Ki'na Galatta Media House

Ki'na Galatta Media House News sources such as sports and other information or real events, thank you and follow this page. let me give you , what is new today.

   🇺🇸ፒኤስጂ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል ! በክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ፒኤስጂ ከኢንተር ሚያሚ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግብ ጇ...
29/06/2025

🇺🇸
ፒኤስጂ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

በክለቦች አለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ፒኤስጂ ከኢንተር ሚያሚ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 4ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የፒኤስጂን የማሸነፊያ ግብ ጇ ኔቬዝ 2x ፣ አሽራፍ ሀኪሚ እና አቪሌስ በራሱ መረብ ላይ አስቆጥረዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ፒኤስጂ ሩብ ፍፃሜውን ሲቀላቀል ኢንተር ሚያሚ ከውድድሩ ተሰናብተዋል።

ፒኤስጂ በሩብ ፍፃሜው የባየር ሙኒክ እና ፍላሚንጎን አሸናፊ የሚገጥሙ ይሆናል።

  🇺🇸በመጀመሪያው አጋማሽ ኢንተር ሚያሚ በተጋጣሚው ፒኤስጂ የሜዳ ክልል ማድረግ የቻለው ቅብብል 25 ነው። ፒኤስጂ በአንፃሩ 257 ኮሶችን በተጋጣሚያቸው የሜዳ ክልል መቀባበል ችለዋል። ፒኤስ...
29/06/2025

🇺🇸

በመጀመሪያው አጋማሽ ኢንተር ሚያሚ በተጋጣሚው ፒኤስጂ የሜዳ ክልል ማድረግ የቻለው ቅብብል 25 ነው።

ፒኤስጂ በአንፃሩ 257 ኮሶችን በተጋጣሚያቸው የሜዳ ክልል መቀባበል ችለዋል።

ፒኤስጂ በመጀመሪያው አጋማሽ ያስቆጥረው ግብ ኢንተር ሚያሚ በሶስተኛ የሜዳ ክፍል ካደረጉት ቅብብል ( 3 ) የበለጠ ነው።

ኢንተር ሚያሚ በጨዋታው ከዚህም የከፋ ውጤት ይዘው ላለመውጣት በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ማድረግ ያስፈልጋቸዋል።

እረፍት ፒኤስጂ 4 - 0 ኢንተር ሚያሚ⚽⚽ ጇ ኔቬዝ⚽ አቪሌስ ( በራስ ላይ )⚽ ሀኪሚ
29/06/2025

እረፍት

ፒኤስጂ 4 - 0 ኢንተር ሚያሚ

⚽⚽ ጇ ኔቬዝ
⚽ አቪሌስ ( በራስ ላይ )
⚽ ሀኪሚ

ቶማስ ፓርቴይ ከአርሰናል ጋር ይለያያል ! የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከጋናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴይ ጋር ለመለያየት መወሰናቸው ተገልጿል። ቶማስ ፓርቴ ነገ ከአርሰናል ጋር ...
29/06/2025

ቶማስ ፓርቴይ ከአርሰናል ጋር ይለያያል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከጋናዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴይ ጋር ለመለያየት መወሰናቸው ተገልጿል።

ቶማስ ፓርቴ ነገ ከአርሰናል ጋር ያለው ኮንትራት ሲጠናቀቅ በነፃ ዝውውር ክለቡን እንደሚለቅ ተረጋግጧል።

አርሰናል ለወራት የቶማስ ፓርቴን ኮንትራት ለማራዘም ቢነጋገሩም ሊሳካ ባለመቻሉ ለመለያየት መወሰናቸው ተዘግቧል።

የ 32ዓመቱ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ቶማስ ፓርቴይ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ስለ ቀጣይ ማረፍያው እንደሚወስን ተነግሯል።

🕊 " ለችግሮቻችን መፍትሄ ከጠመንጃ ይልቅ የጠረጴዛ ውይይት እናስቀድም "  - የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር ➡️ " በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልውና አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራ...
29/06/2025

🕊

" ለችግሮቻችን መፍትሄ ከጠመንጃ ይልቅ የጠረጴዛ ውይይት እናስቀድም " - የሰላም ሚኒስቴር ሚንስትር

➡️ " በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልውና አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " - የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር

በአዲስ አበባ ከተማ " ሰላም ፣ ዲሞክራሲ እና ልማት በትግራይ እድሎችና ፈተናዎች " በሚል ርእስ የውይይት መድረክ ተካሂዶ ነበር።

የውይይት መድረኩ CENTRE FOR RESPONSIBLE AND PEACEFUL POLITICS (CRPP) የተባለ ተቋም ከአዲስ አበባ ዪኒሸርስቲ በመተባበር ነው ያዘጋጁት።

የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር አቶ መሐመድ እድሪስ " ከመነጋገር እናተርፋለን " ብለዋል።

" ሃሳብ ነው ሃገርን የሚገነባው ስለሆነም ለሃሳብ ክብርና ልዕልና እንስጥ ፤ ጠመንጃንና ጦርነትን እንጠየፍ የትግራይ የፓለቲካ ምህዳር ለወጣቶች እድልና ቅድሚያ ይስጥ " ሲሉ ተናግረዋል።

" ' አንዋጋም ይበቃል ' ማለት ታላቅ ድፍረት ይጠይቃል ከተቻለ ግን ውጤቱ እጅግ አመርቂና ፍሬውም ጣፋጭ ነው። ስለሆነም እርስ በርስ መዋጋት ይብቃ ፤ ሳንገዳደል አሸናፊ የምንሆንበት ሰላማዊ መንገድ እናስቀድም የመገዳደል የመተላለቅ ታሪክ ልንዘጋው ይገባል " ሲሉ ተደምጠዋል።

የጠቅላይ ሚንስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፥ " የትግራይ ህዝብ አሁንም ከህልውና አደጋ አልወጣም " ብለዋል።

" ችግሮቻችን በውጭ ምክንያቶች እያሳሰበን ከመኖር ውስጣችን በደምብ በመፈተሽ የተወሳሰቡ ችግሮቻችን መፍታት እንችላለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" ትግራይ ጥቂት አመራሮች ማረምና ማንሳት አቅተዋት በከባድ ፈተና ተዘፍቃ ትገኛለች ፤ ይህንን ከባድ ፈተና ለመወጣትና ለማለፍ ወጣቶችን ወደ መሪነት ማምጣት ይጠበቅበታል " ብለዋል።

" በአሁኑ ሰዓት ትልቅ የህልው አደጋ ለተጋረጠበት የትግራይ ህዝብ ስለ ዴሞክራሲና ልማት ማውራት ቅንጦት ነው " በማለት አክለዋል።

ለአንድ ቀን በተካሄደው የውይይት መድረክ " ሰላምና ደህንነት ፣ ዲሞክራሲ ግንባታ ፈተና እና እድል " የሚሉና ሌሎች የመወያያ ፅሁፎች ቀርበዋል።

በመድረኩ ከትግራይ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ፣ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ ስቪክ ማህበራት እንዲሁም በአዲስ አበባ የሚኖሩ ታዋቂ ሙሁራንን ፓለቲከኞች ተገኝተው ነበር።

ሜሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀድሞ ክለቡ ይጫወታል ! አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒው ሆኖ የሚገጥም ይሆናል። በእግርኳስ ህይወቱ ለሶ...
29/06/2025

ሜሲ ለመጀመሪያ ጊዜ ከቀድሞ ክለቡ ይጫወታል !

አርጀንቲናዊው ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ በእግርኳስ ህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የቀድሞ ክለቡን በተቃራኒው ሆኖ የሚገጥም ይሆናል።

በእግርኳስ ህይወቱ ለሶስት ክለቦች የተጫወተው ሊዮኔል ሜሲ በፒኤስጂ በነበረው ቆይታ ባርሴሎናን በተቃራኒው አልገጠመም።

ፔኤስጂ ታሪክ በማይዘነጋው የሻምፒየንስ ሊግ ምሽት በባርሴሎና ውጤት ሲቀለበስበት የነበረውን የተወሰነ ስብስብ ዛሬ በተቃራኒው ይገጥማል።

ሊዮኔል ሜሲ ፣ ሉዊስ ሱዋሬዝ ፣ ሰርጂዮ ቡስኬት ፣ አሰልጣኙ ዣቪየር ማሼራኖ እና ጆርዲ አልባ በውጤት ቀልባሹ የባርሴሎና ስብስብ ነበሩ።

   ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዙር የፈተና መርሐግብርበወረቀት እና በኦንላይን ...
29/06/2025



ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዙር የፈተና መርሐግብር

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

🍁😎 Mourinho on Messi's goal against Porto I:Mourinho 🗣️ : "Messi scoring a goal? Nothing new. Just a 37-year-old dribbli...
29/06/2025

🍁😎 Mourinho on Messi's goal against Porto I:

Mourinho 🗣️ : "Messi scoring a goal? Nothing new. Just a 37-year-old dribbling like he's 7, and tearing down Porto's defence like a training block. At this level, Messi doesn't even need a team. Give him the ball, and let history do the rest."

"Porto tried to close the space? Yes..But they forgot to close the time too, because Messi plays in another dimension. This guy is not a player..He is a superhuman football application that renews itself every game."

የጨዋታ አሰላለፍ !1:00 ፒኤስጂ ከ ኢንተር ሚያሚ
29/06/2025

የጨዋታ አሰላለፍ !

1:00 ፒኤስጂ ከ ኢንተር ሚያሚ

የምሽቱ ጨዋታ የአየር ንብረት ስጋት አለበት ? ፒኤስጂ እና ኢንተር ሚያሚ ከሰዓታት በኋላ የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን በአትላንታ ማርቼዲስ-ቤንዝ ስታዲየም ያደርጋሉ። በውድድሩ እየተካሄዱ የሚገኙ ...
29/06/2025

የምሽቱ ጨዋታ የአየር ንብረት ስጋት አለበት ?

ፒኤስጂ እና ኢንተር ሚያሚ ከሰዓታት በኋላ የጥሎ ማለፍ ጨዋታቸውን በአትላንታ ማርቼዲስ-ቤንዝ ስታዲየም ያደርጋሉ።

በውድድሩ እየተካሄዱ የሚገኙ ጨዋታዎች በአስቸጋሪ የአየር ንብረት ምክንያት እየተቋረጡ ቢሆንም በዚህ ጨዋታ ይህ አይነት ስጋት እንደሌለ ተገልጿል።

70,000 ተመልካቾች የመያዝ አቅም ያለው ማርቼዲስ-ቤንዝ ስታዲየም የሚዘጋ ጣራ ያለው ሲሆን በውስጡ የአየር መቆጣጠሪያም እንደተገጠመለት ተነግሯል።

ይህንንም ተከትሎ ለጨዋታ መቋረጥ መንስኤ የሆኑት ከፍተኛ ሙቀት እና አስጊ ዝናባማ የአየር ንብረቶች በስታዲየሙ ያን ያህል ስጋት እንደማይሆኑ ተገልጿል።

ስታዲየሙ በቀጣይ አመቱ የአለም ዋንጫ ውድድር አንድ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታን ጨምሮ ስምንት ጨዋታዎች እንዲያስተናግድ ተመርጧል።

“ ሜሲን ለማቆም ከአንድ በላይ ተጨዋች ያስፈልገናል “ ሉዊስ ኤንሪኬ የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ቡድናቸው ዛሬ ሊዮኔል ሜሲን ለማቆም በጋራ መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል። “ ዛ...
29/06/2025

“ ሜሲን ለማቆም ከአንድ በላይ ተጨዋች ያስፈልገናል “ ሉዊስ ኤንሪኬ

የፒኤስጂው ዋና አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ቡድናቸው ዛሬ ሊዮኔል ሜሲን ለማቆም በጋራ መከላከል እንዳለበት አሳስበዋል።

“ ዛሬ ምን አይነት ጨዋታ እንደሚጠብቀን ማወቅ ያስቸግራል ነገርግን ለጨዋታው ዝግጁ ነን ማለት እችላለሁ “ ሲሉ ኤንሪኬ ገልጸዋል።

“ ሊዮኔል ሜሲን ለማቆም ከአንድ በላይ ተጨዋች ያስፈልገናል ካልሆነ እንሰቃያለን “ ያሉት አሰልጣኙ በጋራ ሆነን መከላከል ይኖርብናል ምክንያቱም እሱ የትኛውንም ተጨዋች አታሎ ማለፍ ይችላል ብለዋል።

አክለውም “ የተዘጋጀን መሆን አለብን ምክንያቱም ትክክለኛው ውድድር ዛሬ ነው የሚጀምረው “ ሲሉ ተናግረዋል።

“ የቦሎን ዶር ዋንጫን ዴምቤሌ ማሸነፍ አለበት ዴምቤሌ ቡድኑ አራት ዋንጫ ሲያሸንፍ ለረዳበት መንገድ እና ከሜዳና ከሜዳ ውጪ ላሳየው መሪነት ሽልማቱ ይገባዋል።"ኤንሪኬ

ካልቨርት ሌዊን ከኤቨርተን ጋር ተለያየ ! እንግሊዛዊው የፊት መስመር አጥቂ ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊን ኮንትራቱ መጠናቀቁን ተከትሎ ከኤቨርተን ጋር መለያየቱን በይፋ አስታውቋል። ዶምኒክ ካልቨርት...
29/06/2025

ካልቨርት ሌዊን ከኤቨርተን ጋር ተለያየ !

እንግሊዛዊው የፊት መስመር አጥቂ ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊን ኮንትራቱ መጠናቀቁን ተከትሎ ከኤቨርተን ጋር መለያየቱን በይፋ አስታውቋል።

ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊን ከዘጠኝ አመታት በኋላ ኤቨርተንን በነፃ ዝውውር የሚለቅ ይሆናል።

" ኤቨርተን ለአመታት ቤቴ ነበር ጥሩ ተጨዋች እና ግለሰብ እንድሆን ረድቶኛል አመሰግናለሁ " ሲል ተጨዋቹ በስንብት መልዕክቱ ተናግሯል።

የ 28ዓመቱ አጥቂ ዶምኒክ ካልቨርት ሌዊን በተጠናቀቀው የውድድር አመት በተደጋጋሚ ጉዳቶች ለቡድኑ በቂ ግልጋሎት መስጠት አልቻለም።

ተጨዋቹ በኤቨርተን የዘጠኝ አመታት ቆይታው 274 ጨዋታዎች ሲያደርግ 71 ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ki'na Galatta Media House posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share