
07/11/2024
ሠላሳ አምስት አባላት ያሉት የሰርከስ አርቲስቶች ቡድን በአምስት የአውሮፓ ሀገራት ትርኢቱን ሊያቀርብ ነው፡፡
…
ሠላሳ አምስት አባላት ያሉትና ሙሉ ኢትዮጵያውያን ብቻ የሚሳተፉበት ከተለያዩ የሰርከስ ማዕከላት አርቲስቶችን፣ የውዝዋዜ፣ ታዋቂ የሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋቾችና ታዋቂ ድምጻውያንን ያካተተ ልዩ ቡድን በማዘጋጀት በፈረንሳይ ፓሪስ በሚገኝው በታዋቂው በሰርክ ፊኔክስ CIRK AFRIKA PAR LES ETOILES D’ETHIOPIE 2024/2025 (CIRK AFRIKA BY THE STARS OF ETHIOPIA) “ሰርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮኮቦች” በሚል ርእሰ ትርዒቱን ፖሪስ በፊኔክስ መድረክ፣ እንዲሁም በቤልጅዬም፣ በሞናኮ ሞንቴካርሎ፣ በስዊዘርላንና በአንዶራ የሀገራችን ኢትዮጵያን ባህል፣አለባበስ፣ ሙዚቃና ጭፈራ ያካተተ ሙሉ የሰርከስ ትርኢት የያዘ ቡድን ከህዳር 04 ቀን 2017ዓ/ም ጀምሮ ወደ ፈረንሳይ ሊጓዝ መሆኑን አፍሪካን ድሪም አርትስ እና አፍሪካን ድሪም ሰርከስ ዛሬ ጥቅምት 28 ቀን 2017ዓ/ም በቱሊፕ ኢን ኦሎምፒያ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተገለጸው፤ በሞደርን ሰርክስ የሚታወቀው ሰርክ ፊኔክስ መስራች Alain M. Pacherie ከዚህ ቀደመ CIRK AFRIKA 1፣2 ና 3 ከመላዉ ከአፍሪካ የተወጣጡ የሰርከስ፣ ሙዚቀኞችንና ዳንሰኞችን ከደቡብ አፈሪካና ከምእራብ አፍሪካ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የሰርከስ አርቲስቶችን ይዞ ያቅርብ እንደነበረ ይታውሳል፡፡ ይህ የሰርክ ፊኔክስ ካምፓኒ በአገር ደረጃ የቻይና፣ የኩባ፣ ሞንጎልያ… ወዘተ ሙሉ ትርዒት ያቀርቡበት ሲሆን አሁን ደግሞ የሰርክ አፍሪካ አዲስ ሾው ከምድረ ቅደምት አገር ከኢትዮጵያ ብቻ ሙሉ አርቲስቶችን በመያዝ የማይረሳ ጉዞ ሊያደርግ እና አስደናቂ የባህል ውዝዋዜ፣አለባበስ፣ ዜማንና ሙዚቃ ለአውሮፓውያን ለማሳየትና ለማዝናናት በሰርክ ፊኔክስ CIRK AFRIKA PAR LES ETOILES D’ETHIOPIE 2024/2025 (CIRK AFRIKA BY THE STARS OF ETHIOPIA) “ሰርክ አፍሪካ የኢትዮጵያ ኮኮቦች” በልዩ የሰርከስ፣ የዳንስ እና የሙዚቃ ጥበብ ብዙ አስገራሚ ስራዎችን ይዞ በብሔር ብሔረሰብ አልባሳት በመዋብ በፓሪስ ውስጥ በልዩ የኪነጥበብ ከሰርከስ ትርኢት መሳጭ የቤተሰብ መዝናኛ ይዞ ፓሪስ በመጀመር በኋላ, ትርኢቱ በመላው ፈረንሳይ ለማሳየትና ከ Cirque Phénix ጋር በአውሮፓ ለመጓዝ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል ፡፡
አዘጋጆቹ ይህ ትርዒት በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሚሆን የሰርከስ፣ የዉዝዋዜና የሙዚቃ ባለሙያ የሚሳተፉበት ትልቅ ትርዒት መሆኑን በመግለጫው ተናግረዋል፡፡
አፍሪካን ድሪም አርትስ እና አፍሪካን ድሪም ሰርከስ በታዋቂው የሠርከስ አርቲስት፣ አሰልጣኝ፣ አርቲስቲክ ዳይሬክተርና ማናጅር የኔነህ ተስፋዬ የተቋቋመ ሲሆን ሃሳቡ “በቻይና ህቤይ ውቻው አክሮባቲክ አርት ት\ቤት በነበረበት ወቅት በአውሮፓያን ካላንደር በ2004 የተጠነሰሰው ህልም ሲሆን ወደ ሀገሩ ተመልሶ የአፍሪካ ድሪም ሰርከስን በ2010 ከስራ ባልደረባው ቢኒያም ነጋሽ ጋር መሰረተ። በአዲስ አበባ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ሰርከሶች አዲስ አፍሪካ ሰርከስ ፣ ሸገር ሰርከስ ፣ ዊንጌት ሰርከስ፣ ቢጣ ብራዘር ሰርከስ ወዘተ እየተዘዋወረ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠት አዳዲስ ስራዎችን በአገር ውስጥ በማስተዋወቅ በዳይሬክቲንግ ፣ በኬሮግራፊ ፣ ኮስቲዩም ዲዛይኒንግ ፣ ሙዚቃ ምርጫ እና ማኔጅ በማድረግ ለፕሮፌሽናል የሰርከስ አርቲስቶች የስራ እድል ፈጥሯል።
በተለያዩ አለም አቀፍ ፌስቲቫሎች ላይ አርቲስቶችን በማሳተፍ የወርቅ የብር የነሃስ እና ስፔሻል ፕራይዝ ተሸላሚዎች እንዲሆኑ እና የሀገርን ሰንደቅ አላማ ከፍ በማድረግ መልካም ገፅታዋን በመገንባት ሰርከስ የሃገር የባህል አምባሳደር እንዲሆን ከፍተኛ አስተዋፅዖ በማበርከት በተደጋጋሚ የወርልድ ጊኒየስ ሪከርድ በማስመዝገብ እና ለዓለም አቀፍ የሠርከስ ካምፓኒዎች በማቅረብ ለብዙ ኢትዮጵያዊያንና አፍሪካውያን የስራ እድል ማመቻቸት ችሏል፡፡ በተጨማሪም የተልያዩ ፕሮዳክሽን ሙሉ ሰራ በአሜሪካ፣ በአውስተራሊያ፣ በጃፓን፣ ቱርክና ቤላሩስ ወዘተ ማቅርብ ችሏል።
…
ጥቅምት 28 ቀን 2017ዓ/ም
አዲስ አበባ / ኢትዮጵያ