Axis Law

Axis Law Legal Service

11/09/2024
ክስ ያለ ዳኝነት ክፍያ የሚቀርብበት ሁኔታ (ደሃ ደንብ) ማንኛውም ሰው በፍርድ ቤት ሊታይ የሚችል ጉዳይ ለፍርድ ቤት ሲያቀርብ ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ መክፈል ይጠበቅበታል። ሆኖም ባለጉዳዩ...
03/09/2024

ክስ ያለ ዳኝነት ክፍያ የሚቀርብበት ሁኔታ (ደሃ ደንብ)
 ማንኛውም ሰው በፍርድ ቤት ሊታይ የሚችል ጉዳይ ለፍርድ ቤት ሲያቀርብ ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ መክፈል ይጠበቅበታል። ሆኖም ባለጉዳዩ ክሱን በሚያቀርብበት ጊዜ ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ ለመክፈል አቅም የሌለው እንደሆነ ክሱን በነጻ ማቅረብ እንደሚችል በህጉ ተደንግጓል።
 ይህም የሰዎችን ፍትህ የማግኘት መብት በገንዘብ ምክንያት ቀሪ እንዳይሆን ለማስቻል የታሰበ ነው። ይህም ሲሆን በደሃ ደንብ ክሱን ለማቅረብ የሚጠይቅ ከሳሽ ደሃ መሆኑን ሊያመለክት የሚችል የሚገኝበትን የገንዘብ አቋም የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብና ማረጋገጥ ይጠበቅበታል።
 በቀረበው የደሃ ደንብ ላይ የሚቀርብ መቃወሚያ ካለ ፍርድ ቤቱ በቀረበው የደሃ ደንብ ላይ የሚያከራክር እና ማስረጃ የሚሰማ ሲሆን በዚህ ሂደትም ከሳሽ የዳኝነቱን ክፍያ የመክፈል አቅም እንዳለው ከተረጋገጠ ፍርድ ቤቱ መዝገቡን ይዘጋዋል።
 ይህ በሚሆንበት ጊዜ ከሳሽ ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ በመክፈል መዝገቡን የማንቀሳቀስ ወይንም ይግባኝ የመጠየቅ መብት የሚኖረው ሲሆን በተቀራኒው ፍርድ ቤቱ ከሳሽ ተገቢውን የዳኝነት ክፍያ ለመክፈል አቅም የለውም ብሎ ካመነ ክርክሩ በደሃ ደንብ አንዲቀጥል በሚሰጠው ብይን ላይ ተከሳሽ መዝገቡ እልባት ካገኘ በኋላ ይህንን ብይን እንደ አንድ የይግባኝ ምክንያት ከማቅረብ ውጪ በዚህ በይን ላይ በቀጥታ ይግባኝ መጠየቅ አይችልም።

ይርጋ ወይም የመብት መጠየቂያ የጊዜ ገደብ [𝙋𝙚𝙧𝙞𝙤𝙙 𝙤𝙛 𝙇𝙞𝙢𝙞𝙩𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣]ይርጋ ማለት አንድ መብቱ ወይንም ጥቅሙ የተነካበት ሰው ይህን ጥያቄውን ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችልበት ...
17/08/2024

ይርጋ ወይም የመብት መጠየቂያ የጊዜ ገደብ [𝙋𝙚𝙧𝙞𝙤𝙙 𝙤𝙛 𝙇𝙞𝙢𝙞𝙩𝙖𝙩𝙞𝙤𝙣]

ይርጋ ማለት አንድ መብቱ ወይንም ጥቅሙ የተነካበት ሰው ይህን ጥያቄውን ስልጣን ባለው ፍ/ቤት ማቅረብ የሚችልበት በህግ ተለይቶ የተቀመጠ የጊዜ ገደብ ነው፡፡ ይህም ከሳሽ በተገቢ ትጋት መብቱን እንዲጠይቅ ለማስቻል፣ ተከሳሽ ከጊዜ ርዝመት የተነሳ የቀረበበትን ክስ ለመከላከል የሚያስችሉ ማስረጃዎችን እንዳያጣ ለማድረግ፣ እንዲሁም ከቅን ልቦና ዉጪ የሚቀርቡ ክሶችን ለማስቀረት ህጉ ያስቀመጠው መፍትሔ ነው። ለማሳያ ያክል ከብዙ በጥቂቱ በፍትሐ ብሄር ህጋችን እንዲሁም በሌሎች ህጎች የተቀመጡ የጊዜ ገደቦች እንመለከት፤
ውልን መሰረት ያደረገ ክስ በ 10 ዓመት ውስጥ፤ ከውል ዉጪ የሚመጭ ሃላፊነትን መሰረት ያደረገ ክስ በ 2 ዓመት ውስጥ፤ ውርስን መሰረት ያደረገ ክስ ክሱ በወራሾች መሀከል ከሆነ በ 3 ዓመት ዉስጥ፤ ውርሱ ሲከፈት ከሳሽ በመብቱ ሊሰራበት የማይችል ከነበረ በመብቱ መስራት ከቻለበት ጊዜ አንስቶ በ15 አመት ዉስጥ፤ ክርክሩ ወራሽ በሆነና ባልሆነ ሰው የሆነ እንደሆነ በ10 አመት ዉስጥ፤ ንብረትን መሰረት ያደረገ ክስ ማለትም ንብረቱ የተወሰደበት ወይንም በይዞታው ላይ ሁከት የተፈጠረበት ሰው በ2 ዓመት ዉስጥ፤ በአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ የስራ ውሉ ያለአግባብ ተቋርጧል በሚል የሚቀርብ ክስ ውሉ በተቋረጠ በ3 ወር ዉሰጥ፤ የደሞዝ የትርፍ ሰአት እንዲሁም ሌሎች ክፍያን የተመለከቱ ጉዳዮች በ6 ወራት ዉሰጥ፤ የስራ ውል መቋረጥ በተመለከተ የሚቀርብ ማንኛውም ጥያቄ በ6 ወራት ዉሰጥ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ለመሆኑ በይርጋ ቀሪ የማይሆኑ መብቶች ይኖሩ ይሆን?

https://t.me/MrYenesewD/172

   በገበያ ላይ እጥረት ያለበት መሆኑ የተገለፀን የንግድ ዕቃ ወይም ሸቀጥ በማከማቸት ወይም በመደበቅ ወይም በሕገ ወጥ መንገድ በማጓጓዝ የተሳተፈ አሽከርካሪ እስከ ብር 50 ሺህ በሚደርስ የ...
14/08/2024



በገበያ ላይ እጥረት ያለበት መሆኑ የተገለፀን የንግድ ዕቃ ወይም ሸቀጥ በማከማቸት ወይም በመደበቅ ወይም በሕገ ወጥ መንገድ በማጓጓዝ የተሳተፈ አሽከርካሪ እስከ ብር 50 ሺህ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እንደሚቀጣ የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ይደነግጋል።
ተሽከርካሪው የንግድ እቃዎችን ለመደበቅ እንዲያስችል ሆኖ የተሰራ ወይም የተለወጠ ወይም መደበቂያ አካል የተገጠመለት ከሆነ ወይም የተሽከርካሪው ባለቤት የሕገ ወጥ ማጓጓዝ ድርጊቱን እያወቀ እንዳይፈፀም ለመከላከል ወይም ለማስቆም ተገቢውን እርምጃ ሳይወስድ የቀረ እንደሆነ ተሽከርካሪው ከንግድ እቃዎቹ ጋር ይወረሳል።

#መውረስ #ንግድ #ቅጣት #ወንጀል #ሾፌር የሹፌሮች አንደበት #ተሽከርካሪ #ማከማቸት #ህግ #ማሸግ #ጠበቃ

የግል ድርጅት ሰራተኞች የደረሳባቸውን አስተዳደራዊ በደል ወደ ህዝብ እንባ ጠባቂ ማመልከት እንደሚችሉ ያውቃሉ? በዜጎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎች የሚቆሙበትን ወይም የሚታረሙ...
13/08/2024

የግል ድርጅት ሰራተኞች የደረሳባቸውን አስተዳደራዊ በደል ወደ ህዝብ እንባ ጠባቂ ማመልከት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

በዜጎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎች የሚቆሙበትን ወይም የሚታረሙበትን ቀልጣፋ አሰራር በመዘርጋት ለመልካም አስተዳደር መሰረት መጣልን አላማ አድርጎ በአዋጅ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት በማስፋት በግል ድርጅቶች የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችን አቤቱታ መቀበል እና ምርመራ ማካሄድ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት በስራ ላይ የቆየውን የተቋሙን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 1142/2011 ለማሻሻል አዋጅ ቁጥር 1307/2016 ፀድቋል።

ይህ ማሻሻያ አዋጅ የያዛቸው ዋና ዋና ለውጦች ተቋሙ በግል ድርጅቶች ጭምር ስልጣን እንዲኖረው ከማድረግ ጋር የተያያዙ ሲሆኑ እነሱም፤
1. ስልጣን ባለው አካል የወጣ እና በስራ ላይ ያለ ሕግን በመፃረር በግል ድርጅቶች ውስጥ የሚፈፀሙ ድርጊቶች ወይም የሚሰጥ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የአስተዳደር በደል ተደርገው የሚቆጠሩ መሆኑን አካቷል።
2. በግል ድርጅቶች ውስጥ የአስተዳደር ወይም የአስተዳደር ነክ አገልግሎት የሚሰጥ አካል ተመርማሪ አካላት በሚለው ትርጓሜ ውስጥ እንዲካተት አድርጓል።
3. የግል ድርጅት ሲባል በንግድ ህጉ የተገለፁት የንግድ ማሕበር አይነቶች ሆነው የማምረት፣ የማከፋፈል፣ የአገልግሎት እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ተግባሮችንና ከእነዚሁ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በንግድ መልክ የሚሰሩትን ሁሉ እንዲያጠቃልል አድርጓል።
4. አዋጁ በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት እና በግል ድርጅቶች በሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችና ባለሥልጣኖች እና ኃላፊዎች ላይ ተፈፃሚነት እንደሚኖረው ደንግጓል።
5. ለተቋሙ በግል ድርጅቶች ውስጥ የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደል አቤቱታዎችን የመቀበል እና ምርመራ የማካሄድ ስልጣን እና ኃላፊነት ሰጥቷል።
ተቋሙ በፍርድ ቤቶች ወይም በሕግ የመዳኘት ስልጣን በተሰጣቸው አካላት በመታየት ላይ ያሉ ወይም ታይተው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን የመቀበልም ሆነ የመመርመር ስልጣን የሌለው መሆኑ፣ በስልጣኑ ስር በሚወድቁት ጉዳዮችም ቢሆን የመጨረሻ ውሳኔው ምክረ ሃሳብ ከማቅረብ ያልዘለለ፣ አስተዳደራዊ፣ የፍታብሔር ወይም የወንጀል ተጠያቂነት የመፍጠር አይነተኛ ስልጣን የሌለው መሆኑ ሊኖረው የሚችለውን አበርክቶ በእጅጉ የሚገድብ ቢሆንም ዜጎች ደረሰብን የሚሉትን አስተዳደራዊ በደል የግል ተቋማትን ጨምሮ ብሶታቸውን ለማሰማት ተጨማሪ የመፍትሔ አማራጭ ሆኖ እንደሚያገለግል ግን ጥርጥር የለውም።


#ህግ

  አንድ ሰው ለሌላ ሰው ኃላፊነት ወይም ወደፊት ሊመጣበት ለሚችለው ኃላፊነት ዋስ በሚሆንበት ጊዜ በዋስትና ውሉ ላይ ግዴታ የተገባበት የኃላፊነት መጠን ወይም ልኩ ምን ያህል እንደሆነ በዋስት...
12/08/2024



አንድ ሰው ለሌላ ሰው ኃላፊነት ወይም ወደፊት ሊመጣበት ለሚችለው ኃላፊነት ዋስ በሚሆንበት ጊዜ በዋስትና ውሉ ላይ ግዴታ የተገባበት የኃላፊነት መጠን ወይም ልኩ ምን ያህል እንደሆነ በዋስትና ውሉ ላይ በገንዘብ ካልተገለፀ በስተቀር ዋስትናው በህግ ፊት አይፀናም።
ዋስ የሆነው ሰው ለዋስትና ምክንያት የሆነውን ንብረት ለመተካት በሚል ግዴታ የገባ ቢሆንም እንኳ የግዴታው መጠን እስከምን ያህል እንደሆነ በገንዘብ ተገልፆ በውሉ ላይ ካልተመለከተ የዋስትና ውሉ ፈራሽ ነው።

  በአዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መሰረት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የሚቋረጥባቸው መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፤ 1. በመደበኛው የውል አተረጓጎም መሰረት የሚኖር የኪ...
11/08/2024



በአዲሱ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ መሰረት የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል የሚቋረጥባቸው መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፤
1. በመደበኛው የውል አተረጓጎም መሰረት የሚኖር የኪራይ ውል መቋረጥ፦ አከራይ እና ተከራይ የተስማሙበት የኪራይ ውል ዘመን ሲጠናቀቅ የኪራይ ውሉ ያለተጨማሪ ስርዓት ይቋረጣል። የኪራይ የውል ዘመን ከሁለት አመት ላነሰ ጊዜ ሊደረግ እንደማይችል በአዋጁ መደንገጉን ልብ ይበሉ።
2. አከራይ እና ተከራይ በሚያደርጉት ስምምነት የሚኖር የኪራይ ውል መቋረጥ:- አከራይ እና ተከራይ የሚስማሙ ከሆነ የተለየ ስርዓት መከተል ሳይጠበቅባቸው ውሉን በፈለጉት ጊዜ ሊያቋርጡት ይችላሉ።
3. በተከራይ አነሳሽነት የሚደረግ የኪራይ ውል መቋረጥ:- ተከራይ ቤቱን መልቀቅ ሲፈልግ የሁለት ወር የቅድሚያ ማስታወቂያ በመስጠት ውሉን ማቋረጥ ይችላል።
4. በአከራይ አነሳሽነት የሚደረግ የኪራይ ውል መቋረጥ:- አከራዩ ውሉን ለማቋረጥ ሁለት አማራጮች ይኖሩታል። የመጀመሪያው አማራጭ በማስጠንቀቂያ የኪራይ ውሉን ማቋረጥ ሲሆን ይህ ተፈፃሚ የሚሆነው ቤቱ በውርስ፣ በሽያጭ፣ በዕዳ፣ ወይም በሌላ ህጋዊ ምክንያት ለሶስተኛ ወገን በሚተላለፍበት ወቅት ነው። ሁለተኛው አማራጭ ያለማስጠንቀቂያ የኪራይ ውሉን ማቋረጥ ሲሆን ይህ አማራጭ ተፈፃሚ የሚሆነውም ተከራዩ ከሚከተሉት ጥፋቶች ውስጥ አንዱን መፈፀሙ ሲረጋገጥ ነው፤
ሀ/ የመክፈያ ጊዜውን ለመጀመሪያ ከሆነ ከአስራ አምስት ቀን ካሳለፈ፣
ለ/ ለሁለተኛ ጊዜ ከሆነ 7 ቀን ካሳለፈ፣
ሐ/ ቤቱን ያለአከራዩ ፈቃድ ከመኖሪያነት ውጪ ወይም ለንግድ ስራ የሚጠቀምበት ከሆነ፣
መ/የአካባቢውን ሰላምና ጸጥታ በተደጋጋሚ የሚያውክ ከሆነ፥፣
ሠ/ በቤቱ ውስጥ የወንጀል ተግባር የሚፈጽም ወይም ቤቱን ለወንጀል መፈጸሚያ የሚጠቀምበት ከሆነ፣
ረ/ አስቦ ወይም በቸልተኛነት በቤቱ ላይ በመደበኛ አገልግሎት ከሚደርሰው እርጅና ያለፈ የቤቱን ደህንነት እና ዋጋ ግልፅ በሆነ ሁኔታ የሚቀንስ ወይም አደጋ ላይ የሚጥል ጉልህ ጉዳት ያደረሰ እንደሆነ፣ ወይም
ሰ) በሌላ ተመሳሳይ ምክንያት፤

#1320 #ጠበቃ
https://t.me/MrYenesewD/166

አባትነትን በፍርድ ውሳኔ ከማረጋገጥ ጋር በተገናኘ በሚቀርብ አቤቱታ እና ክርክር ወቅት የዲ.ኤን.ኤ (DNA) ምርመራ እንዲደረግለት በመጠየቅ ክርክር የሚያቀርብ ተከራካሪ፣ ለዚሁ የህክምና ምር...
11/08/2024

አባትነትን በፍርድ ውሳኔ ከማረጋገጥ ጋር በተገናኘ በሚቀርብ አቤቱታ እና ክርክር ወቅት የዲ.ኤን.ኤ (DNA) ምርመራ እንዲደረግለት በመጠየቅ ክርክር የሚያቀርብ ተከራካሪ፣ ለዚሁ የህክምና ምርመራ የሚያስፈልገውን ወጪ የመሸፈን ግዴታ ይኖርበታል። ዲ.ኤን.ኤ ምርመራን እንደማስረጃ የቆጠረ ተከራካሪ ማስረጃው በእኔ ቢቆጠርም ወጪውን መሸፈን ስለማልችል ምርመራው መደረግ ያለበት በሌላኛው(ዲ.ኤን.ኤ ምርመራን ባልጠየቀው) ተከራካሪ ወጪ ነው የሚል ክርክር ከመሰረታዊ የማስረጃ ህግ መርህ የሚቃረን ነው። የዲ.ኤን.ኤ (DNA) ምርመራ የህክምና ዘዴን (ሳይንስን) መሰረት በማድረግ የሚከናወን በመሆኑ በማስረጃ ዝርዝር ተካቶ ከሆነ በቂ እና ህጋዊ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ሳይሰማ ሊታለፍ አይገባም።

https://t.me/MrYenesewD

Legal Service | ህግ አገልግሎት

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅን ያሻሻለው አዋጅ ቁ. 1307/2016 ምን ምን ለውጦች ይዟል?በዜጎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎች የሚቆሙበትን ወይም የሚታ...
06/07/2024

የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ማቋቋሚያ አዋጅን ያሻሻለው አዋጅ ቁ. 1307/2016 ምን ምን ለውጦች ይዟል?

በዜጎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎች የሚቆሙበትን ወይም የሚታረሙበትን ቀልጣፋ አሰራር በመዘርጋት ለመልካም አስተዳደር መሰረት መጣልን አላማ አድርጎ በአዋጅ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት በማስፋት በግል ድርጅቶች የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችን አቤቱታ መቀበል እና ምርመራ ማካሄድ አስፈላጊነቱ ስለታመነበት በስራ ላይ የቆየውን የተቋሙን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 1142/2011 ለማሻሻል አዋጅ ቁጥር 1307/2016 ፀድቋል።

ይህ ማሻሻያ አዋጅ የያዛቸው ዋና ዋና ለውጦች ተቋሙ በግል ድርጅቶች ጭምር ስልጣን እንዲኖረው ከማድረግ ጋር የተያያዙ ሲሆኑ እነሱም፤
1. ስልጣን ባለው አካል የወጣ እና በስራ ላይ ያለ ሕግን በመፃረር በግል ድርጅቶች ውስጥ የሚፈፀሙ ድርጊቶች ወይም የሚሰጥ ውሳኔ ወይም ትዕዛዝ የአስተዳደር በደል ተደርገው የሚቆጠሩ መሆኑን አካቷል።
2. በግል ድርጅቶች ውስጥ የአስተዳደር ወይም የአስተዳደር ነክ አገልግሎት የሚሰጥ አካል ተመርማሪ አካላት በሚለው ትርጓሜ ውስጥ እንዲካተት አድርጓል።
3. የግል ድርጅት ሲባል በንግድ ህጉ የተገለፁት የንግድ ማሕበር አይነቶች ሆነው የማምረት፣ የማከፋፈል፣ የአገልግሎት እና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ተግባሮችንና ከእነዚሁ ጋር የተያያዙ ሥራዎችን በንግድ መልክ የሚሰሩትን ሁሉ እንዲያጠቃልል አድርጓል።
4. አዋጁ በየደረጃው በሚገኙ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት እና በግል ድርጅቶች በሚፈፀሙ የአስተዳደር በደሎችና ባለሥልጣኖች እና ኃላፊዎች ላይ ተፈፃሚነት እንደሚኖረው ደንግጓል።
5. ለተቋሙ በግል ድርጅቶች ውስጥ የሚፈፀሙ የአስተዳደር በደል አቤቱታዎችን የመቀበል እና ምርመራ የማካሄድ ስልጣን እና ኃላፊነት ሰጥቷል።
ተቋሙ በፍርድ ቤቶች ወይም በሕግ የመዳኘት ስልጣን በተሰጣቸው አካላት በመታየት ላይ ያሉ ወይም ታይተው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ጉዳዮችን የመቀበልም ሆነ የመመርመር ስልጣን የሌለው መሆኑ፣ በስልጣኑ ስር በሚወድቁት ጉዳዮችም ቢሆን የመጨረሻ ውሳኔው ምክረ ሃሳብ ከማቅረብ ያልዘለለ፣ አስተዳደራዊ፣ የፍታብሔር ወይም የወንጀል ተጠያቂነት የመፍጠር አይነተኛ ስልጣን የሌለው መሆኑ ሊኖረው የሚችለውን አበርክቶ በእጅጉ የሚገድብ ቢሆንም ዜጎች ደረሰብን የሚሉትን አስተዳደራዊ በደል የግል ተቋማትን ጨምሮ ብሶታቸውን ለማሰማት ተጨማሪ የመፍትሔ አማራጭ ሆኖ እንደሚያገለግል ግን ጥርጥር የለውም።

ጉዲፈቻ ምንድን ነው? እንዴትስ ይቋቋማል?ጉዲፈቻ ማለት ለችግር በተጋለጠና በተፈጥሮአዊ ወላጆቹ ሊያድግ ባልቻለ ህጻንና በጉዲፈቻ አድራጊ ወላጆች መካከል ህግን መሰረት አድርጎ የሚመሰረት ቋሚ ...
05/07/2024

ጉዲፈቻ ምንድን ነው? እንዴትስ ይቋቋማል?
ጉዲፈቻ ማለት ለችግር በተጋለጠና በተፈጥሮአዊ ወላጆቹ ሊያድግ ባልቻለ ህጻንና በጉዲፈቻ አድራጊ ወላጆች መካከል ህግን መሰረት አድርጎ የሚመሰረት ቋሚ የወላጅነትና የልጅነት ግንኙነት ነው።

የተሻሻለው የቤተሰብ ህግ በአንቀፅ 193 የውጭ ዜጎች በጉዲፈቻ አድራጊነት ሊቀርቡ እንደሚችሉ ገልፆ የነበረ ቢሆንም ይህንኑ አንቀፅ ለመሻር በወጣው አዋጅ ቁጥር 1070/2010 መሰረት የውጭ ዜጎች በጉዲፈቻ አድራጊነት ሊቀርቡ የሚችሉበትን እድል ዝግ አድርጓል። ሆኖም ትውልደ ኢትዮጵያዊ ሆኖ በዜግነት ግን የሌላ አገር ዜግነት ያለው ቢሆንም ለልጁ ደህንነት እና አስተዳደግ አስተማማኝ ማጣራት ከተደረገ በኋላ ሊፈቀድ እንደሚችል የፌ/ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በመ/ቁ. 189201 አስገዳጅ የህግ ትርጉም ሰጥቷል።

የጉዲፈቻ ግንኙነትን ለማቋቋም ምን ምን ጉዳዮች ሊሟሉ ይገባል?

ስለ ጉዲፈቻ ተደራጊ ህፃናት

§ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህጻናትን እንደየችግራቸው መጠን በሚመለከተው የመንግስት ተቋም በመመዝገብና በመመልመል በቅደም ተከተል መረጃቸው ተደራጅቶ ይቀመጣል።
§ ወላጆቻቸው በህይወት የሌሉ ከሆነ ይህንን የተመለከተ ማስረጃ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ወይም ከማዘጋጃ ቤት፣ ከቀበሌ(ወረዳ)፣ ከእምነት ተቋም ወይም ወላጆች የጠፉ ከሆኑ ከፍርድ ቤቶች መቅረብ ይኖርበታል፡፡
§ የህጻናቱን ጉዲፈቻ በተመለከተ ስምምነት ሊሰጡ የሚገባቸው ወደላይ የሚቆጠሩ አያቶች፣ ወደጎን የሚቆጠሩ አጎትና አክስት በተጨማሪም ስምምነት መስጠት የሚችሉ የህጻናቱ ከ18 ዓመት በላይ የሆኑ ወንድምና እህት ዝምድናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ከሚመለከተው የመንግስት አካል በማቅረብ ስምምነት መስጠት ይችላሉ፡፡
§ በህግ የሞግዚትነት ስልጣን የተሰጣቸው ግለሰቦች፤ የግል ወይም የመንግስት ህጻናት ማቆያና ማሳደጊያ ተቋማት እና የህጻናትን መብትና ደህንነት ለመከታተል ስልጣን የተሰጣቸው አካላት በጉዲፈቻው ላይ ስምምነታቸውን ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
§ ህጻናት ተጥለው ሲገኙ ህጻናቱን ያነሳው የአካባቢው የፖሊስ ጽ/ቤት ተጥለው የተገኙ ስለመሆናቸው ተገቢውን ማስረጃ መስጠት አለበት፡፡
§ ሁለቱም ወላጆቹ በህይወት ያሉ ከሆነ ሁለቱም በማይድን በሽታ የተያዙ መሆኑ በህክምና ማስረጃ መረጋገጥ ወይም ህፃኑን ለመንከባከብ በኢኮኖሚ ብቁ አለመሆናቸውን ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ህጋዊ ማስረጃ በማቅረብ የህጻኑን ደህንነት መጠበቅ የማያስችል ችግር መኖሩ መረጋገጥ አለበት።
§ በህይወት ያለው ወላጅ ልጁን በጉድፈቻ ለመስጠት ሲስማማ ስለ ሌላኛው ወላጅ ግልጽና የማያሻማ ሕጋዊ ማስረጃ ከሚመለከተው የፍትህ አካል ማቅረብ አለበት፡፡
§ ሌላኛው ወላጅ በሕይወት የሌለ ከሆነ ከእምነት ተቋማት፤ ከማዘጋጃ ቤት ወይም ወሳኝ ኩነቶች እንዲሁም ጠፍቶ ከሆነ የፍ/ቤት ማስረጃ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
§ ከጋብቻ ውጭ ስለሚወለዱ ሕፃናት አባታቸው በግልፅ የማይታወቅና እናታቸው ሕፃኑን ለማሳደግ የማትችል መሆኑን የሚገልጽ የህፃናትን ጉዳይ ከሚከታተል የአካባቢው የመንግስት አካል ወይም ከማህበራዊ ፍርድ ቤት የተሰጠ ማስረጃ መቅረብ አለበት፡፡
§ በህይወት ያለው ወላጅ ህጻኑን ለጉዲፈቻ ለመስጠት የፈለገበት ወይም የተገደደበት ምክንያቶችን የህጻናትን ጉዳይ ለመከታተል ስልጣን የተሰጠው የመንግስት አካል ወይም ከማህበራዊ ፍርድ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሊቀርብ ይገባል፡፡
§ በመጨረሻም ህጻኑን በተመለከተ ስላለበት ችግር፣ ወደ ህጻናት ማሳደጊያ የገቡበት ምክንያት በአካባቢው የሚገኝ የህጻናትን ጉዳይ ለመከታተል ስልጣን የተሰጠው የመንግስት አካል የሰጠው የጽሁፍ ማረጋገጫ መቅረብ አለበት::
አስፈላጊ ሰነዶች
§ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ የጉዲፈቻ ውል፤
§ የፓስፖርት መጠን ያለው የህፃኑ አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ
§ የሕፃኑ የሥጋ ዘመዶች ወይም ሞግዚቶች ወይም አሳዳጊዎች ፎቶግራፍ
§ የህጻናት የልደት ማስረጃ፣ አጭር የህይወት ታሪክ፣ የጤና ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የጤና ሁኔታ ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የገቢ ሁኔታ ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ ከወንጀል ነፃ የመሆን ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የትዳር ሁኔታ ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የእድሜ ማስረጃ
§ የጉዲፈቻ አድራጊው/ዋ/ዎች/ የስነልቦናና ማህበራዊ መስተጋብር ጥናት ማስረጃ
ዋና ዋና ሂደቶች
§ አስፈላጊ ሰነዶችን አሟልቶ በፍ/ቤት የጉዲፈቻ ፋይል መክፈት
§ ፍ/ቤት ጉዲፈቻውን ካፀደቀው በኋላ በአቅራቢያው ባለው የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ቀርቦ ጉዲፈቻውን ማስመዝገብ

05/07/2024

የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ እስከ ሐምሌ 24/2016 ዓ.ም ድረስ ተራዘመ
የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 መውጣቱን ተከትሎ እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዋጁ ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 7/2016 በማውጣት ሰኔ 1/2016 ዓ.ም ጀምሮ በ30 ቀናት ውስጥ ምዝገባ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞ በሁሉም ክፍለከተማ እና ወረዳዎች የመኖሪያ ቤት ኪራይ ውል ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ከሰኔ1- ሰኔ 26/2016 ዓ.ም ድረስ 248,469 የኪራይ ውል የተመዘገበ ሲሆን አሁንም ምዝገባው እንደቀጠለ የሚገኝ መሆኑንም የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያሳውቃል።
በመሆኑም በርካታ ተመዝጋቢ በመኖሩ ምክንያት ቀኑ እንዲራዘም በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጥያቄው በስፋት በመነሳቱ እና ቀሪ ያልተመዘገበው የተከራይ አከራይ ውል እስከ ሰኔ 30/2016 መዝግቦ ለማጠናቀቅ አዳጋች እንደሆነ ተቋሙ የተገነዘበ ስለሆነ በጊዜ ገደቡ ሳይመዘገብ የሚቀር ውል እንዳይኖር ለማስቻል የምዝገባ ጊዜውን ማራዘም በማስፈለጉ የምዝገባ ጊዜው እስከ ሐምሌ 24/2016ዓም መራዘሙን ቢሮው ይገልፃል።
የግል መኖሪያ ቤት አከራይም ሆነ ተከራይ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ሳይዘናጉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሳይጠናቀቅ ጊዜያቸውን ተጠቅመው እንዲመዘገቡ ቢሮው በድጋሚ ያሳስባል።
የውል ምዝገባው ከመደበኛ የስራ ሰአት ውጪ በምሽት ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ የሚካሄድ ስለሆነ ተመዝጋቢዎች ሳይጨናነቁ በተመቻቸው ሰአት መሄድ እና መመዝገብ ይችላሉም ተብሏል።

Address

Bole Medhanialem Church, Abrhams Building, 5th Floor
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 16:00
Tuesday 08:30 - 04:00
Wednesday 08:30 - 16:00
Thursday 08:30 - 16:00
Friday 08:30 - 16:00
Saturday 09:00 - 15:00

Telephone

+251913375015

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Axis Law posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to Axis Law:

Share