
29/10/2022
✴✅ አስተማሪ ታሪክ ✅✴
✳ አይጧ የግድግዳውን ቀዳዳ በመጠቀም የቤቱ ባለቤት በታሸገ ካርቶን እቃ ይዞ ሲገባ ትመለከታለች፡፡ አይጧ “ዛሬ ደግሞ ምን አይነት ምግብ ይዞ መጣ!?” ብላ ተደስታለች፤ ነገር ግን ሰውዬው ለባለቤቱ ሊያሳያት የታሸገውን ካርቶን ሲከፍተው ወጥመድ ነው፡፡ አይጧ ደነገጠች፤ ወዲያውኑ ወደ እርሻው ተመለሰችና ጮክ ብላ “በዚህ እርሻ ውስጥ የምትገኙ እንስሳቶች ሆይ! የአይጥ ወጥመድ እየተጠመደላችሁ ነው፤ ወጥመድ! መጥመድ!!” በማለት ትናዘዛለች፡፡
ይህን ድምፅ በንቃት የሰማችው ዶሮ ካጎነበሰችበት ቀና በማለት “አይጦ ላንቺ ምን ያህል እንደሚያስጨንቅሽ ይገባኛል፤ ነገር ግን እኔን አይመለከትም እዛው ጣጣሽን ቻይ” ትላታለች፡፡ መከራ የበዛበት አይጥ የቤቱ በግ ወደሚገኝበት ቦታ ትሄድና የቤቱ ባለቤት የአይጥ ወጥመድ ገዝቶ እንደመጣ ትነግረዋለች፡፡
በጉ በንቀት አይን እየተመለከታት “ይቅርታ አድርጊልኝ አይጦ ምንም ልረዳሽ አልችልም” ይላታል፡፡ እቤት ውስጥ ከሚኖሩት እንስሳቶች የቀረው አንድ በሬ ነበር፤ አይጦ እርሱንም እርዳታ ለመጠየቅ ወዳለበት ትሄዳለች፡፡ “ወጥመድ ወጥመድ የአይጥ ወጥመድ ይዘው መጡ” ትለዋለች፤ በሬው ምንም ሳይመስለው እየሳቀ “አይጦ ምን ነክቶሽ ነው! እኔ እንደሆን ቆዳዬን እንኳ አይጎዳውም፤ ጣጣሽን ቻይ” በማለት ያባርራታል፡፡
አይጧ በጣም ተበሳጭታ አንገቷን አቀርቅራ የገበሬውን ወጥመድ ብቻዋን ልትጋፈጥ ወደ ቤቷ ትመለሳለች፡፡ በዛው ቀን ምሽት ሰው ሁሉ በተኛበት ወጥመዱ ከፍተኛ ድምፅ አሰማ፡፡
የገበሬው ሚስት አስቸጋሪዋ አይጥ ተያዘችልኝ በሚል ሀሳብ ወጥመዱ ወዳለበት ስፍራ ታቀናለች፡፡ ጨለማ ነበርና ምን እንደተያዘም ሳታውቅ የአይጧ ጭራ መስሏት በወጥመዱ የተያዘውን አደገኛ እባብ አፉን ነበር የያዘችው፡፡ እባቡ ነከሳት ነደፋትም፡፡ ገበሬው በፍጥነት ወደ ሆስፒታል ይወስዳታል፤ ከታከመች በሗላ ወደ ቤት ይመልሳታል ነገር ግን አደገኛ ራስ ምታቱ አለቀቃትም፡፡
ዶሮ ደግሞ ለእንደዚህ አይነት ራስ ምታት ፍቱን መድሃኒት መሆኑ የምናውቀው ጉዳይ ነውና ገበሬው ቤት ውስጥ የምትገኘውን ዶሮ “ለመድሀኒትነት” አረዳት፡፡ ነገር ግን የገበሬው ሚስት ከህመሟ ልታገግም አልቻለችም፤ ህመሟ እየበረታ ሄደ፡፡ የአካባቢው ሰው ሊጠይቃት ይጎርፍ ጀመር፤ ገበሬው እነዚህን እንግዳ ያስተናግድበት ዘንድ በጉን አረደው፡፡ የገበሬው ሚስት ህመሟ በርትቶ ሆስፒታል ስትታከም ከቆየች በሗላ ትሞታለች፡፡ ታዲያ ህዝብ ሁሉ ሊያስቀብራት መጣ፤ አስቀበራትም፡፡ ከቀብር ሲመለሱ ገበሬው ለቀባሪዎች በሬውን አረደው፡፡
አይጧ ይህንን ድርጊት በሙሉ በዛቺ ግድግዳ ቀዳዳ እንደ ፊልም ትመለከት ነበር፡፡ በድርጊቱ በጣም አዘነች፡፡
ይህ አጭር ታሪክ ትልቅ ትምህር አለው፡፡ ለሌላ ጊዜ አንድ ሰው ችግር ላይ ነው ሲባል ሰምተን የኔ ችግር አይደለም በምንልበት ጊዜ አስታውሱ አንዱ ተጨቆነ ማለት ሁላችንም መጨቆናችን አይቀርም፡፡
ሁላችንም ህይወት በምትባል ጉዞ ላይ ተሳታፊዎች ነን፡፡ ታዲያ መንገዱ ላይ ዞር ዞር ብሎ በመቃኘት እርስ በርስ ልንረዳዳ ይገባል፤ አይመለከተንም ብለን ብናስብ እርዳታ ከመስጠት ወደ ሗላ ማለት የለብንም፡፡
ከሁሉም በላይ አዛኙን ፈጣሪም እናስብ ለሰው ልጅ ስታዝን ያዝንልሀል ስትረዳ ይረዳሀል ፈጣሪ በእዝነቱ ይመልከተን ለነዚህ ሰዎች ይህን መልዕክት እናስተላልፍ; በህይወታችን ለረዱን በሙሉ እርዳታቸው እንደጠቀመን ይወቁልን እዚህ አለም ላይ አጥብቀህ ልትይዘው የሚገባ ምርጥ ባህሪ-“ቅን አስተሳሰብ” ነውና፡፡
ሼርርርር