Mere Media

Mere Media MERE MEDIA
Welcome to Mere Media Channel.

 ።( )
09/08/2025


( )

09/04/2023

በክልል ልዩ ኃይሎች ላይ የተላለፈው ውሳኔ፤ “ዋጋ ተከፍሎም ቢሆን ተግባራዊ ይደረጋል” ጠሚዶክ አብይ አህመድ. what does it mean?

06/04/2023

"ትልቁ ችግራችን በራሳችን ሀብት ከማመን ይልቅ በውጪዉ ብልጭልጭ ነገር መማረካችን ነው፡፡"
አቶ ወልደሄር ይዘንጋው

የጤና ትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማሻሻል የሚያስችል ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ተካሄደ።April 6, 20234ባሕር ዳር:መጋቢት 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚንስቴር ከሰዎች ለሰዎች ግብረ...
06/04/2023

የጤና ትምህርት ጥራትን ይበልጥ ለማሻሻል የሚያስችል ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ ተካሄደ።
April 6, 20234
ባሕር ዳር:መጋቢት 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚንስቴር ከሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት፤ ከትምህርት ሚንስቴር እና ከትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን እንዲሁም ከመንግሥት የዩኒቨርስቲዎች ኮንሰርቲየም ጋር በመተባበር የጤናውን ዘርፍ ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ለማሳደግ በተለያዩ ዘርፎች እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ለምክክር ቀርበዋል።
በመድረኩም በጤና ሚንስቴር፣ በሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ መካከል ዓለም አቀፍ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና (ECFMG/USMLE) በሀገራችን ለመስጠት የሚያስችል ቅድመ የሦሥትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ የፊርማ ሥነሥርዓት ተከናውኗል፡፡ ይህም የጤና ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም ከሀገር ውጪ ለመስራትም ሆነ ለመማር መመዘኛዎችን አጎራባች ሀገራት ሄደው ለመፈተን ከሚደርሰው እንግልት እና ወጪ የሚያድን ነው ተብሏል፡፡
በውይይቱ ለምክክር የቀረበው የሦሥተኛ ወገን የብቃት ማረጋገጫ ሥርዓት የጤና ሚንስቴር፣ ከትምህርት ሚንስቴር እና ከኢትዮጵያ ትምህርት ባለስልጣን ጋር በመሆን የጤና ትምህርት ተቋማት ተዓማኒ፣ ተወዳዳሪ እንዲሁም የሚያስመርቋቸው ባለሙያዎች የተሻለ ብቃት እንዲኖራቸው የሚያስችል እና ተቋማቱም ባለሙያዎቹም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓት መሆኑ ተገልጿል።
በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የጤና ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ፤ ሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት የትምህርት ጥራት እንዲሻሻል ድጋፍ በማድረግ፣ ዩኒቨርሲቲዎችን በመደገፍ፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅትም አማካሪ ካውንስል በመሆንና የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ በርካታ ሥራዎችን የሰራ መሆኑን ጠቅሰው አሁን ስምምነት የተደረሰበት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና በሀገር ውስጥ መጀመር እንግልትን ከመቀነስ ባለፈ የሌሎች ሀገራት ባለሙያዎች ወደ ሀገራችን በመምጣት መፈተን የሚችሉበትና የውጭ ምንዛሬን የሚሳድግ ነው ብለዋል።
በውይይቱ የሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች፣ የትምህርት ሚንስቴር እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የጤና ባለሙያዎች መሳተፋቸውን የጤና ሚንስቴር መረጃ ያመለክታል።

ባሕር ዳር:መጋቢት 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የጤና ሚንስቴር ከሰዎች ለሰዎች ግብረ ሰናይ ድርጅት፤ ከትምህርት ሚንስቴር እና ከትምህርትና ሥልጠና ባለስልጣን እንዲሁም ከመንግሥት የዩኒቨርስቲ.....

አብን፤ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ
06/04/2023

አብን፤ የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት የተላለፈውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአማራ ልዩ ኃይልን ትጥቅ ለማስፈታት በገዢው ፓርቲ ተላልፏል ያለውን ውሳኔ እንደሚቃወም አስታወቀ። ውሳኔው፤ የአማራ ህዝብን  “ያለ ተከላካይ፣ ለዳግ.....

06/04/2023

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳም የአገራቸው የወሊድ መጠን መቀነስ አገራቸውን አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደጣለው በመግለጽ፣ አረጋውያን መብዛት “አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ አደጋ ነው...

የሕዝባቸውን ቁጥር ለመጨመር ልጆች ለሚወልዱ ዜጎች ማበረታቻ የሚሰጡ አገራትየሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል እና የወሊድ ምጣኔ መቀነስ ለበርካታ አገራት አሳሳቢ ሆኗል።አዲስ የሚተካ ትውልድ ቁጥር እየ...
06/04/2023

የሕዝባቸውን ቁጥር ለመጨመር ልጆች ለሚወልዱ ዜጎች ማበረታቻ የሚሰጡ አገራት
የሕዝብ ቁጥር ማሽቆልቆል እና የወሊድ ምጣኔ መቀነስ ለበርካታ አገራት አሳሳቢ ሆኗል።
አዲስ የሚተካ ትውልድ ቁጥር እየተመናመነ ነው። በአንዳንድ አገራት አረጋውያን ጧሪ አጥተው ፊታቸውን ወደ ሮቦቶች እስከ መዘርጋት ደርሰዋል።
ትኩስ የሠራተኛ ኃይል እጥረትም አጋጥሟቸዋል።
ይህም በምጣኔ ሃብታቸው ላይ ተፅዕኖ እያደረሰ እንደሆነ ጥናቶች እያመለከቱ ነው።
ይህንን ስጋት ለመቀልበስ ታዲያ “እባካችሁ ውለዱ!” የሚል ተማፅኖን ጨምሮ ሌሎች የማበረታቻ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው።
ቻይና በስድስት አስርት ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የሕዝብ ብዛቷ መቀነሱን አስታውቃለች።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳም የወሊድ መጠን መቀነስ አገራቸውን አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደጣላት በመግለጽ፣ የአረጋውያን መብዛት “አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ አደጋ ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጨምረውም “ጃፓን እንደ ማኅበረሰብ እንቅስቃሴ የምታቆምበት አፋፍ ላይ ትገኛለች” ብለዋል።
በአገሪቷ ያለው የወሊድ መጠን አዲስ ክብረ ወሰን በሆነ መጠን መቀነሱን ተከትሎም የቶክዮ ባለሥልጣናት፣ ዜጎቻቸው ልጆችን እንዲወልዱ ለማበረታታት ከሕጻናት ጋር የተያያዙ ፕሮግራሞች ላይ የሚያወጡትን ገንዘብ በእጥፍ እንደሚጨምሩ አስታውቀዋል።
ይሁን እንጂ ይህ ችግር እያሳሰባቸው ያለው ጃፓን እና ቻይናን ብቻ አይደለም።
ሌሎች አገራትም የወሊድ መጠንን ለማሳደግ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰዱ ነው። የተወሰኑትን እንመልከት፦

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳም የአገራቸው የወሊድ መጠን መቀነስ አገራቸውን አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደጣለው በመግለጽ፣ አረጋውያን መብዛት “አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ አደጋ ነው...

05/04/2023

ከኢትዮጵያ ጋር ላለው ግንኙነት መሻሻል በትግራይ ያለው ሁኔታ ወሳኝ ነው:: “የአውሮፓ ኅብረት”

አሜሪካ ወደ ገሃነም ትገባለች:: “ትራምፕ”መረጃዎችን ለመደበቅ የንግድ መዝገቦችን አጭበርብረዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ወደ ገሃነም ትገባለች ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው በድፍ...
05/04/2023

አሜሪካ ወደ ገሃነም ትገባለች:: “ትራምፕ”

መረጃዎችን ለመደበቅ የንግድ መዝገቦችን አጭበርብረዋል የሚል ክስ የቀረበባቸው ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ወደ ገሃነም ትገባለች ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው በድፍረት ተናግረዋል።
ትራምፕ ማክሰኞ፣ መጋቢት 26/2015 በዋለው ችሎትም በሰጡት የምስክርነት ቃል ጥፋተኛ አይደለሁም ብለዋል።
የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ መዘገቦችን አጭበረበሩ የተባለው ለአውሮፓውያኑ 2016 ምርጫ እየተሰናዱ በነበረበት ወቅት ነው።
ትራምፕ በኒውዮርክ በሚገኘው የማንሃተን ፍርድ ቤት 34 ክሶች ቀርቦባቸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ ለፕሬዝዳንትነት በተወዳደሩበት ዋዜማ ከወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ጋር ምሥጢር አታውጪብኝ በሚል ከፈሉት በተባለው ገንዘብ እና ገንዘቡን ለማወራረድ ያቀረቡት ምክንያት ለዚህ የወንጀል ክስ ዳርጓቸዋል።
ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ በወንጀል የተከሰሱ የመጀመርያው ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
“የፈጸምኩት ብቸኛው ወንጀል አገራችንን ለማፍረስ እየጣሩ ካሉ ኃይሎች መከላከሌ ነው” ሲሉ የ76 ዓመቱ ትራምፕ ከፍርድ ቤት መልስ ፍሎሪዳ በሚገኘው ማር አ ላጎ መኖሪያ ቤታቸው ለተሰበሰቡ ደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል።
• 34 ክሶች የቀረቡባቸው ትራምፕ ጥፋተኛ አይደለሁም አሉ5 ሚያዚያ 2023
• ካረን ማክዱገል፡ ከትራምፕ ጉዳይ ጋር የተያያዘችው ሁለተኛዋ ሴት ማን ናት?5 ሚያዚያ 2023
• ትራምፕ የተጋረጠባቸውን የሕግ ፈተና የሚያስረዱ 7 ቁልፍ ጥያቄዎች3 ሚያዚያ 2023
የቀድሞው ፕሬዚዳንት በሚቀጥለው ዓመት አገሪቷ በምታካሂደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ጣልቃ ለመግባት በዲሞክራቲክ ፓርቲ የተቀነባበረ የሴራ አካል ነው ሲሉም ክሱ ሃሰተኛ ነው ሲሉ አጣጥለውታል። ትራምፕ በሚቀጥለው ዓመትም በሚደረገው ምርጫ ለመወዳደር እንዳሰቡም ተገልጿል።
ለአንድ ሰዓት ያህል በነበረው የችሎት ሂደትም ምንም አይነት ቃል ያልተነፈሱት ትራምፕ ዳኛ ሁዋን መርቻን ጥፋተኛ ስለመሆን አለመሆናቸው ብቻ ሲጠይቁዋቸው ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ የክስ መቃወሚያቸውን አሰምተዋል። ከፍርድ ቤትም ሲወጡ ለጋዜጠኞች ትንፍሽ ያሉት ነገር የለም።
ዶናልድ ትራምፕ በ2016 ምርጫ ወቅት እንቅፋት እንዳትሆንባቸው ለወሲብ ተዋናይት ስቶርሚ ዳኒኤልስ “ስለነበረን ነገር ትንፍሽ እንዳትይ” በሚል አፍ ማስያዣ 130ሺህ ዶላር ገንዘብ ዝውውር ያደረጉት በቀድሞ ጠበቃቸው ማይክል ኮህን በኩል ነበር።
እንዲህ ዓይነቱ ክፍያ ህገወጥ ባይሆንም ለፕሬዚዳንታዊ ዘመቻ ያግዝ ዘንድ ገንዘብ ማውጣትና ይህንንም ይፋ አለማድረግ የአገሪቱን የፌደራል የምርጫ ዘመቻ ፋይናንስ ህግን ይጥሳል።
ከትራምፕ በተቃራኒ የቆመው የቀድሞ ጠበቃቸው ኮህን ክፍያው የተፈጸመው በትራምፕ መመሪያ መሆኑን ተናግሯል።

05/04/2023

Address

Addis Ababa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mere Media posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share