ቃለ ጽድቅ - Kale Tsidk

ቃለ ጽድቅ - Kale Tsidk Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቃለ ጽድቅ - Kale Tsidk, Media, Addis Ababa.

"ሕይወት የወለደች፥ የሕይወት እናት፤ ፀሐይን የወለደች፥ የብርሃን እናት፤ የእርሷ ሞት ይደንቃል ያስገርማል።"| ሊቁ ቅዱስ ያሬድ| እንኳን አደረሳችሁ።
29/01/2024

"ሕይወት የወለደች፥ የሕይወት እናት፤ ፀሐይን የወለደች፥ የብርሃን እናት፤ የእርሷ ሞት ይደንቃል ያስገርማል።"
| ሊቁ ቅዱስ ያሬድ
| እንኳን አደረሳችሁ።

 #ቅዱሳን"የእግዚአብሔር ቅዱሳን ራሳቸውን በሁሉም መንፈሳዊ ሀብቶች፥ በሁሉም በጎነት፣ በየዋህነት፣ ትህትና፣ መታቀብ፣ ትዕግስት፣ ታላቅ እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር ያበለጸጉ ናቸው።"| የክሮን...
27/01/2024

#ቅዱሳን

"የእግዚአብሔር ቅዱሳን ራሳቸውን በሁሉም መንፈሳዊ ሀብቶች፥ በሁሉም በጎነት፣ በየዋህነት፣ ትህትና፣ መታቀብ፣ ትዕግስት፣ ታላቅ እምነት፣ ተስፋ እና ፍቅር ያበለጸጉ ናቸው።"

| የክሮንስታድት ቅዱስ ዮሐንስ

  •••"ጌታ ሆይ ድግስህን እንዳታሳንሰውቀርቶ አይቀርምና አንተ የጠራኸው ሰው"እንዳለ ዘማሪው፥ ኹላችን የማንቀርበትን ድግስ ጥሪ ወረቀት የተቀበልነው ገና በጊዜ ልደታችን ነው። የጥሪ ወረቀታ...
24/01/2024

•••

"ጌታ ሆይ ድግስህን እንዳታሳንሰው
ቀርቶ አይቀርምና አንተ የጠራኸው ሰው"
እንዳለ ዘማሪው፥ ኹላችን የማንቀርበትን ድግስ ጥሪ ወረቀት የተቀበልነው ገና በጊዜ ልደታችን ነው። የጥሪ ወረቀታችን ላይ የሰፈረው ጊዜ ሲደርስ ሞት በሚሉት ጋሪ ተጭነን ወደማይቀርበት ልንሄድ ግድ ነው። ይሄን ማወቃችንም ነው "ሞቴን አስቀርልኝ" ሳይሆን "አሟሟቴን አሳምርልኝ" ብለን እንድንጸልይ ያደረገን።

ታላቁ ቅዱስ መቃርዮስ ስለ ጊዜ ሞታችን ሲያስተምር እንዲህ አለ፦
"የሰው ነፍስ ከሥጋ ስትወጣ አንድ ታላቅ ምስጢር ይፈጠራል። በኃጢአት የኖረ ሰው ከሆነች ክፉ መላእክትና የጨለማ ኃይሎች መጥተው ያቺን ነፍስ ወስደው ወደ ጎናቸው ይጎትቷታል። ማንም በዚህ ሊደነቅ አይገባም። ምክንያቱም በዚህ ዓለም በሕይወት እያለ እጁን በሰጣቸውና በተማረከላቸው ሰው ላይ ከዚህ ዓለም ሲለይ የበለጠ ሥልጣን ላይኖራቸው ነውን?

በሌላ በኩል ያሉት ሰዎች (በቅድስና የኖሩት፣ ንስሐ የገቡ፣ ከቅዱስ ቁርባን የተካፈሉ፣ ለሰዉ አዛኝ አጉራሽ የነበሩትን ማለቱ ነው) ነገር የተለየ ነው። ቅዱሳን መናፍስት (መላእክት) ይከቧቸዋል፥ ይጠብቋቸዋል። እናም ነፍሳቸው ከሥጋ ስትለይ፥ የመላእክት ዝማሬ ወደ ኅብረታቸው፥ ወደ ብሩህ ሕይወት ይቀበላቸዋል። እናም ወደ ጌታ ይመራቸዋል።"

ይህን ከተረዳን እኛም፥ ከሞት ባሻገር የሚደረግልን አቀባበል እንደ ኹለተኛው ይሆን ዘንድ "ሞቴን አሳምርልኝ" ማለቱ ደግ ነው። ይሄም በቃል ብቻ ሳይሆን ለዚያ እንደሚገባው በመኖር ነው። አምላከ ቅዱሳን የሁላችንን ፍጻሜ መልካም ያድርግልን።

| ጥር ፲፭ ቀን ፳፻፲፮ ዓ•ም

Address

Addis Ababa

Telephone

+251912466156

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቃለ ጽድቅ - Kale Tsidk posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share

Category