Classic Ethiopia

Classic Ethiopia �መኖሬ እንዲታወቅ አልጮህም �

14/05/2025



ህወሓት ከፖለቲካ ፓርቲነት ተሰረዘ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት) ከፖለቲካ ፓርቲነት መሠረዙን አሳውቋል።

13/05/2025


አቶ ጌታቸው ረዳ‼️

በሰሜኑ ጦርነት ወቅት አንዳንድ የትግራይ ጦር መሪዎች ከ90 ኮሜ ርቀት የሚመሩትን ጦርነት ላይ የሚሸሹ ተውጊዎች ሲረሽ ኑ ነበር።

በወቅቱ ጦርነቱ እየተካሄደ ለምሽግ መቆፈሪያ የተላከን ኤክስካቫተር ለህገወጥ የወርቅ ማውጣት ሂደት ሲጠቀሙበት ነበር።
ኮምቦልቻ ከተማ በትግራይ ኃይሎች እጅ ወድቃ በነበረችበት ወቅት 4 ቢሊዮን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደወጣ እና 1 ቢሊዮን ብር በጄኔራሎቹ መጭበርበሩን ገልፀዋል። ለምሳሌ ጄኔራል ሃይለስላሴ የሚባለው 300 ሚሊዮን ብሩን ወስዷል።
አሁንም ወርቅ የሚነግዱ ጄኔራሎች አሉ።
"የማምንበትን ትግል ነው ያደረኩት ብዬ የማምነው። ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶችን በሚበላበት ወቅት ምሽግ ለመቆፈር የወሰድነውን ኤክስካቫተር ለወርቅ መልቀሚያ የሚጠቀሙበት አዛዦች እንዳሉ አውቃለሁ። አሁን ሲዋሹ በጣም ይገርመኛል። እስካሁን የዋሸሁት ይበቃኛል። እስካሁን የታገስኩት ይበቃኛል። ሰው ሲሸጡ የሚኖሩ ሰዎች አሉ። [በጦርነቱ ወቅት] ኤርትራዊን መሸጥ 'ንብረት' ነው የሚባለው፣ ንብረት መሸጥ። አላማው የኤርትራን ሰራዊት እናፍርሰው የሚል ነበር በኛ በኩል። የኤርትራን ሰራዊት ማፍረስ ዘመቻን እመራለሁ የሚለው ወገን ግን ገንዘብ ያላቸውን ሰዎች ብቻ ነው [የሚያተርፈው]። ስለዚህ የደሃ ልጅ ወጥሮ ሊዋጋ ይገደዳል ማለት ነው። ኤርትራዊ ከያዝክ በኋላ 27 ወጣት አንድ ቤት ትዘጋና ቤተሰቦች አሏቸው የሚባሉትን ሰዎች ውጭ ሃገር አካውንት እየተጠየቀ እያንዳንዱ ሰው በትንሹ 4 ሺ ዶላር እንዲያስገባ እየተጠየቁ፣ 20 ሰው ካፈንክ 80 ሺህ ዶላር ታስገባለህ ማለት ነው። በዚህ የውጭ አካውንት ከፍተው በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እየሸጡ እያገቱ አሁን በኤርትራውያን የተጀመረው ወደ ትግራዋይ ዞሯል። ይህንን አመራር የሚሰጡ ከፍተኛ (የሕወሓት) አመራሮች አሉ"
ጌታቸው ረዳ ዛሬ ከሰጠው ቃለምልልስ ላይ የተወሰደ

ትዝ አለኝ 🤭 ተመችቶኛል ስንቶቻችን ተደብቀን  #ማማን  #ሾላን የጨረስናት 😂
08/05/2025

ትዝ አለኝ 🤭 ተመችቶኛል ስንቶቻችን ተደብቀን #ማማን #ሾላን የጨረስናት 😂

05/05/2025

አርበኞች ይንገሱ

02/05/2025

follow to thes man

አል ሀበሺት 🤩😍🥰😘
01/05/2025

አል ሀበሺት 🤩😍🥰😘

01/05/2025

ኢትዮጵያ ዝቅተኛ ደመወዝ እና ከፍተኛ የስራ ግብር የሚከፈልባት ሀገር ናት- ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ
::::::::::::::::::::::::::::

በኢትዮጵያ 50ኛው ዓለም አቀፍ የላብ አደሮች ቀን በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። የላብ አደሮች ቀን እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1888 ጀምሮ በፈረንጆቹ ግንቦት 1 ወይም ሚያዚያ 23 መከበረ እንደጀመረ ይነገራል።

የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበር ኮንፌዴሬሽን (ኢሰመኮ) ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ኢትዮጵያ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ዝቅተኛ ደመወዝ እና ከፍተኛ ግብር የሚከፈልባት ሀገር ናት ያሉ ሲሆን በሀገሪቷ እየጨመረ በመጣው የኑሮ ውድነት የሰራተኞችን የኑሮ ደረጃን እየፈተነ ይገኛል ብለዋል።

መንግስት ሰራተኞች እየተከፈላቸው ባለው ዝቅተኛ ደመወዝ ኑሮአቸውን መምራት ባለመቻላቸው ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ሊደነግግ እንደሚገባ ፕሬዝዳንቱ አሳስበዋል።ሀገሪቷ ያለችበትን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባትም ፍትሀዊ የታክስ አከፋፈል ሊኖር እንደሚገባም አፅንኦት ሰጥተዋል።

መንግስት እንደ ሀገር ያለውን የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ዝቅተኛ ገቢ ላለው የማህበረሰብ ክፍል እና ሰራተኞች ድጎማ እያደረገ ይገኛል ያሉት የስራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ዳንኤል ተሬሳ ናቸው።

የኢትዮጵያ እና ኢጋድ የአሠሪዎች ኮንፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ዳዊት ሞገስ በኢትዮጵያ የሰራተኞችን መብት የሚያስከበር ህገ መንግስታዊ ህግ ቢኖርም በተፈፃሚነቱ ዙሪያ ግን ክፍቶች ይስተዋላሉ ብለዋል።

መንግስት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች አሰቸኳይ ምላሽ ይስጠን! በሚል መሪ ሀሳብ ነው የዘንድሮ የላብ አደሮች ቀን እየተከረ የሚገኘው።

በእለቱ የሚሰራ ሰው በድህነት መኖር የለበትም! ከደመወዝ የሚቆረጠው የገቢ ግብር ምጣኔ ይቀነስልን! ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወሰን እንጠይቃለን! እና ሌሎች መልዕክቶች ተንፀባርቀዋል።

በአውሮፓውያኑ 2023 የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው 3.62 ቢሊየን ላብ አደሮች በአለምአቀፍ ደረጃ ይገኛሉ። ሜይ ደይ ኢትዮጵያ ጨምሮ በ60 ሀገራት በዛሬው እለት እንደሚከበር መረጃዎች ያመለክታሉ።

ሜይ ደይ ወይም ሌበር ደይ የሰራተኞች ስራ ሰአታት በቀን ወደ 8 ሰአት እንዲቀንስ፣ ሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር እንዲሁም አንፃራዊ የክፍያ መጠናቸው እንዲሻሻል የላቀ ሚናን የተጫወተ እለት ነው።

የዘንድሮ የላብ አደሮች ቀን ዓለም 136ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ50ኛ ጊዜ ይከበራል።

በ-ሀሴት ኃይሉ

"በትግራይ ጦርነት ወቅት ለተፈፀመው ወንጀልለ ፍትህ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ይሁንና በአገር ውስጥ ይህንን ፍትህ ማግኘት አይቻልም፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ዓለም አቀፋዊ እንደመሆኑ አጥፊዎች እንዲ...
27/04/2025

"በትግራይ ጦርነት ወቅት ለተፈፀመው ወንጀልለ ፍትህ ማግኘት ያስፈልጋል፡፡ ይሁንና በአገር ውስጥ ይህንን ፍትህ ማግኘት አይቻልም፡፡ የተፈፀመው ወንጀል ዓለም አቀፋዊ እንደመሆኑ አጥፊዎች እንዲቀጡና ተጎጂዎች ፍትህ እንዲያገኙ ጉዳዩ በዓለም አቀፍ ደረጃ መዳኘት አለበት። ይህ ካልሆነ ዘላቂ ሰላም ይመጣል የሚል እምነት የለኝም።"
ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለዲደብሊው ከሰጡት ቃለምልልስ የተወሰደ
💎⬇️⬇️⬇️
Classic Ethiopia

24/04/2025

ጅቡቲ"፤ የመኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን በተቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት ለቀው የማይወጡ ከሆነ፥ ወደ ካምፕ ማስገባት እጀምራለሁ ስትል አስጠነቀቀች።

Address

Mizan
Addis Ababa
5140

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Classic Ethiopia posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share