Ethiopian Independent

Ethiopian Independent "እንፈተናለን፤ መስዋዕትነት እንከፍላለን ነገር ግን ኢትዮጵያን እናፀናለን።

07/10/2026
"ኢትዮጵያ ትላንት አልተደፈረችም ነገም አትደፈርም በክብርና በነፃነት ለትውልድ የምትሻገር ብቸኛዋ የአፍሪካ ፈርጥ ሆና ትቀጥላለች።የእኛ ዝግጅት በድፍን አፍሪካ ሰላምና ብልፅግናን ለማረጋገጥ ...
07/10/2026

"ኢትዮጵያ ትላንት አልተደፈረችም ነገም አትደፈርም በክብርና በነፃነት ለትውልድ የምትሻገር ብቸኛዋ የአፍሪካ ፈርጥ ሆና ትቀጥላለች።የእኛ ዝግጅት በድፍን አፍሪካ ሰላምና ብልፅግናን ለማረጋገጥ በቀጣናችን ላሉ ሀገራት አለኝታ መከታና ጋሻ ለመሆን ነው።"

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ

“የአፍሪካ ቀንድ በተለይም ቀይ ባሕርና የህንድ ውቅያኖስን ተከትለው የሚገኙ ወደቦች በአጭር ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቀናቃኝ የሆኑ የጦርመንደሮችና ካምፖች መናገሻ እየሆኑ ነው። ...
07/10/2026

“የአፍሪካ ቀንድ በተለይም ቀይ ባሕርና የህንድ ውቅያኖስን ተከትለው የሚገኙ ወደቦች በአጭር ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተቀናቃኝ የሆኑ የጦርመንደሮችና ካምፖች መናገሻ እየሆኑ ነው። ቀጣናው ከአሜሪካ፣ ፈረንሳይ፣ ቻይና በተጨማሪ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ፣ የቱርክ፣ የሳውዲ ዐረቢያ የጦርመንደሮችን ያስተናግዳል። በቻይናና በአሜሪካ መካከል ካለው ዓለም አቀፋዊና ቀጣናዊ መፋጠጥ በዘለለ በአዳዲስ ኃይሎች መካከል ያለው ወዳጅና ደጋፊ ለማፍራት የሚደረግ ሩጫ ተበራክቷል። ይህ አዝማሚያ በክፍለ አህጉሩ የሚገኙ ሀገራትን የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ስስ፣ አጭር _ ርቀትና ወደ ዉጭ ተመልካች እንዲሁም በከፍተኛ መልኩ ተለዋዋጭ እያደረገው ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ፉክክሩ በቀጣናው ግጭትን ለማስቆም፣ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣትና ውሕደትን ለማረጋገጥ የሚሠሩ የበይነ መንግሥታዊ ተቋማትንና የሌሎችን እንቅስቃሴዎች ስኬት አደጋ ላይ ጥሏል። ቀጣናውንም ከፍተኛ የጦር እና የደኅንነት ተቋማት ክምችት ከሚገኝባቸው የዓለማችን ክፍሎች አንዱ አድርጎታል።”

ጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ (መደመር 246)

የሀገር ግንባታ ከልማትና ከኢኮኖሚ እድገት ብቻ አይጀምርም።የሁሉም ነገር መሰረት ሰላም ነው።ጠ/ሚ/ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በጫካ የሚገኙ የ...
07/10/2026

የሀገር ግንባታ ከልማትና ከኢኮኖሚ እድገት ብቻ አይጀምርም።የሁሉም ነገር መሰረት ሰላም ነው።
ጠ/ሚ/ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በጫካ የሚገኙ የታጠቁ ሀይሎች ከጦርነት ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ መንገድ እንዲመጡ በተለያየ ምክንያት የተቀየሙ ወገኖች ያለፈውን በይቅርታ መንፈስ በመሻገር በሀገር ግንባታ እንዲሳተፉ እንዲሁም ተፎካካሪ ፓርቲዎች በአማራጭ ሀሳቦች በሰላማዊ መንገድ እንዲፎካከሩ ጥሪ አቅርበዋል።ይህ የሰላም ጥሪ የሀገራችን ችግሮች በጉልበትና በጦርነት ሳይሆን በውይይት በይቅርታ በመቻቻልና በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል እንዲፈቱ የተሰጠውን አቅጣጫ የሚያሳዩ ናቸው።ጠ/ሚ/ዶ/ር ዐቢይ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምን ለሀገር ግንባታ ዋና መሰረት አድርገው እንደሚያዩ ከዚህ መልዕክት መረዳት ይቻላል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን በመሩባቸው ያለፉ ስምንት ዓመታት የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ከማጉላቱ ጋር ተያይዞ የብልጽግና ከፍታ ጉዞ መስፈንጠሪያ የሆነ ኢኮኖሚያዊ መሰረት ተጥሏል...
07/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያን በመሩባቸው ያለፉ ስምንት ዓመታት የሀገሪቱን መልካም ገጽታ ከማጉላቱ ጋር ተያይዞ የብልጽግና ከፍታ ጉዞ መስፈንጠሪያ የሆነ ኢኮኖሚያዊ መሰረት ተጥሏል። በጠ/ሚር ዐቢይ አመራር ዘመን እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ባሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች፣ በግንባታ ሂደት ላይ በሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶች እና በሰፊ ሀገራዊ የአቅም ግንባታ ሥራዎች የኢትዮጵያን ገጽታ ከመቀየር በተጨማሪ ለብልጽግና ከፍታ ጉዞ መስፈንጠሪያ የሆነ የኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሰረት ተጥሏል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በመደመር እሳቤ መሰረት ኢትዮጵያን በቀጣናው ውስጥ ወሳኝና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር የማድረግ ራዕይ ሰንቀው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።ይህ ራዕይ ከንግግር ባለፈ በተግባር መ...
07/10/2026

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በመደመር እሳቤ መሰረት ኢትዮጵያን በቀጣናው ውስጥ ወሳኝና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር የማድረግ ራዕይ ሰንቀው እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።ይህ ራዕይ ከንግግር ባለፈ በተግባር መለወጥ ያለበት እሳቤ ነው። በተለይም የመደመር መንግስት ምስረታ ወቅት የተሰጡት አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን በልማት በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ አቅም እያጠናከሩ በቀጣናው ውስጥ የራሷን ወሳኝ ሚና እንድትወስድ የሚያስችል አቅጣጫ የሚያመላክቱ ነው።ጠ/ሚ/ዶ/ር ዐቢይ ወደ አመራር ከመጡ ወዲህ ባለፉት አመታት የኢትዮጵያን አለም አቀፍ ተሳትፎና ተፅዕኖ ለማሳደግ በተለያዩ ዘርፎች ጥረቶች ተደርገዋል። ሀገሪቱ በኢኮኖሚ እንድትጠናከር በልማት እንድትራመድ በዲፕሎማሲ እንድትበረታና በቀጣናዊ ጉዳዮች የራሷን ሚና እንድትወጣ የተለያዩ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

በጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ በሳል አመራር ባለፉ ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ዘርፎች የተወሰዱ አጠቃላይ የለውጥ እርምጃዎች ኢትዮጵያን ከነበሩባት ዘሁለገብ ፈተናዎች በማውጣት...
07/10/2026

በጠ/ሚር ዐቢይ አህመድ በሳል አመራር ባለፉ ጥቂት ዓመታት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማኅበራዊ ዘርፎች የተወሰዱ አጠቃላይ የለውጥ እርምጃዎች ኢትዮጵያን ከነበሩባት ዘሁለገብ ፈተናዎች በማውጣት ለቀጣይ ዕድገትና ልማት - ለብልጽግና ከፍታ ጉዞ ስኬት ጠንካራ መሠረት ጥለዋል። በጠ/ሚር ዐቢይ አመራር የኢትዮጵየ የብልጽግና ከፍታ ላይ መድረስ ተጨባጭ እውነታ ነው!

የአይበገሬው ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን አሁናዊ አቅምም የሀገራችንን ሰላም ደህንነትና ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ በአህጉራዊ ደረጃ ለሰላምና ለደህንነት ጥበቃ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚያስችለው...
07/10/2026

የአይበገሬው ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን አሁናዊ አቅምም የሀገራችንን ሰላም ደህንነትና ሉአላዊነት ከመጠበቅ ባለፈ በአህጉራዊ ደረጃ ለሰላምና ለደህንነት ጥበቃ አስተዋፅኦ ማበርከት የሚያስችለውን ብቃትና አቅም እያጎለበተ ይገኛል።ይህም የመከላከያ ሰራዊታችን ሚና ከሀገራዊ ደህንነት ጥበቃ ባሻገር ለአፍሪካ የሰላምና የደህንነት ጥረቶች አስተዋፅኦ የማድረግ አቅም እያሳደገ መምጣቱን የሚያሳይ ነው።ከጠ/ሚ/ዶ/ር/ዐቢይ አህመድ ወደ አመራር መምጣት ወዲህ ጀግናው የመከላከያ ሰራዊታችን ከባህላዊ የጦር አደረጃጀት ባሻገር የዘመኑን የደህንነት ፈተናዎች በሚመጥን መልኩ በተለያዩ የሀይልና የቴክኖሎጂ ዘርፎች አቅሙን እያጎለበተ መጥቷል።

ከለውጡ ወዲህ እንደ አዲስ ህብረ ብሄራዊነትን ተላብሶ የተደራጀውና በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተደረገለት ሪፎርም የዘመነው የመከላከያ ሰራዊታችን በዘመናዊ አደረጃጀት በሙያዊ ብቃት በዲሲፕሊ...
07/10/2026

ከለውጡ ወዲህ እንደ አዲስ ህብረ ብሄራዊነትን ተላብሶ የተደራጀውና በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ በተደረገለት ሪፎርም የዘመነው የመከላከያ ሰራዊታችን በዘመናዊ አደረጃጀት በሙያዊ ብቃት በዲሲፕሊንና በስነ ምግባር እየተጠናከረ ይገኛል።ይህ ሪፎርም የመከላከያ ሰራዊቱን ተቋማዊ አቅም ለማጠናከር የሙያ ብቃቱን ለማሳደግና የሀገርን ሉአላዊነትና የግዛት አንድነት በብቃት ለመጠበቅ የሚያስችለውን አቅም ለማዳበር ያለመ ነው።ዛሬ የምንመለከተው መከላከያ ሰራዊታችንም የኢትዮጵያን ብዝሃነትና አንድነት የሚያንፀባርቅ በእውቀትና በሙያ የተጠናከረ በዲሲፕሊንና በስነ ምግባር የተመራና ለሀገርና ለህዝብ ታማኝ የሆነ ሰራዊት ለመገንባት የተደረገውን ጥረት የሚያሳይ ነው።ይህ ሰራዊት በቅርብ አመታት ውስጥ የዘመኑን የደህንነት ሁኔታ በሚመጥን መልኩ በምድር በአየር በባህርና በሳይበር ዘርፎች ተደራጅቶ አቅሙን እያሳደገ ይገኛል።በዚህም ተልዕኮዎችን በውጤታማነት የመምራት የመፈፀምና ለተለያዩ የደህንነት ፈተናዎች በተቀናጀ መልኩ ምላሽ የመስጠት ብቃቱን አሳድጓል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Independent posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share