07/04/2020
ዛሬ መጋቢት 29,2012 ዓ.ም በኦፋ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮ/ሽን ጽ/ቤት የጽ/ቤቱ ሠራተኞች በወረዳው ከ/ል ከሚተዳደሩ ከ3ስቱ ማዘጋጃ ቤት (ዋጭጋ፤ደቀያና ያኪማ) ሠራተኞች ጋር ህብረት በመፍጠርና ኮሚቴ በመዋቀር በአሁኑ ሰዓት በአለማችን አልፎም በአገራችን በአሳሳቢና በአሰጊ ሁኔታ እየተሰራጨና የብዙሃንን ህይወት እየቀጠፈ ባለው በኮሮና ወረርሽኝ በሽታ (Covid-19) ዙሪያ ለሴክተሩ ሠራተኞችና በ3ስቱ ማዛጋጀ ክልል ውስጥ ለሚገኙ ማህበርሰብ ክፍሎች መንግስትና የሃይማኖት ተቋማት ባስተላለፉት መልዕክትና አስተምህሮ መሠረት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫና የገቢ ማሰባሰቢያ ተግባራት ተካሂደዋል፡፡
በዚህም መሠረት ከአስከፊው ወረርሽኝ በሽታ ራሱንና ወገኑን አስቀድሞ ለመታደግ ከሚያስችሉ ቅድመ ጥንቃቄዎች(መተላለፊያና መከላከያ መንገዶችን መገናዘብ፤ፈፅሞ አለመጨባበጥን፤እጅን በውሃና በሳሙና በየ20 ደቂቃ ልዩነት መታጠብን፤ሳታጠቡ እጅን አፍንጫንና ዓይንን ፈፅሞ አለመነካካትን፤ተራርቆ መቀመጥ መቆምና መሄድ፤የበሽታው ምልክት ከሚታይባቸው ሰዎች ብያንስ 2ሜትር መራቅ…ፈጣሪን መለመንና አለመፍራት አለመደናገጥ…ከመሳሰሉት) ጋር በተያዘ በቂ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡
እንድሁም የቫይረሱን ፈጣን ስርጭትን ለመግታትና ለመከላከል ታቅዶ በመላው አገራችን እየተካሄዴ ባለው ገቢ ማሰባሰቢያ ተግባር መሠረት ከ ጽ/ቤቱ ሠራተኞችና በ3ቱ ማዘጋጃ ቤቶች ክልል ውስጥ ከሚገኙ ማህበርሰብ ክፍሎች የገንዘብና የእህል ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተስተውሏል፡፡
በአጠቃላይ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫና የድጋፍ ገቢ ማሰባሰቢያ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ከኮሚቴውና ከማህርሰብ ክፍሎች ከተነሱ ሀሳቦች መረዳት ተችሏል፡፡
እግዚአብሔር አገራችንንና ምድራችንን ከክፋት ሁሉ ይታደግ!!!
ኦ/ወ/ከ/ል/ኮ/ሽን ጽ/ቤት,አማኑኤል ፋንታ,ከኮሚቴ