20/08/2025
🚨🇪🇹🇪🇷 ''የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ከተጀመረ እንደ ሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ወደ ግዛት ልውውጥ መሄዱ የማይቀር ነው በተጨማሪም ኤርትራ አሰብን ማጣቷ የማይቀር ነው''
አንጋፋው ፖለቲከኛ አቶ በረከት ስምኦን
አቶ በረከት ስምኦን መቀመጫውን አሜሪካ አገር ላደረገ ኢትዮ ሪቪው ለተባለ ድህረገጽ ሰጠው በተባለው ትንታኔ ስለ ኢትዮ ኤርትራ እና ስለ ህወሓት ቤት ስለ ተፈጠረው ሹኹቻ አንዳንድ ነገር ብሏል።
➛በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃል ጦርነት ቢቀሰቀስ አስመራ ጫፍ ደርሶ አይቆምም
➛የኤርትራ ሉዐላዊነት ያበቃለታል
➛ጦርነት ከመጀመሩ በፊት የሻዕቢያ ስርዓት ከተገረሰሰ በኋላ በኤርትራ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር መጀመሪያ ማሰላሰል መቅደም አለበት
➛በህወሓት እና በኤርትራ መካከል የተፈጠረው ግንኙነት ከሁሉም አቅጣጫ መዘጋት የለብንም የሚል የተስፋ እርምጃ ነው ብሏል
➛ግን የህወሓት አመራሮች ኢሳይያስ አፈወርቂ በዓለም ደረጃ የተጠሉ መሪ መሆናቸውን የዘነጉ ይመስለኛል ብሏል።
➛በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ከተነሳ ግን እንደ ራሻ እና ዩክሬን የመሬት ልውውጥ ሊያስከትል ይችላል። ይህ ብቻ ሳይሆን ኤርትራ ሙሉ በሙሉ አሰብን ታጣለች ብሏል።
➛ህወሓት ከዚህ በኋላ ልታደስም ቢል የመታደስ ግዜው ያለፈ መስሎ ነው የሚታየኝ ብሏል።
➛የቀድሞው ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝንም ወቅሷል ጥሩ ጅማሮና ማበብ ላይ የነበረውን የደቡቡን ፖለቲካ እንዲፈርስ አድርጓል ብሏል።
Tigray Communication Affairs Bureau
Abiy Ahmed Ali
@