
15/12/2023
አፍሪካ በአንድ የመገበያያ ገንዘብ ለመጠቀም ልትመክር ነው
አዲስ አበባ፣ ታኅሣስ 2፣ 2016 የአፍሪካ ሀገራት በአንድ የመገበያያ ገንዘብ መጠቀም በሚያስችላቸው ሥርዓት ላይ ሊመክሩ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የሀገራቱ ምክክር የአፍሪካን የገንዘብ ኅብረት በፍጥነት ዕውን ለማድረግ እንደሚያስችል የአፍሪካ ኅብረት መረጃ አመላክቷል፡፡ የሥርዓቱ ዕውን መሆን የአፍሪካን ማዕከላዊ ባንክ ፣ የአፍሪካን ኢንቨስትመንት ባንክ እና የአፍሪካን የገንዘብ ፈንድ ለማቋቋም ያስችላል ተብሏል፡፡