
12/01/2023
ኢትዮ ቴሌኮም በበጀት ዓመቱ መንፈቅ ዓመት 33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል።
ኢትዮ ቴሌኮም አዲስ “ሊድ” የተሰኘ የሦስት ዓመት አዲስ የእድገት ስትራቴጂውን በ2015 በጀት ዓመት መጀመሪያ ካስተዋወቀ በኋላ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት ሪፖርቱን ዛሬ አቅርቧል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈታሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ኢትዮ ቴሌኮም በ2015 በጀት ዓመት አጋማሽ 33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ገልጿል። ኩባንያንያው ይህም የእቅዱን 96% ማሳካቱን ነው የገለጸው።
የተገኘው የገቢ ድርሻ በአገልግሎት አይነት ሲታይ ፦
- የድምጽ አገልግሎት 47.4% ድርሻ ሲኖረው
- ዳታና ኢንተርኔት 28%፣
- ዓለም አቀፍ ገቢ 8.4%፣
- እሴት የሚጨምሩ አገልግሎቶች የ6.5%፣
- እቃ ሽያጭ( Device) 4.3%
- የመሰረተ ልማት ማጋራት Infra.Sharing (2.2)
- ሌሎች አገልግሎቶች 3.2% ድርሻ አላቸው ተብሏል።
የውጭ ምንዛሪ ከሚያስገኙ አገልግሎቶች 64.8 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተገኘ ሲሆን ይህም የእቅዱን 90% ያሳካ ነው ተብላል።
ኩባንያው የደንበኞቹ ቁጥር 70 ሚሊዮን መድረሱንም ወ/ሮ ፍሬህይወት ገልጸዋል ፦
- የድምጽ አገልግሎት 67.7 ሚሊዮን
- ዳታና ኢንተርኔት 31.3 ሚሊዮን
- መደበኛ የብሮድባንድ 566.2 ሺ ተጠቃሚዎች
- መደበኛ የስልክ 862.2 ሺ ተጠቃሚዎች መድረሱን አስታውቀዋል።
በዚህም በበጀት አመቱ ግማሽ አመት 15.1 እድገት ያሳየ ሲሆን 9.2 ተጨማሪ ደንበኞችን ማግኘቱን አስታውቀዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በውድድር ገቢያ ውስጥ ሆነን ደንበኞችን የማቆየትና አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት አመርቂ አፈጻጸም ያስመዘገብንበት ነው ሲሉ ገልጸዋል።
#ቲክቫህ #ኢትዮጵያ