
07/08/2025
የአዲስ አበባ ልማት ማንም የማይሽረው ታሪካዊ ስኬት ነው
ያኔ ቅርስ ፈረሰ ሀገር ተናደ ብለው እንዲጮሁ የተመቻቹና በደቦ እዬዬውን ያስነኩት የዳያስፖራ የኪቦርድ ታጋዮች ዛሬ የከተማዋ ገጽታ ከዝንብ መራቢያነትና ከመንገድ ሽንት ቤትነት ተላቆ እንዲህ ተለውጣ፣ አምራና ተውባ ሲያዩዋት ተሳስተን ነበር ይሉ ይሆን? ወይስ ካፈርኩ አይመልሰኝ ብለው በምን ዋጋ አለው ድባቴ ውስጥ ይቀጥላሉ?
ለማንኛውም እንዲህ ከመሰሉ ለሰው ልጅ ከማይመቹ የሰፈር ሁኔታዎች ውስጥ የከተማችን አስተዳደርና የመንግስት ጠንካራ ፖሊሲ አዲስ አበባን ነፃ እያወጣ ነው! ልማት አስቀድሞ የሚለውጠው ሰውንና አከባቢን ነው የሚለው አዲስ አበባ ላይ በማይፋቅ ዘላለማዊ ማህተም ተመቶ ተረጋግጧል። ሊያሻር የማይችል ታሪካዊ ስኬት ተመዝግቧል!