Ke alemi zuriya-ከዓለም ዙሪያ

Ke alemi zuriya-ከዓለም ዙሪያ ©Ke alemi zuriya-ከዓለም ዙሪያ: ወቅታዊ፣ሀገራዊ እና አለም አቀፋዊ ዜናዎችና መረጃዎችን ያገኙበታል

በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የተመራ የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቡድን  በደቡብ ሱዳን ጉብኝት አካሄደ። የልዑካን ቡድኑ በደቡብ ሱዳን ያለውን የቴሌኮም መሰረ...
21/12/2022

በኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ የተመራ የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ አመራር ቡድን በደቡብ ሱዳን ጉብኝት አካሄደ። የልዑካን ቡድኑ በደቡብ ሱዳን ያለውን የቴሌኮም መሰረተ ልማት ፍላጎት እንዲሁም በሁለቱ እህትማማች ሀገሮች በትብብር ሊከናወኑ ስለሚችሉ የቴሌኮም መሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች ዙሪያ ከኢንፎርሜሽን፣ ኮሙዩኒኬሽን እና የፖስታ አገልግሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ ከብሄራዊ ኮሙዩኒኬሽን ባለስልጣን እና ከሌሎች የደቡብ ሱዳን ሚኒስትሮች እና ከፍተኛ መሪዎች ጋር ተወያይቷል።

የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ሱዳን ያለውን የቴሌኮም ገበያ ለመቃኘት ያለውን ፍላጎት በማድነቅ ኢትዮ ቴሌኮም በዘርፉ ለሚያደርገው ተሳትፎ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ተቋሙ የ128 ዓመታት አንጋፋ እና ከአፍሪካ ቀዳሚ የቴሌኮም ኦፕሬተር መሆኑን ገልፀው ኩባንያው በኢትዮጵያ የቴሌኮም መሠረተ ልማት ግንባታ እና አስተዳደር እንዲሁ የዋጋ ተመጣጣኝነትን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለውን መልካም ተሞክሮ በማጋራት የደቡብ ሱዳን መንግስት የቴሌኮም አገልግሎት ተደራሽነት እና የዋጋ ተመጣጣኝነትን ለማረጋገጥ በሚያደረገው ጥረት ውስጥ አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ ለመሳተፍ ዝግጁነቱን አረጋግጠዋል።

በጉብኘቱም ወቅት ልዑካን ቡድኑ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሀላፊዎ ጋር በደቡብ ሱዳን ባላቸው የቢዝነስ እንቅስቃሴ እና ተሞክሮ ዙሪያ ውይይት አድርጓል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኢንተርናሽናል ኢንተርኔት መገናኛ መስመር፣ በቴሌኮም መሠረተ ልማት ግንባታ እና የቴሌኮም አገልግሎቶች አቅርቦት እና በሌሎች ተያያዥነት ባላቸው አገልግሎቶች ዙሪያ ከቴሌ ሞባይል ደቡብ ሱዳን ሃላፊነቱ የተወሰነ ኩባንያ ጋር የስትራቴጂክ አጋርነት ስምምነት ተፈራርሟል::

ልኡካን ቡድኑ በነበረው ቆይታ የደቡብ ሱዳን ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች እንዲሁም ከቴሌ ሞባይል ኩባንያ አመራር ለተደረገለት አቀባበል እና መስተንግዶ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

ፎቶ ፦ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በታሪካቸው ለሶስተኛ ጊዜ የFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫን አንስተዋል።አርጀንቲና ከ36 ዓመታት በኃላ ነው ዋንጫውን ማሳካት የቻለችው። የ7 ጊዜ ባላንዶር አ...
18/12/2022

ፎቶ ፦ የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በታሪካቸው ለሶስተኛ ጊዜ የFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫን አንስተዋል።

አርጀንቲና ከ36 ዓመታት በኃላ ነው ዋንጫውን ማሳካት የቻለችው።

የ7 ጊዜ ባላንዶር አሸናፊው ሜሲም በእግር ኳስ ህይወቱ የመጀመሪያውን የዓለም ዋንጫ ማሳካት ችሏል።

የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://facebook.com/KeAlemiZuriya1
ኢንስታግራም: https://instagram.com/Kealemizuriya

18/12/2022

🏆 #አርጀንቲና

አርጀርቲና የFIFA የዓለም ሀገራት ዋንጫን አነሳች።

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን የ2018 ዓለም ዋንጫ አሸናፊዎቹን ፈረንሳይን በመለያ ምት በመርታት ሻምፒዮን ሆነዋል።

ሊዮኔል ሜሲ በእግር ኳስ ህይወቱ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫውን ማሸነፍ ችሏል።
የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya1
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

ሜሲ ኮከብ ተጨዋች ሆኖ ሲሸለም ምባፔ ደግሞ ኮከብ ጎል አግቢ በመሆን ተሸልሟልበኳታር የዓለም ዋንጫ አርጀንቲናና ፈረንሳይ ባደረጉት የፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲና አሸናፊ ሆናለች፡፡ አርጀንቲናና ፈ...
18/12/2022

ሜሲ ኮከብ ተጨዋች ሆኖ ሲሸለም ምባፔ ደግሞ ኮከብ ጎል አግቢ በመሆን ተሸልሟል
በኳታር የዓለም ዋንጫ አርጀንቲናና ፈረንሳይ ባደረጉት የፍጻሜ ጨዋታ አርጀንቲና አሸናፊ ሆናለች፡፡
አርጀንቲናና ፈረንሳይ ያደረጉት ጨዋታ በመደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 2 ለ2 አቻ ሆና በመጠናቀቁ ጨዋታው ወደ ጭማሪ ደቂቃ አምርቶ ነበር፡፡
በጭማሪ ደቂቃው ጨዋታ ሜሲ ባስቆጠራት ግብ አርጀንቲና 3 ለ 2 መምራት ችላ የነበረች ቢሆንም ምባፔ ባስቆጠራት ጎል ጨዋታው በ3 ለ3 አቻ ተጠናቆ ወደ መለያ ምት አምርቷል፡፡
በመለያ ምቱ የአርጀንቲና ግብ ጠባቂ ሁለት ምቶችን በማምከኑ፣አርጀንቲና አሸናፊ ሆናለች፡፡
የአርጀንቲና ግብ ጠባቂ ኮከብ ተብሎ ተሸልሟል፡፡
የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya1
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

አርጀንቲና የኳታሩን የዓለም ዋንጫ አነሳችየፈረንሳይ የአርደንቲና መደኛ ጨዋታ 3 ለ3 አቻ ተጠናቆ ወደ መለያ ምት አምርቷል።በመለያ ምትም አርጀንቲና አሽንፋለች።በአርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮነል ...
18/12/2022

አርጀንቲና የኳታሩን የዓለም ዋንጫ አነሳች

የፈረንሳይ የአርደንቲና መደኛ ጨዋታ 3 ለ3 አቻ ተጠናቆ ወደ መለያ ምት አምርቷል።
በመለያ ምትም አርጀንቲና አሽንፋለች።

በአርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮነል ሜሲ የሚመራው የአርጀንቲና ብሄራዊ ቡድን ሲያሸንፍ አርጀንቲናም ለ3ኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫን አንስታለች።

የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya1
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ ላይ “ከባድ ወታደራዊ እርምጃ እወስዳለሁ” በማለት ዛተችፒዮንግ ያንግ አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን በካምቦዲያ ካደረጉት የሶስትዮሽ ስብሰባ በኋላ የመጀመሪያ መግለጫ አውጥ...
21/11/2022

ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ ላይ “ከባድ ወታደራዊ እርምጃ እወስዳለሁ” በማለት ዛተች
ፒዮንግ ያንግ አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን በካምቦዲያ ካደረጉት የሶስትዮሽ ስብሰባ በኋላ የመጀመሪያ መግለጫ አውጥታለች

የሰሜን ኮሪያ የባላስቲክ ሚሳኤል
ሰሜን ኮሪያ አሜሪካ ላይ ከባድ ወታደራዊ እርምጃ ለመውሰድ በመዛት ቁጣዋን ሚሳኤል በማስወንጨፍ አሳይታለች

ሰሜን ኮሪያ አጭር ርቀት ባለስቲክ ሚሳኤል ማስወንጨፏን ደቡብ ኮሪያ ገልፃለች።

ሚሳኤሉ ወንሳን ከተሰኘችው የሀገሪቱ ምስራቃዊ የባህር ዳርቻ ወደ ባህር እንደተወነጨፈ ነው የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ያስታወቀው።

ፒዮንግያንግ የሚሳኤል ሙከራ ያደረገችው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ቾይ ሰን ሁይ አሜሪካን ያስጠነቀቁበትን መግለጫ ካወጡ ከጥቂት ስአት በኋላ ነው።

ሰሜን ኮሪያ ምን አይነት ሚሳዔሎች አሏት?
“አውሬው” የሚል መጠሪያ የተሰጠው የሰሜን ኮሪያው ህዋሰኦንግ-17 ሚሳዔል
አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ባለፈው ሳምንት በካምቦዲያ ካደረጉት የሶስትዮሽ ስብሰባ በኋላ የመጀመሪያ አቋሟን ያንፀባረቀችው ሰሜን ኮሪያ የዋሽንግተን በቀጠናው እጅ መርዘምን ተቃውማለች።

በካምቦዲያው የሶስትዮሽ ስብሰባ አሜሪካ ሁለቱን አጋሮቿን ከሰሜን ኮሪያ ለመጠበቅ ኒውክሌር እስከማስታጠቅ ቃል ገብታለች።

ሀገራቱ የሚያደርጉት የጦር ልምምድም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን መናገራቸውን ሬውተርስ አስታውሷል።

የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቾይ ሰን ሁይም የሶስትዮሽ ምክክርም ሆነ የጦር ልምምድ የወረራ ዝግጅት ነው ብለውታል።

ይህ የወረራ ዝግጅታቸው ግን ይዞባቸው የሚመጣውን ከባድ ስጋት አይቋቋሙትም ሲሉም ዝተዋል። የኮሪያ ልሳነ ምድርን እያወከች ነው ባለቻት አሜሪካ ላይም ሀገራቸው ከባድ እርምጃ እንደምትወስድ ነው ያስጠነቀቁት።

ደቡብ ኮሪያ በበኩሏ ከጎረቤቷ ሊቃጣ የሚችል ጥቃትን ለመመከት ወታደራዊ ሀይሏ በተጠንቀቅ እንደሚገኝ አስታውቃለች።

ሰሜን ኮሪያ በአንድ ቀን ውስጥ 23 ሚሳዔሎችን ተኮሰች
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ያስወነጨፈችው የሚሳኤል ሙከራ ከስምንት ቀናት በኋላ የተደረገ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አከታትላ የሞከረቻቸው የአጭርና ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሚሳኤሎች በአምስት አመት ውስጥ የኒዩክሌር ጦር መሳሪያዋን መጠቀሟ አይቀሬ መሆኑን ያሳያል የሚሉት አሜሪካና አጋሮቿ በጋራ ወታደራዊ ልምምድ ተጠምደዋል።

የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya1
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

በፔሩ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመኪና ጋር ተጋጨየመንገደኞች አውሮፕላኑ ለመነሳት በማኮብኮብ ላይ እያለ ከእሳት አደጋ መኪና ጋር ተጋጭቷልበፔሩ አውሮፕላንና መኪና ግጭት አደጋአውሮፕላንና መኪና...
19/11/2022

በፔሩ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመኪና ጋር ተጋጨ
የመንገደኞች አውሮፕላኑ ለመነሳት በማኮብኮብ ላይ እያለ ከእሳት አደጋ መኪና ጋር ተጋጭቷል

በፔሩ አውሮፕላንና መኪና ግጭት አደጋ
አውሮፕላንና መኪና ግጭት አደጋው የ2 ሰዎች ህይወት አልፏል

በደቡብ አሜሪካዋ ፔሩ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመኪና ጋር ተጋጭቶ በሰዎች ላይ ጉዳት አደረሰ።

ከፔሩ አውሮፕላን ማረፊያ በመነሳት ላይ የነበረው የመንገደኞች አውሮፕላን ከእሳት አደጋ መኪና ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረወሰው።

በሶማሊያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተገለበጠ
የመንገደኞች አውሮፕላን በታንዛኒያ ቪክቶሪያ ሀይቅ ላይ ተከሰከሰ
ንብረትነቱ የላትም አየር መንገድ የሆነው የመገደኞች አውሮፕላኑ ለመነሳት በማኮብኮብያው ላይ በመጓዝ ላይ እያለ ነው ከመኪናው ጋር ሊጋጭ የቻለው።

በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለቀቁ ቪዲዮዎች አውሮፕላኑ ከመኪናው ጋር ከተጋጨ በኋላ በእሳት ተያይዞ መሬት ላይ ሲንሸራተት ታይቷል።

በአደጋው በእሳት አደጋ መኪና ውስጥ የነበሩ የሁለት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፤ እንደ ሰው ደግሞ በአስጊ ሁኔታ ውስጥ መሆኑ ታውቋል።

በመንገደኞች አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎችም ይሁን የበረራ ሰራተኞች ላይ የከፋ ጉዳት እንዳልደረሰ የላትም አየር መንገድ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

የፔሩ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቁ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ እና መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው 20 ሰዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደው ህክምና እየተከታተሉ ነው።

የእሳት አደጋ መኪናው ምን ሊሰራ ወደ ማኮብኮቢያው ገባ የሚለው ግልጽ የሆነ ነገር የለም ተብሏል።

የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya1
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

ፕሬዝዳንት ባይደን፤ “በቻይና በኩል ታይዋንን ለመውረር ምንም ዓይነት የቅርብ ጊዜ እቅድ ያለ አይመስለኝም” አሉጆ ባይደን፤ ቻይና በታይዋን ላይ የፈጸመችው “አስጨናቂ” እርምጃ ሰላምን አደጋ ...
18/11/2022

ፕሬዝዳንት ባይደን፤ “በቻይና በኩል ታይዋንን ለመውረር ምንም ዓይነት የቅርብ ጊዜ እቅድ ያለ አይመስለኝም” አሉ
ጆ ባይደን፤ ቻይና በታይዋን ላይ የፈጸመችው “አስጨናቂ” እርምጃ ሰላምን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ብለዋል

የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ የታይዋን ጉዳይ ሊጣስ የማይገባው “ቀይ መስመር ነው” ብለዋል

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ በታይዋን ላይ “በቅርቡ ጥቃት ለመሰንዘር አቅደዋል” የሚል እምነት የለኝም አሉ፡፡

ባይደን ይህን ያሉት በዋሽንግተን እና ቤጂንግ መካከል እያሽቆለቆለ የመጣውን ግንኙነት ያድሳል በተባለለትና ከኢንዶኔዢያው የቡድን-20 ጉባኤ ጎን ለጎን በአካል ተገናኝተው ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት በተመለከተ በሰጡት መግለጫ መሆኑን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡

“በቻይና በኩል ታይዋንን ለመውረር ምንም ዓይነት የቅርብ ጊዜ እቅድ ያለ አይመስለኝም” ብለዋል ፕሬዝዳንት ባይደን፡፡

ፕሬዝደንቱ አክለውም "አዲስ የቀዝቃዛ ጦርነት መኖር እንደሌለበት ሙሉ በሙሉ አምናለሁ" ብለዋል፡፡

ባይደን በአካል ስላገኘዋቸውና ለሶስት ሰአታት ያክል ለውይይት አብሮዋቸው ስለተቀመጡት የቻይናው መሪ ዢ ጂንፒንግ ሲናገሩም ዢ ቀደም ብየ (በቀድሞው ፕሬዝዳንት ኦባማ የስልጣን ዘመን ምክትል ፕሬዝዳንት ሳሉ) የማውቀው ሰው አይንት ሆኖ ነው ያገኘሁት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

“በጣም ተከራካሪ ወይም ለዘብተኛ ሆኖ አላገኘሁትም። እሱ ሁልጊዜ እንደነበረው ግልጽ እና ቀጥተኛ ሆኖ ነው ያገኘሁት” ሱሉም ነው ዢን የገለጿቸው፡፡

የቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ በበኩላቸው ፤ ባይደንን በታይዋን ደሴት ጉዳይ የቤጂንግን "ቀይ መስመር" እንዳያለፉ ማስጠንቀቃቸው የመንግስት የዜና ወኪል ሺንዋ ዘግቧል ።

ዢ “የታይዋን ጉዳይ የቻይናን ዋና ፍላጎት እንዲሁም ለቻይና እና የአሜሪካ ግንኙነት ፖለቲካዊ መሰረት እንደመሆኑ በቻይና-አሜሪካ ግንኙነት መጣስ የሌለበት የመጀመሪያው ቀይ መስመር ነው” ሲሉ ተናገረዋል፡፡

የቻይናው መሪ ዢ ይህን ይበሉ እንጅ የአሜሪካው አቻቸው ባይደን ግን ቻይና በታይዋን ላይ የፈጸመችው “አስጨናቂ” እርምጃ ሰላምን አደጋ ላይ እንደሚጥል ለ ዢ ገልጿል።

ጆ-ባይደን የቻይና ድርጊት “በታይዋን የባህር ዳርቻ እና በሰፊው ቀጠና ሰላም እና መረጋጋትን ያበላሻል” ሲሉም አክለዋል፡፡

የዋስንግተን እና የቤጂንግ ግንኙነት በተለይም የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ የታይዋንን ጉብኝት ተከትሎ ሲሰነዘሩ በነበሩ ዛቻዎች እጅግ እየተካረረ መምጣቱ የሚታወቅ ነው፡፡እናም የአሁኑ የመሪዎቹ መገናኘት ታይዋንን ሽፋን በማድረግ ተፈጥሮ የነበረውን ውጥረት ያረግበዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የከዓለም ዙሪያ ቤተሰብ ይሁኑ
ቴሌግራም፡ https://t.me/KeAlemiZuriya
ዩቲዩብ: https://youtube.com/c/Kealemizuriya
ድረገፅ: https://kealemizuriya.data.blog
ትዊተር: https://twitter.com/KeAlemiZuriya
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/KeAlemiZuriya1
ኢንስታግራም: https://www.instagram.com/Kealemizuriya

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ke alemi zuriya-ከዓለም ዙሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Ke alemi zuriya-ከዓለም ዙሪያ:

Share