት ልጆቸን በሰላም ተሰናብቶ ወቶ ማታ ከስራ ሲመለስ ለእለት ጉርሳቸው ነዉና ድካሙ ዳቦ ሸክፎ ከስራ ሲመጣ
የሆነው ሌላ ነው በአከባቢው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች እላያቸው ላይ ፎቆ ተደርምሶባቸዋል ከመሬት ስር ሆነዋል አንዳንዴ በሕይወት ዱብዳ አስታሟ አልቅሶ መቅበር ቅንጦት ይሆናል ።

አይደለም ገድለህ አፈናቅለህ የሌላዉን ላብ ልትበላ
በጉንጭህ የጎረስከዉን ስለ መዋጥህ ዋስትና የለህም !!

ሕይወት ለጥቂት ጊዜ ታይቶ እንደ ሚጠፋ እንፋሎት !!
ናት ያእቆብ 4፣14

እግዚአብሔር አምላክ ሰላሙ ያዉርድልን ።

ሕግ አስከባሪው ጅብ,,,,,,,,,ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ ጅብ ገጥሞት ባሰማው የድረሱልኝ ጥሪ በቁጥጥር ስር ዋለ*********************************...
07/02/2023

ሕግ አስከባሪው ጅብ,,,,,,

,,,ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ ጅብ ገጥሞት ባሰማው የድረሱልኝ ጥሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

************************************************

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ ዐ1 ልዩ ቦታው ፖራዳይዝ ሆቴል ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ጫካ በመግባት ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ ጅብ ገጥሞት ባሰማው ጩኸት በቁጥጥር ስር መዋሉን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

ግለሰቡ ከጅማ ዞን ሊሙ ሰቃ ወረዳ የአቃቢ ህግ ባለሙያ መሆኑንና ቴዲ ድሪባ እንደሚባል የመምሪያው የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ዮሀንስ በየነ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቡ የ4ኛ አመት የዩንቨርሲቲ ተማሪ የሆነችውን ፍቅረኛውን ለመጠየቅ ወደ ደብረማርቆስ መምጣቱ ተነግሯል።በሰዓቱ ተጎጂ የሆነችው ግለሰብ ከዚህ በኋላ አንድ ላይ መቀጠል እንደማይችሉ ስትነግረው በጩቤ ወግቶ በጫካ አድርጎ ሲያመልጥ ከምሽቱ 5:00 አካባቢ ጅብ አግኝቶት አላሳልፈው ሲል ባሰማው የድረሱልኝ ጩኸት የመንቆረር ኮንስትራክሽን ጥበቃዎች ደርሰው ለፖሊስ በሰጡት መረጃ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ግለሰቧ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባት ህክምና እየተደረገላት መሆኑን የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ዋና ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ዮሀንስ በየነ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

Via: ዳጉ ጆርናል

የአበባ ደሳለኝ (ከሰሜን አሜሪካ) መልእክት  "በመላው ዓለም ለምትገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ ቤተክርስቲያናችን አርብ ላይ ነች። የሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሁለተኛ መልእክት ምዕራ...
07/02/2023

የአበባ ደሳለኝ (ከሰሜን አሜሪካ) መልእክት

"በመላው ዓለም ለምትገኙ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በሙሉ ቤተክርስቲያናችን አርብ ላይ ነች። የሀዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ሁለተኛ መልእክት ምዕራፍ 1 ቁጥር አስር ላይ እንዳለው መጠራታችሁን ታፀኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ አሁን ትጉ ብለው እንዳስተማሩን ሊቃውንት አባቶቻችንም የስላሴ ልጅነት ያገኘን በሙሉ ከፊት ይልቅ አሁንም እንትጋ።

አንድ ሲኖዶስ
አንድ ፓትርያርክ
አንድ ተዋሕዶ"

30/01/2023
«ነፍሴን አስይዤ እፋለማለሁ፣ የአባቶች አደራ አለብኝና'»እኔ መጀመሪያ ስሾም የቀደስኩት በኦሮሚኛ ቋንቋ ነበር ብዙ አገልግሎቶችን በኦሮምኛ ቋንቋ ነው የምናከናውነው። የነዚህ ሰዎች አላማ ምን...
24/01/2023

«ነፍሴን አስይዤ እፋለማለሁ፣ የአባቶች አደራ አለብኝና'»

እኔ መጀመሪያ ስሾም የቀደስኩት በኦሮሚኛ ቋንቋ ነበር ብዙ አገልግሎቶችን በኦሮምኛ ቋንቋ ነው የምናከናውነው። የነዚህ ሰዎች አላማ ምንድነው? ቅዱስ ሲኖዶስን ማክበር ያስፈልጋል። ከዛ ያፈነገጠ አካሄድ ከባድ መለኮታዊ ቅጣት አለው። እኔ በአንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን፥ በአንድ ቤተክህነት አምናለው ከዚህ ውጭ የሚደረግን እንቅስቃሴ ነፍሴን አስይዤ እፋለመዋለው የአባቶቼ አደራ አለብኝና።"

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋና የምዕራብ ሸዋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ!

የወላይታ ሀገረ ስብከት በወሊሶ በተከናወነው ሕገ ወጥ ሹመት ላይ የተሳተፉትንና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ለሀገረ ስብከቱ በሰጠው ኮታ መሠረት በዩኒቨርስቲው እየተማሩ ይገኙ የነበሩት...
24/01/2023

የወላይታ ሀገረ ስብከት በወሊሶ በተከናወነው ሕገ ወጥ ሹመት ላይ የተሳተፉትንና የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ ለሀገረ ስብከቱ በሰጠው ኮታ መሠረት በዩኒቨርስቲው እየተማሩ ይገኙ የነበሩትን 'አባ' አብርሃም ገብረ መስቀል የተባሉት ግለሰብ ከአገልግሎት አግዷል።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት ውጭ በሆነ መልኩ ተሰጠ የተባለውን "ሲመተ ኤጲስ ቆጶጶስ" እንደማይቀበል የጅማ ሀገረ ስብከት አስታወቀ::በክቡር መልዐከ ሠላም...
24/01/2023

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት ውጭ በሆነ መልኩ ተሰጠ የተባለውን "ሲመተ ኤጲስ ቆጶጶስ" እንደማይቀበል የጅማ ሀገረ ስብከት አስታወቀ::

በክቡር መልዐከ ሠላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ የጅማ ፣ የየም እና የኮንታ አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰብሳቢነት ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም የተሰበሰበው የጅማ ሀገረ ስብከት አስተዳደር ጉባኤ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና እና ሥርዓት ውጭ በሆነ መልኩ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም ተሰጠ የተባለውን "ሲመተ ኤጲስ ቆጶጶስ" እንደማይቀበል አስታወቀ።

ሀገረ ስብከቱ በመግለጫው ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ፣ የየም፣ የኮንታ፣ የዳውሮ፣ የሰሜን ጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጅማ ሀገረ ስብከት ላለፉት 22 ዓመታት በሊቀ ጳጳስነት በቆዩበት ጊዜ ምእመናን በአካባቢው ቋንቋ ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ሳይታክቱ መሥራታቸውንና ውጤት ማምጣታቸውንም አመላክቷል።

የጅማ ሀገረ ስብከት ኦርቶዶክሳውያን ምእመናንም ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ከሀገረ ስብከቱ የሚሰጡ መመሪያዎችን ብቻ በመቀበል እንዲተገብሩም አሳስቧል።

© ጅማ ሀገረ ስብከት

የኢፌዴሪ መከላከያ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ምበማንኛውም ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ገብቶ ግዳጁን በብቃት መፈፀም የሚችል ጠንካራ ሃይል ገንብተናል፡- ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ሌተናል ጄኔራል ...
24/01/2023

የኢፌዴሪ መከላከያ ጥር 15 ቀን 2015 ዓ.ም

በማንኛውም ቦታ እና ሁኔታ ውስጥ ገብቶ ግዳጁን በብቃት መፈፀም የሚችል ጠንካራ ሃይል ገንብተናል፡- ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ

ሌተናል ጄኔራል ዘውዱ በላይ ከሠራዊቱ ጋር ባደረጉት ዉይይት የውስጥም ሆነ የውጭ ፀረ-ሰላም ሃይሎችን በመደምሰስ አንፀባራቂ ድልን ከማስመዝገብ የሚያግደን ሃይል አለመኖሩንም በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለንም ብለዋል።

ሰራዊቱ እንደባለፉት ጊዜያቶች ሁሉ የተሰጠንን ትልቅ ሃገራዊ ግዳጅ ውጤታማ በሆነ መልኩ እየፈፀመ የሚገኝ መሆኑን ገልፀዉ ለተልእኮው ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራት የበለጠ ድል ማስመዝገብ የሚያስችለው የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

አሁን ላይም ሰራዊታችን በተሰማራንበት ቀጠና በሽብርተኝነት ተግባር ላይ ተሰማርተው የሃገራችን የሰላም ማነቆ እየሆኑ ያሉ ፅንፈኛ ሃይሎችን ዳግም የህዝባችን ስጋት እንዳይሆኑ ለማድረግ የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑንም ሌተናል ጄኔራል ዘዉዱ ተናግረዋል፡፡

ከህዝባችን ጋር ያለንን የሰላም እና የልማት ትስስር ይበልጥ አጠናክረን በመቀጠል የኢትዮጵያን ሰላም እና አንድነት አስጠብቀን ማቆየት አለብን ብለዋል።

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተገንብቶ ቅዳሜ ሊመረቅ የነበረው ዘመናዊ የዳታ ማዕከል ትላንት በዚህ መልኩ በእሳት አደጋ ወድሟል ተብሏል።
24/01/2023

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተገንብቶ ቅዳሜ ሊመረቅ የነበረው ዘመናዊ የዳታ ማዕከል ትላንት በዚህ መልኩ በእሳት አደጋ ወድሟል ተብሏል።

"እኔ 3 ነገሮችን ቃል እገባለሁ። እነርሱም ቤተሰቦቼን ላለማሳዘን ፣ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋች ለመሆን እና ወደ ትውልድ ከተማዬ ተመልሼ ትምህርት ቤት ለመገንባት።"- ሳዲዮ ማኔ እግር ኳ...
24/01/2023

"እኔ 3 ነገሮችን ቃል እገባለሁ። እነርሱም ቤተሰቦቼን ላለማሳዘን ፣ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋች ለመሆን እና ወደ ትውልድ ከተማዬ ተመልሼ ትምህርት ቤት ለመገንባት።"- ሳዲዮ ማኔ እግር ኳስ ተጨዋች ከመሆኑ በፊት የተናገራት ንግግር ፦

አሁን ላይ ሳዲዮ ማኔ ፥ ቤተሰቦቹ በእሱ በጣም ተደስተው እና ተገርመው በእሱ ኮርተዋል

ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጨዋች ከመሆን አልፎ ከአለም ምርጦች ጋር ይፎካከራል።

ቃል ከገባው ትምህርት ቤት በተጨማሪ ሆስፒታል በትውልድ ከተማው አስገንብቷል። እንዲሁም በትውልድ ከተማው አካባቢ ለሚኖሩ ህዝቦች የኢኮኖሚ ድጋፍ ያደርጋል።

ማንም ሊጠላው የማይችል ቃሉን ጠባቂ ሰው! ❤

"በሀገራዊ ምክክሩ ከ40 በላይ ፓርቲዎች አብረውን ለመሥራት ተስማምተዋል።"የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያከ40 በላይ የሚኾኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኮ...
24/01/2023

"በሀገራዊ ምክክሩ ከ40 በላይ ፓርቲዎች አብረውን ለመሥራት ተስማምተዋል።"
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ

ከ40 በላይ የሚኾኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኮሚሽኑ ጋር ለመሥራት መስማማታቸውን ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንደተናገሩት፤ ተፎካካሪዎቹን እና ገዢውን ፓርቲ ጨምሮ በምርጫ ቦርድ ከተመዘገቡት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚኾኑ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኮሚሽኑ ጋር ለመሥራት ተስማምተዋል።

ከ40 በላይ ከኾኑት የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር አብረን ለመሥራት ስምምነት ላይ እስክንደርስ ድረስ የራሳቸው ጥርጣሬ ነበራቸው ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ አንዳንዶቹ በአዋጁ አቀራረጽ ሂደት ላይ እንዲሁም በኮሚሽኑ ስም ላይ ጥያቄዎች እንደነበሯቸውም ነው የተናገሩት። በሂደት በተሠሩ ሥራዎች ከ53ቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውስጥ ከ40 በላይ የሚኾኑት አብረዋቸው ለመሥራት የተስማሙ ሲሆን፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥም የስምምነት ማዕቀፍ የሚፈራረሙ መኾኑን ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ አብሮ ለመሥራት ፍላጎት ካላሳዩት ከአስር የሚልቁ ፓርቲዎች ጋርም አብሮ ለመሥራት ጥረቶች መቀጠላቸውንም ተናግረዋል።

"አብረውን ለመሥራት ፈቃደኛ ካልሆኑት ፓርቲዎች ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እየተገናኘን እኛ ማን እንደኾንን እንዲሁም ሥራችን የት ድረስ እንደሚሄድና የሥራ ኃላፊነታችን ምን ምን እንደሆነ በማስረዳት ላይ እንገኛለን ያሉት ፕሮፌሰሩ፤ እኛ የውይይትን ሥራ ማመቻቸትና ማሳለጥ እንጂ ወሳኞች ስላልሆንን ይህንን እያሳወቅናቸው ነው" ብለዋል።

አብላጫው ሕዝብ ዘንድ ተቀባይነት ብናገኝም አብረው ለመሥራት ፍላጎት ያላሳዩትም ኢትዮጵያ ሀገራቸው ነችና ያልሰሙንና ያልፈለጉን ጥቂት የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው ብለን እነሱን ወደ ኋላ መተው የለብንም።

ያልተቀበሉን ወይም የተቃወሙን የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደፊት ሁኔታዎች ከተመቻቹ ሀገር የሚመሩና የሚያስተዳድሩ ስለሆኑ ሕዝብ የተዋደደበትንና የተፋቀረበትን ጠንካራ ሀገርን መምራት ለፖለቲካ ፓርቲዎችም ትልቅ ዕድልና ጸጋ ይመስለኛልም ነው ያሉት።

ፕሮፌሰሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎችም ባሻገር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፤ የሃይማኖት ተቋማት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የአካል ጉዳተኛ ማኅበራት፣ የሴቶች ማኅበራት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሁም እዚህ ሀገር ያሉትን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ተወካይ አምባሳደሮችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን የሚመሩ ኃላፊዎችን ማግኘታቸውንም ገልጸዋል።

ፕሮፌሰር መስፍን ከተቋቋመ ዘጠኝ ወራትን ያስቆጠረው ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቅቡልነቱ እየሰፋ መኾኑንና ወደፊትም ከዚህ በላይ ተቀባይነት እንደሚኖረው ያላቸውን ተስፋም ተናግረዋል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ariti tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share