
04/08/2025
ትክክለኛ ውሳኔ!!
ሐምሌ 27 ቀን 2017 ዓ.ም
ከአፋጎ የተላለፈ መመሪያ
```````````````````````````
አገዛዙ ህዝብን ለማጎሳቆል የማይጠቀመው የድንቁርና እና የሽብር መንገድ የለም። ከዚህ ቀደም ህግ የማያቃቸው እና መንግስት ተብዬው ቡድንም የማይቆጣጠራቸው ኬላወችን አቋቁሞ ከተሳፋሪወች እና ከአሽከርካሪወች ገንዘብ የሚዘርፍ መሆኑም ይታወቃል።
ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ ጠንከር ያለ ምት ሲያርፍበት በህዝብ ላይ ግድያ በመፈፀም ከመበቀል ባሻገር ትላልቅ መንገዶችን በመዝጋት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴወችን ማወክ እና ህዝብን እገታ ውስጥ ማስገባት ጀምሯል።
ከባህርዳር በመርጡለ ማርያም፣ መካነ-ሰላም ኮምቦልቻ የሚወስደውን እና ወሎ እና ጎጃምን የሚያገናኘውን ብቸኛ መንገድ ከመጋቢት 06 ቀን 2017 ጀምሮ እስካሁን ድረስ ማለትም ላለፉት ስድስት ወራት እንደዘጋው ይገኛል።
በዚህ የውንብድና ተግባሩ ያልረካው አረመኔ አገዛዝም ከሐምሌ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ከባህርዳር በሞጣ ወደ አዲስ አበባ የሚወስደውን ዋና የአስፋልት መንገድ ሙሉ በሙሉ በመዝጋት ህዝብን እያሰቃዬ ይገኛል።
በመሆኑም አገዛዙ መንገዱን የማይከፈት ከሆነ የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ የምንገደድ መሆኑን ብናሳውቅም ጠላት መንገዱን እንደዘጋው ይገኛል።
በመሆኑም ከመጪው ሐሙስ ነሐሴ 01 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የባህርዳር-ሞጣ-አዲስ አበባ መንገድ እስኪከፈት ድረስ የባህርዳር -ደብረ ማርቆስ-አዲስ አበባ መንገድ ከአምቡላንስ በስተቀር ለተሽከርካሪወች ዝግ የተደረገ መሆኑን እናሳስባለን።
አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!