Ethio Jupitor Media

Ethio Jupitor Media Like/Follow our page

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው የBRICS ጉባኤ ኢትዮጵያን በአባልነት ተቀብሎ አፅደቀ::
24/08/2023

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው የBRICS ጉባኤ ኢትዮጵያን በአባልነት ተቀብሎ አፅደቀ::

21/08/2023

የፋና ላምሮት ተወዳዳሪዋ አስገራሚ ብቃት
ትዕግስት አስማረ በፋና ላምሮት

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው****** የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ምስረታ ጉባኤ በወልቂጤና አርባ ምንጭ ከተሞች እየ...
18/08/2023

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ምስረታ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
******
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ምስረታ ጉባኤ በወልቂጤና አርባ ምንጭ ከተሞች እየተካሄደ ነው።

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታውን እያካሄደ ያለው ጉራጌ፣ ስልጤ፣ ካምባታ ጠምባሮ፣ ሃላባ፣ ሀዲያ ዞኖችና የም ልዩ ወረዳን በማካተት መሆኑ ይታወቃል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የነባሩን ክልል ህገ-መንግስት ለማሻሻል በተዘጋጀ ረቂቅ ሰነድና በሌሎች የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ምክክር እንደሚደረግ ተጠቁሟል።

በመርሐ ግብሩ የፌዴራል፣ የአምስቱም ዞኖችና የልዩ ወረዳው አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የተለያዩ የህብረተሰብ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።

በተመሳሳይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምስረታ ጉባኤ አካል የሆነው የክልሉ ረቂቅ ህገ-መንግስት ላይ ያተኮረ ውይይት በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በጉባኤው የክልል አደረጃጀት ሂደት በተመለከተ የክልሉ አደረጃጀት የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በኩል ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል ተብሏል።

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በ6 ማዕከላት የተዋቀረ ሲሆን ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ዲላ፣ ጂንካ፣ ሳውላና ካራት ናቸው።

የምስረታ ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በስድስት ዞኖችና አምስት ልዩ ወረዳዎች አካትቶ የሚደራጅ ነው።

18/08/2023

በወያኔ ጊዜ በዓዴን የቤት ሰራተኛ ነበር፤ በአሁን ወቅት የአማራ ብልፅግና የአቢይ አህመድ ገረድ ነው፡፡
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አስገራሚ ንግግር!
ሙሉ ቪዲዮን ይመልከቱ
https://www.youtube.com/watch?v=0v4e0zcZLp4

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ከኃላፊነታቸው ተነስተው “በህግ እንዲጠየቁ” በሲዳማ ክልል ውሳኔ ተላለፈ *******ላለፉት ሶስት ዓመታት ገደማ የሀዋሳ ከተማን በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጸጋዬ ቱ...
17/08/2023

የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ከኃላፊነታቸው ተነስተው “በህግ እንዲጠየቁ” በሲዳማ ክልል ውሳኔ ተላለፈ
*******
ላለፉት ሶስት ዓመታት ገደማ የሀዋሳ ከተማን በከንቲባነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጸጋዬ ቱኬ፤ በ“ብልሹ አሰራር” እና “አፈጻጸም ድክመት” ተገምግመው ከስልጣናቸው መነሳታቸውን የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” የሲዳማ ክልል ምንጮች ገለጹ። አቶ ጸጋዬ ከኃላፊነት እንዲነሱ ውሳኔ የተላለፈው ትላንት ረቡዕ ነሐሴ 10፤ 2015 ከተደረገ ግምገማ በኋላ መሆኑን ምንጮቹ አስታውቀዋል።

በሲዳማ ክልል ደረጃ ያሉ የፓርቲ እና የመንግስት ስራዎች አፈጻጸም እየተገመገሙበት ያለው መድረክ መካሄድ የጀመረው፤ ካለፈው ሳምንት መጨረሻ እሁድ ነሐሴ 7፤ 2015 ጀምሮ ነው። በዚህ መድረክ ላይ የተሳተፉ አንድ ምንጭ፤ ከሀዋሳው ከንቲባ በተጨማሪ ሌሎች የክልሉ አመራሮች ላይ ግምገማ መደረጉን አመልክተዋል። ከእሁድ ጀምሮ የነበሩትን ግምገማዎች በአካል ተገኝተው የተሳተፉት አቶ ጸጋዬ፤ እርሳቸውን በሚመለከተው የትላንት ከሰዓቱ ግምገማ ግን አለመገኘታቸውን እኚሁ ምንጭ አክለዋል።

በትላንቱ ግምገማ ላይ አቶ ጸጋዬ “ከፍተኛ ሙስና ውስጥ መግባታቸውን” የሚያመለክቱ፣ “በሰነዶች የተረጋገጡ” መረጃዎችን መቅረባቸውን በመድረኩ የተሳተፉ ሁለት የ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ምንጮች ተናግረዋል። በዚሁ ግምገማ “ከፍተኛ ተመራጭ የነበረችው የሀዋሳ ከተማ ወደ ኋላ መሄዷ” መነሳቱን የጠቆሙት ምንጮች፤ የከተማዋ ከንቲባ “የአቅም ውስንነት ጭምር አለባቸው” መባሉን ጠቅሰዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ በይፋ ስራውን ጀመረ።********ቦርዱ በዛሬው እለት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ አባላት ጋር የተወያየ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም የመ...
16/08/2023

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ በይፋ ስራውን ጀመረ።
********
ቦርዱ በዛሬው እለት ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ አባላት ጋር የተወያየ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም የመስክ ምልከታ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

በመድረኩም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ እስካሁን ያከናወናቸውን ስራዎችና የቀጣይ እቅዶች ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ አባል የሆኑት አቶ መለሰ ዓለሙ፥ በውይይቱ በቀጣይ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ጋር በጋራ በሚከናወኑ ስራዎች ላይ ምክክር መደረጉን ተናግረዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ ሰላምን ለማስፈን እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት ላይ ዝርዝር ማብራሪያ መሰጠቱንም ነው ያነሱት፡፡

በአዋጁ አማካኝነት በቁጥጥር ስር የዋሉ ሰዎችን ሰብዓዊ መብት አያያዝ በሚመለከት ለመርማሪ ቦርድ አባላቱ ገለጻ መደረጉንም ጠቅሰዋል፡፡

አዋጁ ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ በአማራ ክልል የጸጥታ ችግር ተከስቶባቸው የነበሩ ዋና ዋና ከተሞችና አካባቢዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለስ መቻሉንም ነው የተናገሩት።

በዚህም ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ የግልና የመንግስት ተቋማት ስራ እንደጀመሩ መናገራቸውን ኢዜአ ዘገቧል።

የአዋጁን ተግባራዊነት ተከትሎ የተፈጠረው ሰላም ለአርሶ አደሩ ማዳበሪያ ተደራሽ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም አንስተዋል፡፡

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ ሰብሳቢ አዝመራ አንደሞ በበኩላቸው መርማሪ ቦርዱ ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰው፥ በዛሬው የውይይት መድረክ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ እዝ እስካሁን ያከናወናቸው ተግባራት ላይና የቀጣይ እቅዶች ላይ ዝርዝር መረጃ ማግኘታቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ይህንን ተከትሎ በቀጣይ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባና በአማራ ክልል የመስክ ምልከታ እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት፡፡

ቦርዱ የአዋጁን አፈጻጸም እየገመገመ ውጤቱን ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግም አስረድተዋል፡፡

ሳፋሪኮም የሞባይል የገንዘብ ማዘዋወሪያ አገልግሎቱን ኤም-ፔሳ በኢትዮጵያ ጀመረ----------ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኤም-ፔሳ የተባለውን በሞባይል የሚደረግ የገንዘብ ዝውውር አገልግሎቱን ዛሬ በይ...
16/08/2023

ሳፋሪኮም የሞባይል የገንዘብ ማዘዋወሪያ አገልግሎቱን ኤም-ፔሳ በኢትዮጵያ ጀመረ
----------
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ኤም-ፔሳ የተባለውን በሞባይል የሚደረግ የገንዘብ ዝውውር አገልግሎቱን ዛሬ በይፋ ሥራ ሊያስጀምር ነው።
ሳፋሪ ኮም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ በተሰጠው በሦስተኛው ወሩ ዛሬ ከሰዓት በኋላ 9 ሰዓት ላይ አገልግሎቱን በይፋ እንደሚጀምር አስታውቋል።
ሳፋሪኮም ባለፉት ሦስት ወራት ኤም-ፔሳን ወደ ሥራ ለማስገባ ባደረገው ዝግጅት የሙከራ ሥራዎችን ማከናወኑን፣ የቴክኒክ ዝግጁነቱን ማረጋገጡን፣ ከባንኮች ጋር ውል መፈጸሙን፣ ሠራተኞቹን ቀጥሮ ማሠልጠኑን እና የኤም-ፔሳ ወኪሎችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል።
የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እናት ድርጅት የሆነው ቮዳኮም ግሩፕ ሊሚትድ የኤም-ፔሳ አገልግሎቱን በመጪው ዓመት መስከረም 2016 ዓ.ም. አጋማሽ በኢትዮጵያ እንደሚጀምር ከዚህ ቀደም ገልጦ ነበር።
ሁሉም የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ደንበኞች *733 # በመደወል የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ የተገለጸ ሲሆን፣ መተግበሪያውም በአምስት ቋንቋዎች መዘጋጀቱን ድርጅቱ አሳውቋል።
ደንበኞች ኤም-ፔሳን በመጠቀም ወደ አገር ውስጥ ክፍያ መፈጸም፣ ከአገር ውስጥ እና ከውጭ ገንዘብ መቀበል፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች ክፍያ መፈጸም፣ የአየር ሰዓት መግዛት፣ ከኤም-ፔሳ ወደ ባንክ ገንዘብ መላክ እንዲሁም ከባንክ ወደ ኤም-ፔሳ ገንዘብ ማዘዋወር ይቻላሉ ብሏል ግዙፉ የቴሌኮም ኩባንያው።

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ከባድ ውጊያ እያደረገች መሆኑን አስታወቀችከተያዙባት ግዛቶች የሩሲያ ወታደሮችን ለማስወጣት በያዘችው ዘመቻ በደቡባዊው ምስራቅ ክፍል "አንዳንድ ስኬት" እያስመዘገበች መሆኑ...
16/08/2023

ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ከባድ ውጊያ እያደረገች መሆኑን አስታወቀች

ከተያዙባት ግዛቶች የሩሲያ ወታደሮችን ለማስወጣት በያዘችው ዘመቻ በደቡባዊው ምስራቅ ክፍል "አንዳንድ ስኬት" እያስመዘገበች መሆኑን ተናግራለች።
https://am.al-ain.com/article/ukraine-engage-heavy-fighting-russia?fbclid=IwAR0cYKCi1Ir6vrTc1hBalP76xKUIYoBTePN78bavrc2HuFQZnnDoGlrCZNg
*******-

በሩሲያ ፈንጂዎችና ጠንካራ ምሽጎች ምክንያት የኪየቭ እርምጃ እክል ገጥሞታል ተብሏል

ነጻ  ሕክምናየከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ላለባቸው፣ዕድሜያቸው 3 ወርና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሕጻናት ኮሌጃችን  ዳይሬክት ኤይድ  ከተባለ ድርጅት ጋር  በመተባበር ነጻ ሕክምና ይሰጣል፡፡በተጨምሪም...
16/08/2023

ነጻ ሕክምና
የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ላለባቸው፣ዕድሜያቸው 3 ወርና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሕጻናት ኮሌጃችን ዳይሬክት ኤይድ ከተባለ ድርጅት ጋር በመተባበር ነጻ ሕክምና ይሰጣል፡፡
በተጨምሪም የጣት አበቃቀል እና መዛባት ችግር ያለባቸውም ሕጻናት አገልግሎቱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
አገልግሎቱን ለማግኘት በ976 በመደወል ወላጆች ተራ ማስያዝ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የአዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የምስረታ በዓል በመጪው ቅዳሜ በአርባ ምንጭ ከተማ ሊካሄድ ነው*******የነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤትም ለሳምንቱ መጨረሻ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቷልበህዝበ ...
16/08/2023

የአዲሱ የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የምስረታ በዓል በመጪው ቅዳሜ በአርባ ምንጭ ከተማ ሊካሄድ ነው
*******
የነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤትም ለሳምንቱ መጨረሻ አስቸኳይ ጉባኤ ጠርቷል

በህዝበ ውሳኔ የተመሰረተው 12ኛው የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ይፋዊ የምስረታ በዓሉን በሳምንቱ መጨረሻ በአርባ ምንጭ ከተማ ሊያደርግ ነው። የነባሩ የደቡብ ክልል ምክር ቤትም በተመሳሳይ ቀናት አስቸኳይ ጉባኤ መጥራቱን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

በአርባ ምንጭ ከተማ የሚካሄደው የ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” ምስረታ ለሁለት ቀናት የሚቆይ መሆኑን የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ኤደን ንጉሴ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል። ከነገ በስቲያ አርብ ነሐሴ 12፤ 2015 በሚኖረው መርሃ ግብር፤ የአዲሱ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤውን እንደሚያደርግ ኃላፊዋ አስረድተዋል።

በዚሁ ጉባኤ ላይ የምክር ቤቱ አባላት የአዲሱን ክልል ህገ መንግስቱን ተወያይተው ያጸድቃሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ተናግረዋል። በማግስቱ ቅዳሜ ደግሞ 12ኛው የፌደሬሽኑ ክልል በይፋ የምስረታ ፕሮግራሙን እንደሚያካሄድ ኤደን ጠቁመዋል። የአዲሱ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የካቤኔ አባላትም በዚሁ ቀን ይሾማሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኮሚዩኒኬሽን ኃላፊዋ አክለዋል።

በ“ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የምስረታ በዓል ላይ “ተጋባዥ” እንግዶች እና የፌደራል መንግስት የስራ ኃላፊዎች ይገኛሉ ተብሏል። ለዚሁ ስነ ስርዓት ከዛሬ ረፋድ ጀምሮ የአርባ ምንጭ ከተማን የማጽዳት ክንውኖች ሲካሄዱ መዋላቸውን እና የ“እንኳን ደህና መጣችሁ” መልዕክት የያዙ ባነሮች ሲሰቀሉ መመልከታቸውን የከተማይቱ ነዋሪዎች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

Address

Megenaga
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio Jupitor Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ethio Jupitor Media:

Share