ሲራራ - Sirara

ሲራራ - Sirara Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ሲራራ - Sirara, Addis Ababa.

Sirara is an independent Amharic [weekly] newspaper that envisages providing reliable news and news analysis, and creating platform for discussions on the economic, political and social issues of Ethiopia, The Horn of Africa and beyond.

18/11/2023

ዋጋ ግሽበት እና ዋጋ ንረት

ዋጋ ግሽበት ማለት የምርቶች ዋጋ መጨመር መናር ማለት ነው። የኑሮ ውድነት ደግሞ የምርቶች ዋጋ መጨመር ሲደመር የዜጎች የመግዛት አቅም መዳከምማለት ነው። በአንድ አገር የምርቶች ዋጋ እየጨመረ የኑሮ ውድነት ላይ ፈጠር ይችላል። ምክንያቱም የዜጎች ገቢ እየጨመረ ከሄደ የምርቶች ዋጋ ጭማሪን ሊቋቋሙት ይችላሉና ። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው ምንድ ነው ካልን የዋጋ ንረት ሲደመር የኑሮ ውድነት። ለዚህ ጥሩ ማስረጃው በቅርቡ ኢትዮጽያ ካሉ ባንክ አስቀማጮች ከ መቶ ሺህ ብር በላይ ያለው ሰው አሥር በመቶ የማይሞላ ነው የሚለው ማስረጃ ነው ። ይህ ምን ያሳያል ካልን የዜጎች ገቢ ሳያድግ የምርቶች ዋጋ ግን እያደገ መሄዱን ነው። እንወያይበት

23/04/2023

የዶላር ዋጋ ለምን ጨመረ?

(ፀጋዬ ዳባ)

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በትይዩ (ጥቁር) ገበያው እና በባንኮች መካከል ያለውን የውጭ ምንዛሪ ተመን ልዩነት ለማጥበብ የተለያዩ እርምጃዎችን ሲወስድ ቆይቷል፡፡ በዚህም የተገኙ ውጤቶች ነበሩ፡፡ አሁን ግን በትይዩ ገበያው እና በባንኮች መካከል ያለው ልዩነቱ ከዚህ ቀደም ከነበረውም ከፍ ብሏል፡፡ አንድ ዶላር በባንክ ቤት 45 ብር እየተመነዘረ ሲሆን፣ በትይዩ ገበያው ላይ ግን ከ60 እስከ 70 ብር ድረስ ሲመነዘር ሰንብቷል፡፡ ይህም ከባንክ ጋር ያለውን የተመን ልዩነት ከ20 ብር እስከ 25 ብር እንዲደርስ አድርጎታል፡፡ ትይዩ ገበያው ሊረበሽ የሚችባቸው በርካታ ምክንያቶች አሉ፡፡ እነዚህ ምክንያቶች ውስጥ አንዳንዶቹ ከገበያው/ከኢኮኖሚው ጋር የማይገናኙ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

አገራችን ግጭት ውስጥ እንደሆነች ይታወቃል፡፡ አገር በግጭት ውስጥ ስትሆን ለሕገ-ወጥ እንቅስቃሴ የሚውለው ዶላር መጠን እየጨመረ ስለሚሄድ የዶላር ፍላጎቱ ከፍ እያለ ይመጣል፡፡ ጦርነት ሲኖር የመሣሪያ ግዥዎች ይጨምራል፡፡ በአሸባሪው አካል ጦር መሣሪያ ሲፈልግ የሚገዛው በትይዩ ገበያ ላይ ባለ ሕገወጥ ዶላር ነው፡፡

በዓለም ዐቀፍ ላይ ባለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ብዙ አገራት ከገቡበት ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ማገገም አልቻሉም ነበር፡፡ ይልቁንም ሁለተኛው ዓይነት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመነሳቱ ዓለም ስጋት ውስጥ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ከውጭ አገራት በተለያየ መንገድ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው የውጭ ምንዛሪ በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሷል፡፡ በውጭ አገራት የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በትይዩ ገበያ ወደ አገር ቤት የሚልኩትን ዶላር ቀንሰዋል፡፡

ሁለተኛው ለትይዩ ገበያው ትልቅ የዶላር ምንጭ የነበረው የሰዎች ዝውውር (ጉዞ) እና ስብሰባ በኮቪድ-19 ምክንያት ቀንሷል፡፡ ሰዎች ጉብኝት እና ስብሰባ ሲመጡ ያመጡትን ዶላር ይመነዝሩ የነበረው በትይዩ ገበያው ላይ ነው፡፡ አሁን ላይ ይህ የዶላር ግኝት ተቀዛቅዟል፡፡

መንግሥት ከሰሞኑ የሕወሓትን አሸባሪ ቡድን በገንዘብ ሊደግፉ ይችላሉ ያላቸውን ተቋማት እያሸገ እና እየዘጋ፣ ሕገ-ወጥ የገንዘብ ግንኙነቶች ለመያዝ ጥረት እያደረገ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ሁኔታ በተለያዩ አካላት ላይ መደናገጥን ፈጥሯል፡፡ ይህም ሰዎች ተደናግጠው ያላቸውን ንብረት በዶላር ቀይረው ከአገር ለማስወጣት ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡
አሁን በገበያው ላይ ባለው የዋጋ ንረት ምክንያት ሰዎች ገንዘባቸውን በዶላር ቀይረው የማስቀመጥ ልምዳቸው ከፍ ሊል ይችላል፡፡ የተሻለ ገንዘብ ያለው ገንዘቡ በዋጋ ንረት እንዳይበላ መኪና እና ቤት እየገዛ ነው፡፡ እጁ ላይ ለመኪና እና ቤት የሚበቃ ገንዘብ የሌለው ሰው ገንዘቡን በዶላር ቀይሮ ሊያስቀምጥ ይችላል፡፡ በቤት ውስጥ ማስቀመጥ የሚፈጥረው የደህንነት ስጋት እንዳለው ልብ መባል አለበት፡፡

ከዚህ በላይ ባነሳኋቸው የግል ምልከታዎቼ ምክንያት በትይዩ ገበያው ላይ ያለው የዶላር አቅርቦት እና ፍላጎት መጣጣም አልቻለም፡፡ በዚህ ምክንያት የዶላር ዋጋ ሊጨምር ይችላል፡፡የትይዩ ገበያው ላይ መከፋፈል እንዳለ እያየንም ነው፡፡ አንድ ዶላር አንዳንድ ቦታ 55 ሌላ ቦታ 65 እስከ 70 ብር ድረስ እየተሸጠ ይገኛል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አንድ ዶላር እስከ 67 ብር ድረስ ሲሸጥ የሰነበተ ሲሆን፣ ወደ ድንበር አካባቢዎች ላይ ወደ 70 ብር ከፍ ብሎ ነበር። እርግጥ በዚህ ሳምንት ለውጥ አለ።

አንዳንድ ባለሞያዎች የንግድ ባንክ ከሰሞኑን ለነጋዴዎች የለቀቀውን የ‹ኤል.ሲ› ዶላር እንደ ምክንያት ያነሳሉ፡፡ ይህ ምክንያት በተወሰነ መልኩ አስተዋጽዖ ሊያበረክት ቢችልም፣ እንደ ዋና ምክንያት ሊጠቀስ የሚችል አይደለም፡፡ በቅርብ በተደረጉ ጥናቶች የትይዩ ገበያው 60 በመቶ የሚውለው ለነጋዴዎች እንደሆነ ታይቷል፡፡ የተቀረው 40 በመቶ ለጉዞ እና ሕገ-ወጥ እቃዎችን ለመግዛት ነው፡፡ ያ ማለት ቀድሞም ነጋዴው ለንግድ ሥራው የትይዩ ገበያን ይጠቀማል፡፡ የንግድ ባንክ ‹ኤል.ሲ› መፍቀድ አዲስ ነገር ላይሆን ይችላል፡፡ በእኔ እምነት ትልቁ ምክንያት የፖለቲካው ቀውስ እና መረበሽ ነው፡፡ ፖለቲካው ላይ አለመረጋጋት ሲኖር ሰው በስጋት በሚያደርገው እንቅስቃሴ የዶላርን ዋጋ ሊጨምረው ይችላል፡፡ እሱ መልክ እየያዘ ሲመጣ ሌላውም መስመር ይይዛል።

21/04/2023
የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ውዝግብን ለመፍታት የሚያስችል የድንበር ኮሚሽን ሊቋቋም ነው ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ለገባችበት “የድንበር ይገባኛል” ውዝግብ፤ የድንበር ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያ...
03/02/2023

የኢትዮጵያ እና የሱዳን የድንበር ውዝግብን ለመፍታት የሚያስችል የድንበር ኮሚሽን ሊቋቋም ነው

ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ለገባችበት “የድንበር ይገባኛል” ውዝግብ፤ የድንበር ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ሀገሪቱ ከጎረቤቶቿ ጋር ያለባትን የድንበር ውዝግብ ለመፍታት፤ የፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት በመቋቋም ላይ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህን ያስታወቀው፤ የመሥሪያ ቤቱ የስድስት ወር የሥራ አፈጻጸም በተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ ረቡዕ ጥር 24፤ 2015 በተገመገመበት ወቅት ነው። የመሥሪያ ቤቱን የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለቋሚ ኮሚቴው አባላት ያቀረቡት በሚኒስቴሩ የዕቅድ ክትትል እና ግምገማ ዳይሬክተሩ አቶ ዓለማየሁ ሰዋገኝ፤ ከድንበር ይገባኛል ጋር በተያያዘ ከሱዳን ጋር “ግጭት፣ የጦርነት ጉሰማ እና ትንኮሳዎች” እንደነበር አስታውሰዋል።

ከዚህ ቀደም ከውዝግቡ ጋር በተያያዘ በሱዳን በኩል “ድንበሩ የእኛ ነው፤ መሬቱ የእኛ ነው፤ ያለቀ ጉዳይ ነው” የሚሉ ድምጾች ጎላ ብለው ይደመጡ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ዓለማየሁ፤ ባለፉት ስድስት ወራት ግን “የድንበሩን ውዝግብ በውይይት ለመፍታት ስምምነት ላይ መደረሱን” አስረድተዋል። ለዚህም የሚረዳ “የድንበር ኮሚሽን ለማቋቋም የሚያስችል አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተከናውነዋል” ሲሉ አብራርተዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ከታክስ በፊት የ12 ነጥብ 96 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።የተገኘው ትርፍ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ...
02/02/2023

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ 6 ወራት ከታክስ በፊት የ12 ነጥብ 96 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የተገኘው ትርፍ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ15 ነጥብ 6 በመቶ ብልጫ ማሳየቱን የባንኩ ፕሬዝዳንት አቤ ሳኖ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ የባንኩን የ6 ወራት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳሉት፥ የባንኩ አጠቃላይ ሃብት በ6 ነጥብ 7 በመቶ በማደግ 1 ነጥብ 2 ትሪሊዮን ብር ደርሷል።

የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብም 978 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፤ ይህም ከዕቅዱ ጋር ሲነጻጸር የ10 በመቶ ዕድገት ማሳየቱ ተገልጿል።

ጥር 25/2015

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘ኢትዮ ዳይሬክት’ የተሰኘ ዲጂታል የውጪ ሐዋላ አገልግሎት መስጫ ፕላትፎርም ጥቅም ላይ አዋለየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘ኢትዮ ዳይሬክት’ (EthioDirect) የተሰኘ ዲ...
30/01/2023

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘ኢትዮ ዳይሬክት’ የተሰኘ ዲጂታል የውጪ ሐዋላ አገልግሎት መስጫ ፕላትፎርም ጥቅም ላይ አዋለ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ‘ኢትዮ ዳይሬክት’ (EthioDirect) የተሰኘ ዲጂታል የውጪ ሐዋላ አገልግሎት መስጫ ፕላትፎርም ጥቅም ላይ አዋለ።

አገልግሎቱን በይፋ ስራ ለማስጀመር በተዘጋጀ መርሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንዳሉት፤ ወቅቱን ያገናዘበ ዲጂታል የገንዘብ መላኪያ ዘዴን ተግባራዊ ለማድረግ ፕላትፎርሙ ጥቅም ላይ እንዲውል መደረጉን ተናግረዋል፡፡

ደንበኞች ‘EthioDirect’ መተግበሪያን ከፕሌይ ስቶር እና አፕስቶር በማውረድና ሞባይል ስልካቸው ላይ በመጫን ከውጪ ሀገራት ወደ ሀገር ውስጥ ገንዘብ መላክ እንደሚችሉ የተገለፀ ሲሆን፣ በቀጣይ

https://www.ethiodirect.com ድረ ገጽ አገልግሎቱ እንደሚቀርብ ታውቋል፡፡

መተግበሪያው ደኅንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ መሆኑን የተናገሩት አቶ አቤ፣ ደንበኞች ምቾታቸው እንደተጠበቀ በማንኛውም ጊዜና ቦታ ከክፍያ ነፃ ሐዋላ መላክ የሚችሉበት ዘመናዊ አገልግሎት መስጫ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ደንበኞች እንደ ማስተርካርድ እና ቪዛ የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ የክፍያ ካርዶችን በመጠቀም በመተግበሪያው ገንዘብ መላክ የሚችሉ መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፤ የሚላከው ገንዘብ በቀጥታ ወደ ተቀባዩ የባንክ ሒሳብ የሚገባ ሲሆን በቀጣይ ወደ ሲቢኢ ብር ዋሌት ማስገባት ወይም ተቀባዩ በአቅራቢያው ከሚገኝ የባንክ ቅርንጫፍ እንዲቀበል ለማስቻል ይሰራል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የውጪ ምንዛሬ በመሰብሰብ ለተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የማቅረብ ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት እንዳለበት ይታወቃል ያሉት አቶ አቤ፤ የውጭ ምንዛሬ ግኝቱን ለማሳደግ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን ነድፎ በመሥራት ላይ እንደሚገኝ መግለጻቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ጥር 22/2015

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2015 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡ጉባኤው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የ2015 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት አጠቃላ...
26/01/2023

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ2015 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

ጉባኤው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የ2015 በጀት ዓመት የ2ኛ ሩብ ዓመት አጠቃላይ የሥራ አፈፃፀም እንዲሁም የባንኩን የተለያዩ የሥራ ክፍሎች የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በማዳማጥ እና በመወያየት ከጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

በሥራ አፈፃፀም ግምገማ ጉባኤው የተሻለ አፈፃፀም እንዲሁም ክፍተት የታየባቸው አፈፃፀሞች ተለይተው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን፣ በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚረዱ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ማምሻውን ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ጥር 18/2015

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከሕብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁአንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከሕብረት ባንክ ቦርድ አባልነት በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ።አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ባልጠ...
26/01/2023

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከሕብረት ባንክ ቦርድ አባልነት ለቀቁ

አንጋፋው የፋይናንስ ባለሙያ አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ከሕብረት ባንክ ቦርድ አባልነት በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ።

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ ባልጠቀሱት የግል ምክንያት ከሕብረት ባንክ የቦርድ አባልነታቸው በፈቃዳቸው መልቃቃቸውን ለባንኩ የቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሳምራዊት ጌታ መሳይ በጻፉት የመልቀቂያ ደብዳቤ አስታውቀዋል።

አቶ እየሱስወርቅ ማክሰኞ ጥር 16 ቀን 2015 ዓ.ም.ለባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ በላኩት ደብዳቤ ከዛኑ ዕለት ጀምሮ ከቦርድ አባልነታቸው መልቀቃቸውን ጠቅሰው ፣ በቦርድ አባልነት እንዲያገለግሉ እንደ አዲስ የተመረጡበትን ሙሉ የሥራ ዘመን በአገልግሎት መጨረስ ባለመቻላቸው የባንኩን ባለአክሲዮኖች ይቅርታ ጠይቀዋል።

አቶ እየሱስወርቅ ዛፉ በፋይናንስ ዘርፍ ለረጅም አሥርት ዓመታት ያገለገሉ ባለሙያ ከመሆናቸው ባሻገር የህብረት ባንክ እና ሕብረት ኢንሹራንስ መሥራች እንዲሁም ከፍተኛ ባለአክሲዮኖች መካከል አንዱ ናቸው።

ጥር 18/2015

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ለተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ የሚውል 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ...
26/01/2023

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

የዓለም ባንክ ለኢትዮጵያ ለተሻለ የጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ የሚውል 745 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ።

ባንኩ በዚህ ወቅት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎች በኮቪድ-19፣ ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በደረሰ አደጋና የነበረውን ግጭት ጨምሮ ብዙ ቀውሶች መድረሱን አመላክቷል።

የጤና አገልግሎቶችን አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ በመስተጓጎሉም ባለፉት ዐሠርት ዓመታት በሀገሪቷ የተመዘገበው የጤና ውጤት እና የአገልግሎት አሰጣጥ ዝቅተኛ ሆኖ ተመዝግቧልም ነው ያለው፡፡

ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች ወደ 24 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች በቂ የጤና አገልግሎት እያገኙ ባለመሆኑ ድጋፉ ለዚህ አገልግሎት እንደሚውል ተገልጿል።

ጥር 18/2015

አማራ ባንክ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ  አንስቶ 8.8 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ማግኘቱን እና ከግብር በፊት 237 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተነግሯል።የባንኩ የሀብት መጠን 7.1 ቢሊዮን  ብር ደርሷል። በተ...
29/12/2022

አማራ ባንክ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 8.8 ቢሊየን ብር ተቀማጭ ማግኘቱን እና ከግብር በፊት 237 ሚሊዮን ብር ማትረፉ ተነግሯል።

የባንኩ የሀብት መጠን 7.1 ቢሊዮን ብር ደርሷል። በተጨማሪም የተከፈለ የካፒታል መጠን 4.8 ቢሊዮን መሆኑ ተመላክቷል።

አማራ ባንክ አንድ መቶ አርባ አንድ ሺህ የሚሆኑ ባለአክስዮኖች እንዳሉት እና የባንኩ የደንበኞች ቁጥር በአሁን ሰዓት ከአምስት መቶ አምስት ሺህ በላይ ደንበኞች መድረሱ ተገልጿል።

ባንኩ የቅርንጫፎቹን ቁጥር ከ201 በላይ ያሳደገ መሆኑ የተለጸ ሲሆን በተጨማሪም ባንኩ አዳዲስ ቅርንጫፎችን ለመክፈት ማቀዱንና ያሉትን 8 የኤቲኤም ማሽኖች ቁጥር ወደ 125 ለማሳደግ የማሽን ግዢ መፈጸሙ ተነግሯል።

አማራ ባንክ ከ6.5 ቢሊየን ብር በላይ የተፈረመ ፣ 4.8 ቢሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል እንዲሁም ከ170ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖች ይዞ በሰኔ 2014 ወደ ስራ የገባ ባንክ ነዉ፡፡

ይህ የተነገረው የባንኩ ባለ አክሲዮኖች 1ኛ መደበኛ እና አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ነው።

ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 105 ሚሊየን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ።ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር 12ኛ መደበኛና ድንገተኛ የባለአክሲዮኖ...
03/12/2022

ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 105 ሚሊየን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ ማግኘቱን ገለጸ።

ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር 12ኛ መደበኛና ድንገተኛ የባለአክሲዮኖች ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባዔ እያካሄደ ነው። በስብሰባው የ2021/22 በጀት ዓመት የኩባንያውን አጠቃላይ የሥራ አፈፃፀም የሚያሳይ "በውጭ ኦዲተሮች የተጣራ" የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቧል፡፡

በሪፖርቱም በበጀት ዓመቱ አክሲዮን ማኅበሩ ትርፋማ መኾኑ ተገልጿል፡፡ ይሁን እንጅ ከዓረቦን ተመን ጋር በተያያዘ በኢንሹራንስ ኩባንያዎች መካከል የሚታየው ጤናማ ያልኾነ ፉክክር እና በኢንሹራንስ ኩባንያዎች መካከል የተቀናጀ የመረጃ ልውውጥ አለመኖር፣ በዘርፉ በቂ የኾነ የሰለጠነ የሰው ኀይል አለመኖር፣ አዳዲስ ፕሮዳክቶችን ለማካተት የሚጠይቀው ከፍተኛ ወጪ እና ከኢንቨስትመንት የሚገኘው ትርፍ ውስንነት እንዳሉበት ነው የተገለጸው፡፡

ሀገራዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የዋጋ ግሽበት፣ የውጪ ምንዛሬ እጥረትና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ያስከተለው አሉታዊ ተፅዕኖ በአክሲዮን ማኅበሩ ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳስከተለበት ነው የተብራራው። በነዚህ ሂደቶች ውስጥ ግን ያሉትን ችግሮች ተቋቁሞ እየሠራ ያለው ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር ሂደቱን የሚያደናቅፉትን ያህል አበረታች ሁነቶችም ነበሩ ተብሏል።

በተለይም በሀገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተስፋፋ የመጣው የውጭ ኢንቨስትመንት፣ በመድህን ዋስትና የኅብረተሰቡ ግንዛቤ ማደግና ፍላጎት መጨመር፣ የመድን ሽፋን ሰጪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ አወንታዊ ደንቦች እና የቅሬታ አፈታት ሥርዓት መኖር፣ በየጊዜው እያደገ የመጣው የሕዝብ ቁጥር፣ የከተሞች መስፋፋት እና የአደጋ ስጋትን ከመቀነስና ከመቆጣጠር አንጻር የማኅበረሰቡ ባሕልና ንቃተ ህሊና ማደግ አቅም እንደፈጠሩ ተመላክቷል።

ኩባንያው በ2021/22 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 424 ሚሊዮን ብር በላይ ዓረቦን ያስመዘገበ ሲኾን ከዚህ ውስጥ 412 ሚሊዮን ብር በላይ የጠቅላላ መድን ድርሻ ነው፡፡ ቀሪው ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ደግሞ ከሕይወት መድን የተገኘ ነው ተብሏል፡፡

በ2021/22 በጀት ዓመት ከተገኘው አጠቃላይ ዓረቦን መካከል የተሸከርካሪ መድን ዋስትና 43 ነጥብ 4 በመቶ በመያዝ ቀዳሚ ሲኾን፣ ገንዘብ ነክ ከኾነው የመድን ዋስትና 28 ነጥብ 9 በመቶ እና ኢንጂነሪንግ 5 ነጥብ 7 በመቶ በመያዝ ይከተላሉ ተብሏል፡፡ በአጠቃላይ ኩባንያው ላለፉት አስር ዓመታት በአማካይ 27 በመቶ የዓረቦን ዕድገት ማስመዝገብ ችሏልም ተብሏል።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከጠቅላላ የመድን ዋስትና ብቻ 250 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ዓረቦን ያስመዘገበ ሲኾን ይህም አኃዝ ከባለፈው ዓመት አፈጻጸም 197 ሚሊዮን ብር በላይ ጋር ሲነጻጸር 26 ነጥብ 6 በመቶ ዕድገት አሳይቷል።

በሌላ በኩል ኩባንያው በጠቃላይ 49 ሺህ 584 ውሎችን በተለያዩ የዋስትና ዓይነቶች ሸጧል፡፡ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከሕይወት መድን ዋስትና የተገኘው ዓረቦን ብር 11 ሚሊዮን ብር በላይ ሲሆን ይህም ከባለፈው ዓመት 11 ሚለዮን ብር በላይ ጋር ሲነጻጸር 5 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል።

ዓባይ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኅበር በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በአጠቃላይ ከጠቅላላ መድንና ከሕይወት መድን ዋስትና 105 ሚሊዮን ብር በላይ ያልተጣራ ትርፍ መገኘቱን ያረጋገጠ ሲኾን በቀጣይ በተጠናከረ መልኩ ይሠራል ተብሏል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ሲራራ - Sirara posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ሲራራ - Sirara:

Share