
13/05/2025
ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በኮንሶ ዞን የልማት ስራዎችን በመጎብኘት ላይ ይገኛሉ
ርዕሰ መስተዳድሩ በከተማ ውስጥ ያለውን የውሃ ችግር በጊዚያዊነት ለመቅረፍ በማሰብ በክልሉ መንግስት እየተሰራ የሚገኘውን የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ጎብኝተዋል።
ፕሮጀክቱ ስራውን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በመጨረስ የከተማውን ውሃ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጉብኝት ወቅት የተገለፀ ሲሆን በከተማው የለውን የውሃ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የክልሉ መንግስት አቅዶ እየሰራ መሆኑ ተገልጿል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በመቀጠል በኮንሶ ቴክኒክና ሞያ ኮሌጅ በወጣቶች እየተመረተ የሚገኘውን ቴራዞ ማምረቻ ጎብኝተዋል ኮሌጅ ያለበትን ሁኔታ ጎብኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ወጣቶች እንዲህ አይነት ምርቶችን በራስ አቅም ማምረት መጀመራቸው የሚያስደስት መሆኑነው ገልፀው በጥራት ተወዳዳሪ ከሆነ ምርቱን ወደ ሌላ ቦታዎች ወስዶ በመሸጥ ተጠቃሚ መሆን እንደሚቻል አስረድተዋል።