gazeጣው

gazeጣው ወሬኛ ነኝ።

እየመጣን ነው።
24/03/2026

እየመጣን ነው።



💪
10/03/2026

💪

❤
07/03/2026

❤

የእነ አዶኒ ፕላትፎርም—ሲድሮ አሁን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው🙄እንደ አዶኒ በመሐል በመሐል ይምታታበታል።ይሄው ቪዲዮ የሚባል ዐላሳይህም አለኝ።አዶኒም፤ሲድሮም ያድጋሉ ብዬ በትግስት በመጠበቅ ላ...
04/03/2026

የእነ አዶኒ ፕላትፎርም—ሲድሮ አሁን ያለበት ሁኔታ ነው ያለው🙄

እንደ አዶኒ በመሐል በመሐል ይምታታበታል።ይሄው ቪዲዮ የሚባል ዐላሳይህም አለኝ።

አዶኒም፤ሲድሮም ያድጋሉ ብዬ በትግስት በመጠበቅ ላይ ነኝ።ሌላ ታክሲ ታገኘሁ ግን ቆሜ አልጠብቅም።

«[መሳፈር ነውይ ቶሎ ተሽቀዳድሞ
ጊዜ ታክሲ አይደለም፤አይጠብቅም ቆሞ»

ከሚ

ጎጃሜዎች ንግሥታችን እያሏት ነው።በሆነላት🤔ግን የጎጃም ሴት ንግሥታት ሥመ ከባድ ናቸው።ካልነገሰችው ሲጳራ ዮቶር ብንጀምር እንኳን የሙሴ ሚስት ሆና እናገኛታለን።መቼስ ልዕለ አቅም ባይኖራት እ...
04/03/2026

ጎጃሜዎች ንግሥታችን እያሏት ነው።

በሆነላት🤔

ግን የጎጃም ሴት ንግሥታት ሥመ ከባድ ናቸው።ካልነገሰችው ሲጳራ ዮቶር ብንጀምር እንኳን የሙሴ ሚስት ሆና እናገኛታለን።

መቼስ ልዕለ አቅም ባይኖራት እግዜሩ ለሙሴ አልዳራትም።ጎጃሜዋ ሲጳራ ጸዴ ልጅ ነበረች ማለት ነው።

ንግሥት ሰብለወንጌል—ሁላ የባሏን ኮሳሳነት መሸፈን የቻለች ናት።ልብነድንግል ያስወረረውን አገር ነፃ ያወጣችው እሷ ናት።ልጇ ገላውዲዮስ ያስደምመኛል።

የመንጌ ሚስት ውባንች ቢሻው ደሞ በአቅሟ የኢትዮጵያን አብዮት እቴጌ ሆና የመራች ሴት ናት።

ወገን...

መንግሥቱ ኃይለማርያም ወልዴ አያናን ያህል ሞገደኛ ሰው ችሎ ቀዳማዊት እመቤት መሆን'ኮ ያስደንቃል።

በምሥሉ ላይ ያለችው ሰው ጎበዝ ሴት ናት።ሥሟን አላውቀውም።በSM መልዕክት መለዋወጫ ውስጥ በመጠኑ አውግተናል።ጉብዝና ዐይቸባታለሁ።

ደሞ ከተወዳጄ አበረ አረፈዓይኔ አዳሙ መጽሐፍት ጋር ሳያት የጎጃም ሴቶች ትዝ አሉኝ።

የሴት ነገር አይሆንልኝም🙄

═════════════

02/03/2026

ሣቀ፣ ጠላቱም ከሳ፤
ተንቀሳቀሰ ዳኘው ተነሣ፤
አራቱም አሕጉር፣ ለሱ እጅ ነሣ።

ጣልያን ገጠመ፣ ከዳኛው ሙግት
አግቦ አስመሰለው፣በሠራው ጥይት
አሁን ማን አለ፣ በዚህ ዓለም?
ጣልያን አስደንጋጭ ቀን ሲጨልም!

ግብሩ ሰፊ ነው ጠጁ ባሕር
የዳኘው ጌታ ያበሻ አገር
አይኮረተም እጁ የዘናው
ወንዱ ምኒልክ ዝንታለም ይቅናው!
ፈረሱ ዳኘው ሚስቱ ጣይቱ
ምጥዋ ወርዳ ቀዳች ወጥ ቤቱ!»

ሀሰን አማኑ፣ወሎዬው የዐደዋ ዘማች አዝማሪ

በዘመናዊ ታሪክ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ'ን ያህል ያሰበውን ያሳካ መሪ የለም።የሕልማቸው ሥፋት ይደንቀኛል።ማድረግ የነበረባቸውን ያላደረጉት በአቅም መዛል እና በጊዜ እጦት ብቻ ነው።የተሳሳቷቸው ሥህተቶችም እንዲሁ ከሰው ድክመት የሚመነጩ ናቸው።

እወዳቸዋለሁ።አደንቃቸዋለሁ።

እንደየትኛውም የአገሬ መሪ እተቻቸዋለሁ።

በድሉ ለተደሰታችሁ፤ደስታችሁ በሃብት ይባዛ❤

Description:

Today we honor the 130th Anniversary (1️⃣3️⃣0️⃣) of the historic Victory of Adwa 🇪🇹

In this video, I recite a poem dedicated to Menelik II, the visionary leader who guided Ethiopia to victory at the historic Battle of Adwa in 1896.

Adwa was more than a battle — it was a symbol of unity, resistance, and African pride. While much of Africa faced colonization, Ethiopia stood strong and defended its sovereignty.

This poem is a tribute to the bravery and sacrifice of our ancestors.
Adwa lives forever. 🇪🇹





02/03/2026

ለቴዲአፍሮ አድርሱላቸው🤲

02/03/2026









#ሞሐመድአህመድ
#የኢትዮጵያሙዚቃ
#ኢትዮጵያዘፋኝ
#ሀበሻሙዚቃ
#ኢትዮጵያ







Address


Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when gazeጣው posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

  • Want your business to be the top-listed media company?

Share