ጊዮን ፕረስ - Ghion Press

ጊዮን ፕረስ - Ghion Press " Don't push people, Lead them"

28/06/2025
02/05/2025

ቡርኪናፋሶ አልተቻለችም❗️❗️

ቡርኪናፋሶ በ7,000 ዶላር የችርቻሮ ዋጋ ኢታዋ የተባለውን በአፍሪካ የመጀመርያው የኤሌክትሪክ መኪና ለአፍሪካ ገበያ አቀረበች።

የቡርኪናቤ መኪና አምራች በሆነው ITAOUA አማካኝነት የሀገር ውስጥ ሀብቶችን እና እውቀቶችን በመጠቀም በቡርኪናፋሶ ተመርቶ የሚገጣጠመዉ ለከተማ እና ለገጠር አካባቢዎች ተስማሚ የሆነዉ በ30 ደቂቃ ቻርጅ በኋላ 330 ኪሎ ሜትር (205 ማይልስ) ርቀትን መጓዝ የሚችለው AI ቴክኖሎጂዎች ምቾትና ጥንካሬ በቂ መለዋወጫ የአመታት ጋራንት ያለዉ ITAOUA የኤሌክትሪክ መኪና በተመጣጣኝ ዋጋ ለአፍሪካ ገበያ ሊቀርብ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ አገሪቱ በምዕራብ አፍሪካ የቴክኖሎጂ ማዕከል ለመሆን ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል በሀገሪቱ የኢንዱስትሪ እና የቴክኖሎጂ እድገት ውስጥ ትልቅ ምዕራፍ ይከፍታል የተባለው የኤሌክትሪክ መኪና በኦንላይን ገበያ በ7,000 ዶላር የችርቻሮ ዋጋ እየተሸጠ ይገኛል።

ከዚህም በተጨማሪ የአፍሪካ ምርትን በአለም አቀፍ ደረጃ አዲስ እምርታ ያሳዩት እንደ “ቤተኛው” እና “ሳሄል” ያሉ የኩባንያው ሞዴሎች እንደ ጂፒኤስ አሰሳ፣ ብሉቱዝ እና የፀሐይ ኃይል መሙላት ያሉ የተራቀቁ ቴክኖሎጂዎችን በመያዝ በአለም ገበያውን ላይም ተወዳዳሪዎች ይሆናሉ ተብሏል ።

እንደ ሞርዶር ኢንተለጀንስ ዘገባ፣ የአፍሪካ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ገበያ እ.ኤ.አ. በ2021 11.94 ቢሊዮን ዶላር ዋጋ ያለው ሲሆን በ2027 21.39 ቢሊዮን ዶላር ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፣ ይህም በየዓመቱ 10.2 በመቶ ይጨምራል።
ስለዚህም የ ITAOUA የኤሌክትሪክ መኪና መጀመር በቡርኪናፋሶ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር ይጠበቃል ሲል ዘግቧል ።

ይህ አፍሪካ ለቴክኖሎጂ ፈጠራ ያላትን እምቅ አቅም የሚያሳይ ጅምር በማኑፋክቸሪንግ፣ በሽያጭ፣ በጥገና እና በታዳሽ ኃይል ዘርፎች በሺዎች የሚቆጠሩ ስራዎችን ይፈጥራል፣ ይህም ለአገሪቱና ሀጉሪቱ ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ያደርጋል ተብሏል።
- ነጋሪት

02/05/2025

"በጣም አስደንጋጭ ዜና ከአዳማ"
ከእውነተኛ ምንጮች የተገኘ መረጃ ስለሆነ ሁሉም ሰው ጥንቃቄ ማድረግ አለበት እንላለን ፡፡ ይህ መረጃ ቀጥታ ከአንድ ትልቅ ኢትዮጵያዊ የተገኘ ነው,ለመረጀው ከልብ እናመሰግናለን ፡፡
አስቸኳይና አሳሳቢ ማሳሰብያ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የሳምንቱ አነጋጋሪ የህፃናት መጥፋት በአዳማ ናዝሬት ከተማና አካባቢዋ ልዩ ትኩሳትና አነጋጋሪ ጉዳይ ሁላችሁንም ይመለከታል እባካችሁ አንዴ ልብ ብላችሁኝ አድምጡኝ ። ሰው ሆኜ መፈጠሬን የጠላሁበት ዘመን ላይ መድረሴ በጣም ቢያሳዝነኝም ነገሩን ግን ከአድማጭ ጆሮ ላደርስ ዘንድ ውስጤ አስጨነቀኝ ።

በአዳማ ከተማ ሰሞኑን ብዙ ህፃናት በአሮጊቶች እየተሰረቁ መሆኑንና የኩላሊት ስርቆት መጀመሩን ለመታዘብ በቅቻለው ። አንዲት ህፃን ከአዳማ ቡርቃ ትምህርት ቤት ተሰርቃ በማግስቱ ወይም ጠዋት ላይ ኩላሊትዋ ተወስዶ አስከሬንዋ በተወሰደችበት አካባቢ ተጥሎ መገኘቱ ህዝቡን በጣም አስደንግጧል ።

በተመሳሳይ ሁኔታ አንዲት ሴት ስምንት ህፃናትን ታክሲ ኮንትራት ይዛ ልትሰወር ስትል ባለታክሲው ተጠራጥሮ የስምንቱንም ህፃን ህይወት ለመታደግ ሴትየዋ ያለችውን መንገድ ትቶ ታክሲውን ወደ ፖሊስ ጣብያ ይዞ ቀጥታ ኮንትራቱን ፖሊስ ጣብያ ያደርገዋል ሁሉንም ነገር ለፖሊስ ያስረክባል ። ሴትየዋም ስትጠየቅ ተደራጅተው በሀገር ውስጥ እንደተበተኑ ፍንጭ ሰጥታለች ።

ወገኖቼ ንቁ ! የአወሳሰድ ስልታቸውንም ልጠቁማችሁ ፦ እንደ አሮጊት መስለው እቃ ተሸክመው ፣ የደከሙ መስለው ህፃናት ጋር ሲደርሱ እርዱን ይላሉ ። ከዛም ህፃናቱን መድሀኒት ያስነኩና ይከተሏቸዋል ። ሁለት ተከራይ መስለው ቤት በመከራየት ህፃናት ያሉበትን ሰፈር ይቃኛሉ ። ከዛም ሰው አካባቢው ከሌለ ህፃናትን ከአካባቢው ይሰውራሉ ። ወገኖቼ አሁን የሁላችንም ቤት ሳይንኳኳ አልቀረም ።

መፍትሔውን ልንገራችሁ ከንፈር መምጠጥ አይደለም ከከተማ እስከ ገጠር ይህቺን መልእክት በማድረስ ህፃናትን በአይነቁራኛ ልንጠብቃቸው ልንከታተላቸው ይገባል ። ከሰው ጋር እንኳን ሆነው ሲሄዱ የተለየ ባህሪ ሲያሳዩ አቁመን ልንጠይቅና ልንመረምር ይገባል ። የህፃናት ጥበቃ የወላጅ ብቻ ሳይሆን የህብረተሰቡም ክትትል እንዲሆን በጥብቅ አሳስባለው ። ጆሮ ያለዉ ይስማ !

እባክህን ይህቺን መልዕክት ሼር አድርጋትና
በርካታ ነፍሳትን ከሞት አፋፍ አድን !

ሼርርርርርርርርርርርርርርርርርር
ሼርርርርርርርርርርርርርርርር
ሼርርርርርርርርርርርርርር
ሼርርርርርርርርርርርር
ሼርርርርርርርርርር

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Nesredin Muktar, Fuad Shifa Abdella, ሰኢድ የሱፍ, ሙፊቲ ጃማል ሁሴን...
01/05/2025

Shout out to my newest followers! Excited to have you onboard! Nesredin Muktar, Fuad Shifa Abdella, ሰኢድ የሱፍ, ሙፊቲ ጃማል ሁሴን, Teshome Manaye, Atakilt Fikre, Aliyom Ye Riye, Eminet Eyasu, Chalachew Taye, Gir May, Abaa Hirba, Goiteom Welday, ወርቁ መግስቱ, Ifa Press, Mamo Ayalew, Arega Stot, ሊሻን አሊዳውዲ አማኑ, Telaye Abara, መሀመድ አብደለ

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ጊዮን ፕረስ - Ghion Press posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share