Leka Media

Leka  Media media News

أي تهديد لاستقرار إثيوبيا هو تهديد لاستقرار المنطقة بأكملها. يجب على المجتمع الدولي والاتحاد الأفريقي تحميل المتسببين ال...
04/10/2026

أي تهديد لاستقرار إثيوبيا هو تهديد لاستقرار المنطقة بأكملها. يجب على المجتمع الدولي والاتحاد الأفريقي تحميل المتسببين الحقيقيين في التصعيد المسؤولية الكاملة.

የተግባር መሪዋ እና የእውነተኛ ለውጥ ምልክቷ ዳግም ተመርጣልናለችዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከንቲባነት እንድትቀጥል በሙሉ ድምፅ ይሁንታውን ሲሰጥ "እናሳ!?" ነው የሚያስብለው። ም...
30/09/2026

የተግባር መሪዋ እና የእውነተኛ ለውጥ ምልክቷ ዳግም ተመርጣልናለች

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በከንቲባነት እንድትቀጥል በሙሉ ድምፅ ይሁንታውን ሲሰጥ "እናሳ!?" ነው የሚያስብለው። ምክንያቱም የላቀ ውጤት ላስመዘገበ መሪ የሚገባውን እውቅና መስጠት ተፈጥሮአዊና ትክክለኛ ውሳኔ ነው!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ (አዴ) ለስራ እጇን አፈር ለማስነካት የማይዳዱ፣ ሙስናንና ስርቆትን ክፉኛ የሚጠየፉ፣ ለፍትሃዊነትና ለህዝብ ጥቅም ያላቸውን ጠንካራ መርሆ አፅንተው የያዙ እውነተኛ የእናትነትና የመሪነት ጥልቅ ፍቅር ካላቸው መሪዎች አንዷ ናት።

በሁሉም የእድሜ እርከን፣ በሁሉም ብሄርና ጾታ ዘንድ ቅቡልነት ያላት፣ የከንቲባነትን የአመራር መለኪያ ወደ ላቀ ደረጃ ፈቀቅ ያደረገች የዘመናችን ብርቱ የለውጥ ሰው ናት። በብዙ ትግል፣ በትእግስት፣ ስድብና የፖለቲካ ውካታዎችን በስራ በመመለስ ከጠቅላይ ሚኒስትራችን ጋር እጅና ጓንት ሆና በከተማችን የተሰሩት ታሪክ የማይረሳው ስራ በግልጽ የሚታይ፣ የሚጨበጥና የሚዳሰስ እውነት ነው። ማንም ሊፍቀው፣ ማንም ሊያጣጥለው የማይችል የህዝብ ትልቅ ሀብት ነው!

በወሬ ሳይሆን በተግባር ሀገር የሚለውጡ እንደ አዴ ያሉ መሪዎች ይብዙልን! እኛም ወሬን ትተን ስራ፣ ስራ ብቻ ላይ እንድናተኩር ለብዙዎች መንገድ ያሳዩና አርአያ የሆነች የለውጥ ምልክታችን ናት።

ይህ ሹመት ምንም አይነት ድጋፍም ሆነ ተቃውሞ የማያስፈልገው፣ የስራዋ ውጤት ያስገኘላት ፍጹም ተገቢ ውሳኔ ነው። ባለፉት ዓመታት የጀመረችውን ድንቅ የልማትና የለውጥ ጉዞ በቀጣይም በተሻለ ትጋትና ጉልበት አጠናክራ እንደሚትቀጥል ሙሉ እምነት አለን።

እንኳን ደስ አለዎት!
የተባረከ እና የስኬት ዘመን ይሁንልሽ፣ እናት ከንቲባ አዳነች አቤቤ!

ዜና አላማጣ ዙሪያየሠራዊታችን ድል ሲቀጥል ህወሀትና አጋሮቹ የኋልዮሽ ሩጫ ላይ ናቸው።በራያ ግንባር ማለትም ዋጃ፣ ጥሙጋ፣ አላማጣ አየር ኃይል፣ ቤተ ማሪያም" በሚባሉ ቦታዎች በተሰለፈው የህወ...
29/09/2026

ዜና አላማጣ ዙሪያ

የሠራዊታችን ድል ሲቀጥል ህወሀትና አጋሮቹ የኋልዮሽ ሩጫ ላይ ናቸው።

በራያ ግንባር ማለትም ዋጃ፣ ጥሙጋ፣ አላማጣ አየር ኃይል፣ ቤተ ማሪያም" በሚባሉ ቦታዎች በተሰለፈው የህወሀት ታጣቂ ላይ ፀረ-ማጥቃት በመሰንዘር ወደ ፊት እየገሰገሰ የሚገኘው ዕዝ በግንባሩ ቁልፍ ወታደራዊ ገዢ መሬቶችን እየተቆጣጠረ ሲሆን በጠላት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ አድርሷል።

ከመስከረም 17 እስከ 18 ቀን 2019 ዓ/ም በራያ አላማጣ ወረዳ ልዩ ስሙ አሞራ ቀጠያ፣ አዛዥ አምባ እና ጀመዶ ማሪያም በተባሉ አካባቢዎች ባካሄደው ውጊያ ጠላት ሲጠቀምባቸው የነበረ:-

02 = መድፍ 122mm
03 = ሮኬት 107
02 = አምቡላንስ ተሽከርካሪ
07 = ፖትሮል ተሽከርካሪ
02 = ኦራል ተሽከርካሪ
01 = ዶዘር
04 = ጄኔሬተር
07 = መትረየስ
01 = ላዉንቸር
39 = የመድፍ ጥይት
04 = spc የጦር መሳሪያ
02 = ድሽቃ
4,250 = የድሽቃ ጥይት
19 = የፀረ -ታንክ ጥይት ፣
82 = RPG ጥይት ፣
78 = የ82mm ሞርታር ቅንቡላ
18 = 15 inch ድሮኖች ፣
8 = የድሮን ባትሪ
15 = የሪፕተሀ መደብ
01 = የሬድዮ አንቴና
08 = ሞርተር 81 የድሮን ቅንቡላ
07 = 18 የRPG ቁንቡላ እና ሌሎች በርካታ ተተኳሾችንና የመሳሪያ አባሪ እቃዎችን ከጠላት ማርኳል።

ዕዙ በጠላት ላይ የጀመረውን ፀረ- ማጥቃት አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ጠላት ንብረቱ፣ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ በመሸሽ ላይ መሆኑን የዕዙ አመራሮች ገልፀዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊት 13 አካባቢዎችን ከህውሃት የጥፋት  ኃይሎች  ማስለቀቁ ታውቋል።በራያ አላማጣ ግንባር እየተደረገ ባለው ውጊያ የመከላከያ ሰራዊቱ ከተከላካይነት ወደ ማጥቃት በመሸጋገር...
26/09/2026

የሀገር መከላከያ ሰራዊት 13 አካባቢዎችን ከህውሃት የጥፋት ኃይሎች ማስለቀቁ ታውቋል።

በራያ አላማጣ ግንባር እየተደረገ ባለው ውጊያ የመከላከያ ሰራዊቱ ከተከላካይነት ወደ ማጥቃት በመሸጋገር በዛሬው እለት 13 የተለያዩ ስፍራዎችን ሙሉ በሙሉ ማስለቀቁ ተገልጿል።
📍 ራያ አላማጣ ወረዳ እና ራያ ጨርጨር ወረዳ
1. ዋጃ
2. ጥሙጋ
3. አየር ማረፊያ
4. ቢትሞ
5. ኩቢ ቀረንሳ
6. ኩቢ ድርባ
7.በደና ለኮ
8. ትግሬ መንደር
9. ጉበና መንደር
10. ራያ መንደር
11. ባይባዎ
12. መሓጎ
13. ቀይ አፈር
በመከላከያ ሃይላችን ነፃ የኸጡ ሲሆን በአላማጣ የነበሩ የሕወሓት አመራሮች ወደኋላ እየሸሹ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊቱ ወደ ፊት ቀጥሏል።

የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉ.ህ.ዴ.ን) የታጠቁ ሐይሎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች የፈጠሩትን ‹‹ትብብር ለህልውና››የተባለ ጥምረት ውስጥ  የለሁበትም አለ።የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅ...
26/09/2026

የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉ.ህ.ዴ.ን) የታጠቁ ሐይሎችና የፖለቲካ ፓርቲዎች የፈጠሩትን ‹‹ትብብር ለህልውና››የተባለ ጥምረት ውስጥ የለሁበትም አለ።

የጉሙዝ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉ.ህ.ዴ.ን) ዛሬ ባወጣው መግለጫ ጥምረት ፈጠሩ የተባሉ ሰባት የታጣቁ ሐይሎችና ፖለቲከኞች ፓርቲው በማያውቀው ጉዳይ ስሙን ማካተታቸውን አስታውቋል፡፡ መስከረም10/2019 ዓ.ም ሰባት የታጣቁ ሐይሎች ፈጥረናል ያሉት ጥምረት ውስጥ ስሙ የተካተተው የጉሙዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጉ.ህ.ዴ.ን) ድርጊቱን አውግዟል፡፡

ፓርቲው ጥምረት ከፈጠሩት ሀይሎች ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደለለው በመግለጽ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና ያለውና በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በመሳተፍ 14 የክልል ምክር ቤት መቀመጫ ማሸነፉን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ግራኝ ጉዴታ አመልክተዋል፡፡

23/09/2026

Address

Piyassa
Addis Ababa
1000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Leka Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share