
17/08/2024
አዎ እናወቃለን እርሶ ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራርነትን ከለቀቁ በኋላ እግር ኳሳችንን ዉጤት እንደ ሰማይ ርቆታል። የአፍሪካ ዋንጫ ያመለጠን፣ ባለፈዉ ደግሞ የኳታር አለም ዋንጫን አይናችን እያየ አርጀንቲና የገባዉ ፣ ስንት የሚያስቆጩ ዋንጫዎች ለጥቂት ያመለጡን እርሶ ሌላዉም አካል ገብቶ አመራርነቱን ይሞክረዉ ብለዉ ስልጣኖትን በፍቃደኝነት በማስረከቦ መሆኑን ሁሉም የሚረዳዉ ሀቅ ነዉ። እስኪ አሁንም ይሄ በሆነዉም ባልሆነዉም የሚጮኽ ህዝብ በአትሌትክስ ዉጤት ድርቀት እንዲመታ እና 'የዶ/ር አሸብር ያለህ!' ብሎ ፈልጎና አፈላልጎህ አንተ ምራን ብሎ ሰልፍ እንዲወጣ አንዴ ዝም ብለህ በፍቃደኝነትህ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አመራርነትህን አስረክበዉ።
እርሶ እኮ የአትሌቲክሳችን የጀርባ አጥንት፣ በአመራርነት ዘመኖ የመጣዉ አስደናቂ ዉጤት መቼም ቢሆን ከእርሶ አመራርነት ዉጭ መምጣት እንደማይችል፣ ለዚህ ዉጤት መገኘት ግዜዎትን ብቻም ሳይሆን የግል ንብረቶን ጭምር መስዋት ያደረጉ፣ ብዙ ያልተነገረሎት ታሪክ ባለቤት፣ ሀገር ወዳድ እና ህዝብ አክባሪ፣ በተለይ በተለይ ስነ ምግባሮ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት ተደምሮበት ትዉልድን የሚያንፅ፣ ትችቶችን በሆደ ሰፊነት የመመልከቶ ድንቅ ብቃት፣ እንዲሁም በስፖርቱ ዘርፍ የሰጡት በሳል አመራርነት ወደ ፖለቲካዉ ቢመጣ ሀገራችንን በልማቱም፣ በመልካም አስተዳደሩም ሆነ በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የተሻለ እንደሚያደርጉ የምንተማመንቦት መሪያችን ኖት❗️