Abay Tube

Abay Tube I invite you to SUBSCRIBE me 💜 I'm starting my own You Tube channel, Facebook and Instagram accounts to create an honest and approachable conversation.

📰 ABAY TUBE | Fast • Trusted • Informative
Welcome to Abay Tube your reliable source for the latest news from Ethiopia and around the world.
📌 Breaking News
🌍 World News
💻 Technology & AI
💼 Business & Finance
⚽ Sports Updates
🇪🇹 Ethiopia & Global Thank You !!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇

https://www.youtube.com/channel/UCSIvgnvTSV-OLuRhDuOhuyA
•Facebook:- https://www.facebook.com/AbayOnYoutube/
•Instagram:- https://www.instagram.com/abayentertainment
•Telegram: - https://t.me/AbayonYouTube
•YouTube: - https://www.youtube.com/c/AbayTube_Know

እናት ፓርቲ መምህር ዮሐንስ ሸዋቀናን ፕሬዚዳንት እንዲሁም ወ/ሮ ጥሩማር አባተን ም/ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።
10/10/2026

እናት ፓርቲ መምህር ዮሐንስ ሸዋቀናን ፕሬዚዳንት እንዲሁም ወ/ሮ ጥሩማር አባተን ም/ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።

የትግራይ ስቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትና ስምረት ፓርቲን በመቀላቀላቸው ከኃላፊነት የተባረሩት ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በሚኒስትር ዴ...
10/10/2026

የትግራይ ስቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩትና ስምረት ፓርቲን በመቀላቀላቸው ከኃላፊነት የተባረሩት ወ/ሮ ሰብለ ካሕሳይ በዛሬው ዕለት በጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታነት ተሹመዋል።

ዳግማዊት ሽፍራው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።ሃና ተኽልቁ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።አምባሳደር ፍጹም አረጋ የኢሚግሬሽንና...
10/10/2026

ዳግማዊት ሽፍራው የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።

ሃና ተኽልቁ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሹመዋል።

አምባሳደር ፍጹም አረጋ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ።

(ዛሬ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተቋማት ውስጥ ለሚያገለግሉ 11 አመራሮች ሹመት ሰጥተዋል)

በአላማጣ ከተማ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረስ ተጀመረ   በአላማጣ ከተማ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች አስፈላጊውን የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራ ተጀምሯል።ሙሉ በሙሉ በፌደራል መን...
10/10/2026

በአላማጣ ከተማ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ማድረስ ተጀመረ

በአላማጣ ከተማ ለችግር ለተጋለጡ ዜጎች አስፈላጊውን የሰብዓዊ ድጋፍ የማድረስ ሥራ ተጀምሯል።

ሙሉ በሙሉ በፌደራል መንግሥት በተሸፈነው በዚህ የሰብዓዊ ድጋፍ ፕሮግራም ለአስቸጋሪ ሁኔታዎች ተጋላጭ ለሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች አስቸኳይ ዕርዳታ እየቀረበ ይገኛል።

የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ መንግሥት ድጋፉን በአጭር ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ እንዲደርስ ማድረጉ ለዜጎች ፈጥኖ ደራሽ መሆኑን በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል።

የሰብዓዊ ድጋፍ ሥርጭቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፣ ድጋፉ በትክክል ለተቸገሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እንዲደርስ የሚያስችሉ አሠራሮች መዘርጋታቸውም ተመላክቷል።

"ለታላቋ ኢትዮጵያ የሚመጥን የፖሊስ ኃይል እየገነባን ነው" - ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል*****************ለታላቋ ሀገር ኢትዮጵያ የሚመጥን የፖሊስ ኃይል ለመገንባት የሚያስ...
10/10/2026

"ለታላቋ ኢትዮጵያ የሚመጥን የፖሊስ ኃይል እየገነባን ነው" - ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል
*****************

ለታላቋ ሀገር ኢትዮጵያ የሚመጥን የፖሊስ ኃይል ለመገንባት የሚያስችል ሥራ እየተሠራ ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል ገለፁ።

የኢትዮጵያን ሰላምና ደኅንነት ለማወክ የሚንቀሳቀሱ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ላይ የሚሰጠውን ፖሊሳዊ ግዳጅ በብቃት መወጣት የሚችያስችል አቅም እየተፈጠረ መሆኑን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ከለውጥ ወዲህ የሀገሪቱን ፖሊስ ለማዘመን እየሠራ ከሚገኛቸው ሥራዎች አንዱና ዋናው የኦፕሬሽን አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የተለያዩ የስፔሻላይዜሽን ስልጠናዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽነሩ አክለውም፤ ለዚህች ታላቅ ሀገርና ታላቅ ሕዝብ እንዲሁም ትልቅ ርዕይ ላለው መንግሥት የሚመጥን የፖሊስ ኃይል ለመገንባት የሚያስችል ሥራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ በተገኙበት ልዩ የኦፕሬሽን ስልጠና የወሰዱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት በአፋር ክልል አዳይቱ ልዩ የኦፕሬሽን ስልጠና ማዕከል ተመርቀዋል።

በዚሁ ወቅት ኮሚሽነሩ ተመራቂዎች በአስቸጋሪ የአየር ፀባይ እና የመሬት አቀማመጥ የሚሰጣቸውን ማንኛውንም ፖሊሳዊ ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችል በተግባር የተደገፈ ስልጠና ውስጥ ያለፉ መሆናቸውን መግለጻቸውን ከፌደራል ፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

#የመደመርመንግሥት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት ፣ ከዛ በፊት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣ በብሔራዊ መረጃና ደህነትም አመራር ሆነው ያገለገሉት እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ...
10/10/2026

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት ፣ ከዛ በፊት በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣ በብሔራዊ መረጃና ደህነትም አመራር ሆነው ያገለገሉት እንደሻው ጣሰው (ዶ/ር) የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ተደርገዋል።

መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም

እናቅዳለን ፤ ብዙ ሳናስጮህ እንሰራለን ፤ ውጤት ለሕዝባችን እንናገራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖ...
10/10/2026

እናቅዳለን ፤ ብዙ ሳናስጮህ እንሰራለን ፤ ውጤት ለሕዝባችን እንናገራለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባውን ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መርቀው ስራ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፥ የፋብሪካው መገንባት ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ ጥሬ ዕቃዎችን ብቻ ወደ ውጭ ልካና ውድ ዋጋ ከፍላ መልሳ የተሰሩ ምርቶችን የምታስገባበትን ሂደት ለማስቀረት ነው ብለዋል ።

ለአብነትም በቡና ንግድ ሂደት ጥሬ ቡና ተወስዶ ውጭ ሃገር ታሽጎና ተቆልቶ በብዙ እጥፍ ተመልሶ የሚገዛውን ውድ ዋጋ አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በማዕድን ዘርፍ የሰራነው ስራ ውጤት እያመጣ ነው ብለው ይህንን ፋብሪካ አፋችንን ዘግተን ነው የሰራነው ነው ያሉት።

አክለውም እናቅዳለን ፤ ብዙ ሳናስጮህ እንሰራለን ፤ ውጤት ነው ለሕዝባችን የምንናገረው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ ወርቅ ስትልክ ያለማጣሪያ በመሆኑ 30 በመቶ የሚሆነው እንደ ቆሻሻ ተቆጥሮ ይቀነስ ነበር ፤ በዚህ ሂደት ውስጥ ሊገኙ የሚችሉ እንደ ብር እና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ውድ ዋጋ ያላቸው ነገሮችም ይጠፉ ነበር ፣አሁን የተገነባው ማጣሪያ ይህንን ችግር የሚቀርፍ እንደሆነ አመልክተዋል።

ፋብሪካውም በዓመት እስከ 80 ቢሊየን ዶላር የሚደርስ ኤክስፖርት ማከናወን የሚያስችል ትልቅ አቅም ያለውና ከአፍሪካ ቀዳሚ ከሆኑት አንዱ መሆኑን ጠቁመዋል።።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በወርቅ ብቻ ሳይሆን በሌሎችም ዘርፎች ጥሬ ዕቃን የማስገባት እና የማውጣት ሂደትን በማስተካከል የኢትዮጵያን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ ትልቅ ምዕራፍ ተከፍቷል ነው ያሉት።

መቐለ 📍የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን የጫነች አውሮፕላን ዛሬ መቐለ አሉላ አባነጋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መግባቷን የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።ዛሬ መቐለ የገባችው የኢ...
10/10/2026

መቐለ 📍

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞችን የጫነች አውሮፕላን ዛሬ መቐለ አሉላ አባነጋ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ መግባቷን የጀርመን ድምጽ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

ዛሬ መቐለ የገባችው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የአየር መንገዱ የቴክኒክና ሌሎች ሰራተኞችን የጫነች ናት ተብሏል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ጀምሮ ወደ መቐለ ተቋርጦ የነበረው መደበኛ በረራ እንደሚጀምር አሳውቋል።

መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ/ም

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ተሹመዋል።
10/10/2026

ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው በጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ተሹመዋል።

መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ምአዲስ አበባጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦    #የመደመርመንግሥት
10/10/2026

መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም
አዲስ አበባ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦


#የመደመርመንግሥት

Address

Addis Ababa
Addis Ababa
1983/1110

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abay Tube posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Abay Tube:

Shortcuts

Share