Awde news

Awde news Awde news በኢትዮጵያ የፓለቲካ፣የኢኮኖሚና በዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሚዲያ ነው
ገፃችንን ፎሎው በማድረግ ወቅታዊ ጉዳዮችንን ይከታተሉ

🚨 ታላቅ የምስራች! 🚨  #ዜና  #መረጃ ​ሰላም የተከበራችሁ የአውደ ኒውስ ቤተሰቦች!​በእናንተ ታማኝ ድጋፍና እገዛ አውደ ኒውስ በፌስቡክ ገጻችን ከ19,000 በላይ ተከታዮችን፣ በግሩፓችን ...
17/08/2026

🚨 ታላቅ የምስራች! 🚨 #ዜና #መረጃ
​ሰላም የተከበራችሁ የአውደ ኒውስ ቤተሰቦች!
​በእናንተ ታማኝ ድጋፍና እገዛ አውደ ኒውስ በፌስቡክ ገጻችን ከ19,000 በላይ ተከታዮችን፣ በግሩፓችን ደግሞ ከ81,000 በላይ አባላትን ማፍራት ችሏል። ለዚህ ትልቅ ፍቅርና አብሮነታችሁ ከልብ እናመሰግናለን! 🙏✨
​አሁን ደግሞ ይበልጥ ተቀራርበን፣ ፈጣን፣ ጥራት ያላቸውና ታማኝ ወቅታዊ መረጃዎችን በቪዲዮ ወደ እናንተ ለማድረስ አዲስ የዩቲዩብ (YouTube) ቻናል ልንጀምር አቅደናል።
​ይህ ጉዞ ያለ እናንተ ድጋፍ አይሳካም። ስለዚህ፡
​1️⃣ በዚህ እቅዳችን ላይ ያላችሁ አስተያየት ምንድን ነው?
2️⃣ ቻናሉ ሲከፈት ሰብስክራይብ በማድረግና በመከታተል አብራችሁን ለመቀጠል ዝግጁ ናችሁ?
​እባካችሁ ሀሳባችሁን በኮሜንት (Comment) አጋሩን! የእናንተ እያንዳንዱ ኮሜንት ለእኛ ትልቅ ብርታትና መንገድ መሪ ነው።
​አውደ ኒውስ — የእውነተኛና ታማኝ መረጃ ምንጭህ!

የባሕርዳር ስታዲየም እገዳ ተነሳ‼📌 ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግድ ተፈቀደ!የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የተጣሉበትን መስፈርቶች ሙሉ በሙ...
15/08/2026

የባሕርዳር ስታዲየም እገዳ ተነሳ‼

📌 ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግድ ተፈቀደ!

የባሕርዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የተጣሉበትን መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ በማሟላቱ፣ ዓለም አቀፍ ጨዋታዎችን የማስተናገድ ሙሉ ፈቃድ አገኘ።

የተከናወኑ ዋና ዋና ነጥቦች፦
📌 መስፈርቶችን ባለማሟላቱ ምክንያት ለረጅም ጊዜ ተጥሎበት የነበረው እገዳ በካፍ በኩል ተነስቷል።

📌 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሜዳውና በደጋፊው ፊት መጫወት ባለመቻሉ በሰው ሀገር ጨዋታዎቹን ለማካሄድ ተገዶ የነበረው እንግልት አብቅቶለታል።

📌 ባለፉት ዓመታት የስታዲየሙን ደረጃ ለማሻሻልና የካፍን መስፈርት ለማሟላት ሲካሄድ የቆየው የላቀ የግንባታ ሥራ ውጤት አፍርቷል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ደጋፊዎች በገዛ ሀገራቸው ብሔራዊ ቡድናቸውን የምናይበት ጊዜ በመመለሱ እንኳን ደስ አላችሁ! ⚽️🇪🇹
የመረጃ ምንጭ-wasu mohammed
#ዜና #መረጃ
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ

ለሠላም ተስፋ ሰጭ መረጃ‼የፌዴራል መንግስት እና ህወሓት በናይሮቢ ሊወያዩ ነው ተባለ‼የፌዴራል መንግስት እና የህወሓት አመራሮች በሚቀጥለው ሳምንት በኬንያ ናይሮቢ ለዳግም ውይይት ቀጠሮ መያዛ...
15/08/2026

ለሠላም ተስፋ ሰጭ መረጃ‼

የፌዴራል መንግስት እና ህወሓት በናይሮቢ ሊወያዩ ነው ተባለ‼

የፌዴራል መንግስት እና የህወሓት አመራሮች በሚቀጥለው ሳምንት በኬንያ ናይሮቢ ለዳግም ውይይት ቀጠሮ መያዛቸው ተሰምቷል።

📌 በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ትግራይ አነፃራዊ ሰላም ሰፍኖ የቆየ ቢሆንም፣ በዶ/ር ደብረጽዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ ስምምነቱን በመጣስ ዳግም የጦርነት እንቅስቃሴ በመጀመሩ እና የትግራይ ህዝብ "ጦርነት ይበቃናል" ጥሪ በማቅረቡ ነው።

📌 ሂደቱን ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ዊሊያም ሩቶ፣ እና ኡሁሩ ኬንያታ ይመሩታል ተብሏል።

📌ከሰሞኑ በሶማሊያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ "ከሕወሓት ጋር ምንም ዓይነት ድርድር ሊደረግ አይገባም" በማለት መግለፃቸው የድርድር መንገድ መጀመሩን ጠቋሚ ነው በሚል ብዙዎች ሲገልፁ ነበር።
👉በየትኛውም መንገድ ይሁን ብቻ ጦርነትን የሚያስቀር ነገር ይፍጠርልን‼ሠላም ለሀገራችን ሠላም ለህዝባችን‼

የመረጃ ምንጭ-wasu mohammed
#ዜና #መረጃ
👇Like + Follow
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ

በአንቀጽ 39 ላይ ከስምምነት ተደረሰ‼የብሔራዊ ምክክር፡ የተደረሱ ስምምነቶች እና ያልተቋጩ 3 ነጥቦችበ«መንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ» አጀንዳ ከተነሱ 53 ጉዳዮች ውስጥ በ50ው ላይ ስምምነት...
12/08/2026

በአንቀጽ 39 ላይ ከስምምነት ተደረሰ‼

የብሔራዊ ምክክር፡ የተደረሱ ስምምነቶች እና ያልተቋጩ 3 ነጥቦች

በ«መንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ» አጀንዳ ከተነሱ 53 ጉዳዮች ውስጥ በ50ው ላይ ስምምነት የተደረሰ ሲሆን፣ 3 አከራካሪ ነጥቦች ግን ለአስማሚ ኮሚቴ እና ለድምፅ ውሳኔ አልፈዋል።

✅ ለድምፅ የቀረቡ 3 አከራካሪ ጉዳዮች፡

📌 የመንግሥት አወቃቀር፡ «ፕሬዚዳንቱ ከፓርላማ ተመርጦ የጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሥራ ይሥራ» ወይስ «ፕሬዚዳንቱ ቀጥታ ከሕዝብ ይመርጥ»?

📌 የፌዴሬሽን ም/ቤት ውክልና፡ «በሕዝብ ቁጥር ታስቦ ይቀጥል» ወይስ «ሁሉም ብሔረሰቦች እኩል ውክልና ይኑራቸው»?

📌 የተወካዮች አመራረጥ፡ «በክልል ም/ቤቶች ይላኩ» ወይስ «ሕዝቡ ራሱ በቀጥታ ይምረጥ»?
(እነዚህ 75% ወይም 70% ድምፅ ካገኙ ይፀድቃሉ።)

✅ ስምምነት የተደረሰባቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡

📌 ፌዴራሊዝም፡ ህብረ-ብሔራዊ ፌዴራሊዝም እንዲቀጥል፣

📌 አንቀጽ 39፡ «እስከ መገንጠል» እና «ያለገደብ» የሚሉት ድንጋጌዎች እንዲሰረዙ፣

📌 ያልተጠቀሱ ሥልጣኖች፡ በሕገ-መንግሥቱ ያልተጠቀሱ አዳዲስ ጉዳዮች ለክልሎች እንዲሰጡ፣

📌 ሕገ-መንግሥት ትርጓሜ፡ ተርጓሚ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም፤ ሆኖም ስሱ ውሳኔዎች በይግባኝ በፌዴሬሽን ም/ቤት እንዲታረሙ ተስማምተዋል።
የመረጃ ምንጭ-wasu mohammed
#ዜና #መረጃ #ወቅታዊ
👇Like + Follow👇
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ

በብሉ ናይል ግዛት ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ አዲስ ውጊያ መቀስቀሱ ተሰማ‼​📌 ከአንድ ወር በፊት የሱዳን መደበኛ ጦር ስትራቴጂካዊቷን የኩርሙክ ከተማን መቆጣጠሩ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ጦሩ ከ...
11/08/2026

በብሉ ናይል ግዛት ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ አዲስ ውጊያ መቀስቀሱ ተሰማ‼

​📌 ከአንድ ወር በፊት የሱዳን መደበኛ ጦር ስትራቴጂካዊቷን የኩርሙክ ከተማን መቆጣጠሩ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ ጦሩ ከተማዋን ሲቆጣጠር የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ (RSF) ታጣቂዎች ወደኋላ አፈግፍገው ነበር፡፡

​📌 ሆኖም ዛሬ በወጣ መረጃ፤ በሸረሪናው ውጊያ ተሳትፏል በሚል የተወነጀለው የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ በሱዳን ጦር ላይ አዲስ የመልሶ ማጥቃት ከፍቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ከባድ ውጊያ እየተደረገ ይገኛል፡፡

📌 በተጨማሪም በዚህ ቀጠና የሕወሓት የጦር አሃዶች ከአልቡርሃን (የሱዳን ጦር) ጎን ሆነው እንደሚዋጉ ጠቅሶ አንድአፍታ አጋርቷል።
የመረጃ ምንጭ-wasu mohammed
#ዜና #ወቅታዊ #መረጃ
👇Like + Follow👇
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የፌስቡክ ገፃችንን ፎሎው በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ

ብዙዎቻችሁ የራሳችሁን ዩቱብ ቻናል ከፍታችሁ ገንዘብ መስራት በዶላር መከፈል ትፈልጋላችሁ።ነገር ግን እንዴት አድርጋችሁ ትክክለኛ ገንዘብ የሚሰራ የዩቱብ ቻናል እንደምትከፍቱ ካላወቃችሁ ወይም ...
11/08/2026

ብዙዎቻችሁ የራሳችሁን ዩቱብ ቻናል ከፍታችሁ ገንዘብ መስራት በዶላር መከፈል ትፈልጋላችሁ።ነገር ግን እንዴት አድርጋችሁ ትክክለኛ ገንዘብ የሚሰራ የዩቱብ ቻናል እንደምትከፍቱ ካላወቃችሁ ወይም ከዚህ በፊት ከፍታችሁ ግን ገንዘብ መስራት ለከበዳችሁ ይሄ ቪዲዮ መጣም ጠቃሚነው። በዚህ ቪዲዮ ከዜሮ ጀምራችሁ ለYouTube Automation የሚሆን ፕሮፌሽናል YouTube Channel እንዴት ንደምትከፍቱ ከመጀመሪያው Google Account / Gmail አካውንት አከፋፈት ጀምሮ ያንን account ተጠቅማችሁ YouTube Channel እስከመፍጠር እና የመጀመሪያዎቹን አስፈላጊውን የChannel Setup ታገኛላችሁ። የዩቱብ ቻናሉ ስም Habtrek ይባላል ዩቱብ ላይ ሰርች በማድረግ ታገኙታላችሁ ወይም ሙሉ የቪዲዮውን ሊንክ ከታች የኮሜንት መጻፊያው ላይ ታገኙታላችሁ። እመኑኝ ትጠቀማላችሁ ገብታችሁ እዩት

በራያ አላማጣ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ‼በራያ አላማጣ መረዋ በተባለ ት/ቤት ዛሬ ነሐሴ 4 ቀን ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል።📌 የህውሃት ታጣቂዎች ትናንት ምሽት ለየክፍላቸ...
10/08/2026

በራያ አላማጣ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ‼

በራያ አላማጣ መረዋ በተባለ ት/ቤት ዛሬ ነሐሴ 4 ቀን ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል።

📌 የህውሃት ታጣቂዎች ትናንት ምሽት ለየክፍላቸው የጦር መሳሪያ ክፍፍል አድርገው ዛሬ ከመረዋ ት/ቤት ጭነው ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ጥቃቱ መፈፀሙ ተነግሯል።

በታጣቂዎቹ ላይ ጉዳት መድረሱ እና ወደ አላማጣ ሆስፒታል ተሽከርካሪዎች ሲመላለሱ ነበር ተብሏል።በአካባቢው ከፍተኛ የጦርነት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሚያመለክቱ ተደጋጋሚ መረጃዎች እየወጡነው።ምስሉ AI ነው።
የመረጃ ምንጭ-wasu mohammed
#ዜና #ወቅታዊ #መረጃ
👇Like + Follow👇
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የፌስቡክ ፔጃችንን ፎሎው በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ

09/08/2026

የኢራኑ አያቶላ ሙጅተባ ኻመነኢ ቪዲዮ ወጣ‼

በአሜሪካ እና በእስራኤል ጥምር ኃይሎች በተሰነዘረ ጥቃት ምክንያት ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸውና በሕይወት ስለመኖራቸው አጠራጣሪ መረጃዎች ሲሰራጩ የቆዩት የኢራኑ አያቶላ ሙጅተባ ኻመነኢ በሕይወት እንዳሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ቪዲዮው የተቀረጸበት ትክክለኛ ጊዜ ባይታወቅም፣አልጀዚራ እንዳጋራው አያቶላ ሙጅተባ ኻመነኢ ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት ሳይታይባቸው ከሰዎች ጋር ተከበበው ትምህርት ሲሰጡ ያሳያል።በተጨማሪም እሳቸው ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፈዘሽኪያን ጋር ተገናኝተው ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል።
የመረጃ ምንጭ-wasu mohammed

👇Like + Follow👇
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ የፌስቡክ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ

ኢራን የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤን ለመክፈት ከባድ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠች‼​የኢራን ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት አሜሪካ እገዳዋን ሳታነሳ፣ ጦሯን ሳታወጣ፣ የጦርነት ካሳ ሳትከፍል እና የታገ...
09/08/2026

ኢራን የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤን ለመክፈት ከባድ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠች‼

​የኢራን ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት አሜሪካ እገዳዋን ሳታነሳ፣ ጦሯን ሳታወጣ፣ የጦርነት ካሳ ሳትከፍል እና የታገዱ ሀብቶችን ሳታስለቅቅ የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ እንደማይከፈት አስታወቀ።

​የ60 ቀናት የሽግግር ጊዜ ለማጠናቀቅ አንድ ሳምንት በሰጠበት ወቅት የቀረቡት እነዚህ ጥያቄዎች ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን ወደ ወታደራዊ እርምጃ ሊገፋፉ እንደሚችሉ ተንታኞች ገልጸዋል።

​የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በበኩላቸው ዋነኛው ትኩረት በባህረ ሰላጤው የተዘረጉ ፈንጂዎችን ማጽዳት መሆኑን ጠቁመው፣ ኢራን ለውጥ ካላደረገች ዋሽንግተን ጫናዋን አጠናክራ እንደምትቀጥል አስጠንቅቀዋል።
የመረጃ ምንጭ-wasu mohammed
#ሰበርዜና #መረጃ #ዜና
====================
ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ ገጻችንን ፎሎው በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ

የአከራይ ተከራይ የውል እድሳትን በተመለከተ አጭር መረጃ ተሰጥቷል​የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ/ወረዳዎች እና በአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ቅዳሜ ሙሉ ቀ...
09/08/2026

የአከራይ ተከራይ የውል እድሳትን በተመለከተ አጭር መረጃ ተሰጥቷል

​የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በሁሉም ክፍለ ከተማ/ወረዳዎች እና በአዲስ መሶብ አንድ ማዕከል ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጭምር የውል እድሳት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል ብሏል።
​በእድሳቱ ወቅት የሚያስፈልጉ ሰነዶች (ኦርጅናል እና ኮፒ)፡
📌​የቤት ካርታ
📌​ነባሩ የውል ስምምነት ሰነድ
📌​የኪራይ ክፍያ የኤሌክትሮኒክስ ሰነድ
📌​የአከራይና ተከራይ ዲጂታል ወይም ህጋዊ መታወቂያ (የነዋሪነት፣ የመስሪያ ቤት፣ መንጃ ፈቃድ ወዘተ.)
📌​በወኪል ከሆነ ህጋዊ ውክልና እንደሚያስፈልግ ​የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።እድሳቱ እስከ ነሐሴ 30/2018 ድረሰ ይካሄዳል ተብሏል።
የመረጃ ምንጭ-wasu mohammed
#ዜና #መረጃ
video 👇Like + Follow👇

ወቅታዊ እና የታመኑ መረጃዎች እንዲደርሱዎ ገፃችንን ፎሎው በማድረግ በቀላሉ ይከታተሉ

Address

Addis Ababa
1000

Telephone

+251970790150

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Awde news posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Awde news:

Shortcuts

Share