
10/09/2025
የነገው ቀን
ጳጉሜን አምስት "ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ማድረግ!" በሚል መሪ ቃል የነገው ቀን ተብሎ ይታሰባል። ዓለም በቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚጠበቀው በላይ እየፈጠነ ይገኛል። ከዚህ ፍጥነት ወደኋላ መቅረት ዋጋ ያስከፍላል።
ይህን የምታውቀው ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ቀድማ እየሠራችበት ትገኛለች። በዚህም በቴሌ ኮሙኒኬሽን፣ በዲጂታል ፋይናንሲንግ፣ የአገልግሎት ዘርፉን ዲጂታል በማድረግ ረገድ አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛሉ።
ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዕድገት ጎን ለጎን በአሳሳቢ ደረጃ እያደገ የመጣውን የሳይበር ደኅንነት ተግዳሮትን ለመከላከል ራሷን ከማዘጋጀቷም በላይ በዚህ ረገድ የሚቃጡባትን ጥቃቶች በውጤታማነት እየተከላከለች ነው።
መረጃ ሀብት በሆነበት በዚህ ዘመን ኢትዮጵያም የመረጃ ሀብቷን ከማከማቸት እስከ መጠበቅ የዘለቀ እጅግ ስኬታማ ለውጥን በማምጣት የነገ መሰረቷን እያደላደለች ትገኛለች።
የመረጃ ሀብትን ከመጠበቅ ጎን ለጎንም ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመን በተጀመረው ሥራ እንደ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ያሉ በአንድ ቦታ በርካታ አገልግሎቶችን የሚሰጡ ተቋማት እየተስፋፉ ይገኛሉ።
የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ሥልጠና ፕሮጀክት ትውልዱ ከመጪው ዘመን ቴክኖሎጂ ጋር እንዲራመድ የሚያደርግ ሌላው የኢትዮጵያ መንግሥት የነገ ቀን መመልከቻ ነው።