
11/06/2025
በኤምፖክስ በሽታ የተጠረጠሩ ባለሥልጣን ለይቶ ማቆያ አልገባም አሉ
በሽታው በአዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት እየተስፋፋ ነው ተብሏል
በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት 18 እንደሆነ በሚኒስቴሩ ቢገለፅም በሽታው በአዲስ አበባ ከተማ በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሆነ ታውቋል።
የአንድ የግል የጤና ተቋም ሰራተኛ ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ አንድ አሳሳቢ ክስተት ተፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል።
"በኤምፖክስ በሽታ እንደተያዙ የተጠረጠሩ አንድ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊ ወደ ተቋማችን መጥተው ነበር፣ ይሁንና ወደ ለይቶ ማቆያ አልገባም በማለት ጥለው ወጥተዋል" የሚሉት የጤና ባለሙያው ይህም ከፍተኛ መደናገጥን ፈጥሮ እንደነበር ተናግረዋል።
"በተደጋጋሚ የበሽታውን ተላላፊነት ብንነግራቸውም ሊቀበሉን አልፈለጉም፣ እያስረዳናቸው በሽታው የለብኝም ብለው ጥለው ሄደዋል" በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል።
ባለስልጣኑ ከዚህ ክስተት በኋላ አውሮፕላን ተሳፍረው ወደ ጅማ ከተማ በመሄድ አንድ ስሙ አይጠቀስ የተባለ ሆቴል ውስጥ ተቀምጠው ይገኛሉ።
ሌላ ለደህንነቴ ሲባል ስሜ አይጠቀስ ያሉ አንድ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ባልደረባ የጤና ባለሙያ ደግሞ በከተማው እየተመዘገበ ያለው የበሽታው ተጠቂ ቁጥር ምናልባት ይፋ ከተደረገው ከአስር እና ከዛ በላይ ይሆናል ብለዋል።
"ብዙ ኬዞች አሉ፣ ሁሉም ግን ለህዝብ ይፋ እየተደረገ አይደለም። ምናልባት በሽታው ነው አይደለም የሚለው እስኪጣራ ተብሎ ነው ተብሎ ቢታሰብ እንኳን ትክክል ያልሆነ አሰራር ነው፣ ይህ አካሄድ ህብረተሰቡን ለበሽታው የበለጠ ሊያጋልጥ ይችላል" በማለት ተናግረዋል።
መሠረት ሚዲያ እንዳስነበበው የጤና ሚኒስቴር እስካሁን የሚያወጣቸው የታማሚዎች በየት ከተሞች እንደሆኑ ለያይቶ እያቀረበ አይደለም።
Listen
https://onlineradiobox.com/et/agelgl/playlist/
https://zeno.fm/player/agelgl-radio
https://liveonlineradio.net/agelgl-radio
https://radio.menu/stations/agelgl-blogspot-com-agelgl-radio/
https://liveonlineradio.net/agelgl-radio
https://radiofy.online/en/et/agelgl
https://liveradiostations.net/station/agelgl-radio/