Addis-Finfine press

Addis-Finfine press It is the page on Ethiopia political, ecomonic and socail timely development

" ማጥቃት ስንጀምር ማቆምያችን ቀይ ባህር ነው"። የኢትዮጵያ ዩቁርጥ ቀን ልጅ ጀነራል አበባው ታደሰ  ድል ለእናት ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹💪
25/09/2026

" ማጥቃት ስንጀምር ማቆምያችን ቀይ ባህር ነው"።

የኢትዮጵያ ዩቁርጥ ቀን ልጅ ጀነራል አበባው ታደሰ

ድል ለእናት ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹💪

Dawitee ,Irreachaa
25/09/2026

Dawitee ,Irreachaa

👉🌀 #የክህደት መጨረሻ፡ የአጉጉሞ ቡድን ውርደት እና የዘረፋ ዘመቻ!የአጉጉሞ ቡድን የባዕድ አጀንዳዎችን አንግቦ ከአፋር ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር መሠልፉ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ውድመት እና ው...
24/09/2026

👉🌀 #የክህደት መጨረሻ፡ የአጉጉሞ ቡድን ውርደት እና የዘረፋ ዘመቻ!
የአጉጉሞ ቡድን የባዕድ አጀንዳዎችን አንግቦ ከአፋር ህዝብ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር መሠልፉ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ውድመት እና ውርደት ይዞ መጥቷል። ይህ ሃይል ከጥቂት ቀናት ውጊያ በኋላ ወደ ዘረፋ በመሰማራት በዞን 02 ራህሌ እና ካለ መውጫ አከባቢዎች ንጹሀን ተሳፋሪዎችን እየዘረፈ ይገኛል። ተሽከርካሪዎችን እና የተለያዩ እቃዎችን በመዝረፍ የህዝብን ሰላም ማሳጣት ተልዕኮው አድርጎ ተነስተዋል። ከህዝብ ጥቅም ይልቅ የጠላትን ጥቅም የሚያስቀድመው ይህ ቡድን ድርጊቱ የክህደት ቁንጮ መሆኑን አሳይቷል። ከወያኔ እና ከሻዕቢያ ጋር ጥምረት የፈጠረ አካል ሁሉ መጨረሻው የህዝብ ጠላትነት እና መዋረድ ብቻ ነው። የአፋር ህዝብ ይህንን ፀረ-ሰላም ሃይል በአንድነት በመቆም የጥፋት ተግባሩን ከስር ነቅሎ ሊያወጣው ይገባል። የሽፍታው ቡድን መጨረሻም የውርደት እና የሽንፈት ጉዞ ብቻ ሆኖ ተጠናቋል።
​

ሰበር መረጃ!የፈረንሳይ መንግሥት የሕወሃትን ሐላፊነት የጎደለው የጦርነት እንቅስቀሴ በፅኑ አወገዘ!የፈረንሳይ መንግሥት በኢትዮጵያ ባለው ኤምባሲው በኩል ባስተላለፈው መልዕክት፣ “ፈረንሳይ በሰ...
24/09/2026

ሰበር መረጃ!

የፈረንሳይ መንግሥት የሕወሃትን ሐላፊነት የጎደለው የጦርነት እንቅስቀሴ በፅኑ አወገዘ!

የፈረንሳይ መንግሥት በኢትዮጵያ ባለው ኤምባሲው በኩል ባስተላለፈው መልዕክት፣ “ፈረንሳይ በሰሜን ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልል የሁኔታዎች መባባስ በእጅጉ አሳስቧታል። በተለይም የመቀሌ፣ የአክሱምና የሺሬ ኤርፖርቶች መያዝን እንዲሁም ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በአፋርና በአማራ ክልሎች ላይ የፈጸማቸውን ጥቃቶች ታኮንናለች። ሲቪሎችን ለመጠበቅ ሲባል ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት ከፍተኛ ግብረ-መልስ የመግታት እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ ታቀርባለች። ቀጠናዊ ግጭት እንዳይስፋፋ ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ነው።

ፈረንሳይ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋትን በጥብቅ ለማክበር ያላትን ቁርጠኝነት ድጋሚ የምታረጋግጥ ሲሆን፣ ወገኖች ሲቪሎችን የመጠበቅ እና የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትን የማመቻቸት ግዴታቸውን ታሳስባለች። በዚህ ረገድ የሰብዓዊ እርዳታን ማደናቀፍ፣ ማዞር እና ማጥቃት ተቀባይነት የለውም።

ፈረንሳይ ውጥረቶችን ለማርገብ ለሚደረገው አምኖ የተቀበለችው ታማኝ መንገድ ድጋፍ ለመስጠት የቆረጠች ሲሆን፣ በአፍሪካ ህብረት እና በከፍተኛ ተወካዩ ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ የሚመራውን የእርቅ ሂደት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በውጤታማነት ለማስፈጸም ያለመውን ጥረት ትደግፋለች።

24/09/2026
ሻዕቢያን ተማምኖ ያዙኝ ልቀቁኝ ያለ ሁሉ...ገና ጥቁር አምበሳው ሲነሳ.. ደብቁኝ ደብቁኝ ደብቁኝ ... እያለ ነው።
24/09/2026

ሻዕቢያን ተማምኖ ያዙኝ ልቀቁኝ ያለ ሁሉ...ገና ጥቁር አምበሳው ሲነሳ.. ደብቁኝ ደብቁኝ ደብቁኝ ... እያለ ነው።

ሰበር መረጃ 🚨   አርሚ 24 በድሮን ጥቃት ተደመሰሰ  ✈️የኢትዮጵያ አየር ሃይል የሻዕቢያ አጀንዳ ተሸካሚዉ የህዉሃት ቡድን ወታደራዊ ቤዞችን እንዲሁም  በየጦር ግንባሩ የተሰለፉ ታጣቂዎችን ...
24/09/2026

ሰበር መረጃ 🚨
አርሚ 24 በድሮን ጥቃት ተደመሰሰ ✈️

የኢትዮጵያ አየር ሃይል የሻዕቢያ አጀንዳ ተሸካሚዉ የህዉሃት ቡድን ወታደራዊ ቤዞችን እንዲሁም በየጦር ግንባሩ የተሰለፉ ታጣቂዎችን በድሮን ዶግ አመድ እያደረገ ነዉ፡፡

በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ጨርጨር ወረዳ ፋራ በተባለ አካባቢ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው የህወሓት ታጣቂ ቡድን አርሚ 24 ስር የሚገኙ በርካታ የታጣቂ ቡድኑ አባላት በተሰነዘረ የአየር ጥቃት ተደምስሷል፡፡

ከጥቃት የተረፉት ታጣቂዎች እሬሳቸዉን እንኳን ሳያነሱ እግሬ አውጪኝ መፈርጠጣቸዉ ከአከባቢዉ ከደረሱን መረጃዎች ማረጋገጥ ችለናል ።

"ለሚመለከተው ብቻ!ነግሬሽ ነበረ፣ የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም ብዬነግሬሽ ነበረ፣ የድፍድፍ ኩራቱ እስከ ውኃ ብዬነግሬሽ ነበረ፣ ላግባሽ ያለ ሁሉ አያገባም ብዬነግሬሽ ነበረ፣ የማታድሪበት ቤ...
24/09/2026

"ለሚመለከተው ብቻ!

ነግሬሽ ነበረ፣ የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም ብዬ
ነግሬሽ ነበረ፣ የድፍድፍ ኩራቱ እስከ ውኃ ብዬ
ነግሬሽ ነበረ፣ ላግባሽ ያለ ሁሉ አያገባም ብዬ
ነግሬሽ ነበረ፣ የማታድሪበት ቤት አታምሺበት ብዬ
ነግሬሽ ነበረ፣ ውረድ እንውረዱ ያዋርዳል ብዬ
አሁን ምን ያደርጋል ካለቀ በኋላ፣ እዬዬ እዬዬ፤
እዬዬ እዬዬ እዬዬ እዬዬ እዬዬ እዬዬ እዬዬ፤"

ክቡር! ሙሐዘ_ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማሕበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር!

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጅቡቲ-አምቡሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የጅቡቲ ፕሬዝ...
24/09/2026

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጅቡቲ-አምቡሊ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ የጅቡቲ ፕሬዝዳንት ኢስማዔል ኦማር ጉሌህ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

🇪🇹🤝🇩🇯

የኤርትራ ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ 173 ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል አመራሮች በመሆን ያገለገሉ የትግራይ ተወላጆች ለኤርትራ ተላልፈው እንዲሰጡ ባወረደው ቀጭን ትዕዛዝ መሰረት እስከአሁን ጀነራል...
24/09/2026

የኤርትራ ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ 173 ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል አመራሮች በመሆን ያገለገሉ የትግራይ ተወላጆች ለኤርትራ ተላልፈው እንዲሰጡ ባወረደው ቀጭን ትዕዛዝ መሰረት እስከአሁን ጀነራል ምግበይ ሃይለን ጨምሮ 17 ውለዋል። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከፍተኛ ወታደራዊና የሲቪል አመራሮች ወደ #ሰንዓፈ ኤርትራ እንደሚሄዱ የሚጠበቅ ሲሆን ሻዕቢያ በአቶ አባይ ጸሐዬ እና በአቶ ስዩም መስፍን የወሰደውን እርምጃ እንደሚያሳልፍባቸው ይጠበቃል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በፕሪቶሪያ የሰላም ሥምምነት የተደናቀፈበትን ህወሓትን ጨርሶ የማጥፋትና በደለውኛል ያላቸውን የትግራይ ተወላጅ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ለመበቀል ወርቃማ እድል አግኝቷል።

Address

African Union
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis-Finfine press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Addis-Finfine press:

Shortcuts

Share