Wollo Media Corporation - WMC

Wollo Media Corporation - WMC ፍቅር ፍቅር ሁሌም ፍቅር

01/02/2024
01/02/2024
ሰበር መረጃየሰሜን ወሎ ፋኖ መሪ ምሬ ወዳጆ በሰላም ወደ ቤታችን እንድንገባ ይፍቀድልን ሲል ጠየቀበአማራ ክልል የተከሰተውን ቀውስ በግንባር ቀደምትነት የቀሰቀሰው ምሬ ወዳጆ የባለወልድ አባቶች...
11/04/2023

ሰበር መረጃ

የሰሜን ወሎ ፋኖ መሪ ምሬ ወዳጆ በሰላም ወደ ቤታችን እንድንገባ ይፍቀድልን ሲል ጠየቀ

በአማራ ክልል የተከሰተውን ቀውስ በግንባር ቀደምትነት የቀሰቀሰው ምሬ ወዳጆ የባለወልድ አባቶችን ሽምግልና ልኳል። ምሬ ወዳጆ ከልዩ ኃይሉ እና ከህዝቡ ድጋፍ አገኛለው በሚል ወደ ግጭት ቢገባም ባሰበው ልክ ድጋፍ ማግኘት ባለመቻሉ ለመከላከያ ሰራዊት ሽምግልና ልኳል። በዚህ ሽምግልና የተሳትፉ የባለወልድ አባቶችም "ጦርነት በቃን፣ ከዚህ በላይ ጦርነት ውስጥ መቆየት አንፈልግም" ብለው ምሬን የገሰፁ መሆኑን እና መከላከያ ሰራዊትም ኢመደበኛ አደረጄጀቱ ትጥቁን ለመከላከያ ሰራዊት በማስረክብ በሰላም ወደየ ቤቱ እንዲገባ ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ ኢመደበኛ አደረጃጀቱ ተቀብሎታል። በዚህ መሰረት መከላከያ ሰራዊት ያስቀመጠው ቅድመ ሁኔታዎች፤

1. ከዚህ በኋላ ምንም አይነት መንገድ እንዳይዘጋ፣
2. ምንም አይነት የታጠቀ አካል ከተማ ውስጥ እንዳናገኝ እርቅም ይሁን ግጭት ከከተማ ውጭ ጫካ ላይ ይሁን፣

3. አፈሙዝ ወደ መከላከያ ሰራዊት እንዳያዞሩ ሠራዊቱ የሚላቸውን ትዕዛዝ አክብረው ይቀመጡ፣

4. የመከላከያን ጥቁር ክላሽ ሰብስበው ያስረክቡን በሚል ቅድመ ሁኔታ ካስቀመጠ በኋላ የሽምግልና ሂደቱን እንዲያስቀጥሉ ተስማምተው ከሽማግሌዎቹ ጋር ተለያይተዋል። ተለያይተዋል። ።

ይህን ተከትሎ ምሬ ወዳጆ በሰጠው ምላሽ "ግጭቱ ሲፈጠር እኔ ምንም አላውቅም እንደ ቡድንም አልተወያየንበትም አልወሰንም ሁሉም የሆነው በዳንኤል አለሙ ትዕዛዝና ፍላጎት ነው ብሏል። በተጨማሪም "ጫካ የገባነው ራሳችንን ለማዳንና መከላከያ እንደሚመታን ስናውቅ ነው የምንተኩሰው ጥይትም ሰው ላይ እንዲያርፍ አይደለም ለመከላከል ያክል ነው" ብሏል።

በመሆኑም የነ ምሬ ወዳጆ ቡድን በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቶ በሰላም እንደሚገባ ታውቋል።
Via natinael

ልዩ ኃይሉን እንደገና …ምክረ ሃሳብ!★★★//♦//★★★አንድ ሀገር፣ አንድ መንግስት፣ አንድ የሀገር መከላከያ እንዲኖር ለዘመናት ተመኝተናል።የክልል ልዩ ኃይሎች፣ ኢ—መደበኛ አደረጃጀቶች የየክ...
10/04/2023

ልዩ ኃይሉን እንደገና …ምክረ ሃሳብ!

★★★//♦//★★★

አንድ ሀገር፣ አንድ መንግስት፣ አንድ የሀገር መከላከያ እንዲኖር ለዘመናት ተመኝተናል።

የክልል ልዩ ኃይሎች፣ ኢ—መደበኛ አደረጃጀቶች የየክልሉ የናፖሊዮን ውሾች ሆነው ክልሎች በውስጦቻቸው ያሉ ማይኖሪቲዎችን የሚጨፈጭፉበት፣ የሚያፈናቅሉበት፣ የሚያሳድዱበት፣ ተገዳዳሪ እና አዋሳኝ ክልሎችን የሚያስፈራሩባቸው፣ የሌሎች ክልል ተወላጆችን የሚያንገላቱባቸው ሆነው በርካታ ግፍ ተፈፅሟል።

ለአንድ ወሎየ የነዚህ ከሀገር መከላከያ ውጭ ያሉ አደረጃጀቶች መታረም እጅግ ታሪካዊ ስኬት ነው። እናም በመርህ ደረጃ ታሪካዊ ድል ሊባል የሚችል ነው።

ይሁን እንጅ መንግሥት የልዩ ኃይል አደረጃጀቶችንም ሆነ ሌሎች ኢ—መደበኛ ኃይሎች እንደገና በማደራጀት አንድ ሀገራዊ የሆነ የሁሉም፣ ከሁሉም፣ በሁሉም የሆነ የጋራ የአገር መከላከያ ኃይልን ማጠናከር እቅዱን ለማከናወን ሲነሳ የሚከተሉት ክፍተቶች አሉበት ብየ አምናለሁ:—

አንደኛ የቅድመ መረጃ አሰጣጥ፣ የኢንዶክትሪኔሽን ስራና ግልፀኝነት ጉድለት።ይህም የመንግስት እቅድ በተዛባ ሁናቴ ለህዝቡ እንዲደርስ እድሉን ፈጥሯል።

ሁለተኛ አማራ ክልል በብሶት እና ስጋት ላይ ያለ ክልል ነው። በዋናነትም የሚለተሉት መሰረታዊ ስጋቶች አሉት። እነዚህም:—

1⃣ አማራ ክልል ከትግራይ ጋር ያለው የድንበር ነባር ጭቅጭቅ
2⃣ የልዩ ኃይል መልሶ የመከለስና የማደራጀት እንቅስቃሴው በተጓዳኝ በሁሉም ክልል በአንድ ጊዜ ከመጀመር ይልቅ አማራ ክልል ላይ ብቻ የተጀመረ የሚያስመስሉ ሁነቶች መፈጠሩ
3⃣ አማራ ክልል አሁን ባለው የመከላከያ ኃይል ስብጥርና ተክለ ቁመና ላይ እርግጠኛ አለመሆኑ
4⃣የ አማራ ክልል ህዝብ ለባለፉት አምስት አመታት ካሳለፈው ምስቅልቅል ሁኔታ በፌደራል መንግስቱ ላይ አመኔታ ማጣት
5⃣ በፌደራል መንግስቱ አንዳንድ ባለስልጣኖች የተለቀቀው መረጃ የተዛባ መሆኑ

ተጨባጩ ይህ ከሆነ መንግሥት የተለየ ዓላማ ከሌለው ጉዳዩን በሠላምና ሁሉንም አሳማኝ በሆነ መልኩ ማከናወን የሚችልበት እድል እንዳለው ይሰማኛል።

ምክረ ሃሳብ‼
_______

የሁሉንም ክልል ልዩ ኃይሎችና ኢ—መደበኛ ታጣቂ ኃይሎች በተመሳሳይ ሰአት በፌዝ መልሶ ማደራጀት። ለምሳሌ

በመጀመሪያ ዙር— ሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ወቅት 25% ያክል ልዩ ኃይሎቻቸውን መልሰው እንዲያደራጁ

በሁለተኛ ዙር— ሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ወቅት 25% ያክል ልዩ ኃይሎቻቸውን መልሰው እንዲያደራጁ

በሶስተኛ ዙር— ሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ወቅት 50% ያክል ልዩ ኃይሎቻቸውን መልሰው እንዲያደራጁ
©Abdujelil

ደሴ ከተማ ‼️ የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በቀን 2/8/2015 ተሰብስቦ የሚከተሉትን ክልከላዎች አስቀምጧል፦ 1 ....
10/04/2023

ደሴ ከተማ ‼️
የደሴ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኮማንድ ፖስት የከተማዉን ሰላምና የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በቀን 2/8/2015 ተሰብስቦ የሚከተሉትን ክልከላዎች አስቀምጧል፦

1 . በከተማችን በዛሬው ዕለት የፀጥታ እና አለመረጋጋት ችግር ተፈጥሯል። ከዚህ ችግር ጋር በተያያዘ ፀጥታው ወደነበረበት እስኪመለስ ድረስ ላልተወሰኑ ቀናቶች ማንኛውም መጠጥ ቤቶችና ጭፈራ ቤቶች እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ዉጭ አገልግሎት መስጠት የተከለከለ ነው ፤

2 . በከተማው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ባለ 3 እግር ባጃጆች ከንጋቱ 12:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:30 ሰዓት ዉጭ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ፤ በተመሳሳይ የሰው እንቅስቃሴም ከምሺቱ 4 ሰዓት በኋላ የተከለከለ ነው።

3 . የፀጥታ ስምሪት ይዞ ከሚንቀሳቀሰው የመንግስት የፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

4 . ድምፅ አልባ መሳሪያዎችን ስለታማ የሆኑ እንደ ጩቤ ፣ ገጀራ ፣ አንካሴ ፣ ጦርና ፌሮ ብረት ወዘተ የመሳሰሉትን ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው።

5 . በህግ የሚፈለጉ ወይም ተጠርጣሪዎችን ሽፋን የሰጠ ፣ የደበቀ ፣ የሀሰተኛ መረጃ ሰጥቶ ያሰመለጠ ፣ የፀጥታ ሀይሎችን የህግ ማስከበር ተልዕኮ ማደናቀፍ ማወክ በህግ የተከለከለ ነው ።

6 . በማንኛውም ቦታና ስዓት ጥይትም ሆነ ሮኬት ርችት መተኮስ በጥብቅ የተከለከለ ነው ።

7 . ተፈቀደለት አካል ውጭ በከተማችን ውስጥ በማንኛውም ቦታ ቀንም ሆነ ሌሊት የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘትና መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው ::

8 . የሠራዊቱን ሚሊተሪ (አልባሳት) ከሰራዊቱ አባላት ውጭ መልበስ የተከለከለ ነው ፦
-የልዩ ኋይል ፣
-የፓሊስ ፣
-የመከላከያ ሠራዊት ፣
-የፌዴራል ፓሊስ መልበስ የተከለከለ ነው።
9 . ያልተፈቀደ ስብሰባዎችን ማለትም ያለ መንግስት እውቅና ውጭ ስብሰባ ማድረግ ፣ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት የተከለከለ ነው።

10. አድማ መቀስቀስ፣ ማድረግና ማስተባበር እንዲሁም መደበኛ ስራን ማስተጓጎል በጥብቅ የተከለከለ ነው

11. የአማራን ህዝብ ከጥቃትና ከውርደት ለመታደግ መስዋትነት የከፈላችሁ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች ፣ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በተፈጠረው የመረጃ ክፍተት ከተለያየ አካባቢ ተነስታችሁ ወደ ከተማችን የመጣችሁ የልዩ ኃይል አመራሮቻችሁ ባዘጋጁላችሁ ማረፊያ እንድትሰባሰቡ እያሳሰብን ከዚህ ውጭ በተናጠልም ሆነ በቡድን መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ጥይት መተኮስ የተከለከለ ነው

12 . ፀጉረ ልዉጥ/አጠራጣሪ ሰው ከቤቱ ያሳደረ ፣ያከራየ፣ በሆቴሉ አልጋ ያስያዙ እንዲሁም ለሚመለከተዉ የፀጥታ አካል ጥቆማ ያልሰጠ በህግ የሚጠይቅ ይሆናል።

በመጨረሻም የተከበራችሁ የከተማችን ነዋሪዎች በከተማችን እየተሰራ ያለው ልማት ለደቂቃም ሊስተጓጎል አይገባም። ህዝባችን ሰላም ፣ ልማት እንደሚፈልግ ጠንቅቀን እንረዳለን። የደሴ ህዝብ ከእንግዳህ በሴራ እየተጎዳ መቀጠል የለበትም ።

ወጣቶቻችን በሆደ ሰፊነት በትዕግስት በስክነት ነገሮች እንድፈቱ እንደሚፈልጉና ልማቱን ምንም እንቅፋት እንዲፈጠርበት እንደማይፈልጉ ጠንቅቀን እናውቃለን።

መንግስት ህግ ለማስከበር የተደራጀ ኃይል እና ዝግጅት ቢኖረውም ከተማችን ነገሮች በሰከነ መንገድ በውይይት እንደፈቱ ከመፈለግ ታግሰናል።

ዋናው ችግር ከሌላ ቦታ በመጡ ኃይሎች አስተባባሪነት እንጅ የከተማችን ህዝብ እንዳልሆነ ህዝባችን ልብ ሊል ይገባል።

ስለሆነም ይህ የተላለፈ ውሳኔ ተግባራዊ ይሆን ዘንድ ህዝባችን ወጣቱ ከጎናችን እንድሆን ጥሪያችን እናስተላልፋለን።

10/04/2023

ደሴ ላይ ጥንቃቄ ያስፈልጋል!

እናት አለም ደሴኮራንብሽ❤
28/01/2023

እናት አለም ደሴ
ኮራንብሽ❤

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Wollo Media Corporation - WMC posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share