ELF Production & Events

ELF Production & Events An organization established to realize the dream of organizing various events in a beautiful manner.

08/11/2024
ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄንተጠግቼ ሳውራቸው በጣም እያረጁ ነው ግን ያ የሀገር ፍቅር እንዳለ ነው''ጋሼ  አልደከሞትም ብዙ ኮንሰርት ላይ ነበሩ ድካም ፊቶት ላይ አየሁ '' '' አዎ ፈረንሳየም ...
12/10/2024

ዶክተር ሙላቱ አስታጥቄንተጠግቼ ሳውራቸው በጣም እያረጁ ነው ግን ያ የሀገር ፍቅር እንዳለ ነው
''ጋሼ አልደከሞትም ብዙ ኮንሰርት ላይ ነበሩ ድካም ፊቶት ላይ አየሁ ''
'' አዎ ፈረንሳየም ነበረኝ ሰርዤ ነው ይደክማል ግን ብዙ ሰራሁ የተሸለምኩትን አየሽ? 40 አመታት የፈጀ ልፋት ነው ዛሬ ኢትዮጵያ ብቻ አደለችም አፍሪካ ኩራት እና ታሪክ ነህ አሉኝ ግን እዚ ለመድረስ ለፍቻለሁ ጥሩነው ቢደክመኝም ይሁን እወደዋሁ '' አሉኝ
እርጅናው እየተጫጫናቸው ነው ሳውራቸው ድምጼ ከፍ አድርጌ ነበር ፡፡ ገረመኝ በጣም ብዙ አሰላሰልኩኝ ብቻ እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡
ቆንጆ የጃዝ ምሽት አሳለፍን....

ELF
18/09/2024

ELF

The Goat life: ሳኡዲን የናጠው አሳዛኙ የህንድ ስደተኛ ፊልም !ነጂብ ሙሀመድ ህይወቱ ባክኖ የቀረው ከርታታ ከህንድ ከራላ እንደ ጀሀነብ እስከሚፋጀው የሳኡዲ በረሀ !ነጂብ ሙሀመድ ሙስ...
01/09/2024

The Goat life: ሳኡዲን የናጠው አሳዛኙ የህንድ ስደተኛ ፊልም !
ነጂብ ሙሀመድ ህይወቱ ባክኖ የቀረው ከርታታ ከህንድ ከራላ እንደ ጀሀነብ እስከሚፋጀው የሳኡዲ በረሀ !

ነጂብ ሙሀመድ ሙስሊም ህንዳዊ ነው። ድህነት ባኮሰሰው ኑሮው ተደስቶ የሚኖር አግብቶ የልጁን መወለድ የሚጠባበቅ የቤተሰቡ ምሰሶ ነበር። በዚያ ላይ የሚወዳትና የምትወደው እናቱን አብሮ ያኖራል። ታድያ ባለቤቱ ግን ልጇን ሶትወልድ በዚህ በኮሳሳ ጎጆ መውለድ አልሻችም ነበርና ምን እናድርግ ስትል ለባሏ ነጅብ ታጫውተዋለች።
ህንድ ህይወት በቀላሉ የሚቀየርባት ሀገር አይደለችም በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ድሀዎችን በመያዝ በአለም የሚቀድማት የሌላት ህንድ ዜጎቿ ህይወታቸውን ለመቀየር መሰደድ እጣፈንታቸው ነው። እናም ነጅብም ለመሰደድ ወሰነ። ለዚህ ምርጫው ያደረጋት ደግሞ ሙስሊሟን ሀገር ሳኡዲ አረቢያን ነበር።

ሳኡዲ ገብቶ ህይወቱን ሊቀይር የባለቤቱን ህልም ሊያሳካ የእናቱንም ህይወት ሊያቀና ወደ ሳኡዲ የሚወስዱት ደላሎች ጋር ተገናኘ። እና በዚያ ጉዞ ላይ ሔ
ሌላኛውን ህንዳዊ ሀኪምን ያገኘዋል። እናትና ባለቤቱ ነጅብን ለሀኪም አደራ ብለው እያለቀሱ በእንባ ይሸኟቸዋል። ወደ ጨለማው ህይወት!

ነጅብና ሀኪም ሳኡዲ እንደደረሱ አንድ የሳኡዲ ሰው ያገኛቸዋል። እነርሱም ቀርበው ያናግሩታል። ግና እርሱ ቋንቋቸውን አያውቅ እነርሱን ቋንቋውን አያውቁ መጯጯህ ብቻ ይሆናል። በዚህ ጊዜ ነው የሳኡዲው ሰው ለምን ወስጄ አላሰራቸውም ይልና በመኪናው ጭኖ ጭው ወዳለው በረሀ ማንንም ወደሌለበት የወሰዳቸው። እዚያም ሀኪምን ለወንድሙ ልጅ ነጂብን ለራሱ ወሰደና ነጣጠላቸው። ሁለቱ ተላቀሱ ለመኑ ግና የሚለምኑበትን ቋንቋ አረቦቹ አይረዱም። በዚህ ጊዜ ነጅብ ወደ ሳኡዲ ለመምጣት የከፈለውን ገንዘብና ህጋዊ መግቢያ ለአረቡ ያሳየዋል አረቡን ወረቀቱን ይቀበልና ቀዳዶ ይጥልበታል። በዚህ ጊዜ ነው ነጅብ ያለመው ቀርቶ ያቀደው በኖ ህልሙ እንደጉም ሲበን የታየው።

እናም ነጅብን የያዘው አረብ እንደባሪያ ያሰራው እንደባሪያ ያበላው እንደ ባሪያም ያኖረው ያዘ ። ነጅብ እዚያ ሲደርስ ያገኘው ከርሱ በፊት የእርሱ እጣ የደረሰውን ሌላ ህንዳዊ ነበር። ፀጉሩ የተንጨባረረ አጥንቱ የወጣ ልብሱ የቆሸሸ አቧራ የለበሰው ያ ህንዳዊ በነፃ ህይወቱ እስኪያልፍ ያን አረብ ያገለግል ነበርና በዚያ መልክ ሲያየው ግራ ተጋባ። ግና ያ ህንዳዊ ብዙ አልቆየም የበረሀው ሙቀት የልፋቱ ብዛት እንግልታቴው ህይወቱን በአጭሩ ቀጨውና ሞተ። በዚያ በበረሀ ሲሞት ማን ሊቀብረው ? ማንም! እናም አስክሬኑን የሰማይ አሞራዎች ጆቢራዎች ተቀራመቱት።

ነጅብ የዚያን ምስኪን አስክሬን ከአሞራው ለማዳን ሞከረ ግና አልቻለም። ነጅብ የሚያየው ሁሉ ተስፋ እያስቆረጠው መጣ ። ሰርቼ ህይወቴን እለውጥበታለሁ ያላት ሳኡዲ የባርነት ህይወትን አዘጋጅታ ጠበቀቺው ያ ጨካኙ አሳዳሪው በነፃ ላቡን ደሙን ድካሙን ይመጠው ያዘ። የነጅብ መልክ ተቀየረ ድንቡቡሽቡ ወፍራሙና ቀዩ ነጅብ በአጥንቱ ቀረ ። ሰውነቱ ቀመለ ለብሱ ተላ ። ውሀ የማያገኘው ሰውነቱ ራሱን ሲሸተው መሞትን ናፈቀ። ግና እንደት ይሙት ? አመልጣለሁ ብሎ ብዙ ሞከረ ግና አሳዳሪው በመነፅር ይከታተለው ነበርና አልቻለም። የነጅብ እጣ ከእርሱ በፊት የነበረው የዚያ ከርታታ ህንዳዊ እጣ ነበርና!
አመታት በዚህ መልክ አለፉና አንድ ቀን ያ ሲለየው እንደወንድም ያነባውን ሀኪምን ድንገት አላህ አገናኛቸው። ድምፃቸው እንጅ አካላቸውን መተዋወቅ አልቻሉም። ተቃቅፈው ተያይዘው አነቡ አለቀሱ ። የሚፈስ እንባ የሌለው ከውስጥ ተንሰቅስቆ የሚወጣ ደረቅ ለቅሶ። ለእንባ የሚሆን ፈሳሽ ሰውነታቸው ማመንጨት አይችልምና

YOU SEE … እልፍ
31/08/2024

YOU SEE … እልፍ

እልፍ ስራን ከኛጋር 🔥📸📌እልፍ
30/08/2024

እልፍ ስራን ከኛጋር 🔥📸📌እልፍ

🔥📸📌እልፍ
27/08/2024

🔥📸📌እልፍ

እልፍ
25/08/2024

እልፍ

Welcome to Elf Production & Events📲💻🎥
11/04/2024

Welcome to Elf Production & Events📲💻🎥

Address

Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ELF Production & Events posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Business

Send a message to ELF Production & Events:

Share