የጠምባሮ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የጠምባሮ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት We deliver Government information door to door

ሞዴል የገጠር መንደሮች ወደከተማ መዛወር አለብኝ የሚለውን አመለካከት የሚለውጡ ናቸው - አቶ ጌታቸው ረዳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በሞዴ...
11/10/2025

ሞዴል የገጠር መንደሮች ወደከተማ መዛወር አለብኝ የሚለውን አመለካከት የሚለውጡ ናቸው - አቶ ጌታቸው ረዳ

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ በሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ የታየው የአመለካከት ለውጥ የተሻለ ለመሥራት የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

ዘርፈ ብዙው የስነ-ጥበብ ሰው መምህር ሰለሞን ደሬሳ፤ በርካታ ኢትዮጵያዊ ላሊበላ እና አክሱም ፊት ቆሞ ቀድሞ የሚያስበው ቅርሶቹ እንዴት እንደማይሰሩ ነው ማለታቸውን ያስታወሱት አቶ ጌታቸው፤ ይህም ሀገር ለመቀየር በሚደረግ ጥረት ውስጥ ትልቁ ፈተና የአመለካከት ችግር መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

የተሻለ ጥራት እና ንጽህና ለማግኘት ቦታ መቀየር አለብኝ የሚል እንጂ ያለሁበትን ቦታ ማሻሻል አለብኝ ብሎ ያለማሰብ ችግርም እንዳለ አቶ ጌታቸው አንስተዋል።

በዚህ ረገድ የተሻለ አኗኗር ለማግኘት ወደከተማ መዛወር አለብኝ የሚል እሳቤ አያስፈልግም ያሉት አቶ ጌታቸው፤ ይህንን አመለካከት ለመስበር የሚያስችል ሥራ በሞዴል የገጠር መንደሮች አማካኝነት ተሰርቷል ሲሉ አስረድተዋል።

ይህ ሥራ አመራሩ በመኖሩ የተፈጠረ ለውጥ ብቻ ሳይሆን ለተጨማሪ አቅም ጉልበት የሚፈጥርም ነው ብለዋል።

የሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ በታቀደ መልኩ ከተማ ለመፍጠር ዕድል የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል።

በሽታን መከላከልና ጤናን የማበልፀግ ስራዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎና ባለቤትነት ሊመራ እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ ገለጹ።(ጠምባሮ ፡ጥቅምት 1/20...
11/10/2025

በሽታን መከላከልና ጤናን የማበልፀግ ስራዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎና ባለቤትነት ሊመራ እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ ገለጹ።

(ጠምባሮ ፡ጥቅምት 1/2018)

የልዩ ወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት የ2017 ዓ/ም ዓመታዊ የጤና ጉባኤ "በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቅነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መርህ በሙዱላ ከተማ ተካሂዷል።

ጽህፈት ቤቱ በዛሬው ዕለት ባካሄደው ዓመታዊ ጤና ዘርፍ ጉባኤ በበጀት ዓመቱ በሴክተሩ የነበሩ መሰረታዊ ተግዳሮቶችን በመለየት በተሰሩ ስራዎች በስፋት ባለድርሻ አካላት በተገኙት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም ገምግሟል ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ በሽታን መከላከልና ጤናን የማበልፀግ ስራዎች በህብረተሰቡ ተሳትፎና ባለቤትነት ሊመራ እንደሚገባ ተናግረዋል ።

ከጤና ጋር በተያያዘ የመድሃኒት አቅርቦት፣ የጤና ፋይናንሲንግ ስርዓት ማሻሸል ፣ ኤችአይቪ፣ የላብራቶሪ አገልግሎት ማሳደግ፣ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ቁጥጥር፣ እናቶች እና ህጻናት፣ እንዲሁም ክትባት እና የመሳሰሉት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መስረት እንደሚገባ ዋና አስተዳዳሪ አክለዋል ።

የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማሻሻል የጤና ፋይናንስን ማሳደግ እና የሃብት ክትትልን በአግባቡ በመምራትና ለህዝቡ ፍትሐዊ የሆና የጤና አገለግሎት ተደራሽ ለማድረግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት ይገባል ሲሉም ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ ገልጸዋል ።

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተከስተ ሳሙኤል እንደተናገሩት ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ የጤና ስርዓቱን በማዘመን በበጀቱ ዓመቱ በርካታ ለውጦች ማስመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል ።

ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ የጤና ስርዓቱን ማዘመን ስራ በስፋት ተሰርቷል ያሉት አቶ ተከስተ ሳሙኤል የጤና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማሻሻል በተሰራው ስራ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ጨና በመቀነስ ረገድ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅት በመፍጠር በተሰራው ስራ ውጤታማ ስራዎች ተሠርቷል ብለዋል።

የእናቶችና ህፃናት ጤና ሁኔታን ለማሻሻል በተሰራው ቅንጅታዊ ስራ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልፀው ፤ የመድኃኒትና ህክምና ግብአት አቅርቦት፣ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶቾ ግንባታና አገልግሎት ላይ በተከናወኑ ተግባራትም ተጨባጭ ውጤትን ለመምጣት ተችሏል ብለዋል።

የጤና ጉዳይ የሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ መሆኑን ያስታወሱት የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ የጤና ስርዓት ግንባታ ማጠናከር፣ የማህበረሰቡን የጤና ባለቤትነትና ተሳትፎ ማረጋገጥ፣ የማበረታቻና የተጠያቂነት አሰራር ስርዓትን መዘርጋት፣ የአፈፃፀም ውጤታማነት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሰፊ ስራ እንደተሠራ አብራርተዋል ።

በውይይቱ ላይ የተገኙት ባለድርሻ አካላት በሰጡት አስተያየታቸው በሽታን ከመከላከልና ከመቆጣጠር አንፃር በበጀት ዓመቱ የተሸላ ሰራ መሰረቱን ጠቅሰው፤ አምራች ዜጋን ለማፍራት ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ዙሪያ ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ በየደረጃው ለሚገኘው ህብረተሰብ ክፍል የግንዛቤ ማስጨበጥ በተጠናከረ መልኩ መስረት እንደሚገባ የውይይቱ ተሳታፊዎች በአስተያየታቸው ተናገሩ።

በጤናው ዘርፍ የተመዘገበውን ውጤት ለማስቀጠልና የጤናውን ስርዓት በማዘመን ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት መስራት በበጃት ዓመቱ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት የጤናውን የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ትብብርና አንድነት የላቀ መሆን እንደሚገባ ተጠቁሟል ።

በተክሉ ወንድሙ

ለተጨማሪ መረጃ

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/share/1BpQ7kA83j/

በቴሌግራም፦https://t.me/tembarospecialworedacom

በቲክቶክ፦tiktok.com/

ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመጪው ሰኞ ይከበራልጠምባሮ ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‘ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን...
11/10/2025

ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በመጪው ሰኞ ይከበራል

ጠምባሮ ፣ ጥቅምት 1፣ 2018 ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‘ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጲያ ሕዳሴ’ በሚል መሪ ሀሳብ ሰኞ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይከበራል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባወጣው መግለጫ፤ ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መንግሥትና ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ሥልጣን፣ ነፃነት፣ ዕድገትና ማሕበረሰባዊ ትስስር መፍጠሪያ መሣሪያ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ የታተመ የሀገራዊ አንድነትና ነፃነት መገለጫ ታላቅ የብሔራዊ ኩራት አርማ እንደሆነ ጠቁሟል።

ጀግኖች አያቶቻችን ወራሪዎችን አሸንፈው ለመላው የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት የሆነውን ሠንደቅ ዓላማ የሕይወት መስዋዕትን ከፍለው ለአዲሱ ትውልድ ማስረከባቸውን በማንሳት ይህንኑ መሠረት በማድረግ ሠንደቅ ዓላማ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶት የሚከበር ታላቅ ሀገራዊ በዓል መሆኑ ተመላክቷል።

በመሆኑም የሀገራችንን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ተገቢውን ከፍታ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ሀገራዊ ሉዓላዊነትንና የግዛት አንድነትን ማስቀጠል፤ ሕብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት በማጽናት የሀገራችንን የዕድገት ከፍታ ማረጋገጥ ከአሁኑ ትውልድ የሚጠበቅ ሀገራዊ ኃላፊነት እንደሆነ አብራርቷል።

የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ አዋጅ አዋጅ ቁጥር 863/2006 (እንደተሻሻለው) አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ መጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር ተደንግጓል።

በዚህ ዓመትም ሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታን በዋጀ መልኩ ለ18ኛ ጊዜ ከሰንደቅ ዓላማ መርሆዎች ጋር ተገናዝቦና የኢትዮጵያን ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራትና ማንሰራራት በሚያረጋግጡ ውይይቶች ታጅቦ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት መሪነት በመላው ሀገሪቱ እንደሚከበር አስታውቋል።

በፌደራል የመንግስት ተቋማት፣ በክልሎችና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች፣ በመከላከያ ሰራዊት ካምፖች እንዲሁም በኤምባሲዎችና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ሠንደቅ ዓላማ በመስቀልና በሠንደቅ ዓላማ ፊት ቃለ መሐላ በመፈፀም እንዲሁም በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር መግለጫው አመልክቷል። ኤፍ ኤም ሲ

"በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ"  በሚል መሪ ቃል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጤና ጽህፈት ቤት የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሙዱላ  ከተማ እየተ...
11/10/2025

"በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጤና ጽህፈት ቤት የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሙዱላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ "በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት በ2017 ዓ.ም ዓመታዊ በሙዱላ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል ።


"በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው ጉባኤ በበጀት ዓመቱ በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት አፈጻጸምን የጠምባሮ ልዩ ወረዳ የጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተከስተ ሳሙኤል እና የጽህፈት ቤት የልማት ዕቅድ ስራ ሂደት ደይሬክቶሬት በሆኑት በአቶ በጋለ ዘለቀ እያቀረበ ነው።

በዚህም በጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ ላይ የእናቶችና ህፃናት ጤና ሁኔታን ለማሻሻል ፣ የመድኃኒትና ህክምና ግብአት አቅርቦት፣ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶቾ ግንባታና በሌሎችም አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም በዝርዝር በማቅረብ ላይ ይገኛል ።

የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሙዱላ  ከተማ መካሄድ ጀመረ ።የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ "በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ"  በሚል መሪ ቃል ...
11/10/2025

የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ በሙዱላ ከተማ መካሄድ ጀመረ ።

የጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ "በባለቤትነት ላይ የተመሠረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጠምባሮ ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት በ2017 ዓ.ም ዓመታዊ በሙዱላ ከተማ መካሄድ ጀምሯል።

በጤናው ዘርፍ ዓመታዊ ጉባኤ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣የጠምባሮ ልዩ ወረዳ አስተባባሪ አካላት ፣የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት ፣የሙዱላ ከተማ አስተዳዳር አስተባባሪ አካላት ፣የልዩ ወረዳውና የከተማ አስተዳደር አመራሮችና ሌሎችም ተገኝተዋል ።

ጉባኤው በጤናው ዘርፍ የተከናወኑ ዐበይት ተግባራት የሚገመገሙበት እና አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑ ተገልጿል።

በተክሉ ወንድሙ

ለተጨማሪ መረጃ

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/share/1BpQ7kA83j/

በቴሌግራም፦https://t.me/tembarospecialworedacom

በቲክቶክ፦tiktok.com/

የሴቶች ልማት ህብረትን በሁሉም የልማት መስክ ላይ በማሳተፍ ለውጤታማነቱ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።(ጠምባሮ ፦ መስከረም 30/2018) የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጽህፈት ቤ...
10/10/2025

የሴቶች ልማት ህብረትን በሁሉም የልማት መስክ ላይ በማሳተፍ ለውጤታማነቱ በጋራ መስራት እንደሚገባ ተገለፀ ።

(ጠምባሮ ፦ መስከረም 30/2018) የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጽህፈት ቤት የሴቶች ልማት ህብረት ቴክኒክ ኮሚቴ የሴቶች ልማት ህብረትና የሴቶችና ህፃናት ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የ2018 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂደዋል ።

ጽህፈት ቤቱ በዛሬው ዕለት ''የሴቶች የቴክንክ ኮሚቴ የቀጠይ አቅጠጫ'' በሚል መሪ ቃል የ2018 በጀት ዓመት በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በስፋት ውይይት አካሂዷል ።

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ደሰለች ማቴዎስ እንደተናገሩት የሴቶች ልማት ህብረትን በሁሉም የልማት መስክ ላይ በማሳተፍ ለውጤታማነቱ በጋራ መስራት ይገባል ብለዋል።

በየደረጀው የሚገኙትን የሴቶች የልማት ህብረትን በማጠናከር በሁሉም ተግባራት ሞዴል ቀበሌያትን ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል።

በቀጣይም ከተቋማትና ከባለድርሻ አካለት ጋር ያለውን ትስስርን በማጠናከር የሴቶችን ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ በትኩረት መስራት እንደለበት አብራርተዋል ።

የልዩ ወረዳውን ሠላምና ፀጥታ ሁኔታ በዘላቂነት በማስቀጠል ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስረት እንደሚገባ ተገለፀ ።(ጠምባሮ ፣መስከረም 30/2018)ሠላምና ፀጥታ ሁኔታ በዘላቂነት...
10/10/2025

የልዩ ወረዳውን ሠላምና ፀጥታ ሁኔታ በዘላቂነት በማስቀጠል ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስረት እንደሚገባ ተገለፀ ።

(ጠምባሮ ፣መስከረም 30/2018)

ሠላምና ፀጥታ ሁኔታ በዘላቂነት በማስቀጠል ሁለንተናዊ ልማትን ለማረጋገጥ በትኩረት መስረት እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ገልጿል ።

ይህም የተገለፀ ጽህፈት ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ጉባኤ መድረክ በሙዱላ ከተማ ባካሄደበት ወቅት ነው።

በተካሄደው በሠላምና ፀጥታ ምክር ቤት ጉባኤ ላይ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ አስተባባሪ አካላት፣የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት ፣የሙዱላ ከተማ አስተዳደር አስተባባሪ አካላት ፣የልዩ ወረዳና የከተማ አሰተዳደር ፓሊስ አባላትና ማኔጅመንት አካላት፣ፍትህ አካላት ፣የሠላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ማኔጅመንትና ባለሙያዎች ፣የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶች ፣የሁሉም ቀበሌ ባለድርሻ አካላትና ሌሎችም በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል ።

የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ ሠላም ለማህበራዊ ፣ለኢኮኖሚ ዕድገት፣የማህበራዊ እሴት ለማበልፀግና ዲሞክራሲን ለማጎልበት ያለው አስተዋጽኦ የጎላ መሆን እንደሚገባ ገልጸዋል ።

ዘጎች ያለምንም ሠላምና ፀጥታ ችግር ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን በየአካባቢው ህገወጥ ድርጊት የሚፈጥሩ አካላትን በመለየትና በመፈተሽ የህግ በላይነትን ለማስጠበቅ በሚደረገው እንቅስቃሴ ሁሉ የባለድርሻ አካላት የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል ።

ዋና አስተዳዳሪው በገለፃቸው ጠምባሮ በክልሉ ባሉ ዞኖች፣ልዩ ወረዳዎችና ወረዳ በሠላምና ፀጥታ የተሻለ መሆኑን ጠቅሰው ፤ነገርግን በአሁኑ ወቅት ማህብረሰቡን ሠላምና ፀጥታን ለማወክና ለማደፍረስ በሚንቀሳቀሱ አካላት ለይ መንግስት ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ጭምር ገልጸዋል ።

ሠላም ለሁሉም ነገር መሠረት በመሆኑ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት እንዳለባቸው የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ሠላምና ፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደዊት ደለቾ ተናግረዋል ።

ለኅብረተሰቡ ጥቅም የሚከናወኑ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ዕቅዶችና የግለሰቦችን መሠረታዊ መብቶች ለማስከበር ወሳኝ የመረጃ ምንጮች ልደት፣ ጋብቻ፣ ሞትና ፍቺ ያሉ መረጃዎች ላይ የተሻለ ለማድረግ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን ጭምር አያይዘው ገልጸዋል ።

ከዚህ በፊት በወሳኝ ኩነት ምዝገብ ላይ የሚስተዋለውን የኪራይ ሰሳብሰቢነትን አዝማሚያ ለማስቀረት ከዘርፉ ከባለድርሻ አካላት ጋር ጽህፈት ቤቱ በቅንጂት እንዲሚሠራ ጠቁመዋል ።

በሠላምና ፀጥታ ምክር ቤት ጉባኤ የተገኙት የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት እስራኤል አበበ በሰጡት አስተያየታቸው ሠላምና ፀጥታ ጉዳይ የሀገር ሽማግሌዎች ፣የሀይማኖት አባቶችና የአመራር ጉደይ ብቻ ሰይሆን የሁሉ በባለድርሻ አካላት ጉዳይ እንደሆነ አስረድተዋል ።

በበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዕቅድ፣በየቀበሌው እና አካባቢው የሚከሰቱ የህገወጥ ሰዎች ዝውውር ፣ወንጀልን አስቀድሞ ከመከላከል አንፃር የሚታዩ ክፍተቶች ፣ ለሠላምና ፀጥታ ስጋት የሚሆኑ አካባቢዎች ላይ አስቀድሞ የዳሰሰ ጥናት መስረትና ሌሎችም የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማስቀረት በዕቅድ መንቀሳቀስ እንደሚገባ በአስተያየታቸው ተናግረዋል ።

ጠንካራ ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ስርዓትን በመዘርጋት፣ ህዝቡ ከወጣበት በሰላም እንዲገባና ስጋት እንዳይፈጠር በከተማ አስተደደሩና በልዩ ወረዳው በልዩ ትኩረት ተሰቶ መስረት እንደሚገባ ተጠቁሟል ።

በመጨረሻም ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ሀብታሙ በላይነህ በየደረጃው የሚገኘው ህብረተሰብ የህግ የበላይነት በማስፈን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በመደገፍ የድርሻውን እንዲወጣ አሳስበዋል ።

በተክሉ ወንድሙ

ለተጨማሪ መረጃ

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/share/1BpQ7kA83j/

በቴሌግራም፦https://t.me/tembarospecialworedacom

በቲክቶክ፦tiktok.com/

ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ የጤና ስርዓቱን ማዘመን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ገለፀ።(ጠምባሮ ፦ መስከረም 30/2018) ''በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅ...
10/10/2025

ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግና ማረጋገጥ የጤና ስርዓቱን ማዘመን እንደሚገባ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ገለፀ።

(ጠምባሮ ፦ መስከረም 30/2018) ''በባለቤትነት ላይ የተመሰረተ እውቅናና ተጠያቂነት ለጠንካራ የጤና ስርዓት ግንባታ'' በሚል መሪ ቃል የልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት አመታዊ የጤና ጉባኤ በሙዱላ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ዓመታዊ የጤና ጉባኤውን የመክፈቻ ንግግር የጠምባሮ ልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተከስተ ሳሙኤል እንደተናገሩት ለዜጎች ሁለንተናዊ ብልጽግናማረጋገጥ የጤና ስርዓቱን ማዘመን ይገባል ብለዋል።

በበጀት ዓመቱ በሴክተሩ የነበሩ መሰረታዊ ተግዳሮቶችን በመለየት በተሰሩ ስራዎች ውጤት ማምጣት ተችሏል ያሉት ኃላፊዉ በዓመቱ በጤናው ሴክተር ሞዴል የሆኑ በርካታ ተግባራት መከናወኑን ተናግረዋል።

በልዩ ወረዳ ጤና ጽህፈት ቤት በበጀት ዓመቱ የጤና ቁጥጥር ስርዓቱን ለማሻሻል በተሰራው ስራ ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ጨና በመቀነስ ውጤታማ ስራ ተሰርቷል ነው ያሉት።

የጤናው ስራ ተግባቦትን ይጠይቃል ያሉት አቶ ተከስተ ለዘርፉ ውጤታማነት ሁለንተናዊ ቅንጅትና ትብብር ብሎም አመራር ሰጪነት እንደሚያስፈልግም ገልፀዋል።

የእናቶችና ህፃናት ጤና ሁኔታን ለማሻሻል ሰፊ ስራ መሰራቱን ገልፀው የመድኃኒትና ህክምና ግብአት አቅርቦት፣ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶቾ ግንባታና አገልግሎት ላይ በተከናወኑ ተግባራትም ተጨባጭ ውጤትን ለመምጣት ተችሏል ብለዋል።

በቀጣይ የጤና ስርዓት ግንባታ ማጠናከር፣ የማህበረሰቡን የጤና ባለቤትነትና ተሳትፎ ማረጋገጥ፣ የማበረታቻና የተጠያቂነት አሰራር ስርዓትን መዘርጋት፣ የአፈፃፀም ውጤታማነት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል።

ተግባራትን በኃላፊነት በመተግበር የጤናውን ስርዓት በማዘመን ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት መስራት ያስፈልጋል ብለው በቀጣይ ደካማና ጠንካራ ጎኖችን በመለየት በጤናው ዘርፍ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል።

በዛሬው ሰነድ ቀርቦ የቡድን ውይይት በማድረግ ለቀጣይ የጋራ አቅጣጫ ይይዛል ተብሎ ይጠብቃል።

በመድረኩም የልዩ ወረዳና የከተማ አስተዳደር የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች፣ የሆስፒታልና ጤና ጣቢያ ኃላፊዎች ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በተክሉ ወንድሙ

ለተጨማሪ መረጃ

በፌስቡክ፦https://www.facebook.com/share/1BpQ7kA83j/

በቴሌግራም፦https://t.me/tembarospecialworedacom

በቲክቶክ፦tiktok.com/

ዲጂታላይዜሽን ቀጣናውን በማስተሳሰር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል - አቶ አህመድ ሽዴዲጂታላይዜሽን የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣናን በማስተሳሰር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ሲሉ የገንዘብ ሚ...
09/10/2025

ዲጂታላይዜሽን ቀጣናውን በማስተሳሰር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል - አቶ አህመድ ሽዴ

ዲጂታላይዜሽን የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ቀጣናን በማስተሳሰር ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ሲሉ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ገለጹ።

አቶ አህመድ በናይሮቢ፣ ኬንያ የተካሄደውን 24ኛው የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) የመሪዎች ጉባዔ በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ፥ የጉባዔው ዋና አጀንዳ በሆነው ዲጂታላይዜሽን ላይ አመርቂ ውጤት እያመጣች ያለችው ኢትዮጵያ ልምዷን አካፍላለች ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ኢትዮጵያ የዲጂታል መሠረተ ልማትን በመዘርጋት ረገድ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቧን መግለጻቸውን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል።

የዲጂታል ዘርፉ በአሁኑ ወቅት ለኢትዮጵያ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅዖ እያበረከተ እንደሚገኝ ያወሱት አቶ አህመድ፤ በተለይ በፋይናንስ ዘርፉ ዲጂታላይዜሽን ራሱን የቻለ ስትራቴጂ ያለው በመሆኑ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን አክለዋል።

ኢትዮጵያ ከጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ሱዳን እና ሶማሊያ ጋር እያደገ ያለ የዲጂታል መሠረተ ልማት ግንኙነት እንዳላት ጠቅሰው፤ ይህን ግንኙነት ይበልጥ የማጎልበት ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

ከ24ኛው የኮሜሳ የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣናን የማስጀመር ሥራ መከናወኑን አንስተው፤ ይህም የኢትዮጵያ የሪፎርም ሥራ አንዱ አካል እንደነበር አክለዋል።

የአፍሪካ ሀገራትን የንግድ ልውውጥ በማሳደግ ረገድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግንባር ቀደም ተዋናይ መሆኑንም አቶ አህመድ በማብራሪያቸው ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ የአፍሪካን ትስስር በማጠናከር ቀዳሚ ናት ያሉት ሚኒስትሩ፤ ሀገሪቱ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በመሠረተ ልማት ላይ እያከናወነችው ያለው ሰፊ ሥራ በዚህ ረገድ ያላትን አቅም ይበልጥ እንደሚያሳድገው ገልጸዋል።

09/10/2025

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተቋማት መስራችና ግንባር ቀደም ተዋናይ ናት - የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ Part 9

09/10/2025

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተቋማት መስራችና ግንባር ቀደም ተዋናይ ናት - የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ Part 8

09/10/2025

ኢትዮጵያ የአፍሪካ ተቋማት መስራችና ግንባር ቀደም ተዋናይ ናት - የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ Part 7

Address

Tembaro
Addis Ababa
042

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የጠምባሮ ልዩ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share