Lafto werda 06 communication

Lafto werda 06 communication Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lafto werda 06 communication, Digital creator, Addis Ababa.

በመከላከያ የአየር ሀይል አውሮፕላኖች ጥገና እና በመከላከያ ኢንደስትሪ ውስጥ ምርምርን ለማጎልብት፣ ልምድ ልውውጥ እና አቅም ግንባታ እንደሚደረግ መግባባት የተደረሰበት ሌላኛው የቼክ ሪፐብሊክ...
29/11/2023

በመከላከያ የአየር ሀይል አውሮፕላኖች ጥገና እና በመከላከያ ኢንደስትሪ ውስጥ ምርምርን ለማጎልብት፣ ልምድ ልውውጥ እና አቅም ግንባታ እንደሚደረግ መግባባት የተደረሰበት ሌላኛው የቼክ ሪፐብሊክ ጉብኝት ውጤት ነው።
በዚህም መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በእነዚህ ተግባራት ላይ የተሰማራ ተቋምን ጎብኝተዋል።

ሁለተኛ ምዕራፍ አንደኛ አመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የጉድጓድ ቁፋሮ መርሀ-ግብር ተካሄደ ።ላፍቶ ኮሙኒኬሽን :-ሰኔ 15/2015 ዓ. ም   የንፋስ ስልክ...
22/06/2023

ሁለተኛ ምዕራፍ አንደኛ አመት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ የጉድጓድ ቁፋሮ መርሀ-ግብር ተካሄደ ።

ላፍቶ ኮሙኒኬሽን :-ሰኔ 15/2015 ዓ. ም

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ፣የክፍለ ከተማና ወረዳ አመራሮች፣የመንግስት ሰራተኞች፣ የማህበራዊ ሚዲያ አንቂዎች እንዲሁም በጎ ፈቃደኞች በጋራ በመሆን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ መትከያ የጉድጓድ ቁፋሮ መርሃግብር በለቡ ወረዳ ልዩ ስሙ ሁጂያን አከባቢ አከናውነዋል።

የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች ሊግ አስተባባሪ የሆነው ወጣት አብዱልሃኪም ቡልጎ እንደገለፀው ችግኞችን በመንከባከብ መትከል በተፈጥሮ ሀብቷ የለማች ሀገር ለመፍጠር የወጣቱ ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል።

ወጣት አብዱልሃኪም አክሎም የወጣት ሊግ አደረጃጀት በርካታ የበጎ ፍቃድ ስራዎችን ለተከታታይ አመታት ስንሰራ የቆየን እና በመስራት ላይ ያለን መሆኑ አሁንም አጠናክረን ለመቀጠል ከችግኝ መትከያ ቁፋሮ በላይ የሃገራችንን ከፍታ የምናረጋግጥበት፣ ከተማችንን ውብ ለማድረግ የምንተጋበት ነው ብለዋል።

የንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘላለም ብርሃኑ ለወጣቶች ባስተላለፋት መልእክት ክፍለ ከተማችንን በሠላም፣በኢኮኖሚ፣በማህበራዊ እንዲሁም በፖለቲካው ዘርፍ በርካታ ስራዎችን ስንሠራ ቆይተናል ያሉ ሲሆን የዛሬው የጉድጓድ ቁፋሮ መርሀግብር ቁፋሮ ብቻ ሳይሆን የአብሮነትና የመተባበር እሳቤን የምናጎለብትበት፣ ክፍለ ከተማችንን ብሎም ከተማችንን አረንጓዴ በማልበስ ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ውብ ከተማን የመፍጠር ልዪ ተልእኮ ይዞ የሚከናወን መርሃግብር ነው ብለዋል ከዚህም ጋር አያይዘው በቀጣይም ራዕያችንን ከግብ ለማድረስ ለተሻለ ተግባር እራሳችንን ዝግጁ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም በዚህ አረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ላይ ወጣቶች እንዲሁም መላው የክፍለከተማችን ነዋሪዎች እንዲሳተፋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ፅ/ቤቶችንና ሰራተኞችን እውቅና  ተሰጠ ።   #የወረዳ 06 አስተዳደር   ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃይል ልማት ፅ/ቤት በ2015 በጀት አመት የ6 ወር  የተሻለ  ...
27/04/2023

የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ፅ/ቤቶችንና ሰራተኞችን እውቅና ተሰጠ ።

#የወረዳ 06 አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃይል ልማት ፅ/ቤት በ2015 በጀት አመት የ6 ወር የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ፅ/ቤቶችና ሰራተኞች በዛሬው እለት በ53 ቀበሌ አዳራሽ እውቅና ሰጥቷል።
√ በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ የወረዳው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተከተል ላኤቦ ፣ የወረዳው ብልፅግና ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሙሉቀን ታደለ፣ የወረዳው ም/ስራ አስፈጻሚና የስራ እድል ፈጠራና ኢንዱስትሪ ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሃይሉ ገ/አምላክ ፣ የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃይል ልማት ፅ/ቤት ሃላፉ አቶ ለኣ ጊቲቆ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን በየደረጃው ያሉ የወረዳው አመራሮች ፣ የምክር ቤት ቋሙ ኮሚቴ፣ አጠቃላይ የወረዳው ሰራተኞችና ተጋባዥ እንግዶችም ተገኝተዋል ።
√ የወረዳው ንግድና ኢዱስትሪ ፅ/ቤት ፣ የወረዳው አርሶ አደርና ከተማ ግብርና ፅ/ቤት ፣ የወረዳው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት በክፍለ ከተማና በወረዳ ደረጃ በተደረገ ምዘና በአማካኝ ውጤት የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ ከ1ኛ - 3ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫና የሰርትፊኬት ተሸላሚ ሆነዋል ።

√ በእውቅናው ፕሮግራም በ2015 በጀት አመት በ6 ወር አፈጻጸም በክፍለ ከተማ ደረጃ ተመዝነው የተሻለ አፈጻጸም በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ ለያዙ ፅ/ቤቶች እውቅና ተሰጥቷል ። በተመሳሳይ በወረዳ የሪፎርም ቡድን ተመዝነው ከ1 -3ኛ ደረጃ የያዙ የወረዳው መድሃኒትና ቁጥጥር ፅ/ቤት ፣ የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ፅ/ቤት ፣ እንዲሁም የወረዳው ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት የእውቅና ሰርትፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
√ የወረዳ 06 አስተዳደር በ2015 በጀት አመት በ6 ወር አፈጻጸም በክፍለ ከተማው ከሚገኙ 13 ወረዳዎች 1ኛ ደረጃ የወጣ ሲሆን በዚህ አስተዳደሩ ለዚህ ስኬታማ ውጤት በዛሬው እለት እውቅና ሰጥቷል ።
19/08/2015

ለመላው  የእስልምና  እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛ የኢድ  አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።አቶ ተከተል ላኤቦየን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈጻሚ ************...
20/04/2023

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛ የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።
አቶ ተከተል ላኤቦ
የን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈጻሚ
*******************
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች የወረዳችን ነዋሪዎች ፣ በየደረጃው ያላችሁ ሙስሊም አመራሮች ፣ የመንግስት ሰራተኞች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችና አጠቃላይ በመዋቅራችን ውስጥ የምትገኙ ሙስሊሞች ፣ እንኳን ለ1444ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያልኩ ከታላቁ ረመዳን ጾም መግባት ማግስት ጀምሮ ኢትዮጲያዊ አንድነታችንንና የመተጋገዝ በጎ እሴታችንን በማሰብ ማእድ በማጋራትና ሙስሊሙን ማህበረሰብ የጾም አፍጥር በማድረግ በጎና አንድነትን የሚያጠናክር ተግባር ላይ ከወረዳው ጎን በመሆን ለኢትዮጲያዊ መልካም እሴቶታችንን መጎልበት ላደረጋችሁት ሁሉ በወረዳው አስተዳደር ስም አመሰግናለሁ።
በዓሉ የሰላም ፣የፍቅር፣ የአንድነት፣የብልፅግናና የተቸገሩትን በመርዳት የምናሳልፈው በዓል እንዲሆን እየተመኘሁ ይህን ታላቁን የኢድ አልፈጥር በዓል ስናከብር በሮመዳን ፆም ወቅት የተገበርነውን መልካምነት ፣ አዛኝነት በማስቀጠል የተቸገሩትን በመርዳት ፣ አቅመ ደካሞችን በመደገፍ እንዲሁም ለአንድነት ፣ለወንድማማችነትና እህትማማችነት ጸሎት በማድረግና በመተሳሰብ እንዲሆን ስል መልእክቴን አስተላልፋለሁ።
በድጋሚ መልካም የኢድ አልፈጥር በዓል ይሁንላችሁ።

የወረዳ 06 ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተከተል ላኤቦ
12/08/2015

በጸጥታና በወንጀል መከላከል ዙሪያ ከሞተር አሽከርካሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።  06_ኮሙኒኬሽን √ የወረዳ 06 ሰላምና ጸጥታ ፅ/ቤትና የጎፋና አካባቢው ፓሊስ ጣቢያ በወንጀል መከላከልና በ...
04/04/2023

በጸጥታና በወንጀል መከላከል ዙሪያ ከሞተር አሽከርካሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ ።
06_ኮሙኒኬሽን
√ የወረዳ 06 ሰላምና ጸጥታ ፅ/ቤትና የጎፋና አካባቢው ፓሊስ ጣቢያ በወንጀል መከላከልና በጸጥታ ዙሪያ ከንፋስ ስልክና ከጊሽ አባይ ሞተር ማህበር አባላት ጋር በዛሬው እለት በ53 ቀበሌ አዳራሽ ውይይት አካሂደዋል ።
√ የወረዳው ሰላምና ጸጥታ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ከበደ ኢተቻ ፣ የጎፋና አካባቢው ፓሊስ ጣቢያ ዋና አዛዥ ኮማንደር ዘሪሁን አሰፋ መድረኩን የመሩት ሲሆን የወንጀል መከላከል ሃላፊ ዋና ኢንፔክተር ከበደ ተንኩራ እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ፓሊስ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ዘውዱ ሃይሌ በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል። ።
√ በውይይቱ በሞተር ላይ የሚካሄዱ የቅሚያና የስርቆት ወንጀሎች ከመከላከልና ከመቆጣጠር እንዲሁም ሌቦችን አጋልጦ በማውጣት በስራ ዘርፉ ላይ እየታየ ያለውን የወንጀል ተግባር ለማስቀረት በጋራ መስራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
√ በዚህም የሁለቱም ማህበር አባላት በሞተር ላይ የሚሰሩ ወንጀሎችን ከመከላከልና በዚህ ስራ ሽፋን ወንጀል እየሰሩ ያሉ አካላትን በማጋለጥና ለህግ በማቅረብ በኩል ከአካባቢው ፓሊስና ከጸጥታ አካላት ጋር በመስራት ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል ።
26/07/2015

አስተዳደሩ ወርሃዊ የለውጥ አመራር ፎረም መድረክ አካሄደ።   06 _ኮሙኒኬሽን √ የወረዳ 06 አስተዳደር ወርሃዊውን የለውጥ አመራር ፎረም መድረክ  በዛሬው እለት አካሄደ። የወረዳው ምክትል ...
31/03/2023

አስተዳደሩ ወርሃዊ የለውጥ አመራር ፎረም መድረክ አካሄደ።

06 _ኮሙኒኬሽን
√ የወረዳ 06 አስተዳደር ወርሃዊውን የለውጥ አመራር ፎረም መድረክ በዛሬው እለት አካሄደ። የወረዳው ምክትል ስራ አስፈጻሚ አቶ ሃይሉ ገ/አምላክና የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ላኣ ጊቲቆ መድረኩን የመሩት ሲሆን በውይይቱ ላይ የወረዳው ሴክተር ፅ/ቤቶች ሃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።
√በመድረኩ በሰራተኞች የስራ ሰዓት ቁጥጥርና ስምሪት በተመለከተ በድንገተኛ ቁጥጥር የተገኘ ግኝት ሪፓርት ቀርቧል።በተጨማሪም በክትትል ድጋፍ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ሪፓርት ቀርቦ ሃላፊዎችና የቡድን መሪዎች ሰፊ ውይይት አድርገውበታል።
√ ሰራተኞች የመንግስት ሰዓትን በማክበርና የአገልግሎት ቀናትን ለአገልግሎት ብቻ በማዋል በወረዳው አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ ደንበኞች ፈጣንና ፍትሃዊ አገልግሎት የመስጠት ግዴታቸውን መወጣት እንደሚገባቸውና ይህንንም በተለየ ትኩረት መከታተል እንደሚገባ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ለሁለት አመታት. በአንድ ማዕከል የነበረው የሰራተኞች የሰዓት መቆጣጠር አሰራር በየፅ/ቤቱ በመመለስ ሃላፊዎችና ቡድን መሪዎች በሃላፊነት እንዲቆጣጠሩ ውሳኔ ተላልፏል።
√ የስራ ቦታዎችን ምቹ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጥ የማሻሻል ስራ በመስራት በኩል ጥሩ ጅማሮዎች ቢኖርም የአስተዳደሩን ግቢ ሆነ ቢሮዎች ለአካል ጉዳተኞች አገልግሎት ለመስጠት ምቹ እንዲሆኑ በቂ ስራ መሰራት እንደሚገባ ተጠቁሟል።
21/07/2015

የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ቅድመ 1ኛና  የመጀመሪያ ደረጃ ትም/ቤት  አውደ ርዕይ በማዘጋጀት ለዕይታ አበቃ ።  √ በወረዳችን ከሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የአጼ ዘርዓ ያ...
31/03/2023

የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ቅድመ 1ኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትም/ቤት አውደ ርዕይ በማዘጋጀት ለዕይታ አበቃ ።

√ በወረዳችን ከሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ቅድመ 1ኛና የመጀመሪያ ደረጃ ትም/ቤት የፎቶና የቅርጻቅርፅ አውደ ርዕይ በማዘጋጀት በዛሬው እለት ለዕይታ አበቃ ።
አውደ ርዕዩን ያዘጋጁት በትምህርት ቤቱ የሐገርክን እወቅ ክበብ፣ ስፓርት ክበብ እና የስነ ጽሁፍና ስነ ጥበብ ክበብ በጋራ ሲሆኑ በርእይው ላይ ሐገራችንን በተለያዩ ጊዚያት የመሩ መሪዎች ፎቶ፣ ብርቅዬ እና ድንቅዬ እንስሳቶች ፣ ታዋቂ ሰዓሊዎች፣ ደራሲዎችና አትሌቶች ፣ የሐገራችን ታሪካዊ ቦታዎችን የያዙ ቅርጻቅርጾችና ፎቶዎች ለእይታ ቀርበዋል ። በተጨማሪም የሳይንስ ስራዎችን ፣ የስፓርት ሜዳዎችንና መሰል ስራዎች በአውደ ርዕዩ ተካቷል።
√ በአውደ ርእዩ ላይ የወረዳው አስተዳደር አመራሮች ፣ የትምህርት ቤቱ መምህርን፣ ተማሪዎች፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና የትምህርት ፅ/ቤት ሱፐርቫይዘሮች ተገግኝተዋል።
22/07/2015

 ። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር  ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ኘሮጀክት የመሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ አመት ክብረ በዓል መነሻ በማድረግ በወረዳችን ...
21/03/2023



በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ኘሮጀክት የመሠረተ ድንጋይ የተጣለበት 12ኛ አመት ክብረ በዓል መነሻ በማድረግ በወረዳችን በገብርኤል አደባባይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊት ለፊት የህዝብ ንቅናቄ የገቢ አሰባሰብ መርሀግብር ተጀመረ።

መርሃግብሩ ከዛሬ ቀን 12/07/2015 ዓም እስከ 30/07/2015 ዓ/ም ድረስ የሚቆይ ሲሆን የወረዳው አመራሮች፣ባለሙያዎች፣ነጋዴዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በቦድ ግዢ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ስለሆናም ዛሬ የተጀመራው የገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ለስምንት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በመሆኑ በወረዳው የሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በቦንድ ግዢ ንቅናቄ ላይ በመሳተፍ የኢትዮጵያዊነት አሻራቸውን እንዲያስቀምጡ አስተዳደሩ ጥሪውን አስተላልፏል።

07/03/2023
ፅ/ቤቱ በጤና፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች   ሴቶች፣ህጻናትና አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞችን ባማከለ  መልኩ የተሻለ ስራ እንደሰራ ገለጸ።  √የወረዳ 06 ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ...
26/02/2023

ፅ/ቤቱ በጤና፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ሴቶች፣ህጻናትና አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞችን ባማከለ መልኩ የተሻለ ስራ እንደሰራ ገለጸ።

√የወረዳ 06 ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ፅ/ቤት በበጀት አመቱ ስድስት ወር ውስጥ በጤና ፣በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፎች ሴቶች፣ህጻናትና አረጋዊያንና አካል ጉዳተኞችን ባማከለ መልኩ የተሻለ ስራ እንደሰራ በፅ/ቤቱ የህጻናት መብት ድጋፍና ክብካቤ ቀዳማይ ልጅነት እድገት ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ታደሰ ገለጹ።
√እንደ ቡድን መሪው ገለጸ ፅ/ቤቱ በጤና ዘርፍ ለ408 ያህል የህብረተሰብ ክፍሎች በስነ-ተዋልዶ ፣ በኤችአቪ፣ በማህጸር ካንሰር ጫፍ ፣በፌስቱላና በተለያዩ ጤና ነክ ጉዳዮች ግንዛቤ የመስጠት ስራ ተሰርቷል በተጨማሪም የሴፍትኔት መርሃ ግብር የታቀፉና ቀጥታ ተጠቃሚ የሆኑ 575 ያህሉን የጤና መድህን ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማመቻቸትና የማስተባባበር ስራ ተሰርቷል ሲሉ ቡድን መሪው ገልጸዋል
√በትምህርት ዘርፍ 29 ያህል ማንበብና መጻፍ ለማይችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች በተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት እንዲማሩ የተደረገ ሲሆን 21 ሴቶችና ህጻናት ከትምህርት ቤቶች ጋር በመነጋገር ከክፍያ ነጻ ትምህርት እንዲማሩ የማመቻቸት ስራ ተሰርቷል።
√በኢኮኖሚ ዘርፍ በጥቃቅናና መካከለኛ ኢተርፕራይዝ ፣ በገቢ ማስገኛ ዘርፎች፣ በህብረት ስራ ማህበራትና በተስማሚ ጊዞና ጉልበት ቆጣቢ ቴክኔሎጅዎች ዙሪያ እንዲሁም በብድር አወሳሰድና አመላለስ ዘዴ ዙሪያ ለ466 ሴቶች ግንዛቤ የመስጠት ሰፊ ስራ ተከናውኗል
ለ12 ሴቶች ብድር የማመቻቸትና ብድር እንዲያገኙ መደረጉን አቶ ሰለሞን አያይዘው ገልጸዋል ።
√ በማህበራዊ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ጥቃትና በስርአተ ጾታ ዙሪያ ለ975 የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ ጥቃት ለደረሰባቸው 15 ሴቶችና ህጻናት ተለያዩ የህግ ከለላ እንዲያገኙና የፍርድ ሂደቱን የመከታተል ሁኔታዎች ድጋፍ በሚያስፈልገው ጉዳይሽድጋፍ የማድረግ ስራ አከናውነናል ብለዋል
√ በተጨማሪም ለ61 ህጻናትና አጥቢ እናቶችን የአልሚ ምግብ ድጋፍ እንዲያገኙ ፣ ለ70 ያህል አካል ጉዳትኞች፣ አረጋዊያን፣ ሴቶች ህጻናት የተለያዩ ድጋፎች እንዲያገኙ መደረጉን የገለጹት አቶ ሰለሞን በግማሽ አመቱ የተሻለ አገልግሎት በመስጠት የደንበኛ እርካታ ከ85% ወደ 87% ከፍ ማለቱን አሳውቀዋል።
19/06/2015

በወረዳ 06 ፋይናንስ ፅ/ቤት የመንግስት  ህንጻና ንብረት አስተዳደር ቡድን 1ኛ በመውጣት  የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ።  √ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የመንግስት ህንፃና ንብረት አስተዳደር ...
23/02/2023

በወረዳ 06 ፋይናንስ ፅ/ቤት የመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ቡድን 1ኛ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ።

√ የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የመንግስት ህንፃና ንብረት አስተዳደር ጽ/ቤት 2015 በጀት አመት የስድስት ወር አፈጻጸም ባደረገው ምዘና ላይ በዛሬው እለት እውቅና የሰጠ ሲሆን የወረዳችን የመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ቡድንን 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ በመሆን ፅ/ቤትንና ወረዳውን የሚያኮራ ውጤት ተመዝግቧል ።
√ በእውቅና ፕሮግራሙ ላይ በወረዳ 06 ፋይናንስ ፅ/ቤት የመንግስት ህንጻና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰርካለም እሸቱ ተገኝተው ሽልማታቸውን ተቀብለዋል.

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lafto werda 06 communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Lafto werda 06 communication:

Share