Ethio journal ኢትዮ ጆርናል

Ethio journal ኢትዮ ጆርናል Ethio Journal is an Ethiopian digital media platform News campany established 2021G.C

ክፍት የሥራ መደብከ JMNt.me/ethiojournal2021
02/01/2025

ክፍት የሥራ መደብ
ከ JMN

t.me/ethiojournal2021

የጥበቃ ሠራተኛው የዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር አጨ!!! ነገሩ የሆነዉ ኡጋንዳ ዉስጥ ነዉ በሌክቸረሯ ፍቅር የተማረከዉ የጥበቃ ሠራተኛ ለ2 አመታት በግቢዋ አጥር ዙሪያ ይመላለስ ነበር በዚህ ወቅት ሌ...
02/01/2025

የጥበቃ ሠራተኛው የዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር አጨ!!!


ነገሩ የሆነዉ ኡጋንዳ ዉስጥ ነዉ በሌክቸረሯ ፍቅር የተማረከዉ የጥበቃ ሠራተኛ ለ2 አመታት በግቢዋ አጥር ዙሪያ ይመላለስ ነበር በዚህ ወቅት ሌክቸረሯን ለማማለል አስቂኝ ቀልዶችንና የፍቅር ቃላትን እያቀረበ ያዝናናት ነበር።

እልል ብሎ በአደባባይ የታገብኛለሽ ጥያቄ ጠይቋታል ሌክቸረሯም አላሳፈረችዉም የታገብኛለሽ ጥያቄዉን ተቀብላ'ትምህርት ቤት ገብቶ እንዲማር አደርገዋለሁ::

የወደፊቱም የልጄ አባት ይሆናል ብላለች የአለም ሚዲያዎች ይህንን ክስተት እወነተኛ ፍቅር ብለዋል።

t.me/ethiojournal2021

መረጃ ‼️ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ከጥር እስከ መጋቢት ባሉት ሦስት ወራት ከተለመደው የከፋ ደረቅ የአየር ንብረት እንደሚጠብቃቸው የኢጋድ የአየር ትንበያ ተቋም አመል...
02/01/2025

መረጃ ‼️

ኢትዮጵያን ጨምሮ በርካታ የምሥራቅ አፍሪካ አገራት ከጥር እስከ መጋቢት ባሉት ሦስት ወራት ከተለመደው የከፋ ደረቅ የአየር ንብረት እንደሚጠብቃቸው የኢጋድ የአየር ትንበያ ተቋም አመልክቷል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ደረቅ የአየር ንብረት የሚኖራቸው አገራት፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ፣ ታንዛኒያና ቡሩንዲ እንደሚኾኑ ተቋሙ ገልጧል።

በተለይ የአፍሪካ ቀንድ ቀጠና፣ ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ወቅት ለድርቅ፣ ጎርፍና የሰብል ተባይ ተጋላጭ እንደሚኾን የተቋሙ መረጃ ያመለክታል።

t.me/ethiojournal2021

02/01/2025
ፈረንጁ ቄስ በካናዳ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን   | ዳንቴ አሎንዞ ተወልደው ያደጉት በሩቅ ምሥራቋ አገር ፊሊፒንስ ነው፣ በሀገረ ካናዳ ፣በቶሮንቶ ከተማ ውስጥ ኑሯቸውን ካደረጉ 40 ዓመት አል...
02/01/2025

ፈረንጁ ቄስ በካናዳ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን

| ዳንቴ አሎንዞ ተወልደው ያደጉት በሩቅ ምሥራቋ አገር ፊሊፒንስ ነው፣ በሀገረ ካናዳ ፣በቶሮንቶ ከተማ ውስጥ ኑሯቸውን ካደረጉ 40 ዓመት አልፏቸዋል።

ዳንቴ፣ አንድ ቀን፣ “የእግዚአብሔርን መንግሥት ለማወቅ” መጽሐፍ ቅዱስ ገልጠው ማንበብ ጀመሩ። መፅሐፍ ቅዱስን ከኦሪት ዘፍጥረት ጀምረው ማንበብና ማጥናት ጀመሩ፣ ኢትዮጵያ የሚለውን ቃል ተደጋግሞ መፅሐፍ ቅዱሱ ውስጥ ያገኙታል ፣ ስለ ኢትዮጵያም ለማወቅ እጅጉን ይጎጎሉ።

ቅድስት ማርያም የምትባል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በአቅራቢያቸው እንዳለች ይሰማሉ፣ አንድ እሁድ ጠዋትም ወደ ቤተክርስቲያኒቷ ለመሄድ ይወስናሉ፣
“ገና በሩ ላይ ስደርሰና የቅዳሴውን ድምፅ ሰሰማ ልቤ ቀለጠች ፣ ትክክለኛ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ስፍራ እንደሆነ ተረዳሁ፣ ቋንቋውን ባላቀውም በቅዳሴው ቅላፄ አይኖቼ በእምባ ተሞሉ ይላሉ ቀሲስ ዳንቴ”።

ከዛን ቀን በኋላ የቤተክርስቲያኒቷ ምዕመን ሆንኩ፣ እጅግ ትልቅ ፍቅር ፣ አክብሮትና ቤተሰባዊነት ከምዕመናት አገኘሁ ፣ ከቤተክርስቲያኒቷ ጋር ህይወቴ ተቆራፕ። ዳንቴ የቤተክርስቲያንን መሰረታዊ ትምህርት ከተማሩ በኋላ ፣ ተጠምቀው እና ተፀልዬላቸው የኦርቶዶክስ እምነትን ተቀብለው ማህተም አሰሩ።

የቤተክርስቲያኒቱ አግልግሎት በግዕዝ እና በአማርኛ መሆኑ የቀሲሱ ዳንቴን የአገልግሎት ጉዞ ፈታኝ አድርጎታል። በእንግሊዘኛ የሚያስተረጉሙልኝ አገልጋዮች ነበሩ ፣ ግዕዝና አማረኛም በጥቂቱ ማጥናት ጀመርኩ ፣ ውሎዬና አዳሬ ቤተ ክርስቲያኒቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ሆነ።

ከዓመታት የትምህርት እና የቤተክርስቲያን አገልግሎት በኋላ ድቁናን እንዲቀበሉ መወሰኑ ተነገራቸው። አላመኑም። “በወቅቱ የተፈጠረብኝን ስሜት ቃላት አይገልጸውም” ይላሉ።

ዳንቴ ከ15 ዓመት በፊት ቶሮንቶ በምትገኘው የቅድስት ማሪያም ቤተክርስቲያን ዉስጥ. ድቁናን ከአቡነ መቃሪዮስ ተቀበሉ። ይኼኔ ዕድሜያቸው 39 ዓመት ነበር።

በግዕዝ እና በአማርኛ የተጻፉ ግን በላቲን ፊደል የተቀረጹ መጻህፍትን አጥንተዋል። ቋንቋውን ለመናገር ይቸገሩ እንጂ አንዳንድ መጽሐፍትን በቃላቸው ይዘዋል።በዚህ ሁኔታ፣ በተለይ በእንግሊዝኛ የቤተ ክርስቲያንን አግልግሎት መስጠት ጀመሩ።

ከ10 ዓመታት የቤተክርስቲያን የድቁና አገልግሎትበኋላ ዳንቴ ቅስናን ተቀበሉ። ቀሲስ ዳንቴ (ቀሲስ ገብረ መድኅን) ተባሉ።

ቀሲስ ዳንቴ በቅዳሴ ወቅት ረዳት ወይም ሁለተኛ ቄስ በመሆን ሥርዓቱን ይመራሉ። ከቅዳሴ በኋላ ምዕመናንን ያቆርባሉ። በክብረ በዓላት ወቅት ደግሞ ታቦት ተሸክመው ይይዛሉ።

ለመጀመሪያ ጊዜ ታቦት እንዲይዙ ሲነገራቸው “ይህንን ለማድረግ ብቁ አይደለሁም” ብለው ተከራክረዋል።

የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ምዕመናን መንፈሳዊ አባታቸውም ሆነው ያገለግላሉ ።

ቀሲስ ዳንቴ ባለ ትዳርና በአጠቃላይ አምስት ልጆች ያላቸው ሲሆን፣ የኦርቶዶክስ ተከታይ ከሆኑ በኋላ የወለዷቸውን ሁለት ልጆ ቻቸው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሥርዓት የክርስትና ጥምቀት ተደርጎላቸዋል።
ዮሐንስ እና ማክዳ የሚል ስምም ተሰጥቷቸዋል።

ቀሲስ ዳንቴ ወደዚህ ሕይወት ከመጡ በኋላ ወንድ ልጃቸው ዮሐንስ ከቤተክርስቲያን ጋር የተለየ ቁርኝት እንዲኖረው ወሰኑ። ከ 20 ዓመታት በፊት የሆነውን ልክ ዛሬ እንደሆነ ያስታውሱታል። “ኦርቶዶክስን በተቀልኩበት የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት ዮሐንስ የጸሎቴ ሁሉ አካል ነበር። “ፈጣሪ ወንድ ልጅ ስጠኝ። ስሙን ዮሐንስ ብዬ አንተን እንዲያገለግል እሰጠዋለሁ” ስል ለመንኩ። ይህ ከሆነልኝ ወደ ኢትዮጵያ እሄዳለሁ [ብዬ ተሳልኩ] አልኩ። ይገርማል፣ ፈጣሪ አደረገው። ዮሐንስ በ1996 ዓ.ም. ተወለደ። እኔ ደግሞ በ2001 ላይ ወደ ኢትዮጵያ ሄድኩ” ይላሉ።

በኢትዮጵያ የአንድ ወር ቆይታቸው በርካታ አካባቢዎችን ረግጠዋል። በርካታ ገዳማትን እና አብያተ ክርስቲያናትን ተሳልመዋል።

ወደ ጣና፣ አክሱም፣ ጎንደር ላሊበላ፣ ደብረዳሞ እና ሌሎች ቦታዎች ተጉዘው በገዳማቱ “ለጸሎታቸው ምላሽ የሰጣቸውን” ፈጣሪ አመሰግነዋል።

ልጃቸው ዮሃንስ ከ13 ዓመቱ ጀምሮ ላለፉት አስር ዓመታት ዲያቆን እና ዘማሪ ሆኖ ቤተክርስቲያንን በማገልገል ላይ ይገኛል። ዮሐንስ ክራር ይገርፋል፣ ማሲንቆም ይጫወታል፣ ከበሮ ይመታል።
ከዚያም አልፎ፣ እንጨት ቆርጦ፣ ክሮችን ወጥሮ ክራር እና ማሲንቆን ይሠራል።
ዮሐንስ ስለ ቤተክርስቲያኑ ሲናገር “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ካልኖርክበት አትረዳውም. . . እኔ እዚያ ነው ያደግኩት። ሁልጊዜ በየሳምንቱ እሄዳለሁ። የሳምንቱን ጉልበት የማገኘው ከቤተ ክርስቲያን ነው” ይላል።

የንግሥተ ሳባን ታሪክ እጅግ እንደሚወዱት የሚናገሩት ቀሲሱ፣ በንግሥቲቱ ሌላኛው ስም የመጨረሻዋን ልጃቸውን ‘ማክዳ’ ብለዋታል።

በትውልድ አገራቸው ፊሊፒንስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የማስገንባት ዕቅድም አላቸው። ዕቅድ ብቻ ሳይሆን ሥራ ጀምረዋል። 10 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ቤተክርስቲያን ለማስገንባት የሚሆን መሬት በግላቸው ገዝተዋል።

“በአገሬ ፊሊፒንስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ማስተዋወቅ እፈልጋለሁ። ሰዎች በዚያ እንዲያመልኩ፣ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲመጡ እፈልጋለሁ” ይላሉ።

ወደ ኢትዮጵያ ዳግም የመመለስ ሀሳብ እንዳላቸው እና አማርኛ መማር እንደሚፈልጉ የሚገልጹት ቀሲስ ዳንቴ ኢትዮጵያ የእኔ ዕጣ ፈንታ ነች። ለኢትዮጵያ ያለኝ ፍቅር መቼም አይቀየርም” ብለዋል።

የቀሲስ ዳንቴን አጭር ታሪክ በቪዲዮ ለመመልከት ከዚህ በታች ያለዉን ሊንክ ተጭነው ይመልከቱ::
https://youtu.be/0_CWASUg7rA?si=sU9NZNr8PFVS-oRR

መዝናኛ ሚዲያ፣ ዳንኤል ገብረማርያም፣ ከአሜሪካ

t.me/ethiojournal2021

በነገራችን ላይ እኛ ሀገር ላይ እየጮሁ ማውራት'ና መነፅር አድርጎ ሙሁር ሙሁር መጫወት ስለሚወደድ ነው እንጂ ቲክቶክ ላይ ዜና በማቅረብ ከሚታወቁት ከብሩክ ኒውስም ሆነ ከሙሴ ሰለሞን ይሄን ል...
01/01/2025

በነገራችን ላይ እኛ ሀገር ላይ እየጮሁ ማውራት'ና መነፅር አድርጎ ሙሁር ሙሁር መጫወት ስለሚወደድ ነው እንጂ ቲክቶክ ላይ ዜና በማቅረብ ከሚታወቁት ከብሩክ ኒውስም ሆነ ከሙሴ ሰለሞን ይሄን ልጅ በጣም የተሻለ ነው።

ጫፉ ላይም አይደርሱም !

ሁለቱ ብሩክ'ና ሙሴ ቲኪቫ የቴሌግራም ቻናል ላይ የሚለቀቁ ዜናዎችን ተሽቀዳድመው ከማንበብ ውጪ የሚጨምሩት ነገር የለም። አብዛኛው ጊዜ የተሰራ ዜና መድገም ነው ስራቸው።

በሚያቀርቡት ዜና ላይም የእነሱ ድርሻ የበቀቀን አሊያም የገደል ማሚቱ ነው። ቀድሞ የተባለ ዜናን መድገም'ና ማስተጋባት። ከዛ ባለፈ ከእነሱ የሚመጣም ሆነ የሚጨምሩት የራሳቸው ነገር የለም።

ጋዜጠኛ ስሞን ግን ዜና ከማንበብ በዘለለ ፖለቲካዊም ሆነ ኢኮኖሚያዋ እንዲሁም ማህበራዊ ጉዳዬች ላይ የሚሰጠው ትንታኔ የሚገርም'ና ፀዴ ነው። ስፖርቱ ላይም የዋዛ አይደለም። ልጁ በደንብ እንዳነበበ ያስታውቃል። የሚሰራውን ያውቃል። ሁሌም ቢሆን እሱ የሚሰራቸው አብዛኛው ዜናዎች አሊያም ዘገባዎች ላይ የእራሱን እውቀት'ና አተያይ ይጨምርበታል። ሲፈልግ በደንብ ይሞጎታል !

እናም ቲክቶክ ላይ እሱ እያለ የሁለቱ ፉክክር የዚህን ያህል መጮሁ አንድም የዘመናችን መገለጫ ነው። ህዝቡም ያለበትን የአስተሳሰብ ደረጃ የሚያሳይ ነው። በተለይ ይሄ ቲክቶክ የሚባል ነገር ከመጣ በኋላ በሰዎች ዘንድ እውቀት ያለው ሳይሆን ሙቀት የሚፈጥር ሰው ነው ተመራጭ።

[ሙስተጃብ ነኝ]

"የኦቲዝም ምስጢሮች" መጽሃፍ ምረቃ መርሃግብር በካፒታል ሆቴል !   | ትኩረቱን በኦቲዝም ላይ ያደረገውና በህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሃዲያ ይማም ተጽፎ አርትኦትና ቅንብሩ በጋዜጠኛ ...
01/01/2025

"የኦቲዝም ምስጢሮች" መጽሃፍ ምረቃ መርሃግብር በካፒታል ሆቴል !

| ትኩረቱን በኦቲዝም ላይ ያደረገውና በህጻናት ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሃዲያ ይማም ተጽፎ አርትኦትና ቅንብሩ በጋዜጠኛ መላኩ ብርሃኑ የተዘጋጀው "የኦቲዝም ምስጢሮች" መጽሃፍ አርብ ታህሳስ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ በ12 ሰዓት በካፒታል ሆቴል በታላቅ ሥነ- ሥርዓት ይመረቃል።

በምረቃው ላይ የማህበረሰብ መሪዎች፣ ታዋቂ የህክምና እና የጥበብ ሰዎችና በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ።

በመርሃ ግብሩ ላይ የሚሸጡት መጽሃፍት ለነህምያ ኦቲዝም ማዕከል ድጋፍ የሚውሉ ይሆናሉ፡፡ በኦቲዝም እና ተያያዥ የህጻናት አዕምሮ እድገት ሥርዓት መዛባት ምንነት ላይ በዘርፉ በታወቁ ምሁራን ትምህርታዊ ገለጻ ይደረጋል። ኦቲዝምን ታግለው ልጆቻቸውን የታደጉ ጀግና ወላጆች ተሞክሮ ይቀርባል።

የማይቀርበት ኹነት ነው። ኦቲዝምና ተያያዠ የህጻናት የዐዕምሮ እድገት ስርዓት መዛባት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ነው፡፡ ያገባናል !

ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

Face book

https://www.facebook.com/profile.php?id=100068924987163&mibextid=ZbWKwL

You Tube

https://youtube.com/?si=cc1RY82wDaEZQtny

Telegram

t.me/ethiojournal2021

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፀሙትን የመብትና የሃይማኖት ጥሰቶችን በሚመለከት ወቅታዊ መግለጫ ሰጥቷል።የመግለጫውን ሙሉ ቃል ተያይዞ ቀርቧል።👇👇👇...
01/01/2025

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የሚፈፀሙትን የመብትና የሃይማኖት ጥሰቶችን በሚመለከት ወቅታዊ መግለጫ ሰጥቷል።

የመግለጫውን ሙሉ ቃል ተያይዞ ቀርቧል።
👇👇👇
t.me/ethiojournal2021

«ጊዮን ሆቴል በየቀኑ የዋና እየከፈሉ ሚለማመዱ ልጆች አግኝቼ ሳወራቸው ፣ ለካ ጊዮን እየከፈሉ ዋና የሚለማመዱት በህገወጥ መንገድ ሲሰደዱ ባህር ለማቋረጥ ነው።»👇👇👇የታሪክ ተመራማሪ ኢብራሂም...
01/01/2025

«ጊዮን ሆቴል በየቀኑ የዋና እየከፈሉ ሚለማመዱ ልጆች አግኝቼ ሳወራቸው ፣ ለካ ጊዮን እየከፈሉ ዋና የሚለማመዱት በህገወጥ መንገድ ሲሰደዱ ባህር ለማቋረጥ ነው።»
👇👇👇

የታሪክ ተመራማሪ ኢብራሂም ሙሉ ሸዋ

የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች የትግራይ ክልል ት/ት ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ መሰረት ወደ ትምህርት ቤት ያቀኑ ቢሆንም በአድማ ብተና ፖሊስ እንዲመለሱ መደረጉ ተገለፀ!- አንድ ታዳጊ ተማሪ ላይ...
01/01/2025

የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች የትግራይ ክልል ት/ት ቢሮ በፃፈው ደብዳቤ መሰረት ወደ ትምህርት ቤት ያቀኑ ቢሆንም በአድማ ብተና ፖሊስ እንዲመለሱ መደረጉ ተገለፀ!

- አንድ ታዳጊ ተማሪ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል፣ በጉልበት ሂጃባቸውን ለመንጠቅም ተሞክሯል።



በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ በሂጃባቸው ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው የተፈናቀሉ ተማሪዎችን አስመልክቶ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ትላንት በፃፈው ደብዳቤ አዲስ የወጣ መመሪያ ባለመኖሩ ተማሪዎች በቀደመው አለባበሳቸው ይማራሉ ማለቱ ይታወሳል።

በዚህ መሰረት ተማሪዎቹ በዛሬው ዕለት ወደ ትምህርት ቤቱ ያቀኑ ቢሆንም በፀጥታ ሀይሎች እንዲበተኑ መደረጉን ከስፍራው ለሀሩን ሚዲያ የደረሰው መረጃ ያመላክታል።

የፀጥታ ሀይሎች በተማሪዎች ላይ ድብደባ መፈፀማቸው የተገለፀ ሲሆን አንድ ታዳጊ ሙስሊም ሴት ተማሪ ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባት ተሰምቷል።

የከተማው ትምህርት ቢሮ እና ከንቲባ ከክልል የተፃፈው ደብዳቤ እንደማይቀበሉት በመግለፅ ተማሪዎቹን በፀጥታ ኋይሎች እንዲበተኑ እና ተማሪዎቹን ሒጃቦቻቸውን ለመቀማት እንደሞከሩ ለማረጋገጥ ተችሏል።

የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በትምህርት ቢሮ የተፃፈው ደብዳቤ በሶስት ቀናት ውስጥ ተተግብሮ የሂጃብ ክልከላው በአዎንታዊ መልኩ ካልተፈታ በቀጣይ እንደ እስልምና ጉዳዮች ከህዝቡ ጋር በመመካከር የሚወሰዱ ሰላማዊ እርምጃዎች እንደሚያሳውቁ መግለፃቸው ይታወሳል።

© ሀሩን ሚዲያ

t.me/ethiojournal2021

🎺🎺🎺ጨርቆስ ላይ 2000 በላይ ነድያን ምገባ ሊካሄድ ነውየክራር ንግስቷ አርቲስት ሜሪ አርምዴ ሙት አመት መዝጊያ ፕሮግራም  ጥር 18 ቀን2017 አመተ ምህረት ጨርቆስ ላይ ከተክለሀይማኖት በ...
01/01/2025

🎺🎺🎺ጨርቆስ ላይ 2000 በላይ ነድያን ምገባ ሊካሄድ ነው

የክራር ንግስቷ አርቲስት ሜሪ አርምዴ ሙት አመት መዝጊያ ፕሮግራም ጥር 18 ቀን2017 አመተ ምህረት ጨርቆስ ላይ ከተክለሀይማኖት በጎ አድራጎት ማህበር ጋር በመተባበር በአይነቱ ለየት ባለመልኩ ከሁለት ሺ(2000) በላይ ነድያንን ምገባ ይደረጋል።

በእለቱም ለነድያኖች ልብስ በመስጠት ፕሮግራሙን ለመደገፍ የምትፈልጉ የጨርቆስ ልጆች ታዋቂ ኢትዮጵያን እንዲሁም ሚዲያዎች ተጋብዛችኋል።

ይህንንም መልካም ሀሳብ ሼር በማድረግ ተባበሩን ለምታረጉልንም መልካምነት እመ ብርሀን ትስጥልን።

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000644713605

ለበለጠ መረጃ
ስልክ 0922451317

[Abel Tesfaye]

Address

Addis Ababa

Telephone

+251952768656

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio journal ኢትዮ ጆርናል posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio journal ኢትዮ ጆርናል:

Share