
07/08/2025
ሰበር ዜና
አውሮፕላን ተመታ
የሱዳን ጦር በሱዳን ዳርፉር በኒያላ አየር ማረፊያ ሲያርፍ የነበረ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አይሮፕላን ላይ ጥቃት መሰንዘሩ ተሰማ።
የሱዳን ጦር የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች አውሮፕላን በዳርፉር ግዛት ስትራቴጅካዊቷ ኒያላ ከተማ ሲያርፍ ኢላማ አድርጓል ሲል የሱዳን ቴሌቪዥን ዘግቧል።
አውሮፕላኑ የኮሎምቢያ ቅጠረኛ ተዋጊዎችን ይዞ እንደነበር እና ሲያርፍ በትናንትናው ዕለት August 6/2025 በሱዳን ጦር ጥቃት እንደደረሰበት ዘገባው ጠቅሷል።
በጥቃቱ ከ40 በላይ የኮሎምቢያ ቅጥረኛ ወታደሮች/Colombian mercenaries/ መሞታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
ኒያላ አየር ማረፊያ በጄኔራል ሀምዳን ደጋሎ በሚመራው የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ቁጥጥር ስር ይገኛል።
የሱዳን ጦር አረብ ኢምሬትስ ለሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ጦር ድጋፍ ታደርጋለች ብሎ ያምናል።
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀላሉ
https://t.me/ethiopostnews