
15/02/2024
የኢትዮጵያ የህይወት ብርሃን ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ታሪኩ ብርሃኑ ከሲንቄ ባንክ ከመጡ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ አብረው በሚሰሩበት ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡
በባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በፍጥነት እያደገና ተደራሽነቱነቱን እያስፋፋ ከመጣው ከሲንቄ ባንክ ጋር የተለያዩ የልማት ስራዎችን አብሮ ለመስራት የተነጋገሩ ሲሆን የባንኩ የስራ ኃላፊዎችም ቤተ ክርስቲያኒቱ ለልማት ስራ የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚደግፉና አብሮ ለመስራት በመወሰናቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡