03/09/2025
!
ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::
በሃገሪቱ የተከሰተውን ደዌ ከማዳመጥ ይልቅ በሽሙጥ አንዱ አንዱን እየወገረው በመብረር ላይ እንገኛለን :; እርስ በእርስ ከመወጋገር ያድነን እንዳንል እየተወጋገርን ጸሎት ለቅጽበት ነው::ማን ከማን ይማር ሎሌ ከንጉሱ ሆኖብን ሆነና የራሳችንንም ሆነ የሃገራችንን ህመም ተጋግዘን እንዳናድን ራሳችን በሽታ ሆነናል::ምን እንደተባልን እንኳን ማዳመጥ አለመቻላችን አንዱ ደንቃራችን ሲሆን የምንናገረውንም ከማንነገርው መራርጠን መተንፈስ እስኪያቅተን ድረስ እያቃተትን በሽታችንን እያባስን ብዙሃዊ ተላላፊ ህመም አድርገነዋል ከዚህ ይሰውረን እንዳንል ራሳችን አሁንም ደንቃራ ሆነናል::
የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::ልዩነት እንዳለ ሆኖ በጋራ ሃገራዊ መርህ ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ እንዴት ህዝባዊ መተሳሰብ ሊፈጥር እንደሚችል በሃገራችን የሚገኙ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ አልተረዱትም ወይንም አውቀው እየተባሉ እያባሉን እያነካከሱን ነው:: በጋራ መተሳሰብ ላይ ያልተመሰረተው ፖለቲካችን እና በመጭበርበር የሚያጭበረብሩን ገዢዎቻችን ለነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ አደገኛ የሆነ የፖለቲካ በሽታ እያወረሱ ይገኛሉ፤ የፖለቲካ በሽታ ብቻ ሳይሆን በአንድ ወጥ መርህ ላይ የተመሰረተ እና የደቀቀ ኢኮኖሚ ጭምር:: ይህ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ የህዝቦችን የጋራ መደጋገፍ በማስመጥ ገዢው መደብ በፍጹም ከኔ ውጪ የሚነካ ካለ እሳት እንደነካ ነው በማለት በፍራቻ ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ዜጎች በሃገራቸው ብሄራዊ አጀንዳ ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዳይተሳሰቡ እንዳይደጋገፉ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል::ከማህበረሰቡ ተገልሎ እየተሰራ ያለውን ውጤት እያየነው ነው::
በሃገራችን በመጀመሪያ ደረጃ ሁሌ ለገዢዎቹ የሚነግራቸው ቢኖር የህግ የበላይነት እንዲከበር ነው:: የስልጣን እድሜ ለማስረዘም ሲባል በሃገሪቱ ገንዘብ የተገዙ የፓርቲ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከህግ በላይ በመሆን አሳር እና አበሳ እያሳዩን ሲሆን ይህንንም ከተራ ዜጋ ጀምሮ እስከ ሃይማኖት መሪዎች ድረስ አበቱታ እያሰሙ የህግ ያለህ የመንግስት ያለህ እያሉ ነው::ሲታይ ግን ምንም መፍትሄ ያለው አይመስልም ይህ ደግሞ ገዢ ነኝ ባዩ አካል የስርኣት ለውጥ ማምጣት ስለማይችል በህዝቦች የጋራ ትግል ለውጡን ተከትሎ ህግና ደንብ ሊከበር እንደሚችል የሚታወቅ እና የተጠና ነው::በዚሁ ከቀጠለ ግን አገር ከገባችበት አደጋ ወደ ሌላ አደገኛ አደጋ እንደምትሸጋገር ለመናገር እወዳለሁ::
ሌላው የተንሰራፋው ሙስና የሃገር ሃብትን በተገቢው ቦታ ላይ እንዳናውል እንቅፋት ሆኗል::ሁሉም በተደጋጋሚ ታግለው ስልጣን እንደያዙ የሚደነፉት የወያኔ ጁንታ አባላት በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው አገሪቷን እርቃኗን አስቀርተዋታል:: ይህ አደገኛ የሙስና ሂደት ህዝብን ወደ ኑር ውድነት እና ድህነት እስር ውስጥ ከቶታል:: ተናግረን የማንጨርሳቸው እስር፣ ስደት ፣ስራ አጥነት ፣ግድያ ፣ክስራ መፈናቀል፣ ተመሳሳይ ምእንግስታዊ ውንብድናዎችቸና ሽብሮች በዜጎች ላይ እየተፈጸሙ በገሃድ እየታዩ እንዲሁም መንግስትዊ ቅጥፈት/ውሸቶች በአደባባይ እየተደሰኮሩ የትውልድን ሞራል ለመግደል ካለመታከት እየተውተረተሩ ነው። ራሳችንን ማንቃት ለለውጥ መነሳት ግድ ይለናል ፤ ደጋግመን እንናገራለን በሕዝብ ልጆች አፋጣኝ ትግል እጅግ ሊለወጥ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ :: በተጨማሪ በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::
የፖለቲካ ካንሰራችንን ተነጋግረን እና በጋራ ሆነን ከማዳን በጉልበት በሽሙጥ እና እኔ አውቅልሃለሁ በሚል አባዜ እስከመቼ ድረስ እንደምንቀጥል አልታወቀም:: ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: ሁላችንም ዜጋ እስከሆንን ድረስ ለሃገራችን እኩል አስታውጾ ማበርከት አለብን ።….እየተገፋን እስከመቼ?? ተነስ እንጂ ወገነ!
ብዙ ጊዜ ዲዚንፎርሜሽን የሚለው ቃል ዲዚንፎርማቲያ ከሚለው የሩስያ ቃል የተገኘ ነው በማለት የመስኩ አጥኚዎች ይከራከራሉ፣ በመቀጠልም ጆሴፍ ስታሊንን የቃሉ ፈጣሪውና እና ለጦር መሳሪያነት የተጠቀመው አርክቴክት ነው የሚል ክስ ያቀርባሉ። እንዲህ ዓይነቱ ግንዛቤ የቃሉን ወቅታዊ ፍቺ እና አተገባበር በእጅጉ ይቀርፃል። በይበልጥ የሚገርመው፣ በሐሰት መረጃ እና በ Populist አገዛዝ ወይንም መንግሥታት እና ‘የሐሰት መረጃ ስርጭት’ መካከል ያለው ታሪካዊ ዳራና ዝምድና ሰፊ ነው። እንደ ኦክስፎርድ መዝገበ-ቃላት የመሰሉትን ከእውነት የራቁ – እና የተሳሳቱ መረጃዎችን የቃል ፍቺ ከተመለከትን፣ “ሆን ተብሎ እና ዓላማ ያለው የውሸት መረጃ ስርጭት” በማለት ይገልፃል። ነገር ግን፣ የሀሰት መረጃ የሚለው ክስተት ከቋንቋ አመጣጥ ያለፈ ፣ ሳይኮሎጂስቶች እና አንትሮፖሎጂስቶች ታክቲካል ማታለል በሰው ልጅ የትብብር ተፈጥሮ ዝግመተ ለውጥ ውስጥ ወሳኝ እንደሆነ ይከራከራሉ። በፖለቲካውም መስክ፣ የሀሰትና የተዛባ መረጃ ማሰራጨት ብዙውን ጊዜ ስልታዊ በሆነ መንገድ የሰዎችን የትብብር አቅም ለመበዝበዝ ወይም ለመሸርሸር አገዛዞች የሚጠቅሙበት አይነተኛ ስልት ነው። ይህ ሆን ተብሎ የሚደረግ ማጭበርበር በማህበረሰባችን መካከል ትብብርንና ትስስርርን የሚያዳብሩትን ወሳኝ የሆኑ የመሰረተ ልማት አውታሮችን ይጨምራል። ከዓለም አቀፋዊ የድህረ-እውነት ሁኔታ (post-truth condition) ውስብስብነት ጋር ስንጋፈጥ፣ የሐሰት መረጃ ክስተት በራሱ ባለብዙ ትርጉሞች (polysemic) እና ሁለገብ (ተግባራዊ) ተፈጥሮን መረዳት አስፈላጊ ያደርገዋል።
ይህ ትንታኔ ስለ መሠረተ ልማት ዓለም በተለይም ከእውነት በኋላ ባለው የፖለቲካ ማዕቀፍ (post-truth politics) ውስጥ የመሠረተ ልማት አውታሮችን “የመገንባት” ወይም “የማውደም” እንድምታን ይመለከታል። ፖለቲከኞች እንዴት መሰረተ ልማትን እንደ ኢላማ እና ለሃሰት መረጃ ተግባራታቸው መሳሪያ አድርገው እንደሚጠቀሙበት በማሳየት በሐሰት መረጃ፣ በማህበራዊ ትብብር እና በመሰረተ ልማት መካከል ያለውን መስተጋብር በመመርመር በሀሰተኛ መረጃ ስርጭት የሚከሰቱ ተግዳሮቶች እና ከእውነት በሁዋላ ባለው የፖለቲካ ዘይቤ መሰረተ ልማቶችን እንደ ኢላማ እና መሳሪያነት መጠቀም አስመልክቶ በንቃተ ህሊናችን ላይ ግንዛቤዎችን ይጭምርልናል።