Qubee TV- አማርኛ

  • Home
  • Qubee TV- አማርኛ

Qubee TV- አማርኛ Qubee TV Is An Entertainment, Educational and News Media Established With A Great Vision To Be The Best In Ethiopia And East Africa.

በቡራዩ የውንብድና ወንጀል በመፈጸም የተከሰሱ ግለሰቦች በ18 እና 17 ዓመት እስራት ተቀጡ ቁቤ ቲቪ፣ ሐምሌ 18፣ 2017( ፊንፊኔ ) የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወ...
25/07/2025

በቡራዩ የውንብድና ወንጀል በመፈጸም የተከሰሱ ግለሰቦች በ18 እና 17 ዓመት እስራት ተቀጡ

ቁቤ ቲቪ፣ ሐምሌ 18፣ 2017( ፊንፊኔ ) የኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በቡራዩ ክ/ከተማ በተለያዩ ግለሰቦች ላይ የውንብድና ወንጀል በመፈጸም የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች በ18 እና 17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወሰነ፡፡

የቅጣት ውሳኔ የተወሰነባቸው ተከሳሾች ወንድዬ ወይም ናቲ ከፍያለው እና ግርማ ወይም አስራት ቦጋለ በሚል ሁለት ስም ይጠቀሙ የነበሩ ግለሰቦች ናቸው።

የኦሮሚያ ክልል የሸገር ከተማ ቅርጫፍ ጽ/ቤት ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ፣ ለ እና አንቀጽ 671 ንዑስ ቁጥር 1 ሀ እና ለ ስር የተመላከተውን ድንጋጌ ጠቅሶ ተደራራቢ ከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸው ነበር።

በዚህም በቀረበው ክስ ላይ እንደተመላከተው 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች በመጋቢት 2 ቀን 2017 ከቀኑ 8:00 ላይ በቡራዩ ከተማ በተለምዶ 105 ተብሎ በሚጠራ አካባቢ የመከላከያ አባል ሳይሆኑ ተመሳሳይ አልባሳት ለብሰው አባል ነን በማለት የውንብድና ወንጀል ሲፈጽሙ የነበሩና አምስት ግለሰቦችን በማስፈራራትና በማስገደድ የሞባይል ስልክን ጨምሮ የተለያየ ንብረት አስገድደው መውሰዳቸው በክሱ ላይ ተመላክቷል።

ተከሳሾቹ በዚህ መልኩ የቀረበባቸውን የክስ ዝርዝር በችሎት ቀርበው እንዲደርሳቸውና በንባብ እንዲሰሙ ከተደረገ በኋላ የወንጀል ድርጊት አለመፈጸማቸውን ጠቅሰው፤ የዕምነት ክህደት ቃላቸውን መስጠታቸውን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ ለወንጀሉ መፈጸም የሚያስረዱ የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርቦባቸዋል።

ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃን መርምሮ እንዲከላከሉ ብይን የሰጠ ቢሆንም ተከሳሾቹ በተገቢው ማስተባበል ባለመቻላቸው የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ከዚህም በኋላ ዐቃቤ ሕግ ተከሳሾቹ የመከላከያ አልባሳትን ለብሰው በቡድን የፈጸሙት ወንጀል መሆኑን እና አንደኛ ተከሳሽ ቀደም ሲል ጉዳዩ ከሚታይበት ችሎት ወጥቶ ለማምለጥ ሲሞክር በፀጥታ አካላት ክትትል በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቅሶ ቅጣቱ ከብዶ እንዲጣልለት የቅጣት ማክበጃ አስተያየት አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ የቅጣት አስተያየት መርምሮ በዛሬው ቀጠሮ በዕርከን 40 መሰረት 1ኛ ተከሳሽ በ18 ዓመት ጽኑ እስራት 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ በ17 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፌስ ቡክ ገጽ ከኮሚሽኑ ቁጥጥር ውጪ ሆኗል-  የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮቁቤ ቲቪ ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ፊንፊኔ ) የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፌስ ቡክ ገጽ ከ...
23/07/2025

የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፌስ ቡክ ገጽ ከኮሚሽኑ ቁጥጥር ውጪ ሆኗል- የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ቁቤ ቲቪ ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ፊንፊኔ ) የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፌስ ቡክ ገጽ ከኮሚሽኑ ቁጥጥር ውጪ ሆኗል አለ የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ፡፡

የቢሮው ሃላፊ አቶ መሃመድ አሊ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የፌስ ቡክ ገጽ ከኮሚሽኑ ቁጥጥር ውጪ መሆኑን ለፋና ዲጂታል አረጋግጠዋል፡፡

በአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፌስ ቡክ ገጽ አሁን ላይ እየተላለፉ የሚገኙ መልዕክቶች የክልሉን መንግስት እና ሕዝብ እንደማይወክሉም ተናግረዋል፡፡

በክልሉ በአሁኑ ወቅት ምንም አይነት የጸጥታ ችግር እንደሌለ ገልጸው ÷ ሁሉም አካባቢዎች እንደከዚህ ቀደሙ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኙ አስገንዝበዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከ51 ሺህ በላይ የሚሆኑ የፍርድ ሂደቶች በኦንላይን ተካሄዱ ቁቤ ቲቪ፤ ሐምሌ12 ፣ 2017 (ፊንፊኔ ) በኦሮሚያ ክልል በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ከተካሄዱ የፍርድ ሂደቶች...
19/07/2025

በኦሮሚያ ክልል ከ51 ሺህ በላይ የሚሆኑ የፍርድ ሂደቶች በኦንላይን ተካሄዱ

ቁቤ ቲቪ፤ ሐምሌ12 ፣ 2017 (ፊንፊኔ ) በኦሮሚያ ክልል በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ ከተካሄዱ የፍርድ ሂደቶች መካከል ከ51 ሺህ በላይ የሚሆኑት የፍርድ ሂደቶች በኦንላይን ተካሂደዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ 6ኛው ጨፌ ኦሮሚያ 4ኛ ዓመት 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የክልሉን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ይገኛል።

የፍርድ ቤቶችን የስራ አፈፃፀም አስመልክቶ እንደተናገሩት፤ በክልሉ በሶስቱም ደረጃ ባሉ ፍርድ ቤቶች በዓመቱ 548 ሺህ 744 ጉዳዮች ቀርበው 532 ሺህ 724 ጉዳዮች እልባት አግኝተዋል።

ከእነዚህ መካከል 51 ሺህ 911 ጉዳዮች በቪዲዮ ኮንፍረንስ የተካሄዱ ናቸው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፤ ከተገልጋዩ 976 ሚሊየን 332 ሺህ ብር ወጪ ለማዳን ማስቻሉንም አንስተዋል።

በእንቅስቃሴ ላይ ከነበሩ አጠቃላይ ጉዳዮች 761 ሚሊየን 945 ሺህ 543 ብር ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።

በፍርድ አሰጣጥ ሂደት ውስጥ የዲጂታል መንገድን በመጠቀም ፈጣንና ግልፅ አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ ለመሆኑ አመላካች እንደሆነም ገልጸዋል።

ወደ ፍርድ ቤቶች የሚመጡ ጉዳዮች ከቀደመው በጀት አንጻር በ37 ሺህ 573 ጉዳዮች መቀነሱን ጠቅሰው፤ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት የመደበኛ ፍርድ ቤቶችን ጫና እያቃለለ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በባህላዊ ፍርድ ቤቶች ውስጥ ሲታዩ ከነበሩ 482 ሺህ 556 ጉዳዮች መሀከል 443 ሺህ 686 ጉዳዮች ውሳኔ ማግኘታቸውን ጠቅሰው፤ ባህላዊ ፍርድ ቤቶች ከፍተኛ አስተዋእጾ እያደረጉ እንደሆነ አመልክተዋል።

የመዲናዋ የ2017 እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 እቅድ ውይይት ተጀመረ ቁቤ ቲቪ፤ ሐምሌ12 ፣ 2017 (ፊንፊኔ )የአበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ20...
19/07/2025

የመዲናዋ የ2017 እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 እቅድ ውይይት ተጀመረ

ቁቤ ቲቪ፤ ሐምሌ12 ፣ 2017 (ፊንፊኔ )የአበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2018 ዓ.ም እቅድ ውይይት መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንዳሉት፤ ዓመቱ የእቅዳችንን 95 በመቶ ያሳካንበት ነው ብለዋል።

በዚህም የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች የተመለሱበት፣ ከ15 ሺህ 900 በላይ ፕሮጀክቶች የተጠናቀቁበት፣ በኮሪደር ልማት የከተማዋን ውብ ገፅታ ያላበስንበት እና ምትክ ቦታዎችን ለማህበረሰቡ የሰጠንበት ነው ብለዋል።

አክለውም ኢንዱስትሪዎች ያለባቸውን ችግር በመቅረፍ ምርታማነትን በመጨመር ተኪ ምርቶችን ማምረት መቻሉን ተናግረዋል።

የማህበረሰቡን የኑሮ ጫና እና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ ምርቶች በተለያዩ አቅጣጫዎች እንዲገቡ፣ በተለያዩ የገበያ አማራጮች እንዲቀርቡ ከማድረግ ባለፈ ዜጎች አምርተው እንዲጠቀሙ አድርገናል ሲሉ ተናግረዋል።

ሁሉንም ታሳቢ ያደረጉ የልማት ሥራዎች መተግበር መቻሉን ያነሱት ከንቲባዋ፤ በ2017 በጀት ዓመት ጥሩ የገቢ አሰባሰብ ውጤት የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።

ከተሰበሰበው ገቢ 71 በመቶ የሚሆነው ለዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሳ መዋሉንም አብራርተዋል።

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ቡድን ወደ ቻይና ሊያቀና ነው ቁቤ ቲቪ፤ ሐምሌ 11፣ 2017 (ፊንፊኔ ) "ኪን ኢትዮጵያ - የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት" በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያን...
18/07/2025

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ቡድን ወደ ቻይና ሊያቀና ነው

ቁቤ ቲቪ፤ ሐምሌ 11፣ 2017 (ፊንፊኔ ) "ኪን ኢትዮጵያ - የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት" በሚል መሪ ሀሳብ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቀው የኪነ ጥበብ ቡድን የፊታችን እሁድ ወደ ቻይና ያቀናል፡፡

መርሐ ግብሩን አስመልክቶ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ፣ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) እና አርቲስት ካሙዙ ካሳ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል።

አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ÷ መንግስት የኪነ ጥበብ ዘርፉ በሀገር ግንባታ ሥራ ላይ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ትክክለኛ ገጽታዋን ለማስገንዘብ የምታደርገው ጥረት በኪነ ጥበብ መታገዝ እንዳለበት ገልጸው÷ የዚሁ አካል የሆነው የኪነ ጥበብ ቡድን የመጀመሪያ ጉዞውን ወደ ቻይና እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

ቡድኑ በቻይና ቤጂንግ እና ናንጅንግ ከተሞች የኢትዮጵያን ባህል እንደሚያስተዋውቅ ጠቅሰው፤ መርሐ ግብሩ በመንግሥት ለመንግሥት ግንኙነት ጭምር የተደገፈ መሆኑን ገልጸዋል።

ለቱሪዝም መስፋፋትና ለኢንቨስትመንት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ይህ የኪነ ጥበብ ጉዞ፤ በተለያዩ ዘርፎች ጥሩ ግንኙነት ያላቸውን የኢትዮጵያ እና ቻይና ትስስርን የበለጠ ያጠናክራል ብለዋል።

ነብዩ ባዬ (ረ/ፕ) በበኩላቸው÷ ከ70 በላይ የሚሆኑ ከያኒያን የሚሳተፉበት የኪነ ጥበብ ጉዞ ከ39 ዓመታት በኋላ የሚደረግ ታሪካዊ ጉዞ ሲሆን ከ50 በላይ የሚሆኑ ብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃዎችና ጥበባት እንደሚቀርቡበት አመላክተዋል፡፡

በተጨማሪም በጉዞው ከትርኢቶች ባሻገር ኢትዮጵያ የአልባሳት ዲዛይን፣ የቡና ቅምሻ እና የአመጋገብ ባህሏን ታስተዋውቅበታለች ብለዋል።

አርቲስት ካሙዙ ካሳ በበኩሉ÷ የኢትዮጵያን ባህል ለማስተዋወቅ አራት ወር የፈጀ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ገልፆ፤ በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያን ቱባ ባህሎች የሚያስተዋውቁ አዳዲስ ስራዎች ተካተውበታልም ብሏል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ተሰራጨ ቁቤ ቲቪ (ሀምሌ፥ 9 ፣ 2017 ) ፊንፊኔ    በኦሮሚያ ክልል ለ2017/18 የምርት ዘመን ከ5 ሚሊየን ...
16/07/2025

በኦሮሚያ ክልል ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ተሰራጨ

ቁቤ ቲቪ (ሀምሌ፥ 9 ፣ 2017 ) ፊንፊኔ
በኦሮሚያ ክልል ለ2017/18 የምርት ዘመን ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ በዩኒዬኖችና ሕብረት ስራ ማሕበራት በኩል ለአርሶ አደሮች ተሰራጭቷል።

የክልሉ የሕብረት ስራ ማሕበር ኤጀንሲ ለምርት ዘመኑ ከ10 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ከውጪ ለማስገባት አቅዶ እስካሁን ከ7 ሚሊየን 200 ሺህ ኩንታል በላይ ማስገባቱን የአጀንሲው ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ፊሮምሳ አበራ ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል፡፡

ከዚህም ውስጥ ከ5 ሚሊየን ኩንታል በላይ በዩኒዬኖችና ሕብረት ስራ ማሕበራት በኩል ለአርሶ አደሩ መሰራጨቱን አንስተው÷ የቀረው በዩኒዬኖች መጋዘን እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡

የአፈር ማዳበሪያን ህገወጥ ግብይት ለማስቀረት የክትትልና ድጋፍ ስራ በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

ባለፉት ዓመታት የተስተዋሉ ህገወጥ ተግባራትን ለማስቀረት የግብይት ሂደቱ በዲጂታል መንገድ እንዲሆን በማድረግ ችግሮቹን መቅረፍ እንደተቻለም ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል የአረም መድኃኒቶች በክልሉ የግብርና ሕብረት ስራ ፌዴሬሽን በኩል መቅረቡን ገልጸው÷ 2 ሚሊየን ሊትር የአረም ማጥፊያ ኬሚካል መዘጋጀቱንና 700 ሺህ ሊትር ለአርሶ አደሮች መሰራጨቱን አስረድተዋል።

በተመሳሳይ 457 ሺህ ኩንታል የምርጥ ዘር ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ ታቅዶ እስካሁን 386 ሺህ ምርጥ ዘር ማከፋፈል መቻሉንም አቶ ፊሮምሳ አንስተዋል፡፡

ኢራን ኳታር በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ፈጸመችቁቤ ቲቪ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ፊንፊኔ )ኢራን ኳታር በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈጸመች
23/06/2025

ኢራን ኳታር በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ፈጸመች

ቁቤ ቲቪ፣ ሰኔ 16፣ 2017 (ፊንፊኔ )ኢራን ኳታር በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ የሚሳኤል ጥቃት ፈጸመች

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጅማ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲዎች  በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል ።
21/06/2025

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፣ ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ፣ ጅማ እና አርሲ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል ።

አሜሪካ በግጭቱ እጇን ካስገባች አደገኛ ሁኔታ ይፈጠራል - ኢራንቁቤ ቲቪ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ፊንፊኔ ) አሜሪካ በእስራኤል ኢራን ግጭት አጇን ካስገባች አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የኢ...
21/06/2025

አሜሪካ በግጭቱ እጇን ካስገባች አደገኛ ሁኔታ ይፈጠራል - ኢራን

ቁቤ ቲቪ፣ ሰኔ 14፣ 2017 (ፊንፊኔ ) አሜሪካ በእስራኤል ኢራን ግጭት አጇን ካስገባች አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራጋቺ አስጠንቅቀዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት በቱርክ ኢስታንቡል በኢራን የኒውክለር ዝግጅት ዙሪያ እየተካሄደ በሚገኘው ውይይት ላይ ሲሆን÷ ሀገራቸው በቦምብ እየተደበደበች ባለበት ሰዓት ከአሜሪካ ጋር ንግግር እንደማይካሄድ ተናግረዋል፡፡

ኢራን በግጭቱ እስካሁን 430 ዜጎቿ እንደተገደሉባት ገልጻለች፡፡

እስራኤል ትናንት ምሽት የኢራኑን አዛዥ ኮማንደር ሳኢድ ኢዛዲንን በሀገሪቱ ሰሜን ምስራቅ አካባቢ በቆም ከተማ መግደሏን ይፋ አድርጋለች፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ በሁለቱ ሀገራት ግጭት መሳተፍ እና አለመሳተፏ በሁለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ውሳኔ እንደሚያገኝ ገልጸው÷ በሀገራቸው ብሔራዊ ደህንነት መረጃ መሰረት በኢራን የኒውክለር ፕሮግራም ላይ ያለው መረጃ ስህተት ሳይሆን እንዳልቀረ ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ የአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ዳይሬክተር ቱልሲ ጋባርድ ኢራን በሳምንት ጊዜ ውስጥ የኒውክለር መሳሪያ ልታመርት ትችላለች ሲሉ መግለጻቸውን ቢቢሲ ዘግቧል

ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ግምባር ቀደም ሀገር እየሆነች ትገኛለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)ቁቤ ቲቪ፤  ግንቦት 9፣ 2017  ) ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ ...
17/05/2025

ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ግምባር ቀደም ሀገር እየሆነች ትገኛለች - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)

ቁቤ ቲቪ፤ ግንቦት 9፣ 2017 ) ኢትዮጵያ በአርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና በክሕሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች አርአያ እየሆነች መምጣቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን ለአፍሪካ ብልጽግና እና ትብብር” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ባለው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ለአፍሪካ መድረክ ላይ ተሳትፈዋል፡፡

በመድረኩ ባደረጉት ንግግርም አፍሪካ በሀገር በቀል የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተመራ አካታች ብልጽግና በማምጣት የአጀንዳ 2063 ግቦችን ለማሳካት እየሰራች መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያም በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ በዲጂታል መሠረተ ልማት እና በክሕሎት ማበልጸጊያ ሥራዎች ግምባር ቀደም ሀገር እየሆነች መምጣቷን ነው የገለጹት፡፡

በኢትዮጵያ የተጀመሩ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ዲጂታል መታወቂያ እንዲሁም የአምስት ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና የኢትዮጵያን የዲጂታል ሕልሞች ወደ ተጨባጭ ለውጥ የሚቀየሩ ናቸው ብለዋል፡፡

አፍሪካ በ2030 አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በሥነ ምግባርና በአካታችነት መርሕ በአህጉራዊ መልክ ልትገነባ እንደሚገባ አጽንኦት መስጠታቸውንም የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5 ጨዋታዎች ይደረጋሉቁቤ ቲቪ  (  ሚያዝያ 11፣ 2017) ፊንፊኔዛሬ በ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።ዛሬ ከሚደረጉ...
19/04/2025

በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 5 ጨዋታዎች ይደረጋሉ

ቁቤ ቲቪ ( ሚያዝያ 11፣ 2017) ፊንፊኔ
ዛሬ በ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር አምስት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ዛሬ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ አስቶንቪላ በሜዳው ቪላ ፓርክ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር የሚያደርገው ጨዋታ ይጠበቃል።

በ54 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው አስቶንቪላ በፒኤስጂ በድምር ውጤት ከአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ከተሰናበተበት ጨዋታ መልስ የሚያደርገው ፍልሚያ ነው።

በ59 ነጥብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 3ኛ ላይ የሚገኘው ኒውካስል ዩናይትድ በሁሉም ውድድር ካደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች አልተሸነፈም።

ሁለቱ ቡድኖች በሁሉም ውድድር ባደረጓቸው ያለፉት አምስት የእርስበርስ ግንኙነቶች ኒውካስል ዩናይትድ ሶስቱን ሲያሸንፍ አስቶንቪላ በአንዱ ድል አድርጎ በቀሪው አንድ ጨዋታ አቻ ተለያይተዋል።

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ አመሻሽ 11 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ተጉዞ ኤቨርተንን ይገጥማል።

በሚቀጥለው የውድድር ዓመት በአውሮፓ ሻምፒዮን መድረክ ቦታ ለማግኘት እየተፋለመ የሚገኘው ማንቼስተር ሲቲ በ55 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ማንቼስተር ሲቲ በሁሉም ውድድር ካደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች በሶስቱ አሸንፎ በሁለቱ አቻ ተለያይቷል።

ባለሜዳው ቡድን ኤቨርተን በሊጉ ካደረጋቸው ያለፉት አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው በአንዱ ብቻ ነው።

ሁለቱ ቡድኖች በፕሪሚየር ሊጉ ካደረጓቸው ያለፉት አምስት የእርስበርስ ጨዋታዎች ማንቼስተር ሲቲ በሶስቱ ሲያሸንፍ በሁለቱ ደግሞ አቻ ተለያይተዋል።

በተመሳሳይ አመሻሻ 11 ሰዓት ላይ ብሬንትፎርድ ከብራይተን፣ ክሪስታል ፓላስ ከቦርንመዝ እንዲሁም ዌስትሀም ዩናይትድ ከሳውዛምፕተን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ሊጉን ሊቨርፑል በ76 ነጥብ ሲመራው አርሰናል በ63፣ ኒውካስል ዩናይትድ በ59 እንዲሁም ኖቲንግሀም ፎረስት በ57 ነጥብ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

ወራጅ ቀጠናው ላይ ኢፕስዊች ታውን፣ ሌስተር ሲቲ እና አስቀድሞ መውረዱን ያረጋገጠው ሳውዛምፕተን ይገኛሉ።

ከጋዛ የተተኮሱ ሮኬቶች በእስራኤል ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተገለጸ።ቁቤ ቲቪ  ( መጋቢት 29፣ 2017) ፊንፊኔበትናንትናው ምሽት ከጋዛ የተተኮሱ ሮኬቶችና ሚሳኤሎች አስቀላን፣ ቴልአቪቭ እና ኡ...
07/04/2025

ከጋዛ የተተኮሱ ሮኬቶች በእስራኤል ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ተገለጸ።

ቁቤ ቲቪ ( መጋቢት 29፣ 2017) ፊንፊኔ
በትናንትናው ምሽት ከጋዛ የተተኮሱ ሮኬቶችና ሚሳኤሎች አስቀላን፣ ቴልአቪቭ እና ኡስዱድ በተባሉ የእስራኤል ከተሞች ላይ መጠነኛ ጉዳቶች ማድረሳቸው ተገልጿል።

እስራኤል እና ሀማስ ለሁለት ወራት ገደማ የተኩስ አቁም ስምምነት አድርገው የነበረ ሲሆን እስራኤል ከሳምንታት በፊት እንደ አዲስ በጀመረችው መጠነ ሰፊ የአየር ድብደባ በርካታ ንጹሃን መገደላቸው ተገልጿል።

በትናንትናው ዕለት ከጋዛ የተተኮሱ ሮኬቶች እና ሚሳኤሎች የእስራኤል ባለስልጣናት ሀማስን አዳክመነዋል (አጥፍተነዋል) ብለው በተደጋጋሚ ሲናገሩ የነበሩትን ቃላት ጥያቄ ውስጥ የከተተ ጉዳይ መሆኑ ተገልጿል።

ሀማስ በበኩሉ የአለማቀፉ ማህበረሰብ በጋዛ ንጹሀን ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት ለማስቆም ምላሽ መስጠት ባይችልም የጽዮናውያኑን የጅምላ ጥቃት እያየን እጃችንን አጣጥፈን አንቀመጥም ሲል ገልጿል።

በተጨማሪም የአለማቀፉ ማህበረሰብ እስራኤል በጋዛ ንጹሀን ላይ የምታደርገውን ጥቃት እንድታቆም ተቃውሞውን እንዲያሰማ ጥሪ አቅርቧል።

Address


Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Qubee TV- አማርኛ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Qubee TV- አማርኛ:

Shortcuts

  • Address
  • Telephone
  • Alerts
  • Contact The Business
  • Claim ownership or report listing
  • Want your business to be the top-listed Media Company?

Share