NBE News

NBE News NBE News Brings you daily and Breaking News concerning about Ethiopia. Peace To Ethiopia

11/07/2021

Virgin Galactic founder Richard Branson is about to go to space, attempting to become the first billionaire to fly in his own rocket-powered plane.

Hillary Clinton called out the Republican-led crackdown on voting rights and urged Americans to fight for access to the ...
08/07/2021

Hillary Clinton called out the Republican-led crackdown on voting rights and urged Americans to fight for access to the ballot box in an op-ed published Wednesday

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ስብሰባውን ያደርጋል።5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በስድስተኛው ዓመት የስራ ዘመኑ 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ሰኔ ...
04/07/2021

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት ስብሰባውን ያደርጋል።

5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በስድስተኛው ዓመት የስራ ዘመኑ 4ኛ ልዩ ስብሰባውን ነገ ሰኔ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ያካሂዳል፡፡

ምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባውን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ነው የሚያካሂደው።

ም/ቤቱ የፌዴራል መንግስትን የ2014 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያፀድቀው ይጠበቃል፡፡

በስብሰባው ላይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች፣ የአለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ስብሰባው የምልክት ቋንቋን ጨምሮ በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ የሚተላለፍ ይሆናል፡፡

መረጃው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነው።

 አሜሪካ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዜጎቿን ለማስወጣት ጥረት እያደረገች ነው።የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በትዊተር ገጹ ባሰራጨው " የጥንቃቄ መልዕክት " መቐለ የሚገኙ የአሜሪ...
03/07/2021



አሜሪካ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ የሚገኙ ዜጎቿን ለማስወጣት ጥረት እያደረገች ነው።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በትዊተር ገጹ ባሰራጨው " የጥንቃቄ መልዕክት " መቐለ የሚገኙ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ዜጎች ለማስወጣት ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

በመቐለ የሚኖሩ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሰዎች ለደኅንነታቸው ተጠልለው እንዲቆዩ መስሪያ ቤቱ መክሯል።

በክልሉ ያሉ አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ወይም በመቐለ የሚኖር #አሜሪካዊ ቤተሰብ ያላቸው ሰዎች ከመስሪያ ቤቱ ጋር ግንኙነት እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

 በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ 02 ሳቢያን መስቀለኛ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 6 ገደማ በግንባታ ላይ በሚገኝ ህንፃ ሳቢያ ከሚገነባው ህንፃ ጎን ያሉ ሁለት ...
03/07/2021



በድሬደዋ ከተማ ቀበሌ 02 ሳቢያን መስቀለኛ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ 6 ገደማ በግንባታ ላይ በሚገኝ ህንፃ ሳቢያ ከሚገነባው ህንፃ ጎን ያሉ ሁለት የግለሰብ መኖሪያ ቤቶችና አንድ መፀዳጃ ቤት በመፍረሱ በህንፃው ግንባታ ስራ ላይ የነበሩ 2 ሰራተኞች ህይወት ማለፉን በአንድ ሌላ አብሮ በስራ ላይ የነበረ ግለስብ ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የድሬ ፖሊስ ሪፖርት አደረገ።

አደጋው እንደ ደረሰ ከአካባቢው ህ/ብ እና ወጣቶች ጋር የፖሊስ ሀይል ከፍተኛ የነፍስ አድን ስራ ቢሰራም ሁለቱም ግለሰቦች በከፍተኛ ሁኔታ ፍርስራሽና አፈር ሸፍኗቸው የነበረ በመሆኑ ህይወታቸውን ማተረፍ አልተቻለም።

ሌላኛው የአደጋው ተገጂ በአሁኑ ወቅት በህክምና ክትትክ ላይ የሚገኝ ሲሆን መልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝም ፖሊስ ገልጿጻ።

በሌላ በኩል በደረሰው አደጋ ሳቢያ 250 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት እንደወደመ ተገልጿል።

ከተከሰተው አደጋ ጋር ተያይዞ እየተገነባ ያለው ህንፃ ባለቤት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራ እንደሆነም ድሬ ፖሊስ አሳውቋል።

በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር “በኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም እየተሰራጨ ነው” ያለውን “የሽግግር መንግስት” አዋጅ እንደማይቀበል ገለፀ፡፡ፓ...
03/07/2021

በአቶ አራርሶ ቢቂላ የሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር “በኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር ስም እየተሰራጨ ነው” ያለውን “የሽግግር መንግስት” አዋጅ እንደማይቀበል ገለፀ፡፡

ፓርቲው ባወጣው ባለሰፊ አተታ መግለጫው በአቶ ዳውድ ኢብሳ በሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይፋዊ ገፅ የወጣውን የሽግግር መንግስት ምክረ ሀሳብ ጥሪንም ነቅፎ አቋሙን ገልጾበታል፡፡የፓርቲው ባለስልጣናት ለዶይቼ ቬለ በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያም ፓርቲያቸው ስልጣን በምርጫ እንዲተላለፍ ያምናል ብለዋል፡፡

[DW]

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በቀጣዩ ሳምንት በሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ላይ እንደሚወያይ ዐለማቀፍ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በመድረኩ ላይ ስጋታቸውን እንዲገልጹ እ...
03/07/2021

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት በቀጣዩ ሳምንት በሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ላይ እንደሚወያይ ዐለማቀፍ ዜና ምንጮች ዘግበዋል፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በመድረኩ ላይ ስጋታቸውን እንዲገልጹ እና ለችግሩ ራሳቸው መፍትሄ እንዲፈልጉ ለማበረታታት እንጅ ምክር ቤቱ እምብዛም ሊያደርገው የሚችለው ነገር እንደሌለ የምክር ቤቱ የወቅቱ ፕሬዝዳንት የፈረንሳዩ አምባሳደር ኒኮላስ ሪቬራ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል ተብሏል፡፡ ጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ እንዲወያይ ሱዳን፣ ግብጽ እና ዐረብ ሊግ ቀደም ሲል መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

[Wazema]

ግዳጅ ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈ የፖሊስ አባላት ቤተሰቦችና ወላጆች  የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ።የድሬደዋ ፖሊስ ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር በመሆን በስራና ግዳጅ ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈ የፖ...
03/07/2021

ግዳጅ ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈ የፖሊስ አባላት ቤተሰቦችና ወላጆች የገንዘብ ድጋፍ ተደረገ።

የድሬደዋ ፖሊስ ከድሬደዋ አስተዳደር ጋር በመሆን በስራና ግዳጅ ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈ የፖሊስ አባላት ቤተሰቦችና ወላጆች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

አስተዳደሩ በፖሊሳዊ ግዳጅ ፣ስራና ሃላፊነት ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈና ጉዳት ለደረሰባቸው አባላት ቤተሰቦች ዘጠኝ መቶ ሺ ብር ነው ድጋፍ ያደረገው::

በእዚሁ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡሁ ባስተላለፉት መልእክት ህይወትን ለሀገርና ሰቶ ማለፍ በጀግንነት በትውልድ እየታሰቡና እየተዘከሩ መኖር መቻል ነው ለዚህም አስተዳደሩ ትልቅ ክብር አለው ብለዋል።

የድሬደዋ ፖሊስ ኮሚሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው የፖሊስ አባል በስራና ግዳጅ ላይ እያለ ህይወቱ ሲያልፍ አሊያም አካል ሲጎል ሁል ግዜም የአባል ቤተሰብን የመደገፍ የመርዳት ተግባር ተቋማዊ ባህል በማድረግ እየሰራን ነው ይሄም በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በመርሀ-ግብሩ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ስራ ላይ በትራፊክ አደጋ ህይወቱ ላለፈው ሳጅን እዮኤል ሀይሉና ለአፋር ክልል የተደረገን ድጋፍ አጅቦ ሄዶ ሲመለስ በግዳጅ ላይ እያለ ህይወቱ ላለፈው ኮ/ል ሳሙኤል ከተማ ለእያንዳዳቸው አባላት ቤተሰቦች ሁለት መቶ ሺ (200.000)ብር ድጋፍ ተደርጓል።

በተጨማሪም ለሌች በስራ ላይ እያሉ ህይወታቸው ላለፈና የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እንደየ ጉዳታቸውና የስራ ግዳጃቸው ሁኔታ ከአንድ መቶ ሺ ብር እስከ አስራ አምስት ሺ ብር ድረስ በአጠቃላይ ለአስራ ስምንት አባላት የዘጠኝ መቶ ሺ(900.000)ብር ድጋፍ ተደርጎላቸዋል::

 ኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን "ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ" የመሬት መንቀጥቀጥ ምልክት በመታየቱ 2 ሺህ 303 የቤተብ አባላት አከባቢያቸውን ለቀው መውጣታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘገበ።የኦሮሚያ ውሃና ኢንርጂ...
03/07/2021



ኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን "ዝዋይ ዱግዳ ወረዳ" የመሬት መንቀጥቀጥ ምልክት በመታየቱ 2 ሺህ 303 የቤተብ አባላት አከባቢያቸውን ለቀው መውጣታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘገበ።

የኦሮሚያ ውሃና ኢንርጂ ቢሮ የመሬት ምህዳርና የውሃ ባለሙያ የሆኑት አቶ አብዱለጢፍ ሙሀመድ ምልክቱ የመሬት መንቀጥቀጥ መሆኑን ገልፀዋል።

የተለካው ማግኒቲውድ ውጤቱ ተመልሶ ለህብረተሰቡ እስኪነገር ድረስ ባሉበት መቆየት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በመሬት መንቀጥቀጥ ምልክት ከአከባቢው ራቅ ብለው የሚኖሩ ሰዎች የምግብና የውሃ አቅርቦት ያስፈልጋቸዋል ተብሏል። #ኤፍቢሲ

 ስለ2ኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት !ፕ/ር አታላይ አየለ ለSBS ሬድዮ ከተናገሩት ፦"እንኳን ሁለተኛ ተሞልቶ ይቅርና የመጀመሪያው ሙሌት ቀላል የማይባል ውሃ ነው ያለው።ግብፆች ግ...
03/07/2021



ስለ2ኛው ዙር የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሌት !

ፕ/ር አታላይ አየለ ለSBS ሬድዮ ከተናገሩት ፦

"እንኳን ሁለተኛ ተሞልቶ ይቅርና የመጀመሪያው ሙሌት ቀላል የማይባል ውሃ ነው ያለው።

ግብፆች ግድቡን እንመታለን ምናም የሚሉት፣ የሚያስፈራሩት ነገር አለ። በእርግጥ አሁንም ቢሆን ያለው የግድቡ ግዝፈት እና የሚሰራበት ጥራት እውነት ለመናገር መቼውንም ቢሆን ተመቶ ይፈርሳል ተብሎ የሚታሰብ አይደለም።

እንደው ተሳክቶላቸው እንኳን ቢሆን 2ኛው ሙሌት ከተሞላ በኃላ ልክ እንደ ኒውኩሌር ቦምብ ማለት ነው ለራሳቸው የሚሆነው ፤ ጠራርጎ ሜዴትራንያን ባህር ውስጥ ነው የሚጨምራቸው። የቀድሞ ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በአንድ ወቅት " ግድቡን እኛ ሳንሆን እነሱ ናቸው የሚጠብቁት " ብለዋል።

ስለዚህ ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ ብዙ የሚያስጨንቃት አይደለም። ቢፈልጉ ይደራደሩ በአካሄድ በሌሎችም ጉዳዮች ፣ የውሃ፣ አካባቢ ጥበቃና በሌሎች የመሳሰሉት ጉዳዮችን ፤ የላይኛው የወንዙ ተፋሰስ ሀገሮችን ጨምሮ ሊደራደሩ ይችላሉ የሚል ተስፋ አለን።

ሁለተኛው ዙር ተሞላ ማለት ኃይል ማመንጨት ይቻላል ፤ በነገራችን ላይ ኃይል ለማመንጨት የተርባይኖቹ አለመጠናቀቅ ነው እንጂ አሁን እራሱ የተያዘው ውሃ በቂ ነው፤ የሁለቱን ተርባይነሮች ለማስጀመር።

ሁለተኛው ከተሞላ ቀላል የማይባል ውሃ ነው የምን ይዘው።

አስገዳጅ ስምምነት የሚሉት ሌላ የልማት እንቅስቃሴ ወይም ደግሞ ሌላ ግድብ ኢትዮጵያ እንዳትሰራ ለማሰር ነው፤ የአሁኑ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ወንጀል ሰርተው የሚያልፉበት ምክንያት አይኖርም፤ ይሄ መቼም የሚደረግ አይደለም።

ግብፅ እና ሱዳን እስካሁን የተሳካላቸው አይመስልም፤ ያደረጉትም ጫና ውሃ የቋጠረ አይመስልም።

ሁለተኛው ሙሌት እንደሚሞላ ተስፋ አለን፣ እስካሁን በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ነው።"

በደቡብ ክልል ተመዝብሯል የተባለውን 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የማስመልስ ተግባር በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የክልሉ መንግስት አስታወቀ!የክልሉ መንግስት ይህን ያስታወቀው ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከ...
03/07/2021

በደቡብ ክልል ተመዝብሯል የተባለውን 1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር የማስመልስ ተግባር በማከናወን ላይ እንደሚገኝ የክልሉ መንግስት አስታወቀ!

የክልሉ መንግስት ይህን ያስታወቀው ዛሬ ጠዋት በሀዋሳ ከተማ በተጀመረው የክልሉ ምክር ቤት 5ኛ ዙር 12ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የመንግስታቸውን ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ለምክር ቤቱ ባቀረቡበት ወቅት ነው።

ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ ርእስቱ ይርዳው በሪፖርታቸው ያቀረቡት ሰነድ በክልሉ በበጀት ዓመቱ በሙስና ፣ በታክስ ማጭበርበር እና በውል አስተዳደር 1, 439, 635, 699 ብር ተመዝብሯል ብለዋል።የተመዘበረውን የህዝብ ሀብት በክልሉ ጠቅላይ ዐቃቢ ህግ አማካኝነት የማስመለስ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ያለው የምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ ሪፖርት > በማለት አብራርተዋል ።

ሪፖርቱ በክልሉ ተካሂዷል ያለው ምዝበራ በየትኞቹ ተቋማትና በእነማን እንደተፈፀመ ግን የጠቀሰው ነገር ያለም።አቶ ርእስቱ ከዚህ በተጨማሪ በእርሻ ፣ በጤና፣ በትምህርት ፣ በመሰረተ ልማት ግንባታዎች ፣ በሰላምና ፀጥታ ረገድ ተከናውነዋል ያሏቸውን ተግባራትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በሪፖርታቸው ዘርዝረዋል።

ዛሬ ጠዋት የጀመረውና እስከ ነገ የሚቆየው ጉባኤ በአሁኑሰዓት በምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በቀረበው የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ እየተወያየ ይገኛል።ምክር ቤቱ በቆይታው አዳዲስ ሹመቶችንና የተጨማሪ በጀት ጥያቄዎችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when NBE News posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share