
18/07/2025
ከሚዲያ ራሴን ስለማግለሌ ዕና የመጨረሻ ጉዞዬ ስለማሳወቅ !
እኔ ጁሃር ሳዲቅ እንደሚታወቀዉ ላለፉት አምስት አመታት በሚዛን ሚዲያ እንዲሁም የሱፍያዉን የሚዲያዉን ዘርፍ ሳግዝ ቆይቻለሁ ። በመጣንባቸዉ አመታ የአህለሱናዉ አካባቢ ሲታይ የነበረዉ የሚዲያዉን ክፍተት ለመሙላት በተቻለኝ አቅሜ በፈቀደልኝ መጠን ሰርቼ እዚህ አድርሻለሁ ብዬ አስባለሁ ።
ነገር ግን በዚሁ በሚዛን ሚዲያ ከፍተኛ የሚዲያ ሽፋን ሰጥቼ በተቻለኝ መጠን ከህዝብ ጋር እንዲተዋወቅ ህዝብን እንዲያገለግል ሳልሰለች የሰራሁለት ታስክ ፎርስ (ግብረሀይል) ዉስጥ ያሉ ጥቂት መጅሊስ የሚገቡ ተደራረዳሪ ግለሰቦች ፣ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የታስክ ፎርሱ (የተደራዳሪዉን) ሂደት እንደ ሚዲያ ለሚዲያችን ሲቀርብ ቆይቷል በተደጋጋሚም ህዝቡ የሚያነሳዉን ጥያቄ አቅርቤያለሁ ለጥያቄዎች ቀጥታ ይሄ ነዉ የሚል ምላሽ ካለ መገኘቱ አልፎ አትጠይቁን አትችልምም ተብያለሁ ፣ቅሬታዎች ከመዘገብ ብሎም መጅሊስንና ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ አትንኩ ህገ_ወጥ መጅሊስ አትበሉ በሚል ጭምር ተደጋጋሚ በመጡ ጫናዎች እንዳቆም ተነግሮኛል ።
ከዚህ በሗላ ታስክ ፎርሱ ዉስጥ የማከብራቸዉ ለመስመሩ የቆሙ ሰዎች መኖራቸዉ በአክብሮት እየገለፅኩ ሂደቱ ወደ ጥቂት ሰዎች የዞረና በጥቂት ግለሰቦች የሚዘወር በመሆኑ ከተነሳሁለት አላማ ጋር ታስክ ፎርሱም በዉስን ሰዎች ካልዘወርነዉ የሚል ከተቋቋመበት አላማ ዉጪ እየሄደ ነዉ የሚል እምነት ያለኝ ሲሆን የሚያደርገዉ የትኛዉም እንቅስቃሴ የማይመለከተኝና የማይወክለኝ መሆኑንና በሚቀጥሉት ግዜያት ከሚዛን ሚዲያ ራሴን ያገለልኩ መሆኑ ለማሳወቅ እወዳለሁ ።
በምርጫዉ ሂደትም ይሁን በመጅሊሱ በሱፍያዉ ላይ ለሚፈፀሙ ቀጣይ ዙልሞች እነዚሁ ሚዲያዉ መቆም አለበት ያሉ ተደራዳሪ ነን የሚሉ ጥቂት ግለሰቦች ሀላፊነት የሚወስዱ ይሆናል ።
በቀጣይ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የመጅሊስ የሱፍያዉ አመጣጥ ፣መጅሊስ የገባዉ ተደራዳሪዉ አካል ባጠቃላይ እየተሄደበት ያለዉ መንገድ በቪዲዮ ማብራራዉ ይሆናል ።
በተረፈ አልሀምዱሊላህ አምስት አመቱ ቀላል አልነበረም ዉጣ ዉረዶቹ ተግዳሮቶቹ ለአላህ መንገድ (ለአህለሱናዉ መንገድ) የተከፈለ የተሰራ ስለሆነ አላህ እንዲቀበለኝ ዱዓ አርጉልኝ ።
ለመላዉ ዉድ የመሻኢኽ ልጆች እህቶች ወንድሞች ፣አባቶች ስላገለገልኳችሁ አእናንተን መስመሩንም በማገልገሌ ክብር ይሰማኛል ከጎኔ ለነበራችሁም አመሠግናለሁ ።
ማስታወሻ :- ምናልባት የግል ህይወቴን መስመር ካስያዝኩ በቀጣይ አቅም ካገኘሁ የፃፍኳቸዉ "The mother of right movement " በጣም የምወደው እና " የሰዓድ ኢብን አቢ ወቃስ የዝህድና እና የጀግንነት ታሪክ " በተሸኙ ያለቁ መፅሀፎቼ እንገናኝ ይሆናል የሚል ተስፋ አለኝ ኢንሻአላህ ።
አላህ ለአህለሱና ወልጀማአ (ሱፍያ) ሙስሊም ማህበረሰብ ድልን ያጎናፅፍ ዘንድ ምኞቴ ነዉ ።
ወንድማችሁ ጁሃር ሳዲቅ