Ethiopian Press24

Ethiopian Press24 ኢትዮጵያ ፕሬስ 24 ትክክለኛ እና የተረጋገጡ መረጃዎችን ለ ህ?

 #አብን የኦፌኮን መግለጫ ተቃወመ”በኦሮሚያ ክልል ለተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት የአማራን ሕዝብን እና የአማራን የፖለቲካ ኃይሎች የጦስ ደሮ ለማድረግ የሚኬድበትን መንገድ አ...
12/04/2022

#አብን የኦፌኮን መግለጫ ተቃወመ

”በኦሮሚያ ክልል ለተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት የአማራን ሕዝብን እና የአማራን የፖለቲካ ኃይሎች የጦስ ደሮ ለማድረግ የሚኬድበትን መንገድ አብን አጥብቆ ያወግዛል”:- የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ

በተለያዩ የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል እየተደረገ ባለው የፖለቲካ ግብግብ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ለተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት የአማራን ሕዝብን እና የአማራን የፖለቲካ ኃይሎች የጦስ ደሮ ለማድረግ የሚኬድበትን መንገድ አጥብቆ እንደሚያወግዝ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አስታወቀ።

ትናንት ሚያዚያ 3 ቀን 2014 የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ወቅታዊና አገራዊ ሁኔታዎችን አስመልክቶ መግለጫ ማውጣቱ ተከትሎ፤ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫውም፤ ኦፌኮ ወቅታዊው የአገራችን ሰላም ፣ መረጋጋት እና የኑሮ ውድነት የደረሰበትን አሳሳቢ ደረጃ በመረዳት መግለጫ ማውጣቱ የሚደነቅ እና ተገቢነት ያለው ነው ያለ ሲሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በኦነግ ሸኔ እና በክልሉ የጸጥታ ኃይሎች መካከል እየተደረገ ያለውን ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲፈለግለት ጥሪ ማድረጉም የሚደነቅ እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሙሉ ድጋፉን የሚሰጠው አቋም መሆኑን ገልጿል።

ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ ተራ ቁጥር 2 ላይ “ከአማራ ክልል የሚነሱ የታጠቁ ሃይሎች በአማራ ክልል መንግስት ድጋፍ እየተደረጋላቸው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተለይም በምስራቅ ወለጋ ፤ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ፤ ሰሜን ሸዋ ፤ ምዕራብ ሸዋ እና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች፤ በተቀናጀ አኳኋን የጦር ዘመቻ እና የመሬት ወረራ እያካሔዱ እንደሚገኝ ከአባሎቻችን እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ለመረዳት ችለናል” በማለት መግለጫ ማውጣቱን ያስታወሰው አብን፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ በየትኛው ክልል፣ ዞን ወይም ቀበሌ በየትኛውም ኃይል ሆነ ታጣቂ የሚፈጸም ጥቃትን፣ ትንኮሳን እና ግጭትን ያወግዛል ብሏል።

ንቅናቄያችን የትኛውም ልዩነት በጦር ኃይል እና በጉልበት ይፈታል ብሎም አያምንም። ከየትኛውም ክልል ተነስቶ እና በየትኛውም አካል ተደግፎ ፣ በየትኛውም አካባቢ እና ሕዝብ ላይ ጥቃት የሚፈጽም አካል ካለ ፣ ጥቃቱን ለማስቆምም ሆነ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት አብን በሙሉ አቅሙ ይደግፋል ሲልም በመግለጫው አስታውቋል።

ነገር ግን በተለያዩ የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል እየተደረገ ባለው የፖለቲካ ግብግብ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ለተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት የአማራን ሕዝብን እና የአማራን የፖለቲካ ኃይሎች የጦስ ደሮ ለማድረግ የሚኬድበትን መንገድ አብን አጥብቆ ያወግዛል ነው ያለው አብን።

ኦፌኮ በመግለጫው የጠቀሳቸው ምስራቅ ወለጋ ፤ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ፤ ሰሜን ሸዋ ፤ ምዕራብ ሸዋ እና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች ውስጥ በብዙዎቹ አካባቢዎች በንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ ተደጋጋሚ ጭፍጨፋ እና መፈናቀል የሚፈጸምባቸው ቦታዎች እንደሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ በግልጽ የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች የሚንቀሳቀሱባቸው እና ታጣቂዎቹ አብዛኛዎቹን አካባቢዎችን የሚቆጣጠሯቸው መሆኑ ይታወቃል ያለው መግለጫው፤ በእነዚህ አካባቢዎች ለተፈጠረው የጸጥታ መደፍረስ እና የሰላም እጦት አማራ ተጠያቂ የሚሆነው፣ “ኦነግ-ሸኔ አማራ ነው፣ ታጣቂዎቹም የአማራ ገበሬዎች ናቸው” ከተባለ ብቻ ነው፡፡ ኦፌኮ ኦነግ-ሸኔን እና ታጣቂዎችን በአማራነት እንደማይከስ ተስፋ እናደርጋለን ብሏል፡፡

የኦነግ-ሸኔ ታጣቂዎች በኦሮሚያ ክልል ውስጥ እየፈጠሩ ካሉት የጸጥታ መደፍረስ እና ሰላም እጦት በተጨማሪ በቤንሻንጉል-ጉሙዝ ክልል፣ በሲዳማ ክልል፣በደቡብ ክልል እና በአማራ ክልል በርካታ አካባቢዎች በንጹሃን ዜጎች እና በሕዝብ መሰረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ሲያደርሱ እንደቆዩ እና እያደረሱ ለመሆኑ ከበቂ በላይ ተጨባጭ ማሳያዎች አሉ ሲልም አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ገልጿል፡፡

”እውነቱ ይሄ ሆኖ ሳለ ኦፌኮ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና በኦነግ-ሸኔ መካከል እየተካሄደ ያለውን ደም አፋሳሽ ግጭት እና በተለያዩ የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ያለውን የፖለቲካ ውጥረት ያረግባል በሚል ስሌት ኦነግ-ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው እና በሚቆጣጠራቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች፣ ከአማራ ክልል የተነሱ ታጣቂዎች ወረራ ፈጸሙ የሚል መግለጫ ማውጣቱ አብንን አሳዝኗል።” ብሏል።

አብን በመግለጫው አክሎም ንቅናቄያችን አብን ኦፌኮ እና መሰል የፖለቲካ ኃይሎች ለአገራችን ሰላም እና ለሕዝባችን አንድነት መጠበቅ ቁልፍ ሚና አላቸው ብሎ ያምናል፤ የሚያራምዷቸው የፖለቲካ አቋሟች ከጊዚያዊ የፖለቲካ ጥቅም ባሸገር ዘላቂ የአገር ሰላም እና ጥቅም የሚያስከብሩ እንዲሆኑ ይጠብቃል ሲል ገልጿል

"የጋራ ጠላት በመፈብረክ እና በመፍጠር የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች አንድነት መፍጠር ይቻላል" የሚለው የፖለቲካ ስሌት ለበርካታ አስርት ዓመታት ተሞክሮ የከሸፈ እና በውጤቱም ከኦሮሞ ሕዝብ አልፎ ለመላው የሀገራችን ሕዝብ እና ለአገራችን አንድነት የማይበጅ አካሄድ መሆኑ በበቂ ተሞክሮ እና ማሳያዎች የተረጋገጠ ነው ያለው አብን፤ ኦፌኮም ሆኑ በመሰል የፖለቲካ ስሌት የሚንቀሳቀሱ ኢትዮጵያውያን የፖለቲካ ኃይሎች ከመሰል አካሄዶች እንዲቆጠቡ ጥሪውን አስተላልፏል።

”የትኛውንም ሕዝብ እወክላለሁ ብሎ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ኃይል፣ “እነሱ” ብሎ በሚጠራው ሕዝብ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ፖለቲካ እያራመደ፣ “የእኛ” ብሎ ለሚጠራው ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እና ጥቅም ማረጋገጥ እንደማይችል ከአሸባሪው ትሕነግ በላይ ምሳሌ ለመሆን የሚችል የፖለቲካ ኃይል የለም፡፡ “እነሱ” ለምንለው ሕዝብ ሰላም እና ጥቅም መስራት ፣ “የእኛ” ለምንለው ሕዝብ ሰላም እና ጥቅም መስራት መሆኑን ሁላችንም ግንዛቤ ልንውሰድበት ይገባል፡፡“ ሲልም ገልጿል።

በኹሉም የአገራችን አካባቢዎች እየተፈጠሩ ያሉ የሰላም እጦቶች እና የጸጥታ መደፍረሶች መንስዔ መዋቅራዊ እና ሥርአት-ሰራሽ ለመሆኑ ከማንም አገር እና ሕዝብ ወዳድ ኢትዮጵያዊ የተሰወረ አይደለም፡፡ ሲል የገለፀው አብን፤ የአንድ ቡድንን ጠባብ የፖለቲካ ጥቅም ለማስከበር ሲባል እና በሂደትም ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመበተን የተዋቀረው ሥርአት እና የአስተዳደር መዋቅር እስከቀጠለ ድረስ የየትኛውም አካባቢ ሕዝብ ዘላቂ ሰላም እና ጥቅም ማስከበር የሚቻል አይደለም ብሏል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎች መካከልም ሆነ በኹሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች መካከል ያለውን ልዩነት ማጥበብ የሚቻለው እና እንወክለዋለን ለምንለው ሕዝብ እና አካባቢ እንዲሁም የአገራችን ኢትዮጵያን ሰላም እና ኅልውና ማረጋገጥ የሚቻለው ተቀራርቦ በመስራት ፣ በመደማመጥ እና የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥቅሞች እና መብቶች የሚከበሩበት አማካኝ እና አስቻይ የፖለቲካ ሥርአት በመፍጠር ነው ብሎ እንደሚያምን የገለፀ ሲሆን፤ ኦፌኮን ጨምሮ በሕጋዊ መንገድ ፓርቲ መስርተው ከሚንቀሳቀሱ ከየትኛውም የፖለቲካ ኃይሎች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ዝግጁ መሆኑንም በመግለጫው አስታውቋል።

ምንጭ:- አዲስ ማለዳ

“ከአማራ ክልላዊ መንግስት በመነሳት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በኃይል በመጣስ ጦርነት አውጀው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ"፦ ኦፌኮ -----------...
11/04/2022

“ከአማራ ክልላዊ መንግስት በመነሳት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በኃይል በመጣስ ጦርነት አውጀው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ"፦ ኦፌኮ
----------------------------------------------------------------------

ከአማራ ክልላዊ መንግስት በመነሳት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በኃይል በመጣስ ጦርነት አውጀው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ሲል የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ገለፀ።

ኦፌኮ መንግስት ሰሞኑን በአዲስ መልኩ ያወጀው ዘመቻ በጥቂቱ ፈንጥቆ የነበረውን የሰላም ጭላንጭል መልሶ የሚያደበዝዝ፤ ኦሮሚያና አገሪቱን ለተጨማሪ አደጋ የሚያጋልጥ እንጂ ዘላቂ መፍትሄ የማይሰጥ ነው ብሏል።

በኹለቱ አካላት መካከል ያለው ግጭት ፖለቲካዊ መንስዔ ያለው ሲሆን መፍትሄውም ፖለቲካዊ መሆን አለበት ብሎ እንደሚያምንም አስታውቋል፡፡

በአጎራባች የኦሮሚያና የአማራ ክልሎች መካከል የሰላምና ፀጥታ ችግር እየተባባሰ ነው ያለው መግለጫው፣ ከሰሞኑ ይፋ እየተደረጉ ካሉ ዘገባዎች መረዳት እንደሚቻለው ከአማራ ክልላዊ መንግስት በመነሳት የጦር መሳሪያ የታጠቁ ኃይሎች በተለያዩ ሥፍራዎች በኩል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስትን የታወቀ ወሰን በኃይል በመጣስ ጦርነት አውጀው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ተግባር ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ሲል በመግለጫው አስታውቋል፡፡

እነዚህ ኃይሎች ሰላማዊ ሰዎችን በመግደል፤ አርሷደሮችን ከመሬታቸው በማፈናቀል ክልሉን ወደማያባራ የግጭት ቀጠና እየለወጡት እንደሚገኙ፣ በተለይም ይህ የጦር ዘመቻና የመሬት ወረራ በምስራቅ ወለጋ፣ ሆሮ ጉድሩ ወለጋ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ምዕራብ ሸዋና በምስራቅ ሸዋ ዞኖች፣ በተቀናጀ አኳኋን እየተካሔደ እንደሚገኝ ከአባሎቻችን እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ለመረዳት ችለናል ብሏል፡፡

ታጥቀው ወረራ እያካሔዱ ባሉ የአማራ ክልል ኃይሎች በሚዲያ የሚሰጡት መግለጫም ይህንኑ ያረጋግጣል ሲልም ገልጿል፡፡

ይህን ወረራ የሚያካሂዱት ከክልሉ መንግስት እውቅና ውጪ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ “ጽንፈኛ” ኃይሎች ናቸው ቢባልም ይህ እውነት እንዳልሆነ የሚያመላክቱ ማስረጃዎች አሉ ያለው ኦፌኮ፣ እንዲህ ያለው አሰራር ህገመንግስቱን ከመፃረር አልፎ የሁለቱ ክልሎች ወንድማማች ህዝቦች ወደለየለት ጦርነት እንዲገቡ በር የሚከፍት መሆኑን አበክሮ አስጠንቅቋል፡፡

ይህ በጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እየታገዘ የሚካሔደው የመሬት ወረራና የግዛት ማስፋፋት ዘመቻ ቀድሞውንም ባልሻረ ቁስል ላይ ጨው በመነስነስ የኹለቱን ህዝቦች ግንኙነት ወደከፋ የመጠፋፋት ጦርነት ሊገፋ እንደሚችል ኹለቱም ወገኖች ሊገነዘቡ ይገባል ሲልም ገልጿል፡፡

በኹለቱ ክልሎችና እነዚህ ትልልቅ ህዝቦች መካከል የሚደረገው ጦርነት አገሪቱንም ለብተና፤ የአፍሪካን ቀንድ ደግሞ ለከፋ አለመረጋጋት የሚያጋልጥ መሆኑ ታውቆ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ኦፌኮ ባወጣው መግለጫ አሳስቧል፡፡

ምንጭ:- አዲስ ስታንዳርድ

 #የሰብአዊመብትተሟጋቾቹ የሰላም አስከባሪ እንዲሰማራ ጠየቁአምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ በአፍሪካ ሕብረት የሚመራ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ጠየቁ።...
06/04/2022

#የሰብአዊመብትተሟጋቾቹ የሰላም አስከባሪ እንዲሰማራ ጠየቁ

አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ በአፍሪካ ሕብረት የሚመራ ሰላም አስከባሪ ኃይል እንዲሰማራ ጠየቁ።

ሁለቱ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋች ቡድኖች ይህን የጠየቁት ዛሬ በምዕራብ ትግራይ የትግራይ ተወላጆች ላይ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ተፈጽመዋል ባሉበት የጋራ ሪፖርታቸው ነው።

ሁለቱ ተቋማት ላለፉት 15 ወራት ያካሄዱትን ምርመራ ውጤት ተከትሎ በአካባቢው ያለውን አስከፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለማስቆም በአፍሪካ ሕብረት የሚመራ ሰላም አስከባሪ ኃይል ማሰማራት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

ተቋማቱ ረቡዕ መጋቢት 27 ይፋ ባደረጉት ሪፖርታቸው በሁለቱም ተዋጊ ኃይሎች መካከል የሚደረጉ ስምምነቶችም የሰላም አስከባሪ ኃይል ወደ ምዕራብ ትግራይ በአስቸኳይ ማሰማራትን ያጠቃለለ እንዲሆንም ጥሪ አቅርበዋል።
እንደ መብት ተሟጋቾቹ ከሆነ የሰላም አስከባሪ ኃይል በስፍራው መሰማራት፤ የሰብዓዊ መብቶችን ለማረጋገጥ፣ የሰብዓዊ እርዳታን ለማድረስ እና በትግራይ አደጋ ላይ የወደቁ ሰዎችን ለመድረስ ቁልፍ እርምጃ ይሆናል ብለዋል።

በአካባቢው ያለው ችግር ውስብስብ እና በቀላሉ የማይፈታ ስለሆነ ዘላቂ መፍትሄ እስኪገኝ የሰላም አስከባሪ ኃይሉ በሁለቱም ወገን ያሉ ሲቪሎችን ሊከላከል ይችላል ብለዋል።

"ይህ የተለመደ ወይም በቀላሉ የምንሰጠው ምክረ ሃሳብ አይደለም። ነገር ግን የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና የጸጥታ ኮሚሽን የኢትዮጵያን ጉዳይ አጀንዳ አድርጎ ተወያይቶ አያውቅም። የተመድ የጸጥታው ምክር ቤትም ተጨባጭ እርምጃ አልወሰደም። ይህንን ምክረ ሃሳብ የምንሰጠው የጉዳዩን አሳሳቢነት እንዲረዱት መነሻ ሃሳብ ለመስጠት ነው" ሲሉ የአምነስቲ ኢንተርናሸናል የአፍሪካ ቀንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ አጥኚ የሆኑት አቶ ፍሰሃ ተክሌ ተናግረዋል።

ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾቹ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሂዩማን ራይትስ ዎች በምዕራብ ትግራይ፣ የትግራይ ተወላጆች ላይ በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ተፈጽመዋል ብለዋል።

ሁለቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንደሚሉት ከሆነ ከጦርነቱ መቀስቀስ ጀምሮ የአማራ ኃይሎች እና ባለስልጣናት በምዕራብ ትግራይ ባሉ የትግራይ ተወላጆች ላይ ከጦር እና በሰብዓዊነት ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች ጋር የሚስተካከሉ መጠነ ሰፊ ወንጀሎች ፈጽመዋል።

የሁለቱን ተቋማት ሪፖርት ተከትሎ ቢቢሲ የኢትዮጵያ መንግሥት አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

በትግራይ ክልል ተቀስቅሶ ወደ ተቀሩት አጎራባች ክልሎች በተስፋፋው የእርስ በእስር ጦርነት ሁሉም ተሳታፊ አካላት በከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲጠየቁ ቆይቷል።

የኢትዮጵያ አገር መከላከያ ሠራዊት፣ የኤርትራ መከላከያ ሠራዊት፣ የትግራይ ኃይሎች እና የአማራ ኃይሎች በሲቪሎች ላይ የመብት ጥሰት በመፈጸም ተጠያቂ ሲደረጉ ቆይተዋል።

አምነስቲ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ባወጣው ሪፖርት ላይ የትግራይ ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ገብተው በቆዩባቸው ጊዜያት ከጦር ወንጀል ጋር የሚስተካከሉ በሲቪሎች ላይ ግድያ እና የአስገድዶ መድፈር ጥቃቶችን መፈጸማቸውን ይፋ አደርጎ ነበር።

ሁለቱ ዓለም አቀፍ የመብት ተሟጋቾች ዛሬ ይፋ ያደረጉት እና " 'ከዚህ ምድር እናስወግዳችኋለን'፡ በሰብዓዊነት የሚፈጸም ወንጀል እና የዘር ማጽዳት በኢትዮጵያዋ ምዕራብ ትግራይ ዞን" የተሰኘው ሪፖርት የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳበት ምዕራብ ትግራይ የሚንቀሳቀሱ የአማራ ልዩ ኃይል እንዲሁም ሚሊሻዎች "የዘር ማጽዳት እንዲሁም በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን" መፈጸማቸውን የሚያሳዩ ግኝቶችን ይዟል።

"የኢትዮጵያ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ አጋሮች በምዕራብ ትግራይ እየተፈጸሙ ያሉ ወንጀሎችን ክብደት ለማሳየት ሳይችሉ ቀርተዋል" ሲሉ የአምነስቲ ዋና ጸሃፊ አግነስ ካላማርድ ወቅሰዋል።

"የሚመለከታቸው መንግሥታት እየተካሄደ ያለው የዘር ማጽዳት ዘመቻን ማስቆም ብሎም ከአካባቢው የተፈናቀሉ የትግራይ ተወላጆችን በፈቃዳቸው እና ደህንነታቸው በተጠበቀ መልኩ ወደ ቀዬያቸው እንዲመለሱ ማስቻል አለባቸው" ሲሉ ዋና ጸሃፊዋ ጥሪ አቅርበዋል። አክለውም ፍትህ ለተበዳዮች እንዲሰጥ መደረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ሪፖርቱ በጦርነቱ የመጀመሪያ ጥቂት ወራት ውስጥ የተፈጸሙ ጥፋቶችን ጭምር የዳሰሰ ሲሆን የትግራይ ሚሊሻዎች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪ ሲቪሎች በማይካድራ ከተማ አካባቢው ነዋሪ በሆኑ እና ለቀን ስራ በመጡ የአማራ ተወላጆች ላይ "የጦር ወንጀሎችን" መፈጸማቸውን አስታውሷል።

ተቋማቱ በዝርዝር ካጠኗቸው ልዩ ክስተቶች መካከል በተከዜ ድልድይ አካባቢ በጥር ወር 2013 ፋኖ በመባል በሚጠራው ሚሊሻ ተፈጽሟል ሲሉ የገለጹት ጭፍጨፋ ይገኝበታል።

ጥር 9 አዲ ጎሹ ተብላ በምትጠራው አነስተኛ ከተማ የፋኖ ሚሊሻዎች ነዋሪዎችን ከሰበሰቡ በኋላ ወንዶቹን በመምረጥ አስረዋል ያለው ሪፖርቱ፤ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት በበኩላቸው 60 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጅ ወንዶችን የተከዜ ድልድይ ጋር ወስደው ረሽነዋል ይላል።

"መንግሥት በምዕራብ ትግራይ ጥቃት የሚፈጽሙ የሚሊሺያ አደረጃጀቶችን ሊያፈርስ እንዲሁም ጥቃት የፈጸሙ አማራ ልዩ ኃይል እና የፌደራል ሃይሎች አባላትን ሊያስወጣ ይገባል" ሲሉ ተቋማቱ በሪፖርታቸው አሳስበዋል።

ምንጭ:-ቢቢሲ

ያልጠፍው የመሳሪያ ድምፅ እን የጦርነት ዝግጅት የሚመስል ድባብ በአፋር::https://youtu.be/C9CF9uXEyhw
05/04/2022

ያልጠፍው የመሳሪያ ድምፅ እን የጦርነት ዝግጅት የሚመስል ድባብ በአፋር::

https://youtu.be/C9CF9uXEyhw

Press 24 የተለያዩ ምረጃዎችህን ወደእናንት የሚያደርስ የዩትዩብ ቻናል ነው መረጃዎቻችን ወደናንት እንዲደርሱ SUBSCRIBE እንዲሁም የደውል ምልክቷን በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።እንዲሁ....

ጋዜጠኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ ተወሰነ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ ለአራት ወራት ገደማ በእስር ላይ የቆየው ጋዜ...
05/04/2022

ጋዜጠኛው በ50 ሺህ ብር ዋስ እንዲፈታ ተወሰነ

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ

ለአራት ወራት ገደማ በእስር ላይ የቆየው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈታ የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ወሰነ። ፍርድ ቤቱ ዛሬ ማክሰኞ መጋቢት 27 ዋስትናውን የፈቀደው፤ ጋዜጠኛው በጠበቃው በኩል ያቀረበውን የዋስትና ጥያቄ ከመረመረ በኋላ ነው።

የጋዜጠኛው ጠበቃ ገመቹ ጉተማ የደንበኛቸው የዋስትና መብት እንዲከበር ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ከ25 ቀናት በፊት መጋቢት 2፤ 2014 ነበር። የዋስትና ጥያቄው የቀረበለት ፍርድ ቤቱ ባለፉት አራት ተከታታይ ቀጠሮዎች በጋዜጠኛ ታምራት የዋስትና ይገባኛል ጥያቄ ላይ ውሳኔ ሳይሰጥ ቆይቷል።

ፍርድ ቤቱ መጋቢት 8፤ 2014 በነበረው የመጀመሪያ ቀጠሮ፤ የጋዜጠኛውን የዋስትና ጥያቄ በመቃወም የኦሮሚያ አቃቤ ህግ በጹሁፍ ያቀረበውን ማመልከቻ በመቀበል ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መጋቢት 13፤ 2014 ከዋለው ችሎት ጀምሮ በነበሩት ሶስት ተከታታይ ቀጠሮዎች፤ የዋስትና ጥያቄውን በተመለከተ “ምርመራውን አለማጠናቀቁን” በመግለጽ ለውሳኔ ቀጠሮ ሲሰጥ ቆይቷል።

መቀመጫውን በአዲስ አበባ ያደረገው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ማዕከላዊ የወንጀል ችሎት በዛሬው ውሎው፤ የክልሉ ዐቃቤ ህግ በጋዜጠኛው የዋስትና ጥያቄ ላይ ያቀረበውን ተቃውሞ ወድቅ በማድረግ፤ ተጠርጣሪው የ50 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና አስይዞ ከእስር እንዲፈታ ውሳኔ አሳልፏል። የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ የታምራት የዋስትና ጥያቄ ውድቅ እንዲደረግ ጠይቆ የነበረው በሶስት ምክንያቶች ነበር።

#ታምራት #ነገራ #ኢትዮጵያ

ምንጭ:- ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

04/04/2022

"ሕዝብን መዋጮ የሚያስከፍሉ ፣ ሕፃናትን በማፈን መደራደሪያ የሚያደርጉ፣ ሴቶችን አስገድደው የሚደፍሩ፣ የመንግሥትን ሥራ የሚያደናቅፉ እና በፀጥታ አካላት ላይ ድንገተኛ ጥቃት የሚፈፅሙ" ኢ- መደበኛ ያሏቸው አደረጃጀቶች መኖራቸውን ተናገሩ።
#ሽኔ #ፋኖ #ኢትዮጵያ

ማህበሩ 200 ቶን አጎጉዟል---------------------------------------------------------------------ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር 200 ቶን የሰብአዊ...
04/04/2022

ማህበሩ 200 ቶን አጎጉዟል

---------------------------------------------------------------------

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር 200 ቶን የሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል በየብስ አጓጉዟል

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር 200 ቶን የሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ ክልል በየብስ ማጓጓዙን አስታወቀ።

ማህበሩ ወደ ትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ከትናንት በስቲያ በየብስ ዳግም ሟጓጓዝ ጀምሯል።

በዚህም 200 ቶን ምግብ፣ የሕክምናና የውሃ ማከሚያ ግብአቶችን የያዙ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር እርዳታ ጫኝ መኪናዎች ወደ ትግራይ ክልል መግባታቸውን የተቋሙ የኢትዮጵያ ቃል አቀባይ ፋቲማ ሳቶር ለኢዜአ ገልጸዋል።

ማህበሩ ወደ ክልሉ በየብስ እርዳታ ማጓጓዝ የጀመረው ከስድስት ወራት በኋላ እንደሆነና በቀጣይ በመደበኛነት ሰብአዊ እርዳታ ማድረሱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ተቋሙ ወደ ትግራይ ክልል የየብስ አርዳታ ከማድረሱ በፊት በአየር በረራ ሕይወት አድን መድሐኒቶችና የሕክምና ግብአቶችን ሲያጓጉዝ ቆይቷል ብለዋል።

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማህበር የመንግስትን የሰብአዊ ተኩስ አቁም ውሳኔ በመልካም ጎኑ እንደሚያየውና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትና ተደራሽነቱን ለማሻሻል አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ነው ቃል አቀባይዋ የገለጹት።

ማህበሩ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነቱ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ለተጎዱ ወገኖች በዋናነት የምግብና የጤና ግብአቶች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም 13 እርዳታ ጫኝ መኪኖች ባለፈው ሳምንት 500 ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍ ትግራይ ክልል ማድረሱን መግለጹ አይዘነጋም።

የኢትዮጵያ መንግስት መጋቢት 15 ቀን 2014 ዓ.ም በትግራይ ክልል የሰብአዊ እርዳታ ተደራሽነት ለማሳለጥ ሲል የሰብአዊ ተኩስ አቁም ውሳኔ እንዳደረገ መግለጹ የሚታወስ ነው።
መንግስት ከመጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ዓለም አቀፍ የእርዳታ አቅራቢ ተቋማት ወደ ትግራይ ክልል በሳምንት ሁለት ጊዜ ያደረጉት የነበረውን የአየር በረራ በየቀኑ እንዲያደርጉ ፈቃድ ሰጥቷል።

ከሐምሌ 14 ቀን 2013 እስከ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ድረስ ወደ ትግራይ ክልል በአጋር አካላት አማካኝነት 51 ሺህ 497 ሜትሪክ ቶን ምግብና ቁሳቁሶች ለተረጂዎች መጓጓዙን ኢዜአ ከአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

 #የእሳት አደጋ በኤሊያስ ጨርቃጨርቅበእሳት አደጋው 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ-------------------------------------------------------------...
03/04/2022

#የእሳት አደጋ በኤሊያስ ጨርቃጨርቅ

በእሳት አደጋው 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ
-------------------------------------------------------------------

ቃሊቲ ኢንዱስትሪ መንደር በኤሊያስ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ 350 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ላይ ውድመት መድረሱ ተገለጸ።

አደጋው የደረሰው ትላንት መጋቢት 24 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 3:15 ሰዓት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ እሳት እና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ተናግረዋል።

በፋብሪካው ያሉት የጨርቅ ማቅለሚያ ኬሚካሎች እና በመጋዘን ውስጥ የሚገኙ ጥሬ እቃዎች እሳቱ ፈጥኖ እንዲስፋፋ ከማድረጋቸውም በላይ በፋብሪካው ቅጥር ግቢ ውስጥ ለመግባት አመቺ አለመሆኑ እንዲሁም ፋብሪካው ሕንፃ ላይ መሆኑ እሳቱን በቀላሉ መቆጣጠር እንዳይቻል አድርጎታል ብለዋል።

በተከናወነው የአደጋ መቆጣጠር ርብርብ ከሌሊቱ 7 ሰዓት እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን ገልጸዋል።

የእሳት አደጋው በአካባቢው ባሉ ሌሎች ፋብሪካዎች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ በተደረገ ርብርብ 2.5 ቢሊየን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን መቻሉን ኢዜአ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ቦታው ድረስ በመገኘት በአደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ባለንብረቶችን አፅናንተዋል

የመንግስት መግለጫhttps://youtu.be/CjoPXGmi5uA
02/04/2022

የመንግስት መግለጫ

https://youtu.be/CjoPXGmi5uA

#ዜና የመንግስት ኮምዩንኬሽን አገልግሎት መግለጫየመንግሥ ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሠ ቱሉ "ሕዝብን መዋጮ የሚያስከፍሉ ፣ ሕፃናትን በማፈን መደራደሪያ የሚያደርጉ፣ ...

02/04/2022

በሶማሌ ክልል ከወራት በፊት በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ሶስት መቶ ሺህ የሚጠጉ እንስሳት ሲሞቱ የመኖ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው እንስሳት ሶስት ሚሊየን ደርሰዋል።

በሶማሌ ክልል ከወራት በፊት በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ሶስት መቶ ሺህ የሚጠጉ እንስሳት ሲሞቱ የመኖ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው እንስሳት ሶስት ሚሊየን ደርሰዋል።https://youtu.be/uqx7BR...
02/04/2022

በሶማሌ ክልል ከወራት በፊት በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ሶስት መቶ ሺህ የሚጠጉ እንስሳት ሲሞቱ የመኖ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው እንስሳት ሶስት ሚሊየን ደርሰዋል።

https://youtu.be/uqx7BRZlgkk

በሶማሌ ክልል ከወራት በፊት በተከሰተው ድርቅ ሳቢያ ሶስት መቶ ሺህ የሚጠጉ እንስሳት ሲሞቱ የመኖ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው እንስሳት ሶስት ሚሊየን ደርሰዋል፡፡

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Press24 posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share